የኢትዮጵያን ነፃነት ትግል ስናስብና ስናራምድ
ተስፋዬ ደምመላሽ
ያለንበት ዘመን ኢትዮጵያዊነትን በስሜት ብቻ ሳይሆን በሃሳብና በስልት አድሶ ማረጋገጥ አዳጋች የሆነበት ጊዜ
ነዉ። የአገር ወዳድ ዜጐችና ወገኖች ተቆርቋሪነት እጥረት ባይኖርም የአገር ማዳን ጥያቄዎችን ሰፋና ጠለቅ
አድርገን ማንሳት፣ መልሳቸዉንም በተቀናበሩ ቀጣይ ዉይይቶች፣ የሃሳቦች ልዉዉጥና የህብረተሰብ ንቅናቄ
ምንም ያህል አንፈልግም። ዉስን ያጭር ጊዜ ፖለቲካ ተልዕኮዎችና ጥረቶች ላይ ብቻ በማተኮር ዘላቂዉንና
ሰፊዉን የኢትዮጵያ ነፃነት ትግል አድማስ ሆን ብለንም ባይሆን በዉጤት ከራሳችን እንሰዉራለን። ብሔራዊና
ስልታዊ ራዕይን በድርጅታዊ መላዎችና ትብብር ሙከራዎች ቀደም ቀደም እያልንና እየደጋገምን እናደበዝዛለን።
የትግል ምኅዳሩን በበዙና በተባዙ ተቃዋሚ ቡድኖች እናጣብባለን።
የዚህ ሁኔታችን ምንጩ ምንድን ነዉ? ጥልቅ ታሪካዊ ሥር ያለዉ፣ አንድነትንና ነፃነትን ለዘመናት መገለጫ
ባህሪዎቹ ያደረገ ኢትዮጵያዊነት ዛሬ ይህን ያህል ምን አዳከመዉ? የገጠሙት ችግሮችና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸዉ? የኢትዮጵያ
መንግሥት የአገሪቱን አንድነትና ሉአላዊነት በሚጻረር ሞገደኛ ህዝብና ምሁራን ከፋፋይ ፈላጭ ቆራጭ የጐሣ ስብስብ ቁጥጥር ሥር
መዉደቁ ዋና ምክንያት መሆኑ እዉቅ ነዉ። ግን እንደ አገር ያለንበትን ዉስብስብ ዉጥረት በይበልጥ ለመረዳትና በመሠረቱ ለመወጣት
ይህን ምክንያት ሰፋ ባለ፣ አብዮታዊ ልምዳችን ዉስጥ አገባብ ባለዉ፣ መንገድ ማየት ይጠቅማል። እይታዉ ደግሞ ከዉጥረቱ መዉጫ
ዘላቂ መንገድ ለመቀየስና ለመጥረግ ይረዳል። ይህን በመገንዘብ በዝች ጽሑፍ አግባብነት ያላቸዉ ጉዳዮች ላይ ዉይይት የማደርገዉ
ከተለመዱ ክርክሮች በተለየ ጠበቅ ያለ የትንተና አቀራረብ ስለሆነ የአንባቢዎችን ትዕግሥትና ልብ ባይነት ከወዲሁ እጠይቃለሁ።
እንደምናዉቀዉ አብዮታዊ ልምዳችን በጐ ምኞት በነበረዉ ግን ራሱን ከአገራዊ መሠረቱና ቅርሱ ጋር ባቃቃረ፣ “ስር ነቀል” ነኝ ባይ ግን
ብሔራዊ ስር የሌሽ የተማሪዎች ንቅናቄ ተጀመረ። ጅምሩ የትግል ልብና መንፈስ ባልተጓደለበት ግን ከብሔራዊ ህልዉናችን ጋር
የተጣጣመ ስልታዊ ራዕይና አስተዉሎ ባልነበረዉ የኢሕአፓ ወጣቶች ዉጊያ ቀጥሎ የደርግን ጨፍጫፊ አብዮታዊ አገዛዝ አስከተለ።
በመጨረሻም ኢትዮጵያን “ብሔሮች” ከተባሉ ወገንተኛ የጐሣ ስብስቦችና ድርጅቶች ጥርቅም ባሻገር ማየት በማይፈልገዉ ወይም
በማይችለዉ ዘረኛ የንኡስ ከበርቴ ብሔርተኝነት አራማጁ አብዮተኛ ወያኔ ቡድን የመንግሥት ሃይል ተቆጣጣሪነት ተደመደመ። በዚህ
መልክ ርዝራዡ ዛሬ ካልተለየንና አዙረን መፈተሽና መለወጥ ካለብን ከትናንቱ የትግል ልምዳችን ተነስተን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
መንገድ ያሁኑ አሳዛኝ ሆኔታችን ላይ ደርሰናል። ብሔራዊ ህልዉናችንን፣ ነፃነታችንን አስከፊና አደገኛ ሁኔታ ላይ ጥለናል።
እዚህ ላይ በዛሬ የአገር ጉዳዮች ዉይይቶቻችን የሚገባዉን ትኩረት የማንሰጠዉ አንድ ነገር አለ። ይኸዉም ረጅሙና በአመዛኙ የአገር
ባለቤትንት ያልነበረዉ፣ እንዲያዉም በዉጤት የፀረ ኢትዮጵያነት አዝማሚያ ያሳየዉ፣ የአብዮት ጉዟችን የዚህ ወይም የዚያ ወገንን
አምባገነናዊ አገዛዝ ከማትረፍ አልፎ ጠቅላላ አገር ከፋፋይ፣ “ብሔሮች” ተብዬዎችን ከዜጐችና ከህዝብ አንድነት ጋር አጣይ፣ ጠቅላላ
የፖለቲካ አስተሳሰብና አሠራር ልምድ አገሪቱ ላይ የጫነ ነዉ። ጭነቱ በትግሬ ነፃ አዉጭ ነኝ ባዩ የመንግሥት ሃይል ተቆጣጣሪ ወያኔ
ቡድን ወደር በሌለዉ መልክና መጠን ይባባስ እንጂ በወያኔዎች የተጀመረ አለመሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። ወያኔዎች ያስፋፉትና የኦነግና
የሌሎች “ብሔሮች” ተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች አደራጅ ፎርሙላ የሆነዉ “አብዮታዊ” የማንነት ፖለቲካ ከሞላ ጐደል የተጠነሰሰዉ
በአገሪቱ ተማሪዎች ንቅናቄ ዉስጥ በነዋለልኝ መኮንን ፅንፍ ግራ ክንፈኛ አመራር ነበር። ይህን የምለዉ የተሳተፍኩበትን የተማሪ ንቅናቄ
በቀላሉ ለመንቀፍ ወይም ያለፈ ታሪክ ለመገዝገዝ ሳይሆን ዛሬ አገሪቱ ያለችበትን ዉጥረት ሰፋ አድርጌና ጠለቅ ብዬ ለመገንዘብ
በመሞከር ነዉ። ይህ ግንዛቤ ከብሔራዊ ዉጥረታችን በመሠረቱ ለመላቀቅ ይረዳናል ብዬ እገምታለሁ።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ነፃነት ትግል መቋቋም ያለብን እንግዲህ የአንድ ዘረኛ አምባገነን ወገን አድራጊ ፈጣሪነት ብቻ አይደለም። ጨቋኙ
ወገን የተቋቋመበትንና ዛሬም እንደ አገር ገዢ ሃይል ራሱን አደራጅቶ የሚንቀሳቀስበትን ፈላጭ ቆራጭ የፖለቲካ “ሥርዓት” ወይም
ባህልም ጭምር ነዉ። በዛሬና በትዉልድ ዘለል የኢትዮጵያዊያን ትግል መወገድ ያለበት ከወያኔዎች እንቅስቃሴዎችና ድርጊቶች ሥር
ያለ፣ ዘረኛዉ ገዢ ወገን ከሌሎች የጐሣ ነፃ አዉጪ ነን ባይ ስብስቦች ጋር የሚቀራረብበትና ከሞላ ጐደል የሚጋራዉ የፖለቲካ
ሰዋሰዉና ቃላት፣ እንዲሁም የአስተሳሰብ፣ የዲስኩርና የእንቅስቃሴ መዋቅር ነዉ።
ይኼን ጨቋኝ መዋቅር ለማስወገድ የምንይዘዉ የትንተና፣ የግምገማና የተግባራዊ እንቅስቃሴ መንገድ ወደ ቅድመ አብዮቱ ሥርዓት
የሚመልሰን ሳይሆን የአብዮቱን ኪሳራና ዉድቀት መወጣት የሚያስችለን፣ ወደ ተሻለ የነፃነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ መዳረሻ
የሚወስደን ጐዳና እንደሆነ መረጋገጥ አለበት። ለምሳሌ የተወሰኑ ለንናዊ-ስታልናዊ የርእዩተ ዓለም ፈርጆችን ወይም ስያሜዎችን
(በተለይ “ብሔሮች” እና “ብሔራዊ ራስ ዉሰና” የተባሉትን) ለጽንሰሃሳባዊና ተግባራዊ ጥያቄ መክፈት፣ በተገቢ ትንተናና ትችት
ዶ/ር ተስፋዬ ደምመላሽ2
ብልሹነታቸዉን ወይም ጉድለታቸዉን ማሳየት፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ እዉን ባህላዊ ብዙሃንነትንና እኩልነትን አለመቀበል ማለት
አይደለም። የወያኔንና የኦነግን የተወሰነ ወገንተኛ የማንነት ፖለቲካ መፈተሽ፣ መገምገምና የተሻለ አማራጩን ማሳየት በጅምላ
የትግሬዎችንና የኦሮሞዎችን ባህላዊ ወይም አካባባዊ ማንነቶችና የስቭል መብቶች መጻረር ማለት አይደለም። ይህ በጨቋኙ ፖለቲካዊ-
ርእዩተ ዓለማዊ መዋቅር ዉገዳ ትግል ግልጽ መሆን አለበት። ምክንያቱም ጉዳዩ በቀኖናዊ የማንነት ፖለቲካ አራማጆችና ደጋፊዎች፣
እንዲሁም በአንዳንድ መልሰዉ ባልታነጹ የአገሪቱ ተራማጆች ብዙዉን ጊዜ ተምታቶ ይታያል።
አሁን ባለዉ የጭቆና መዋቅር ዉስጥ እየተንቀሳቀሱ፣ በተለያየ ዘዬም ቢሆን የተለመደዉን አብዮተኛ የፖለቲካ ቋንቋ እየተናገሩ፣
ከቋንቋዉ ጋር የሚሄደዉን የአስተሳሰብ ሥርዓት እያስተጋቡ፣ ተጨባጭ ትርጉም ያላቸዉ የአንድነት፣ የነፃነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ
ዕሴቶችን በኢትዮጵያ ማረጋገጥና ማራመድ የሚሆን ነገር አይደለም። ለማንም የአገሪቱ ዜጋ ወይም ባህላዊ ማህበረሰብ አይበጅም።
መዋቅራዊ የፖለቲካ ለዉጥ እስካልተኪያሄደ ድረስ፣ ዕሴቶቹን ማንኛዉም ተቃዋሚ ፓርቲ ወይም ጐሠኛ ወገን በብቸኝነት ያንሳቸዉ
ይጣላቸዉ በይዘታቸዉ የመነመኑ ሸንጋይ የፖለቲካ ቃላት ከመሆን በቀር ምንም ጽንሰሃሳባዊ ወይም ተግባራዊ ፋይዳ አይኖራቸዉም።
ስለዚህ የምንፈልገዉ ለዉጥ በዉስኑ መንግሥት ላይ ያተኮረ ሳይሆን ገዢዉ ፓርቲ ከአንዳንድ ተቃዋሚ ወገኖች ጋር ይነስም ይብዛ
የሚጋራዉ በጥልቅ እንከናማ የሆነ ጠቅላላ የአስተሳሰብ ልምድና የአገዛዝ ቅርጽ ላይ ያነጣጠረ ነዉ። እንደ አገር የሚያስፈልገን
ሥርዓታዊ የፖለቲካ ለዉጥ ነዉ።
እርግጥ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዛሬም ራሱን የትግሬ ነፃ አዉጪ ብሎ የሚጠራዉን ወገን አክሎ የተለያዩ አብዮተኛ ፓርቲዎች ተነስተዋል፣
ወድቀዋል። በጠበበና በከረረ ወገንተኛነት እርስ በርስ ተጋጭተዋል፣ ተፋጅተዋል። አሸናፊና ተሸናፊ፣ ለጣፊና ተለጣፊ ሆነዋል። ሁሉም
ወገኖች በአንድ መልክ ወይም መጠን ኢትዮጵያ ዛሬ ለወደቀችበት ሁኔታ አስተዋጽዎ አድርገዋል ማለት አንችልም። ነገር ግን በተናጠል
እንቅስቃሴም ሆነ በትግግዝ ትግል፣ በአብዮተኛ አስተሳሰብ ፉክክርም ሆነ ትብብር፣ በአሸናፊነትም ይሁን ተሸናፊነት የተጋሩት ጠቅላላ
የፖለቲካ “ፓራዳይም” ኢትዮጵያን ከሞላ ጐደል ያለማቋረጥ ከተጫናት አራት አስርተ ዓመታት ሆነዉ። በጥቅሉ ስናየዉ ብሔራዊ
ህይወታችንን ደርቦ ደራርቦ የቦረቦረዉ፣ ያዳከመዉና ያመነመነዉ የተለዋዋጭ አብዮተኛ አድራጊ ፈጣሪዎች ሥራ ብቻ ሳይሆን
የሥራቸዉ ጠቅላላ ቅርጽና ይዘትም ነዉ። ሆን ብለዉም ሆነ በዉጤት አገር ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሱት በሂደት በተጠራቀመ
የቅብብሎሽና የጋራ ተጽእኖ ነዉ።
ስለዚህ ዛሬ በኢትዮጵያዊነታችን ተማምነን ለአገር ነፃነት ትግል በሙሉ ልብ መነሳሳት ቢያዳግተን በጣም የሚገርም አይደለም። እዚህ
ላይ አግባብነት ያለዉ ሌላ ነጥብም አለ። ይኸዉም ባለፈዉ ዘመን አገር ወዳድ ተማሪዎችና የኢሕአፖ ታጋዮች በቅን ልቦና
ለኢትዮጵያ መሠረታዊ የፖለቲካና የህብረተሰብ ለዉጥ በጀግንነት ሲታገሉ ነፍጥ አንስተዉ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰርጐ የገባ
ዓለም አቀፍ አብዮታዊ የእምነትና የሃሳብ እርግጠኛነትን ታጥቀዉ፣ እንዲሁም በተያያዥ ድርጅታዊ ፎርሙላና ዘዴዎች ተደግፈዉ
ነበር። ዛሬ ተመሳሳይ ጠቅላላ ርእዩተ ዓለማዊ እርግጠኛነት፣ ድርጅታዊ ድጋፍና መሣሪያ የለም። የአገርና የዓለም ሁኔታዎች
ተለዋዉጠዋል። ይባስ ብሎም ባለፈዉ ዘመን አብዮተኞቻችን ለአገር ችግሮች ያቀረቧቸዉ “መፍትሔዎች” እራሳቸዉ ከችግሮቹ ብሰዉ
አገሪቱን ይበልጥ ወጥረዉ የያዙበት ጊዜ ዉስጥ ነዉ ያለነዉ።
ይሁን እንጂ ያለንበት ጊዜ አካቶ የጨለመ ሳይሆን ለመሠረታዊ ለዉጥ እድል የፈጠረም ነዉ። በለንናዊ-ስታልናዊ ብቸኛ ወገንተኛነት
የተቀረጸ ፈላጭ ቆራጭ ፖለቲካና “ብሔራዊ ራስ ዉሰና” የትም እንደማያደርስ፣ እንዲያዉም በመርህም በተግባርም ከስሮ አክሳሪ
የሆነበት ጊዜ ነዉ። ይህን እዉነታ በግልጽ ለመረዳት የኤርትራን ሁኔታ ማየት ይበቃል። የወያኔዎች አምባገነናዊ “ትግሬ ነፃ አዉጪ”
የፖለቲካ እቅድም በተመሳሳይ መልክ የሚታይ ነዉ፣ ምንም እንኳን “ነፃ አወጣጣቸዉ” ኢትዮጵያን በጠቅላላ ከፋፍለዉ ከመግዛታቸዉ
ጋር የተቆራኘ ቢሆንም።
ስለዚህ የተለወጠዉ የዓለም ሁኔታ ዛሬ የኢትዮጵያን ነፃነት ጉዳዮች ስንከታተል በሃሳቦችና ዕሴቶች መስክ በራሳችን ተማምነን
ከመንቀሳቀስ ወደ ኋላ ለማለታችን በቂ ምክንያት አይደለም። ለዉጡ የዛሬዉን አገር የማዳን ትግል ምሁራዊ፣ ሞራላዊና ፖለቲካዊ
ተግዳሮቶች ከመግጠም መቆጠብ ያስገድደናል ማለት አይደለም። ከአበዮታዊ ልምዳችን የወረስነዉ፣ አንድነታችንን በመሠረቱ
የሚጻረር፣ የገዢና ተቃዋሚ ወገኖች ርዝራዥ ስታልናዊ የፖለቲካ ባህልን ጥልቅ እንከናማነት ከማሳየት አይገታንም። ባህሉ ታሪካዊ
የጋራ ብሔራዊ ህይወታችንን በጠባብ ወገንተኛና ዘረኛ አይን ብቻ አይቶ ዛሬም የሚከተለዉን የአገር ግምገማ ወግ መልሰን ከመገምገም
አያግደንም። እንዲያዉም የተለወጠዉ የዓለም ሁኔታ ለመላ የኢትዮጵያ ዜጐች ነፃነትና ደህንነት በእዉነት የሚበጁ ተራማጅ ሃሳቦችን
በአዲስ የብሔራዊ አንድነት መንፈስ ዛሬ መልሰን አርቅቀን ማራመድ ይበልጥ የሚያስችለን ይመስለኛል።
የአገር ነፃነት ትግል?
“የአገር ነፃነት ትግል” ስል በቅጩ ምን ማለቴ ነዉ? እርግጥ ኢትዮጵያ በዉጭ ቅኝ ገዢ ሃይል በቀጥታ አልተያዘችም። ጥያቄዉን
ከሁለት የተያያዙ አንጻሮች መመለስ ይቻላል። በአንድ በኩል ከፋፍሎ ከተጫናት ከመሃሏ የበቀለ አብዮታዊ ተብዬ ዘረኛ ፈላጭ ቆራጭ
አገዛዝና ከዜጐቿ ስቭል መብቶች እጦት አንጻር ስናያት ኢትዮጵያ ነፃነት የላትም። አገር ነፃ ህዝብ ወይም ህብረተሰብ ከሆነ፣ አገር3
አንድነት ወይም የጋራ ብሔራዊ ህይወት ከሆነ (ነዉ ብዬ አምናለሁ)፣ ነፃ ህብረተሰብና ነፃ ዜጐች በሌሉበት፣ የአገር አንድነት
በተጨቆነበት ሁኔታ የአገር ነፃነት በእዉንቱ አለ ማለት አይቻልም። ከዚህ አኳያ ሲታይ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝብት ሁኔታ እንግዲህ
የአገር ነፃነት ትግልን አስፈላጊነት የሚያሳይ ነዉ።
ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ሁኔታ ለየት ካለ አንጻር ስናየዉ ደግሞ ዉስጣዊ ቅኝ አገዛዝ ልንለዉ የምንችል ነዉ። ራሱን የትግሬ ነፃ
አዉጪ ብሎ የሚጠራዉ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚቆጣጠረዉ ብቸኛ ስብስብ በጥቂት ተለጣፊ አማራና ኦሮሞ ወገኖች ዋና
ተባባሪነት አገሪቱ ላይ አስፋፍቶ የጫነዉን ህዝብ ከፋፋይ የፖለቲካ መዋቅር እንዳለ የዉጭ ወራሪ ሃይል ቢፈጥረዉ ኖሮ በቀላሉ የቅኝ
አገዛዝ መዋቅር ሊባል የሚችል ነዉ። ማለትም፣ ቁም ነገሩ የአገዛዙ አድራጊ ፈጣሪ ማነዉ፣ የዉጭ ሃይል ነዉ ወይስ የዉስጥ፣ ሳይሆን
ድርጊቱ በቅርጽና ይዘት አገር ላይ ያሳረፈዉ ጐጂ ከፋፋይ ተጽዕኖ ነዉ።
ስለሆነም የምናተኩረዉ የወያኔዎች ማንነት ወይም ምንነት ላይ ሳይሆን የከፋፍለህ ግዛ አስተሳሰባቸዉና አሠራራቸዉ ላይ ይሆናል።
ወያኔዎች በትዉልዳቸዉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸዉ የሚካድ አይደለም። ቢሆንም በዘረኛ፣ በተለይ በፀረ አማራ የትግል አነሳሳቸዉና
አኪያሄዳቸዉ፣ በጨቋኝ የፖለቲካ ጐሠኝነታቸዉ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሉአላዊነትና ለባህላዊ ቅርሶቻችንን (ለምሳሌ ለዋልድባ ገዳም)
ባሳዩት ክብር ነሽነት ከባዕድ ወራሪ ሃይል ምንም ያህል አይለዩም። እንዲሁም በኢኮኖሚዉ ዘርፍ ዛሬም ራሱን የትግሬ ነፃ አዉጪ ነኝ
ባይዉ ስብስብ በቀጥታ የዉጭ ከበርቴዎችና ሃይሎች መጠቀሚያም ተጠቃሚም በመሆን በሚያደርጋቸዉ ሙስና የሰፈነባቸዉ፣
ወገንተኛና ዘረኛ የሆኑ ስግብግብ ሃብት አከማች “የልማት” እንቅስቃሴዎች የስብስቡን የቅኝ ገዢነት/ተገዢነት መንፈስና ባህሪ ያሳያሉ።
ይህ የወያኔዎች ቅኝ አገዛዝ ባህሪ የኢትዮጵያን መላ ዜጐች በየአካባቢዉ የአገዛዙ መሣሪያም ተጠቃሚም በሆኑ ንኡስ ጐሠኛ
ብሔርተኞች የሚያስጠቃና የሚያስደቁስ፣ ትልቁን የጋራ ብሔራዊ ህይወታችንን የሚያሳንስ፣ የሚያኮስስና ጥግ የሚያስይዝ፣ በመሠረቱ
የአገርና ህዝብ አንድነት ተጻራሪ ነዉ። የመንግሥት ሥልጣን በጦር ሃይል የያዘዉ “የትግሬ ነፃ አዉጪ” ወገን የአገዛዝ መዋቅሩን
የዘረጋዉ ከኢትዮጵያ መልክአ ምድር ዉጭ መጥቶ ባይሆንም እራሱን ሆን ብሎ ለብሔራዊ ባህላችን፣ ልምዳችንና ስሜታችን ባዕድ
አድርጐ ነዉ። ዜጐችን በገዛ አገራቸዉ ባይታዉር አድርጐ፣ አገር ለቃቂም ዉስጣዊም ስደተኞች አባዝቶ ነዉ። ስለዚህ የብሔራዊ
ተቃዉሞዉ አላማ በቀላሉ አንድን አገራዊ መንግሥት በሌላ መለወጥ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወጥሮ ከያዛት መሰሪ የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ
ማላቀቅ ነዉ የሚሆነዉ።
በአገሪቱ የዜጐች ስቭል መብቶች፣ የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር በእዉነት የሚሰፍኑበትና የሚከበሩበት፣ እንዲሁም የአገሪቱ
ጥቅም የሚጠበቅበት ብሔራዊ-ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት የመገንባቱ ሥራ እንግዲህ ይህን አገዛዝ ከመሠረቱ የሚንድ፣ በተለያዩ
መስኮችና ደረጃዎች በቅንብር የሚኪያሄድ የአገር ነፃነት ትግል ይጠይቃል። ትግሉን በሚገባ ለመቅረጽ ነፃነት በታሪካችን ብቻ ሳይሆን
በመርህና በተግባር ዛሬ ስለሚኖረዉ ፍቺ ዘርዘር አድርገን መወያየት እንችላለን። ማለትም፣ “በዲሞክራሲ” ዙሪያ በተደረገዉ መልክ
“ነፃነት” እንደ ሃሳብ፣ ዕሴትና ስልት ትርጉሙ በቅጡ ሳይስተዋልና ሳይጨበጥ ተደጋግሞ በመባል ብቻ የተለመደ ህይወት የሌሽ ቃል
ሆኖ እስካልቀረ ድረስ።
ለዉይይቱ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ጥቂት ሃሳቦች እዚህ ባጭሩ ልጠቁም። በመጀመሪያ ነገር ነፃነት ኢትዮጵያዊያን የወያኔን አገዛዝ
በመቃወም በየረድፉ ለሚያደርጓቸዉ እንቅስቃሴዎች መሠረታዊ አደራጅ መርህ ሆኖ ነጥሮ ሊወጣና ሥራ ላይ ሊዉል ይችላል። በዚህ
ቅርጹና ይዘቱ ለተቃዉሞ ትግሉ የላቀ ጥራት ሊሰጥና የዕሴት መሃል ሊሆን ይቻላል። ሁለተኛ፣ ያለፉ አገር ወዳድ የኢትዮጵያ
ትዉልዶችና ጅግኖች ካደረጓቸዉ ዓለም ያወቃቸዉ የአገር ነፃነት ጥበቃ ክንዉኖች ጋር፣ ከብሔራዊ ቅርሳችንና ልምዳችን ጋር፣ ይበልጥ
ያቀራርበናል። በዚህ መንገድም የዛሬዉን የኢትዮጵያዊያን አገር የማዳን ትግል ያጠናክራል። ለትግሉ በሙሉ የኢትዮጵያዊነት ልብና
መንፈስ፣ እንዲሁም በግልጽ ስልታዊ ራዕይ፣ ተነሳሽነታችንን ያቀላጥፋል። በተጨማሪ ነፃነትን በዘመናዊ ሃሳብና መርህ ደረጃ ከዜጐች
ስቭል መብቶችና ከብሔራዊ ህልዉናችን ጋር በሚጣጣም አዲስ መልክ ተንትኖ፣ ተወያይቶና በስምምነት ተቋማዊ ቅርጽ ሰጥቶ
መጠበቅና ማሳደግ ያስችለናል።
የነፃነት ትግሉ መስኮችና ሃይሎች
ኢትዮጵያዊያን አገር ቤትና ዉጪ በተለያዩ ሁኔታዎችና ጊዜዎች የተቃዉሞ ጥረቶች ከማድረግ አቋርጠዉ ባያዉቁም እንደ አገር ከያዘን
ዉስብስብና ሁለገብ ዉጥረት የምንወጣዉ በምን አይነት የተቀናበሩ የትግል ዘዴዎችና እንቅስቃሴዎች ነዉ የሚለዉ ጥያቄ ዛሬም
አከራካሪ ጉዳይ ነዉ። በአመዛኙ የሚደመጠዉ ክርክር ሁለት አቀራረቦችን በአማራጭነት ያነጻጽራል - ሰላማዊ እንቅስቃሴ ወይስ
የትጥቅ ተጋድሎ? በቅርቡ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ እንዳቀረበዉ ሃሳብ ከሆነ ደግሞ ያለን አማራጭ በአንዱ ወይም በሌላዉ የትግል
ጐዳና መጓዝ ሳይሆን ትግሉ በሁለቱ አይነት አኪያሄዶች ተጨባጭ ወይም የተሰላ ጥምረት የሚጠናከር መሆኑን በመገንዘብ ነዉ።
የአገር ነፃነት ትግሉን አቃለን አንድ ጐሣ ነፃ አዉጭ ነኝ ባይ ብቸኛ ወገን ያቋቋመዉን የማንነት ፖለቲካ ያማከለ አገዛዝ አስወግዶ በሌላ
ተመሳሳይ “የብሔሮች” ፖለቲካ አራማጅ ወገን አገዛዝ የሚተካ አድርገን የምናየዉ አይደለም። አለበለዚያ ከችግራችን ዞር ማለት እንጂ4
መራቅ አይሆንም። ትግሉ ዜግነትን ቀደምትነት የሚሰጡ የተለያዩ ግን ተደጋጋፊ የሆኑ ገጽታዎች፣ ቅርጾችና ዘርፎች ይኖሩታል።
እነዚህም የህብረተሰብ፣ የባህል፣ የሃሳብ፣ የእምነት፣ የፖለቲካና የስነልቦና ስምሪቶችን ያጠቃልላሉ። ወደ ኢትዮጵያ ነፃነት የሚወስደዉ
መንገድ በዘላቂ እንቅስቃሴ እንዴት ይቀየስና ይጠረግ ለሚለዉ ከባድ ጥያቄ የተለያዩ፣ ሰላማዊ ዉጊያንና የነፍጥ ትግልን አማራጭነት
ያካተቱ፣ አከራካሪ መልሶች በተለያዮ አገር ወዳድ ወገኖች በቀጣይነት ሊቀርቡ ይችላሉ።
ግን ትግሉን ዉጤታማ በሆነ መንገድ ወደፊት ለማራመድ ልዩነቶችንና ክርክሮችን በቅድሚያ አካቶ መወሰን ወይም ሙለ በሙሉ
መቋጨት አስፈላጊ የሚሆን አይመስለኝም። ከወዲሁ አንድ ወገን ለአንዴና ለሁሌ ይህ የትግል ዘዴ ወይም አማራጭ ያዋጣል፣ ያ ስልት
ትክክል አይደለም ወይም አያዛልቅም ብሎ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ወገኖችም ሊወስን የሚችልበት ሁኔታ አለ ማለት አይቻልም።
እኔ በበኩሌ በልዩ ልዩ የማህበረሰብ፣ የባህል፣ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ፣ እንዱሁም በተለያዩ ተቋማትና ህዝባዊ ድርጅቶች
አካባቢዎች የወያኔን ጨቋኝ አገዛዝ በሰላም ዉጊያ ለመቋቋም የተነሱና የሚነሱ የዜጐች ስብስቦችን በስልት የሚያቀናብርና አቅጣጫ
የሚሰጥ ሰፊ አገር አቀፍ የህብረተሰብ እንቅስቃሴ መጀመር፣ በሂደትም ማሳደግ ወሳኝ ይመስለኛል።
የኢትዮጵያ ነፃነት ትግል በዘላቂነት እንዴት ተደራጅቶ ይኪያሄድ የሚለዉን ከባድ ጥያቄ ለመመለስ አማራጮች አነጻጽሮ ይህ መንገድ
ወይም ያ ዘዴ ይሻላል ከማለት ባሻገር በጠቅላላ የትግሉን አስፈላጊ መስኮች ወይም ደረጃዎችና እዉንም ሆኑ እምቅ አቅሞች መለየት፣
በትስስር የሚገነቡበትን መንገድም በቅጡ ተንትኖ መረዳት ይጠቅማል።
በመጀመሪያና በመሠረቱ ኢትዮጵያዊነት የአገር ነፃነት ትግሉ ዕሴት መሃልና ዋና አንቀሳቃሽ ሃይል ነዉ። ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ዛሬ
በስሜት ብቻ የምናረጋግጠዉ፣ በበቂ ዝግጁነት አነሳሽና አታጋይ አቅም ሆኖ የተሰጠ ወይም የቀረበ ሳይሆን በእምነት፣ በሃሳብ፣
በስልትና በእንቅስቃሴ እሱን ራሱን ማደስና ማጠናከር አስፈላጊ ሆኗል። እንደምናዉቀዉ፣ ከተማሪዉ ንቅናቄ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ
ድረስ የጋራ ብሔራዊነታችን በሆኑ ባልሆኑ አብዮተኞች ቅጥና ወሰን ባጣ አቀራረብ ሲገመገም፣ ሲጣጣል፣ ሲካድና ሲቦረቦር ቆይቷል።
የተገላቢጦ በጠባብ ጐሠኛ ፖለቲከኞች የበላይነትና መሃልነት ጥግ እንዲይዝ ተደርጓል። በወያኔዎች “አበዮታዊ”/ “ልማታዊ” አገዛዝ
አይን ያወጣም መሰሪም የዘረኛ ፖለቲካ ጥቃት ከዉስጥ እየተኪያሄደበት ነዉ። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ለነፃነት ትግሉ አንቀሳቃሽ ሃይልና
አቅም ብቻ ሳይሆን ራሱ በትግሉ መነቃቃት፣ ማንሰራራትና መበረታታት የሚያስፈልገዉ ነዉ። በዚህ ደርጃ ኢትዮጵያዊነትን ለማደስና
ለማጠናከር የምናደርገዉ ጥረት ሁሉ የአገር ነፃነት ትግሉ ዋና አካል ነዉ የሚሆነዉ።
ጥረቱ በሦስት አንጻራዊ ልዩነት ያላቸዉ ግን የተሳሰሩ የትግል ሜዳዎች ወይም ደረጃዎች የሚደረግ ነዉ። አንደኛ፣ሃሳብ በሰፊዉ
(ማለትም ራዕይን፣ ዕሴቶችን፣ እምነቶችን፣ መርሆችን፣ ትንተናንና ትችትን አጠቃሎ) ተንቀሳቃሽና አንቀሳቃሽ አቅም የሆነበት ወይም
ሊሆን የሚችልበት የትግል መስክ አለ። ሁለተኛ፣ መሠረታዊ ሃሳቦች ከተጨባጭ የአገር ጉዳዮችና ከህብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄዎች፣
ጥቅሞች፣ ሆኔታዎችና እንቅስቃሴዎች ጋር ተቀነባብረዉና ተጣጥመዉ የሚቃኙበትና የሚስተዳደሩበት የፖለቲካ ስልት ደረጃ ይገኛል።
ሦስተኛ፣ ስልታዊ ግቦችና ተልዕኮዎች ተፈጻሚ የሚሆኑባቸዉና ለስልት ህያዉ ቅርጽ ሰጪ የሚሆኑ የተለያዩ የአካባቢዎች ጉዳዮች፣
የአገር ወዳድ ታጋይ ድርጅቶች እቅዶችና የሚንቀሳቀሱባቸዉ ታክቲኮች ወይም ዘዴዎች መስክ ነዉ። እነዚህን የተዛመዱ የኢትዮጵያ
ነፃነት ትግል ክፍሎች እዚህ በዝርዝር ልሄድባቸዉ ሳልሞክር በጉዳዮቹ አግባብነት ያለዉ፣ ሃሳቦችና ስልት ላይ ያተኮረ፣ መጠነኛ
ዉይይት በቀረዉ የዚህ ጽሁፍ ክፍል አቀርባለሁ። ይህን ከማድረጌ በፊት ግን ስለኢትዮጵያዊነት ራሱ ማለት የጀመርኩትን ልጨርስ።
በአገር ነጻነት ትግሉ ኢትዮጵያዊነት ወሳኝ ሃይል የሚሆነዉ እንዴት ነዉ? ይህ ጥያቄ በቅድሚያ የጋራ ብሔራዊነታችንን ይዘት ወይም
ትርጉም ይመለከታል። አያይዞም የኢትዮጵያዊነትን ጥበቃና ቀጣይነትና ጉዳይ ያነሳል። በይዘት ደረጃ ኢትዮጵያዊነት መሠረቱ በረጅም
ታሪክ ሂደት የዳበረ፣ ሊካድ የማይቻል፣ ተጨባጭ ብሔራዊ ህልዉናችንን፣ እንዲሁም የሚሰማንንና የምንኖረዉን ልምዳችንን፣ አገር
ወዳድ ስሜታችንንና ዕሴቶቻችንን ያካትታል። ይህ አገራዊ መነሻችን ለዛሬዉ የነፃነት ትግል ቀዳሚነት ያለዉ እዉንና እምቅ አንቀሳቃሽ
ሃይል ነዉ። ስለሆነም በመተማመን የምንቀበለዉ፣ በነፃ ራሱን ገላጭ ከማድረግ የማናግደዉ ሁኔታ ነዉ።
ይህን ስንል ግን ከዛሬዉ የነፃነት ትግል ክብደትና ዉስብስብነት ጋር በማይመጣጠን የተለምዶ ወይም ስሜታዊ ብሔርተኝነት ተወስንን
አይደለም። ለትግሉ አንቀሳቃሽ “ነዳጅ” የሚሆን በቂ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዜጐችና ታጋይ ወገኖች ዘንድ ቢኖርም ትግሉን አቅጣጫ
ሰጪ ወይም ነጂ የፖለቲካ ሃሳብና ስልት ሊጓደል ይችላል፣ በእርግጥም ተጓድሏል። ወይም የተደራጀ አገር አቀፍ ምሁራዊ፣ ሞራላዊና
ፖለቲካዊ አመራር እጥረት ሊኖር ይችላል፣ በእዉነቱም አለ።
የብሔራዊ ህልዉናችንን ታሪካዊና ባህላዊ መሠረት ማረጋገጥ ያለብን ቢሆንም ኢትዮጵያዊነት ዛሬ ከቅድመ አያቶቻችን ኢትዮጵያዊነት
በተለየ መልክና መጠን የተወሳሰበ ነዉ። ማለትም፣ በሰፊዉ የጋራ ብሔራዊ ህይወታችን አካላትና ገጽታዎች ከሆኑ የዜጐች፣ የበዙሃን
ማህበረሰቦችና ፖለቲካ ወገኖች ጉዳዮች፣ ጥቅሞች፣ ፍላጐቶችና ምኞቶች ሽግሽግ ወይም ቅንብር ተለይቶ የሚታይ አይደለም።
ኢትዮጵያዊነት ዛሬ የሚረጋገጠዉ በታሪካዊ መሠረቱና ክንዉኖቹ ብቻ ሳይሆን በዘማናዊ አብዮታዊ ለዉጡና እድገቱ ጭምር እንደሆነ
እናዉቃለን፣ ምንም እንኳን የለዉጡ እንከናማነትና ከልክ ማለፍ የሚካድ ባይሆንም።5
ኢትዮጵያዊነትን ከመጠበቅና ቀጣይ ከማድረግ አኳያ ዋናዉ ተግዳሮት በአብዮቱ ጊዜና በድህረ አብዮቱ ዘመን አገራዊ ህልዉናችን
ከተለያዩ የዉስጥም የዉጭም ወገኖች፣ በተለይ ከትግሬ ነፃ አዉጪ ነኝ ባዩ ገዢ ስብስብ፣ የደረሱበትን የርዕዩተ ዓለም፣ የፖለቲካና
የስነልቦና ጥቃቶች በብቃት የመቋቋሙና የመወጣቱ ጉዳይ ነዉ። እዚህ ላይ ቁም ነገሩ ኢትዮጵያዊነትን የብሔራዊ ብሶታችን፣
ስጋታችንና ተጐጂነት ስሜታችን መገለጫ ከማድረግ አልፈን፣ ሲበዛ ተከላካይ የሆነ የአገር ወዳድነት አዝማሚያን ተሻግረን፣ በሃሳብ፣
በስልትና በእንቅስቃሴ አመንጭነት የነፃነት ትግሉ ሃይል ማድረግ ነዉ።
ይህንኑ ነጥብ በይበልጥ ትኩረት ለመግለጽ፣ የአገር ጥቃቱን መከላከል ማለት ኢትዮጵያዊነትን በተጐዳና በተዳከመ ሆኔታዉ እንዳለ
ማትረፍ ሳይሆን በትግል ማረጋገጥ፣ ማደስ፣ ማሻሻልና ማጠናከር ማለት ነዉ፤ ያሉ አስከፊ ሆኔታዎችን መለወጥ፣ የፈረሰዉን እንደገና
መገንባት፣ የጠፋዉን መልሶ ማልማት ነዉ የሚሆነዉ። ብሔራዊ ህልዉናችንን መተንፈሽና መላወሻ የነሳ፣ ለአገሪቱ ዜጐች ነፃነት
የማይበጅ ተደራራቢ አምባገነናዊ የርዕዩተ ዓለም ቀኖና እና የዘረኛ ፖለቲካ ቅርፊት ደለል በደለል ላልጦ ማስወገድ የሚያስችለን
ተከላካይም አጥቂም የኢትዮጵያዊነት ትግል ማኪያሄድ ማለት ነዉ።
ኢትዮጵያዊነትን ዛሬ ለአገር ነፃነት ትግል ብቁ ሃይል የማድረጉን ተግዳሮት በሁለት የተያያዙ አነሳሶች መግጠም እንችላለን። በአንድ
በኩል፣ የመላ ዜጐችን እኩል ስቭል መብቶች ለማረጋገጥና የጋራ በሔራዊ ህይወታችን ታሪካዊና ወቅታዊ ጉድለቶች ለሟላት ስንጣጣር፣
በብቸኝነት ወገንተኛ የሆኑ የአገር ህልዉና ተጻራሪና ተፈታታኝ ዘረኛ የፖለቲካ እቅዶችን፣ በጠቅላላ ደግሞ ጥልቅ ታሪካዊ መሠረት
ያለዉን ብሔራዊ ባህላችንን በጅምላ አጉዳፊና አጣጣይ ጥራዝ ነጠቅ ዘመናዊነትን፣ በሃሳቦችና ዕሴቶች መስከ ከመቋቋም ወደ ኋላ
በማፈግፈግ እንዳልሆነ በማመን ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ የብሔራዊ ህይወታችን በጐ አካላትና ገጽታዎች የሆኑ የባህል፣ የእምነትና
የፖለቲካ ብዙሃንነትን በመርህና በተግባር ግልጽ አገራዊ አገባብና አቀማመጥ በመስጠት፣ እንዲሁም ከወገንተኛ ፖለቲካ እዉን አንጻራዊ
ነፃነት ባለዉ ህገ መንግሥታዊና ተቋማዊ ሥርዓት ዉስጥ መቀረጽና መስተዳደር የሚችሉበትን መንገድ በመቀየስ ነዉ።
ትግሉ በሃሳቦች መስክ
የፖለቲካ ሃሳቦች (እንበል “ነፃነት” እና “ዲሞክራሲ”) ምኞቶች ከመሆነ በተረፈ በአገር የማዳኑ ትግል ሊኖራቸዉ የሚችል ሚናና ሥራ
ምንድን ነዉ? በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጉዳዮች ዉስጥ ያላቸዉ እዉንና እምቅ አገባብ ምን ይመስላል? በጁም አልበጁም ከተማሪዉ ንቅናቄ
ዘመን ጀምረዉ ያልተለዩንን ሃሳቦች ራሳቸዉን በዚህ መልክ ዛሬ ለፈታሽ ትንተናና ዉይይት መክፈት ለትግሉ ጥራት ከመስጠት አኳያ
ጠቃሚ ነዉ። በዋናነት፣ የትግሉ መሠረትና መነሻ የሆነዉን፣ በታሪክ ሂድትም አጋጣሚም ሥር የያዘና በዝግመት የዳበረ
የኢትዮጵያዊነትን ባህል ተራማጅ በተባሉ ሃሳቦች ለመቅረጽ ከምንሞክረዉ ዘመናዊ የፖለቲካ ብሔርተኝነት በቅጡ ለመለየት ይረዳናል።
አንዱ የብሔርተኝነት ሞድ በሌላዉ ተለዋጭ አለመሆኑን ወይም በተናጠል የኢትዮጵያን ነፃነት ዛሬ ሙሉ በሙሉ ማረጋገጫ መሆን
እንደማይችል ያስገነዝበናል። የታሪካዊና ዘመናዊዉ ኢትዮጵያዊነታችን ዉርርስ እዉን እንደሆነ በመገንዘብም ሁለቱ የብሔራዊ
ህይወታችን መገለጫዎች ግንኙነት አላቸዉ ወይስ የላቸዉም የሚለዉን ጥያቄ ወደ ጐን ትተን የዝምድናቸዉን ቅርጽና ይዘት በትኩረት
መፈተሽ፣ ማድስና ማሻሻል ያበቃናል።
የህ አይነት ከአገር ህልዉና ጋር የተያያዘ ትንተናና ግንዛቤ ተጨማሪ ጥቅም አለዉ። ከተማሪዉ ንቅናቄ ዘመን ጀምሮ አገሪቱ ዉስጥ
የተስፋፋዉንና በወያኔዎች አገዛዛ የተለየ ፀረ ኢትዮጵያ ቅርጽ የያዘዉን አምባገነናዊ የአብዮታዊነት አስተሳሰብና አሠራር ልምድ
ሥርዓታዊ እንከናማነት በግምገማ ግልጽ በማድረግ ለሰፊና ጥልቅ አገር አቀፍ የፖለቲካ ለዉጥ መንገድ ይከፍታል። ይህ ጥረት
በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ይበልጥ ተቀባይነት ለሚያገኝ የተሻለ የፖለቲካ ሃሳቦች አቀራረብና አፈጻጸም ቦታ መፍጠር ያስችለናል።
የፈጠራዉ ሥራ ቀላል ባይሆንም አስፈላጊነቱ ግልጽ ይመስለኛል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጠቅላላ ለብዙ አመታት ተራማጅ
ለተባለ አምባገነናዊ ርዕዩተ ዓለም ተገዢ ሆኖ የቆየ ቢሆንም ተገዢነቱ የፖለቲካ ጽንሰሃሳቦችንና መርሆችን በአገሪቱ ከማዳበር አኳያ
ምንም ያህል ትርፍ ወይም እድገት አላመጣም። ይባስ ብሎ የፖለቲካና የብሔራዊ አስተሳሰብ ኪሳራ አድርሶብናል። በተራ ዜጐች
መካከል ብቻ ሳይሆን በምሁራዊና ፖለቲካዊ ሊህቃን አካባቢዎችም ቢሆን ነፃነትን፣ ዲሞክራሲን፣ የህግ በላይነትን፣ ፌደራላዊ
መንግሥትንና ሌሎች ቁልፍ ዕሴቶችን በሚመለከት እንደ አገር ምንም ያህል ተጨባጭ እዉቀትና ልምድ ወይም ጠቃሚ የዉይይትና
የድርድር ባህል አላካበትንም።
ሆኖም በነዚህ ዕሴቶች ስም የኢትዮጵያ ህዝብ ታምሷል፣ አገር ተበጥብጦና ተከፋፍሎ እንዳልነበረ ሆኗል፣ ብዙ ደም ፈሷል። “በሰፊዉ
ህዝብ” ስም ብቸኛ አድራጊ ፈጣሪ የሆኑ ጠባብ አብዮተኞች፣ ወገንተኞችና ዘረኞች ብዙ ተናግረዋል፣ ጽፈዋል፣ ተንቀሳቅሰዋል። ይሁን
እንጂ ታጋይ ወገኖችና ምሁራን የዕሴቶቹን ጽንሰሃሳባዊ ይዘት፣ ተጨባጭ ትርጉምና አገራዊ አገባብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን
ለራሳቸዉም በስፊዉና በጥልቀት አብራርተዉት አያዉቁም። ከወገንተኛና ጐሠኛ ንትርክ ወይም ከአምባገነናዊ ገዢዎች አገልጋይነት
ወጣ ብለዉ አገር ጠቃሚ ትንተና፣ ክርክርና ዉይይት እምብዛም አላኪያሄዱም። ስለዚህ ተራማጅ ሃሳቦች ቃል በቃል ወይም በተለምዶ
አባባል በአገሪቱ ፖለቲካ ዉስጥ መዘዋወር ባያቋረጡም በቅጡ ሳይረቁና ተቋማዊ ቅርጽ ሳይዙ ባንዴ ተድበስብሰዉም ግትር ፎርሙላ
ሆነዉም ቀርተዋል። ይህ ደግሞ ሃሳቦቹን በድፍኑ፣ በጭፍን ቀኖናዊነት፣ የባሰ አጨቃጫቂ፣ አወዛጋቢና አጣይ አድርጓቸዋል።6
የዛሬዉ የኢትዮጵያ ነፃነት ትግል የሚነሳዉ እንግዲህ ከዚህ የብሔራዊ ዉጥረታችን አካል የሆነ የሃሳቦችና ዕሴቶች ኪሳራ ነዉ። ትግሉ
የሚጠበቅበት በሕይወት አልባነት፣ ተደጋግመዉ በመባል ብቻ፣ የአነጋገር ዘዬ ወይም ፎርሙላ ከመሆን ሳያልፉ የቀሩ የፖለቲካ
ቃላትንና ፈርጆችን ከብሔራዊ ህልዉናችን ጋር የሚግባባ ህያዉ አተረጓጐም መስጠት፣ ጽንሰሃሳባዊና መርሃዊ ይዘታቸዉን በሰፊዉ
ለኢትዮጵያ ህብረተሰብና መንግሥት የሚለቁባቸዉን ሁኔታዎች በተቻለ መጠን ማመቻቸት ነዉ። ይህን ማድረግ የሃሳቦችን መስክ
ራሱን መኮትኮት፣ ማረምና ማጥራት ማለት ነዉ። መስኩን የአገር ነፃነት ትግሉ ዕሴቶች፣ አላማዎችና ስልቶች ነጥረዉ የሚወጡበት፣
ምሁራዊ ሥራ በቀጣይነት የሚሠራበት፣ በአንጻር ራሱን የቻለ ሜዳ ወይም መድረክ ማድረግ ማለት ነዉ። ችግሩ ግን ተቃዋሚ
ፓርቲዎችና አገር ወዳድ ወገኖች በጠቅላላ፣ ምሁራንም ጭምር፣ እንዲህ አይነት የሃሳብ እንቅስቃሴ ከማድረግ ወደ ኋላ ይላሉ።
ይህ ለምን ይሆን? ዋናዉ ምክንያት መሠረታዊ ሃሳቦችን መፈተሽና መቀበል አለመፈለግ ወይም አለመቻል ሆኖ አይታየኝም፣ ምንም
እንኳን በሃሳብ መስክ ተንቀሳቃሽ መሆን ለማንም ሰዉ ቀላል ነዉ ባይባልም። በኔ ግምት ብዙዎቻችን የአገር ችግሮችን ስንመለከትና
ስለችግሮቹ ስንወያይ ሃሳቦችና ዕሴቶች ራሳቸዉን በቀጥታና በግልጽ የትንተና ወይም የፍተሻ ኢላማ አድርገዉ ስለማያቀርቡ ነዉ።
በአንድ በኩል የሃሳቦች፣ የእምነቶችና የዕሴቶች ትርጉሞች አብዛኛዉን ጊዜ ትንታኔ በማያስፈልግበት ሆኔታ ይበልጥ በሚስቡን ጭብጥ
ጉዳዮች፣ ክርክሮች፣ ምስሎች፣ ምልክቶችና ትረካዎች ተጠቃለዉ በአንድ አፍታ ይካተታሉ። ለምሳሌ ሰንደቅ ዓላማና የክርስቶስን
ስቅለት ወካይ መስቀል ብሔራዊ ዕሴትንና መንፈሳዊነትን በተጨባጭ መልእክትነት ወይም ምስልነት ይይዛሉ፣ “ይሸፍናሉ”።
እዚህ ላይ ቁም ነገሩ ብዙዉን ጊዜ የመልእክቶቹ ተጨባጭ ጉዳይና የሚዳሰስ ቅርጽ ከሚወክሉት ረቂቅ ትርጉም ልቆ ይስባል።
ዉክልናቸዉ ራሱ ከሚወክሉት ጥልቅ ፍሬ ነገር ጐልቶና አይሎ ንቁ ሃሳብን ወይም እምነትን ጥግ ያስይዛል። በሌላ በኩል ደግሞ
በብዙዎቻችን ዘንድ ሃሳቦች ምንም ያህል ሳቢ ወይም አወያይ የማይሆኑት “በረቂቅነታቸዉ” ከተለምዶ ግንዛቤ ወይም ከተጨባጭ
ሁኔታዎች የራቁ ስለሚመስሉን ነዉ። “የራቁ ስለሚመስሉ” የምለዉ ሃሳቦች በእዉነቱ ብዙዉን ጊዜ በቀጥታ ከሚስቡን ጉዳዮችና
ሆኔታዎች ብዙ የማይርቁ መሆናቸዉን በመረዳት ነዉ።። አንድን መሬት ላይ አለ የተባለ እዉነታ ወይም ጉዳይ ትንሽ ገባ ብለን
ስንፈትሸዉ ሃሳብ ወይም ትርጉም ይወጣዋል። ከአንጻራዊ አመለካከት፣ ከአተረጓጐም፣ ከትረካ አካቶ ነፃ ነዉ የሚባል አይደለም።
ይሁን እንጂ በወያኔ አገዛዝ ተቃዉሞ እንቅስቃሴዎቻችን ብዙዎቻችን በአመዛኙ ይበልጥ የምንሳበዉ በአንድ አፍታ በሚታዩንና
በምንጨብጣቸዉ ገዳዮች፣ ችግሮች፣ ፖሊሲዎች፣ ድርጊቶችና ሁኔታዎች እንጂ እነዚህ ሥር ወይም ኋላ ባሉ ሃሳቦችና የፖለቲካ
አስተሳሰብ ሰዋሰዉ አይደለም። የፖለቲካ ሃሳብ ወይም መርህ ግድ ሲለንም የቃል በቃል ዝዉዉሩን ወይም ፍቺዉን አልፈን ስለ እዉን
ትርጉሙ ፈጠራ፣ አስተዳደርና ጥበቃ እምብዛም አንጨነቅም። በተለያዩ የአገር ማዳን እንቅስቃሴዎች ስንሳተፍ ድርጊትና ሃሳብ በስልት
የሚተባበሩባቸዉን፣ እርስ በርስ የሚቀራረጹባቸዉን፣ ሁኔታዎቸ መፍጠር አስፈላጊነት በሚገባ ባለማስተዋል ሃሳብ በተጠናቀቀ ቅርጽና
ይዘት ተሰጥቶ በቀጥታ በድርጊት የሚወሰድና ተግባራዊ የሚሆን ይመስለናል።
በኢትዮጵያ ነፃነት ትግል እነዚህን ዉስንነቶች እንዴት እንወጣ? በኔ ግምት በሃሳብ መስክ የምናደርገዉን የተለመደ ወገንተኛ ወይም
ድርጅታዊ አቀራረብ ዘልቀን በመስኩ ስምሪታችንን፣ በተለይ የትግሉን አመራር፣ በሁለት የተያያዙ አቋሞች ወይም አገባቦች መቃኘት
ያስፈልጋል። አንዱ አገባብ የተመዛዘነ ተጨባጭ ትንተናና ትችት በቀጣይነት ማድረግ የሚያስችል የተቀናበረ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ነዉ።
ይህ አገባብ በጠባቡ የአመራር ቡድኖች ወይም የባለሙያ ምሁራን ሃላፊነትና ቃል ኪዳን ብቻ ሆኖ የሚታይ አይደለም። ብዙዎቻችን
በየደረጃዉ እንደያቅማችንና ሁኔታችን ልንሳተፍበት እንችላለን፣ ይገባናልም። ሌላዉ በሃሳብ መስክ የሚኖረን ስምሪትና አመራር ራዕያዊ
ወይም ትንቢታዊ ሊባል ይችላል። ይህ አገባብ በኢትዮጵያ ነፃነት ብርቱ እምነት ማሳደርንና ተስፋ ማድረግን፣ በነፃነት እንቅስቃሴዉ
ድል መጠባበቅን፣ እንዲሁም የትግሉን ዕሴቶች ለህዝብ በሰፊዉ ተደራሽ የሆነ አንቂና አነሳሽ አተረጓጐም መስጠትን የሚያካትት ነዉ።
ስልት በነፃነት ትግሉ
በኢትዮጵያ ነፃነት ትግል መሠረታዊ ዕሴቶችንና አላማዎችን በሚገባ ቀርጾ የመከታተል አስፈላጊነት ግልጽ ነዉ። አያይዞም የትግሬ ነፃ
አዉጪ ነኝ ባዩን ገዢ ወገን የማንነት ፖለቲካ ቀኖና በተጨባጭ ሁኔታዎች አገባቡና መገለጫዎቹ ብቻ ሳይሆን በመርህና ሃሳብ መስክም
መቋቋም ግድ ይላል። የአገሪቱን ዜጐች ስቭል መብቶችና ህብረተሰባዊ ጥቅሞች በሰፊዉ ወክሎ፣ በአገር ተቆርቋሪነት ስሜት ተነሳስቶ
መንቀሳቀስም ያስፈልጋል። ነገር ግን እነዚህ ጥረቶች እንዳሉ፣ ተደማምረዉም ቢሆን፣ የወያኔን መሰሪ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በብቃት
ሊዋጉትና ከሥሩ ሊመነግሉት አይችሉም። እርግጥ ያለ አገር ወዳድነት ስሜትና ያለ ፖለቲካ ሃሳብ የኢትዮጵያ ነፃነት ትግል በሚገባ
ሊኪያሄድ አይችልም፤ ግን ደግሞ ስሜትና ሃሳብ ያለ ስልት ትግሉን አቀናብረዉ፣ መሰናክሎቹን ተቋቁመዉ፣ ወደ ፊት አያራምዱትም።
እንደ ግለሰብ ወይም ድርጅት አባል ሃቀኛ ሆኖ በአንድነት፣ በዜጐች ስቭል መብቶች፣ በፍትህና በዲሞክራሲ ማመን ራሱ በአንድ አፍታ
የአገር ነፃነት ትግሉን አቅጣጫና መንገድ አይቀይስም። እምነቱ ለትግሉ ጥራትና ዘላቂነት አስፈላጊ እንጂ በቂ ሆኔታ አይደለም።
ስላልሆነም አያይዘን ማንሳት ያለብን ዋና ጥያቄ የአገር ማዳን ትግሉ ምን አይነት ሃሳቦች፣ ዕሴቶችና የህብረተሰብ ጥቅሞች ይወክላል
ብቻ ሳይሆን እንደ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ምን አይነት ስልታዊ ቅርጽ ይይዛል፣ እንዴትስ ይኪያሄዳል ነዉ። ስልት ስል የማተኩረዉ
ከተወሰኑ ታጋይ ወገኖች ተልዕኮዎች፣ ድርጅታዊ ስሌቶችና የእንቅስቃሴ መላዎች ባሻገር በግልጽ ኢትዮጵያዊነትን ያማከለ፣ የጋራ7
ብሔራዊ ህይወታችን ላይ የተመሠረተ ሰፊና ጥልቅ የትግል ቅንብር ላይ ነዉ። ጉዳዩን ከተለምዶ ግንዛቤ አልፈን ትንሽ ተንተን አድርገን
ማየቱ ጠቃሚ ይመስለኛል።
ስልት የሚያቀናብረዉና አቅጣጫ የሚያስይዘዉ ተጨባጭ የትግል ሃይሎችን፣ ፀጋዎችንና እንቅስቃሴዎችን ብቻ ሳይሆን ሃሳቦችንና
ዕሴቶችንም ጭምር ነዉ። ኢትዮጵያዊነት ራሱ በፖለቲካ ሃሳብ ወይም በስሜት ብቻ የማናራምደዉ፣ በታሪክ ሂድት የዳበረ ተጨባጭ
ብሔራዊ ህልዉናችንና ልምዳችን ቢሆንም ከገባበት ከባድ ዉጥረት ለማዉጣት በምናደርገዉ ትግል ስሜትንና ሃሳብን በጥልቀት
አቀናብሮ የያዘ ስልታዊ ራዕይና ዘዴ ዛሬ ከመቸዉም ጊዜ ይበልጥ ያስፈልገናል። ከዚህ ሆኔታ ጋር የተያያዘ የነፃነት ትግሉ ስበት መሃል
ወይም አስኳል ሊሆን የሚችል አገራዊ እንቅስቃሴ ነጥሮ የመዉጣት አስፈላጊነትም አለ።
የፖለቲካ ሃሳቦች (ለምሳሌ “አንድነት”፣ “ነፃነት”፣ “ዲሞክራሲ” እና “ፌደራላዊ መንግሥት”) ለአገር ማዳን ትግሉ መመሪያ ወይም
መመዘኛ (አርአያ) ብቻ ሳይሆኑ በትግል አቅም ገምቢነታቸዉ በተለያዩ ሁኔታዎች ስልታዊ መስተዳደርና ይዘት የሚሰጣቸዉ ናቸዉ።
እዚህ ላይ የስልትን ወሳኝ አገባብ ወይም ሚና በግልጽ መገንዘብ ይረዳል። ስልትን ለአንድ የአገር ማዳን ትግል መሠረታዊ ተግዳሮት
መልስ አድርገን ልናየዉ እንችላለን። ተግዳሮቱ የአገር ጉዳዮችን፣ ችግሮችንና ሁኔታዎችን በተመዛዘነ ተጨባጭ አቀራረብ የሚገልጹ
ጥናቶችን፣ ትንተናዎችንና ሃሳቦችን ፍቱን ከሆኑ ወይም ከተለያዩ እንቅስቃሴዎችና የተወሰኑ ድርጊቶች ጋር በሥራዓታዊ መንገድ
ማገናኘት ነዉ፤ ጠቅላላ ሃሳቦችንና ዕሴቶችን በመለስተኛ የአገር ወዳድ ታጋይ ወገኖች ተልዕኮዎች፣ ግቦች፣ ታክቲኮችና ተግባሮች በሚገባ
መተርጐምና መመንዘር ነዉ፤ የተለያዩ የትግል ደረጃዎችን፣ መስኮችንና ስምሪቶችን በቀጣይነት ማቀናበር ነዉ።
እዚህ ላይ መረዳት ያለብን ሁለት የተያያዙ ዋና ነገሮች አሉ። አንደኛ፣ ስልት የሚነደፈዉ በመሠረታዊ ሃሳቦችና ዕሴቶች መስክ ዉስጥ
ቢሆንም ቅርጽ የሚይዘዉ ራሱን በተወሰነ ደረጃ ከመስኩ ገለል አድርጐ ነዉ። በሌላ አባባል፣ ከረቂቅ ሃሳብ ወይም መርህ አንጻራዊ
ነፃነቱን ጠብቆ፣ ማለትም የራሱን ተግባራዊ አስተዉሎ፣ የራሱን የትግል ስነአመክንዮ ይዞ ነዉ። ይህ በአንጻር ራስ ቻይ ምክንያታዊነቱ
ነዉ ስልትን የተለያዩ የትግል መስኮች በአገር ደረጃ ማቀናበርና ማስተዳደር የሚያስችለዉ። ሁለተኛ፣ ስልት የሚነደፍባቸዉና ተፈጻሚ
የሚሆንባቸዉ አገራዊ ጉዳዮች፣ ስሜቶችና ዕሴቶች፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሃሶቦች፣ እንቅስቃሴዎችና ሁኔታዎች ለስልት ህያዉ ቅርጽ
ያዥነትና ዉጤታማነት አስተዋጽዎ አላቸዉ። እነዚህ ነገሮች የተወሰኑ ወገኖች ወይም ድርጅቶች በቀላሉና በጠባቡ የሚያነሷቸዉ
የሚጥሏቸዉ ሳይሆኑ በህያዉነት የአገር ነፃነት ትግሉ ስልት ዉስጥ የሚካተቱ፣ ስልቱን ተንቀሳቃሽ ቅርጽ የሚሰጡ ወይም ሊሰጡ
የሚችሉ ናቸዉ።
ለማጠቃለል፣ በዚህ ስልትን በሰፊዉና በጥልቀት ባማከለ መንገድ ማሰብና ተባብሮ መንቀሳቀስ የኢትዮጵያን ነፃነት ትግል በብርታት፣
በብቃትና በዘላቂነት ለማኪያሄድ ይረዳል። አንዱ የዚህ አይነት አስተሳሰባና እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጥቅም ከተማሪዉ ንቅናቄ ዘመን ጅምሮ
እስከዛሬ ድረስ “ተራማጅ” የፖለቲካ ባህላችንን ያልተለየ ዋና እንከን በሚገባ ተገንዝበን መክላት ያስችለናል። እንከኑ የተለያዩ የትግል
መስኮችና ደረጃዎች (በተለይ የመሠረታዊ ሃሳቦችና መርሆች እርከንና የድርጅቶች ዉስጣዊ እምነቶች፣ አቋሞችና ተልዕኮዎች ደረጃ)
መዘባረቅ ነዉ።
ዝብርቁ በሃሳብም በተግባርም ረገድ ኪሳራ አምጥቷል። ሃሳቦች ከጽንሱ ይህ ወይም ያ ብቸኛ ወገን፣ የፖለቲካ ድርጅት፣ የጐሣ ስብስብ
ወይም ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ቡድን እንዳሻዉ አጣቦና አወላግዶ የሚቀርጻቸዉ ወይም የሚተረጉማቸዉ ከመሆን አልፈዉ አያዉቁም።
ይባስ ብሎ የቃል በቃል አባባላቸዉ ወይም ፍቻቸዉ በእዉን ትርጉማቸዉ ተቀልብሷል። ለምሳሌ የደርግም የወያኔም “ዲሞክራሲ”
በተጨባጭ ይዘቱ አምባገነናዊ አገዛዝ አመልካች የነበረና የሆነ ነዉ። በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ተግባራዊ ፖለቲካ ትናንትም ዛሬም
ሃቀኛ ሃሳባዊ፣ መርሃዊና ተቋማዊና ትርጉምና ቅርጽ ተነፍጐታል። ዛሬ ልንቀርጸዉና በሂድት ልናዳብረዉ የምንችለዉ የአገር ነፃነት
ትግል ስልታዊ ራዕይና አስተዉሎ ይህን የፖለቲካ ባህላችን ጥልቅ ብልሹነት የማስወገድ ችሎታ ይሰጠናል ብዬ እገምታለሁ።
ይህ ስልታዊ አቀራረብ ለኢትዮጵያ ነፃነት ትግል ሌላ ተያያዥ ጥቅም አለዉ። ይኸዉም የነገደ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን የጋራ ብሔራዊ
ልምዶች፣ ዕሴቶች፣ ስሜቶችና ጉዳዮች ያጥለቀለቀና የዋጠ ፈላጭ ቆራጭ የማንነት ፖለቲካን አረንቋ በማጠፈፍ የአገር ነፃነት ትግል
ማራመጃ ጽኑ መሬት የማጥራትና መልሶ የማልማት አቅም ይሰጠናል። ኢትዮጵያ ላለፉት አርባ አመታት በተለያዩ የአገር ዉቃቢ
የራቃቸዉ አብዮተኛ ተቀናቃኞቿና ገዢዎቿ ተፈራራቂነት ያለማቋረጥ ከተጫናት የፖለቲካ ባርነት ነፃ የምትወጣበትንና ለመላ ዜጐቿ
የሚበጅ ተሃድሶ የምታገኝበትን መንገድ መጥረግ ያስችለናል።
tdemmellash@comcast.net
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
September 18, 2014

No comments:
Post a Comment