ለዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት ድጋፍ አሰባሳቢ
ኮሚቴ፤መላው አባላትና ደጋፊዎች
ባላችሁበት
ጉዳዩ፡-አስቸኳይ ጉባኤ ለማድረግ የቀረበው ጥያቄ በመታፈኑ
የሚመለከተው ሁሉ እንዲያውቀውና መፍትሄ እንዲያፈላልግ ስለ መጠየቅ
ይመለከታል፤
ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ
ዲሞክራሲያዊ፤ፍትሃዊና ተጠያቂ ስርአት ለመገንባት በሰላማዊ መንገድ እየተታገለ የሚገኝ ሕጋዊ
ፖለቲካዊ ፓርቲ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው የኢህአደግ ስርአት የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች
ከመርገጥ አልፎ የሃገራችን ሉአላዊነትና ጥቅም አሳልፎ በመስጠት ከባድ ወንጀል ሲፈፅም ቆይቷል እየፈፀመም ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ
የፈረመቻቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች (universal declaration of human rights)ና በኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት
የሰፈሩ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በመጣስ ጠፍጥፎ የሰራቸው ፓርቲዎች እያስከተለ በስመ ዲሞክራሲ በዜጎች ላይ እየቀለደ
ይገኛል፡፡
ይህ የሃገራችን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት ብቸኛው አማራጭ ትግል መሆኑ በማመን ዓረና ትግራይ ተመሰረተ፡፡
እኛም ፓርቲው ከተመሰረተበት ጥቂት ወራት በኋላ ፓርቲው በመቀላቀል በሃገራችን ኢትዮጵያ ለሚፈጠር ዲሞክራሲያዊ ስርአት፤
ግልፅነትና ተጠያቂነት የነገሰበት፤የዜጎቿን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያለ ምንም ገደብ የሚያስከብር፤ለሃገራችን ዳር ድንበርና
ጥቅሞች የቆመና በአጠቃላይ የሃገራችን ፖለቲካዊ፣ማሕበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ዘርፈ ብዙ ችግሮቿ የሚፈታ ስርአት ለመገንባት ለሚደረግ
ሃቀኛና እውነተኛ ትግል የራሳችን አስተዋፅኦ እያደረግን እንገኛለን፡፡
ፓርቲው ከተቀላቀልንበት ቀን ጀምሮ በምንም ዓይነት ፈተና ሳንምከረከክ በቆራጥነትና በቅንነት ከአባልነት እስከ አመራርነት ፓርቲው
እያገለገልን እንገኛለን፡፡
ከሃገር ውጭ የምትገኙ አባላትና ደጋፊዎችም ከእናት ሃገራችሁ ተለይታችሁ በሰው ሃገር ሁናችሁም ስለ ሃገራችሁ በመቆርቆር ፤
በሃገር ውስጥ ያለችሁም የህወሓት አፈናና ጫና በመቋቋም ከፍተኛ የገንዘብ፡ የሃሳብና የማተርያል ድጋፍ ስታደርጉ ቆይታቿል፡፡ይህም
ለሃገራችሁ ያላችሁ ፍቅርና ስሜት ማሳያ ሲሆን ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል ፡፡የፓርቲው አባላትም የህዝቡ ድጋፍና የለውጥ ፍላጎት
በማየት ትልቅ የሞራል ስንቅ እየሆነባቸው ከህወሓት ለሚመጣባቸው ማንኛውም ዓይነት አፈናና ጫና በመቋቋም በቆራጥነት
እየተታገሉ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፓርቲው ውስጥ አንዳንድ ችግሮች በመከሰታቸው ለአባላቱና አመራቹ ትልቅ ፈተና እየሆነባቸው
መጥቷል፡፡ይህ ችግር ቀደም ብሎ የነበረ ሲሆን ከግዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ለፓርቲው አደጋ ላይ ጥሎታል፡፡
ከችግሮቹ መካከል ዋናዋናዎቹ፦
1.በፓርቲው ውስጠ-ዲሞክራሲና ነፃነት የሌለው ስለ መሆኑ
2.ድርጅታዊ አሰራር አለመኖሩና ህገ-ደንብን አለማክበር
3.በፓርቲው ውስጥ ምንም ዓይነት ፓለቲካዊ ይዘት ያለው ስልጠናና ውይይት ተደርጎ የማያውቅ መሆኑ
4.በፓርቲው ውስጥ ቡድናዊነት ስለ መንገሱ
መ/ር ገብሩ ሳሙኤል ሽሻይ አዘናው 5.በፓርቲው በተለይ በፓርቲው ሊቀ መንበር የአቋም መለሳለስ መኖሩ
6.የፋይናንስ ስርአት ግልፅነትና ተጠያቂነት የሌለው ስለ መሆኑ
7.አሳታፊነት አለመኖሩ(የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባላት በተሰጣቸው ስልጣንና ሃላፊነት መስራት ሲገባቸው ከሁሉም ነገር መገለላቸው)
8.ውህደትን በተመለከተ በድብቅ እየተከናወነና ለአብዛኛው አመራርና አባላት ሚስጥር መሆኑ
9.የፓርቲው አመራርና አባላት በአደባባይ ሲደበደቡና ሲታሰሩ እስከ አለም አቀፍ የሚሄድ ጉዳይ ሁኖ እያለ ተደፎኖ እንዲቀር
መደረጉ(ፍትህ ባይገኝም በሕግ መክሰስና እስከ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት መሄድ ሲገባው ጠንከር ያለ መግለጫ እንኳን አልተሰጠም)
10.የፓርቲው ጠንካራ አመራርና አባላት ከፓርቲው እንዲወጡ በፓርቲው ሊቀ መንበር ግፊት መደረጉና የመሳሰሉ ሲሆኑ እነዚህ
ችግሮች በግዜው እንዲፈቱ ለፓርቲው ስራ አስፈፃሚ በቃል ብንወተውትም ምንም አይነት መልስ አልተሰጠንም ፡፡
ችግሮቹ ወደ መጨረሻ ጠርዝ ከመሄዳቸው በፊት አመራሩ በአስቸኳይ ተሰብስቦ መፍትሄ እንዲያበጅለት፦
1.በ14/05/2006 ዓ.ም ሽሻይ አዘናው የፓርቲው ማእከላይ ኮሚቴ አባል
2.በ04/06/2006 ዓ.ም መ/ር ገብሩ ሳሙኤል የፓርቲው ቁጥጥር ኮሚሽን አባል የሆንን ለፓርቲው ፅ/ቤት ደብዳቤ የፃፍን ሲሆን
ለደብደዳቤችን ምንም አይነት መልስ አልተሰጠንም፡፡
የፓርቲው ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸው በፓርቲው ሕገ-ደንብ አንቀፅ 26 መሰረት አስቸኳይ ጉባኤ እንዲጠራ በ13/08/2006 ዓ.ም
ደብዳቤ የፃፍን ሲሆን አሁንም ምንም አይነት መልስ አላገኘንም፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ በ06/09/2006 ዓ.ም አጀንዳችን ለአባሎቻችን እንድናስተዋውቅና የድጋፍ ድምፅ ለማሰባሰብ በጀት እንዲበጀትልንና
መድረክም እንዲዘጋጅልን፤መልሱም በ5ቀናት ውስጥ እንዲነገረን ብንጠይቅም ምንም አይነት መልስ ሊሰጠን አልቻለም፡፡
ጥያቄዎች የማፈን ድርጊት በኛ ብቻ ሣይሆን እነ አቶ አስገደ ገ/ስላሴና መ/ር ታደሰ ቢተውልኝ(የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል)
በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄዎች ታፍኖ ቀርቷል፡፡ እነሱም አስቸኳይ ጉባኤ ጠይቀው ጥያቄያቸው በመታፈኑ በክርክር ላይ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ሰዓት ፓርቲው በመንታ መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ችግሮቹ ከመብዛቱ የተነሳ የፓርቲው አመራሮች ከፓርቲው ራሳቸው ማግለል
የተለመደ ሁኗል፡፡
ከፓርቲው 3ኛ ጉባኤ በፊት አስራት አብርሃምና ጉዕሽ ገ/ፃዲቕን ጨምሮ 3 ስራ አስፈፃሚ፤4 ማ/ኮሚቴና አንድ ቁጥጥር ኮሚሽን
ከፓርቲው ራሳቸው ያገለሉ ሲሆን አሁን ደግሞ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና የፅ/ቤቱ ተጠሪ የነበረ ወጣት ፖለቲከኛ ስልጣኑ ሕሸ
ፓርቲው ውስጥ በተለይ ከፓርቲው ሊቀ መንበር ጋር በተያያዘ ምክንያት ከፓርቲው ራሱ አግልሏል፡፡ በርካታ አባላትም ፓርቲው
ውስጥ ባለው ችግር ምክንያት ራሳቸው አግልለዋል፡፡
ይህንን የሚያሳየው በፓርቲው ውስጥ ያለው ችግር ስር የሰደደና እያደረ የሚፈነዳ ቦምብ የተቀበረ መኖሩ ማሳያ ነው፡፡ እነዚህ የውስጥ
ችግሮች ተሸክመህ ራስህን ነፃ ሳትወጣ ፤ራስህን ዲሞክራት ሳትሆን ህዝብን ነፃ አወጣለሁ ማለትና ዲሞክራሲያዊ ስርአትን እገነባለሁ
ብለህ መታገል ዜጎችን ከማታለልና የቁማር ፖለቲካ ከማራመድ ባለፈ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡
ስለሆነም ይህንን የፓርቲው ኢ-ዲሞክራሲያዊና አምባገነን ባህሪ በምንም መልኩ ከህወሓት የማይለይና አስቸኳይ መፍትሄ የሚሻ
ነው፡፡
ፓርቲው ጓደኛችንና ወንድማችን አረጋዊ ገ/ዮሃንስ የከፈልንበት፤ከፍተኛ የሆነ የሞራል፤የጊዜና ገንዘብ መስዋእትነት የከፈልንበት፤
ህዝባችን በአምባገነኑና ሙሰኛ ስርኣት እየተሰቃየ ባለበትና በኛ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ተስፋ በጣለበት ሁኔታ ፤በስመ ተቃውሞ መቀለድና
የውሸት ትግል ማካሄድ የሃገራችን የፖለቲካ ቁመና የሚያበላሽ፤ህዝቡም በተቃዋሚ ሃይል ያለው እምነት እንዲመናመን ከማድረግ
ባሻገር በታሪክም ጊዜ ይረዝማል እንጂ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም፡፡
ስለዚህ እያንዳንዱ የፓርቲው አባልና ደጋፊ የራሱ አሻራ ያኖረበት ፓርቲ በመሆኑ ጉዳዩን አውቆ ፓርቲው ከዚህ መስቀለኛ መንገድ
አውጥቶ በእውነተኛ የትግል ማእበል ላይ እንዲራመድ የማድረግ ግዴታም ሃላፊነትም ስላለበት ይህንን ጉዳይ እንድናሳውቃችሁ ግድ
ይለናል፡፡ በመሆኑም በፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ በተለይ በፓርቲው ሊቀ መንበር የታፈኑ አጀንዳዎቻችን ለአባላት ለማሳወቅ እንዲሁም
ጉባኤው በማካሄድ የፓርቲው ችግር እንዲፈታና ወደ ነበረበት የትግል አቅጣጫ፤ ጥንካሬና እውነተኛ ትግል ለማስመለስ ለምናደርገው
ትግል ማንኛውም አይነት ድጋፍ ታደርጉልን ዘንድ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡
እንዲሁም ፓርቲው ውስጥ ችግር እየፈጠሩ ያሉ አካላትም ጫና በመፍጠር ፓርቲው ለማስተካከል ትግላችሁ እንድትቀጥሉበት
እናሳስባለን፡፡
ምርጫ ቦርድም የፓርቲዎች ውስጠ-ዲሞክራሲያዊነትና ህገ-ደንባቸው የማክበር ጉዳይ የመከታተል ግዴታ ስላለበት የፓርቲውን ችግር
ለመፍታት በምናደርገው ትግል ህጋዊ ድጋፍ እንዲያደርግን እንጠይቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
ሽሻይ አዘናው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል
መ/ር ገብሩ ሳሙኤል የፓርቲው ቁጥጥር ኮሚሽን አባል
ግልባጭ
ለዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት
መቀሌ
ማንኛውም አይነት አስተያያት በስ/ቁጥራችን
በ0921389153 መ/ር ገብሩ ሳሙኤል ወይም
በ0914514427 ሽሻይ አዘናው
በe-mail አድራሻችን፡-
sazenaw@gmail.com ወይም
gebrusamuel75@gmail.com እንቀበላለን፡፡
ድል ለእውነተኛ ትግል!!
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
June 8, 2014

No comments:
Post a Comment