Monday, November 25, 2013

ኢሕአዴግİ የዕድር ዳኛ? ወይስ መንግሥት?

 ኢሕአዴግİ የዕድር ዳኛ? ወይስ መንግሥት?

 ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ካሉ ጥንታውያንና ጥንታውያንና ጥንታውያንና ታሪካውያን ሀገሮች አንዷ ናት::::::::
 እንደሚታወቀው ሀገራችን ለብዙ ሺህ ዓመታት የዳበረና የካበተ በዓይን የሚታይና በእጅ የሚዳሰስ ታሪክ ያላት ሀገር ናት የሀገራችን
ታሪክ አሁን እንዳሉት ሀያላንና ገናና ሀገሮች በጉልበትና በዘረፋ የተመዘገበ የግል ታሪክ ሳይሆን በታላቁና ዓለም አቀፍ በሆነው መጽሐፍ
ቅዱስ እንደተጻፈው በንግድና በብልፅግና በከበረ ሀብትና በሰላማዊ አስተዳደር ከሩቅ ምሥራቅ፣ መካከለኛው ምሥራቅና ከጎረቤት
ሀገሮች ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበራት ሀገር ነበረች፤ ሕዝቦቿም በዘላንነትና ንዝህላልነት ሳይሆን ሥርዓት ባለው አስተዳደር በመሪነትና
ተመሪነት፣በሕገ መንግሥት ታስረው፣ በአንድ ዙፋን ተቀምጠው፣ በአንድ ማኅተም እየተዳደሩ በማይደገምና ዓለምን በሚያማልል
ጥበብና ሥልጣኔ አጊጠው፣ ፍቅርና ሰላምን ተላብሰው፣ በሰላም የሚመጣውን በፍቅር አስተናግደው፣ በጥፋት የሚመጣውን በአንድ
አዋጅ በአንድ ክንድ የጠላትን ክንድ አጥፈው፣ አባርረው፣ ዳር ድንበራቸውን አስከብረው፣ ነፃነታቸውን አስጠብቀው፣ ለጠላት
ሳይንበረከኩ፣ ለድህነትና ለድንቁርና ሳይረቱ ኖረው ነበር:: የዛሬን አይበለውና፦
 አሁን ግን ስለ ረጅሙ ታሪካችን እያወራን ጊዜ የምናባክንበት ሰዓት ሳይሆን ሀገራችን አሁን ስላለችበት ሁኔታና ስለ ወደፊቱ ህልውናዋ
ነው መተንፈስ ያለብን ምክንያቱም ስለ ጥንቱ ሥልጣኔያችንና ነፃነታችን ባወራን ቍጥር የባዕዳንን ቀልብ እየሳብን በመጣንበት ዘመን፣
ሰሚዎቻችንም እንዴትና በምን ከሌሎች ሀገሮች ልዩ ሆናችሁ? እያሉ እውነቱን ለመረዳት ልባቸውን ለግንዛቤ ባዘጋጁበት በዚህ ዘመን፣
በብዙ ሀገሮች ላይ የነበረው የጨቋኝና ተጨቋኝ ሥርዓት ተገርስሶ በተወገደበት በዚህ ሥልጡን ዘመን፣ ብዙ ሀገሮች ከዚች ካለንባት
ምድር አልፈው ሌሎች ፕላኔቶች ላይ ለመኖር ደፋ ቀና በሚሉበት አስደናቂ ዘመን፣ አህጉሮች ሁሉ በአስተዳደር ሥልጣኔና በሀብት
ምጣኔ እየተሻሻሉ እንደ ማራቶን ሩጫ ወደ ፊት ብቻ በሚገሰግሱበት ዘመን! የእኛዋ ኢትዮጵያ ለምን በወያኔ ዘመን እንደ ገመድ ስፖርት
ወደ ኋላ እያፈገፈገች መሮጥ ጀመረች? ጥንት ብዙ ሀገሮች በባርነት ቀንበር ተጠምደው ደም ዕያነቡ ሲጨነቁ በነበሩበት ዘመን የነፃነት
ዝማሬ ስታሰማ የነበረች ሀገር፣ የነፃነትና የሰላም ማማ የተተከለባት ምድር አሁን የመርዶ ድንኳን ተተከለባት፣ እጆቿን ወደ እገዚአብሔር
ዘርግታ በደስታ ስትዘምር የነበረች ሀገር አሁን በሀዘን ጉም ተዋጠች፣ በዓለም ላይ የነፃነት ፀሐይ በወጣበት ሰዓት እኛ በዘረኝነት ጨለማ
ተዋጥን ኧረ ለመሆኑ በየቦታው በግፍ የምንጨፈጨፈው ለምን ይሆን? በሱዳን በረሀ የምንሞተው እኛ ብቻ፣ በሳሀራ በረሀ የምንሞተው
እኛ ብቻ፣ በሊብያ ወደብና በረሀ የምንሞተው እኛ ብቻ፣ በዐረብ ሀገራት የምንገደለው እኛ ብቻ፣ በባሕር ላይ የምንሞተው እኛ ብቻ፣
መንግሥትና ሕገ መንግሥት የሌላቸው ሕዝቦች እንኳ መብትና ነፃነት ባገኙበት ዘመን ምነው ይኼ ሁሉ መከራ የሐበሻ ብቻ ዕጣ ፈንታ
ሆነ? በእርግጥ ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንደተባለው ሆኖ እንጂ ባለቤት ቢኖረንማ ኖሮ እነዚህ በደም የሰከረ ሕግ የተሸከሙ
ልበ ጥቁሮች፣ በሰው ደም ታጥበው የሚበሉ ቃኤሎች፣ የጻድቅ ደም የሚልሱ የኤልዛቤል ውሾች፣ ጭካኔን ጌጥ ያደረጉ አረመኔዎች፣
በተፈጥሮ የተሰጣቸውን የሕሊና ሕግ የሻሩ ዘላኖች፣ ስብእናቸውን የዘነጉ ሰው መሰል አውሬዎች፣ በአጠቃላይ ዓለምን ለማሸበር የሰውን
ሰላም ለማደፍረስ ደፋ ቀና የሚሉ የጥፋት ሠራዊትና የሀዘን ድባቦች አይንቁንም ነበር፦
 ነገር ግን ማንም እንደሌለን ስላረጋገጡ እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩን፣ ስብእናችንን ንቀው እንደ አውሬ አደኑን፣ በዱርና በጫካ የሚኖሩ
አራዊት እንኳ ያለ አግባብ እንዳይገደሉ ዓለም አቀፍ ሕግ ወጥቶላቸው አራዊት ያለ ስጋትና ያለ ፍርሃት ከመኖር አልፈው ጥበቃና
እንክብካቤ ባገኙበት ዘመን እኛ የአውሬ ያህል መብት አጣን በመሆኑም ዱሮ ከሞት አፍ አምልጠው ሲመጡ ያለ ቪዛ እና ያለ ኤምባሲ
ውክልና ተቀብለን፣ ቤተ መንግሥት አስገብተን፣ ሳሎን አስቅምጠን፣ በጉዞ የተበላሸ እግራቸውን ሳንፀየፍ አጥበን፣ የላመ የጣመውን
አብልተንና አጠጥተን ስጋታቸውን አስወግደን፣ ሀዘናቸውን አስረስተን፣ የክፉ ቀን ጓዳ የሆንናቸው ውለታ ቢሶች እንደ አውሬ አድነው
በጽሑፍ እንኳ ለመግለጥ ከሚከብድ ቦታ አውጥተው እንደ ቅርጫ ከብት በአደባባይ አረዱን ደማችንን ተፀይፈው አሸዋ ነሰነሱበት
መስጊዳቸውን ከትቢያ እያፀዱ ምድራቸውን በእኛ ደም አጨቀዩዋት በነፃ የሚያገኙትን የነዳጃቸውን ዋጋ ሰማይ ሰቅለው ዓለምን
እያተራመሱ የእኛን ደም ዋጋ ነፈገው እንደ ክረምት ጎርፍ ቆጠሩት፣ ክብራችንን ንቀው በጭካኔ ረገጡት፣ ስብእናችንን ጥሰው ነፃነታችንን
አሳደፉት፣ ዱሮ የነፃነት ምሳሌ ነበርን አሁን የድህነት፣የስደት፣ የውርደት ምሳሌ ሆንን ዕድሜ ለወያኔ ታሪከ ቢስና የበቀል ቋቱ
መንግሥታችን!
 ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገርና ለወገን የማያስብ መንግሥት ተሾምባት፤ ይህ መንግሥት የሀገር ቅርስ ያወደመ የድሀ ጓዳ
የበዘበዘ የተፈጥሮን ሀብት ያራቆተ የሕዝቡን ፍቅርና አንድነት ያመከነ በጥቅሉ የታሪክ ፋይላችንን ያጠፋ አንቲ ቫይረስ ያልተገኘለት…..
ነው፤ ይህ መንግሥት ለሀገርና ለወገን የቆመ ቢሆን ኖሮ ዜጎቹ ያለ ፍትሕ ሲጨፈጨፉ ለምን!ማለት ይችል ነበር ካስፈለገም
እነሱ ንጹሕ አየር ለመቀበል ሲመጡ ያለ ስጋት እንዲዝናኑ ጠባቂ ፌደራል ከመመደብ እነሱም የሚፈስስ ደምና የሚታረድ አንገት
እንዳላቸው መናገር ይችል ነበር ግን እርሱስ ማን ሆነና? ይህ መንግሥት እኮ ደም ረግጦ ደም ጨብጦ የሚኖር አረመኔ ስለሆነ ለድሀ
ደም አይጨነቅም እርሱም በሀገሪቱ ላይ የሚፈፅመው ተግባር ስለሆነ ለሕዝብ የሚያስብ ቢሆን ኖሮማ ከየአቅጣጫው በግፍ ያለቀው
ሕዝብ በሳጥን ሲመጣ አስከሬን ተቀባይና ድንኳን ተካይ አይሆንም ነበር ለመሆኑ ወያኔ የዕድር ዳኛ ነው? ወይስ መንግሥት? ለነገሩ
የሚመች መንግሥት ቢሆን ኖሮ ሕዝቡስ መች ስደቱን ይመርጥ ነበር አንድ እሳት ላይ የተጣደ ነገር ወደ ውጭ የሚገነፍለው እኮ
የውስጡ ትኩሳት ሲበረታበት ነው ስለዚህ ሕዝቡ የሚሰደደው እሬሳውን ለማራቅ ፈልጎ ሳይሆን ችግሩ የበረደለት መስሎት ነው ይህ
መንግሥት በሀገሪቱ ላይ ለመጋዘን ንብረትና ለድሀ ኪስ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሲያቋቁም ከአንድ ጎሣ ብቻ 2.500.000 ሕዝብ ያለመረጃ
የገባበት ሲጠፋ እንደ አላቂ ንብረት በሪፖርት ብቻ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በዝምታ ያለፈ መንግሥት ነው ኧረ ለመሆኑ ፀረ ሙስና
ኮሚሽን የሚያስፈልገው የመጋዘን ንብረት ሲጎድልና የድሀ ኪስ ለመበዝበዝ ሲፈለግ ብቻ ነው? የሕዝብ ቊጥር በሙስና ሲጎድል ፀረ
ሙስና የለውም? እስከ ዛሬ በሆነው ነገር ሁሉ ለበጎ ነው እየተባለ ተዘፈነ፣ ለበጎ ነው እየተባለ ተዘመረ አሁንስ ይህ በሳዑዲ እየፈሰሰ
ያለውን ደምስ ለበጎ ነው ብለን እንለፈው? ግዴለህም ወገኔ አሁን ዝምታችን ተሰብሮ የአዞ ሳይሆን የራሄል ዕንባ በጩኸት ወደ ላይ
መሰማት አለበት ምክንያቱም የኦርዮንንና የአቤልን ደም ተቀብላ በፈጣሪዋ ፊት አፏን ከፍታ የጮኸችው ምድር አሁንም በዚህ ሰዓት
የወገኖቻችንን ደም ይዛ በእውነተኛው ፈራጅ ፊት እየጮኸች ነው ምንጊዜም ንጹሕ ደም ወደ ላይ እንጂ ወደ ምድር ሰርጎ አያውቅምና
ስለሆነም አብረናት እንጩኽ ድምጻችን ይሰማ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጠን አሜን።
 አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ድንቅነህ
 Wetzlar (Germany Wetzlar (Germany Wetzlar (Germany)
 ቀን ቀን 4 , 3, 2006 E,C , 3, 2006 E,C , 3, 2006 E,C

No comments:

Post a Comment