የትግራይ ህዝብና ህወሓት
(ጌታቸው ፏፏቴ)
ባለፈው ጹሑፌ የህወሃት ሠራዊት ከጉናው ጦርነት በኋላ እኛ የታገልነው የትግራይን ሕዝብና ትግራይን ነፃ ለማውጣት ነው ። ያ ደግሞ
ተከናውኗል። ከአሁን በኋላ አንዲት ርምጃ ወደፊት ስንዝር አንልም ባለበት ወቅት የህወሃት አመራር ዘመቻውን ወደ ትግራይ በማድረግ
የታጋይ (የህወሃት ሠራዊት አባላት) ቤተሰብ ወደሚገኙበት በመሄድ ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላዋን ኢትዮጵያ ለመግዛት “በለስ
ቀንቶናልና ልጆቻችሁን አሁንም መርቃችሁ ስጡን” በማለት መማፀናቸውን ጠቅሼ ነበር። አሁን ደግሞ በቅርቡ የህወሃት ቱባ ቱባ
ባለሥልጣናትና ቱጃሮች “አረና በትግራይ” እያደረገ ያለውን ሰላማዊ ትግል ለማስቀልበስ ሁለተኛ ዙር ዘመቻ ማድረጋቸውን ስሠማ
ህወሃት በቀውጢና አጣብቂኝ ሁኔታ ላይ መሆኑን ተረድቻለሁ። ነገር ግን ህወሃት አንበሳም ሆነ ዝሆን ሆኖ ወደ ትግራይ ዘመቻ
ቢያደርግም “እናቴ ድሮ በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ” የተባለውን ተረት ከመድገም ሊያልፍ አይችልም። አሁን ትግራይና የትግራይ ሕዝብ
የተለያዩ ናቸው። የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንና የሚኮራ ። ሕወሃት ደግሞ የኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ ታሪክ
የሚያሳፍረው ሆነው ይገኛሉ።
ወደ ዋናው ጉዳይ ልመለስና ስለትግራይ ከሰማሁት ካየሁት በመነሳት የሚከተለውን ለማቅረብ ሞክሬያለሁ። መረጃው ብዙ ዝርዝር
ሁኔታዎችን የሚጠይቅ ቢሆንም ከሀገር ርቄ ስለምገኝ አእምሮ ላይ የሰፈረውን እንደ ወረደ ማካፈሉ ክፋት የለውም ከሚል ነው። ህወሃት
ማን ነው በሚለው መጣጥፌ ለማስረዳት ሞክሬ ነበር፤ ምን ያህሉ አንብባችሁታል? ግድ የለም ከዚያው ሳልርቅ እንዲህ ልጀምረው።ፈሪሃ
እግዚአብሔር የሌለው የህወሃት ቡድን ደርግን ለመጣል ከፍተኛ ውጊያ ማካሄዱ ግልጽ ነው። ነገር ግን በዚያ ውጊያ የማን ልጅና ማንስ ነው
የሞተው? ቆሞ የሚሄድ ቤተሰብ ያልተረፈበት፤ ወላጆች ጧሪ አልባ የቀሩበት ፤ በጦርነት አካላቸውን ያጡ ቀደምት ታጋዮች ጎዳና ላይ
የተጣሉበት፤ ህወሃትን በወታደራዊ ትምህርት ያሠለጠነው አንጋፋው የህወሃት ታጋይ የነበረው አስገደ ገ/ሥላሴ እስከ ቤተሰቡ እስረኛ
የሆነበት፤ በአመለካከት ልዩነት 06 ገብቶ ስንቱ ነው ደብዛው የጠፋ? በ1976ና 1977 ድርቅ ወቅት ህዝቡን በደርግ እንዳይታገዝ መንገድ
ላይ ጠብቆ በእግት ይዞ የውጭ እርዳታ መለመኛ የተደረገበትና እርዳታው ለድርጅት አገልግሎት (ለህወሃት) መዋሉን የትግራይ ህዝብ
ያጣው ይሆን? የውጭ እርዳታ ስንዴ ወደየ ካምፑ ገብቶ ተራራ መስሎ ተከምሮ በስሙ የተነገደበት ምስኪን የወሎና የትግራይ ህዝብ ግን
በርሃብ ጠኔ ይረግፍ ነበር ።
የሐውዜን ህዝብ በደርግ ሮኬት ቦንምብ እንዲያልቅ ያደረገስ ማን ነበር? ስለዚህ ብዙ ተብሏልና ልጨምር አልፈልግም ነገር ግን ነገርን ነገር
ያነሳዋልና አንድ ገጠመኝ ልንገራችሁ። ጎንደር ውስጥ ጣሊያን ይጠቀምባቸው የነበሩ አሮጌ ጀኔሬተሮች ነበሩ። እነዚህን ህወሃት ሌሊት
ሌሊት ሲያወላልቅ እያደረ ከርሞ በኋላ ሞተሩ በጨለማ ተጭኖ ወደ ሐውዜን ይሄዳል። ከዚያም ገጣጥመው ለማሰራት ሲሞክሩ ሞተሩ
አልነሳ ይላል። እናም የሐውዜን ህዝብ ምን እንዳለ ታውቃላችሁ? ላላጣችሁት ዛሬ ኢትዮጵያን እየመራችሁ ምነው ከነዚያ ምስኪን
ወገኖቻችን ነጥቃችሁ ያረጀ ሞተር ያመጣችሁልን ነበር ያለው? ሌላስ ህወሃት ጦርነት ሲናፍቀው የት ላይ እንደሚጀምር ታውቃላችሁን?
ከተማ ላይ፤ ህዝብ በብዛት በሚገኝበት የገጠር መንደርና ቤተክርስቲያን ላይ ነው። ለምን? መልሱን ለእናንተው ልተወው።
እዚህ አሜሪካ አገር ይኖር የነበረ የህወሃት እንደራሴ አንድ ወቅት ላይ በአንድ ስብሰባ ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ጥያቄው
ህወሃት የትግራይን ሕዝብ አማራ ጠላትህ ነው እያለ ቀስቅሶታል። እውነት የትግራይ ሕዝብ ጠላት አማራው ነውን? ተጠያቂው አሁን
በህይወት የለም፤ ስሙ አሰፋ ማሞ ይባል ነበር። ለጥያቄው የሰጠው መልስ የሚያሻማ አልነበረም። የትግራይን ሕዝብ ከኛ ጎን ለማሰለፍ
የተጠቀምንበት የፕሮፓጋንዳ ጉዳይ እንጅ እውነታ የለውም የሚል ነበር። ይህ ደግሞ የድርጅቱን ዋና ዓላማና ዘላቂ ግቡን ስቶ በመናገሩ
አሰፋ ማሞ በአሁኑ ሰአት ቢኖር ይህ ጉዳይ ተነስቶ ምላሱ ወይም እጁ ይቆረጥ ነበር ማለት ነው። ሌላው በየትኛውም ክልል ሂዱ የህወሃት
አባል የየትኛውም ክልል ከቀበሌ እስከ ከፈተኛው እርከን የምክር ቤት ኃላፊነት ቦታ ሲኖረው ትግራይ ውስጥ ግን ከትግራይ ውጭ የነገድ
አባል ከሆነ አይደለም በቁልፍ ቦታ ሊገባ የቀበሌ ምክር ቤት አባል መሆን እንኳን አይቻልም።
በህወሃት የታጠረች ትግራይ። ትግራይ ውስጥ ከወይን ራዲዮ ወይን ጋዜጣና መጽሔት ውጭ አንድም ሌላ ነገር ማድመጥ ማንበብም
መስማትም አይቻልም ነበር። የራስ አሉላ አባ-ነጋ አገር ትግራይ እዚህም ደረሰች። በጣም አሳፋሪ ከሆነው የህወሃት ተግባር አንዱ ደግሞ
ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን ወደ ደርግ ካምፕ እየላከ ከመኮንኖች ጋር እየተዳሩ መረጃ እንዲያቀብሉት ያደርግ እንደነበርስ ስንቶቻችን ነው
የምናውቀው? እነዚያ ህወሃት ለገበያ ያእቅረባቸው ሴቶች ዛሬ በመጠኑም ቢሆን ቀልፍ ቦታ ያላቸውና ጥሩ ገቢ ያላቸው ባለውለታዎች
ሆነው ይገኛሉ። ህወሃት አሁንም ይህን መንገዱን እየተከተለ ያለ ስለሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆናችሁ በየትኛውም መንገድ
በሙያ ፤ በልማት ፤ በመረዳጃ ማህበር ስም የተሰባሰባችሁ ጠንቀቅ በሉ!። እንግዲህ የዚህ ሁሉ አባዜ ማጠንጠኛው ምንድን ነው?
የሚለው ቁልፍ ነገር እንድንመረምር ያመጣሁት ማጫሪያ ነው። ለመሆኑ የህወሃት አብዛኛው መሪዎች አባትና አያቶቻቸው እነማን ነብሩ?
ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኢትዮጵያስ ምን አበረከቱ? ግድ የለም መልሱን እኔው ልንገራችሁ። የህወሃት መሪዎች አባቶቻቸውና አያቶቻቸው
የጣሊያን አሽከር (ባንዳዎች የነበሩ ሲሆን በጣሊያን ክብር ተሰጥቷቸው የለበሱ የጎረሱ) ሲሆን ጀግኖች አርበኞቻችንን ለማስገደል በስለላ፤
መንገድ በመምራት ግንባር ቀደም በመሆን ወገናቸውን ያስጨረሱ፤ አገራቸውን ያስደፈሩ ነበሩ። ልጆቻቸው ደግሞ በዚህ የድናቁርት
የአባት ታሪክ ተገንብተው ተኮትኩተው የኢትዮጵያዊነት ክብራቸውንና ወዘባቸውን እንደ እባብ ገላ ገፈው በመጣል ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠልተው እንዲያድጉ በመደረጉ ተከፍተው በጥላቻ ተመርዘው ኢትዮጵያዊ መንፈስ ሳይኖራቸው የመጡ ናቸው።
እዚህ ላይ ህወሃት ውስጥ ኢትዮጵያዊነታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ የሉም ማለቴ አይደለም ህወሃትን አላወገዙም አልታገሉም የሚልም
አልወጣኝም።ነገር ግን ያ! ሁሉ ቀንዳም ቀንዳም የህወሃት ታጋይና አመራር ምን እየሠራ የትስ መሽጎ ነው ድምጹ የማይሰማው ለማለትና
አሁን ለተፈጠረው ችግርም ተጠያቂነት ስለአለበት አንድ ካላለ የባሰ ችግር ይፈጠርበታል ያበላሹትን ማስተካከል የግድ ይላል። ዝምታ
ወርቅ ነው አይሰራም ለማለት ነው።
እንግዲህ ከዚያ ሁሉ የትግራይ ሕዝብ አፈናና የህወሃት አፋኝ አገዛዝ ተነስተን ሁኔታው አሁን ካለበት ከደረሰ ህወሃት በትግራይ ውስጥ
እሳት እንደበላው ፕላስቲክ እየተኮማተረ የትግራይ ሕዝብ የነጻነት ያንድነትና የአብሮነት ትግሉን እያሰፋ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር
የሚያገናኘው እድል ይፈጠራል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው በትግራይ ህዝብ ልብ ውስጥ ተረግዞ የቆየ ሲሆን
የአመጽ መንገዱን እያሳየ ያለው አረና ትግራይ ስለሆነ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። አረና በዚህ አሁን በሚሄደው አይነት መንገድ ከሄደ ግን
ጥሩ አይመስለኝም። ከሌሎች የተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ መታገል ይኖርበታል። ይህን ስል ህወሃት ይውጠዋል ማለቴ ሳይሆን
ብዙ መስዕዋትነት እንዲከፍል ያደርገዋል ለማለት ነው። በውጭ ያለው የትግራይ ነገድ ተወላጅ የሆነ እንዲሁም በሟቹ ጠቅላይ
ሚንስትርና በእነ አዲሱ ለገሰ መጥረጊያ የተወገዱት የህወሃት አባላት የትግራይን ህዝብ እምብኝ ባይነትና የአረናን የትግል ጉዞ ሊደግፉ
ይገባቸዋል። ህወሃት እየሄደ ነው ኖሮም አላማረበትም። ትግራይ ላይ የህወሃት እግር ከተነቀለ “ፈጣን ነው ባቡሩ” እያልን ህወሃትን
የምንዳበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። “በማርች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ሴቶች የሴቶችን ቀን በሩጫ ለማሳለፍ
ወጥተው እግረ መንገዳቸውን ብሶታቸውን፤ የህዝቡንም ብሶት በማሰማታቸው የሆነውን ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም ጥርት ባለ
መልኩ አስቀምጦታል። ከዚያ በኋላም ዳኛቸው ቢያድግልኝ ዘርዘር አድርጎ በማቅረብ ስለአስነበበን ሁለቱንም አመስግኛቸው አልፋልሁ።
ዋናው መነሻየ ግን ህወሃት ጀግኖች ነን ጎበዝ ከሆናችሁ ግጠሙን እያሉ የጦርነት ዛቻ ይዝታሉ በሌላ መልኩ ደግሞ የወጣት ሴቶች ድምጽ ፤
የነስክንድር፣ ርዕዮትና አንዱዓለም የሌሎችም የሕሊና እስረኞች በኅይማኖት ፣ በፖለቲካና በነጻ ብእር ባደረጉት እንቅስቃሴ
አስደንግጠውት መፍትሄውን በማሰር አድርጎት እንመለከታለን። ጥቂቶችን ማሰር ይቻላል እያየን ነው የሕዝቡን ትግል ግን ማሰር
አይቻልም ግፉ ተቆጥሮ የማያልቅና የሁሉንም ጓዳ ጠርጎ የበላ በመሆኑ መነሻው ብዙ የሆነውን የሕዝብ ስሜት ለመግታት የተሞከረበት
መንገድ መክሸፉን አምነው ባይቀበሉትም የሕዝቡ ትግል እያደገና እየጐለበተ መጥቷል። እነዚህ ሁሉ ምልከታዎች የሚያሳዩት ሥርዓቱ
እያበቃለት መምጣቱን ነው የሚያሳየን።ምናልባት አንድ የቀረ የምጠብቀው ነገር ቢኖር እርስ በርሳቸው የሚገዳደሉበት ቀን ቶሎ
አለመፈጸሙ ነው። መሆኑ ግን ይጠበቃል።
መተኛትና ማንጐላቸት የየቅል ናቸው፦የልብን ገልጦ አያዩም እንጅ ለ23ና 40 ዓመታት በህዝብና በሀገር ላይ የወረደው ዶፍ
ያላንገበገበው፤ ያልከነከነው ይኖራል ብየ አላስብም ቀን እየጠበቀ እንጅ የተቋጠረ ፤ የታመቀ የሕዝብ ሕመም አላስተኛህ አላስቀምጥህ
ያለው ሁሉ ሆ! ብሎ እንደሚነሳ የዘነጉት ባለቀኖች ምን አልባት በዘመናዊ ፋሽዝም የተካኑ ከደርግ የከፉ በቶርች በግልበጣ እስራት አጥንቱ
እስኪታይ ሥጋውን በመቀጥቀጥ አንገቱን ቀና ያደረገውን ሁሉ ገድለን ጨርሰነዋል ብለው ስለሥልጣን ማራዘሙ ጉዳይ ብቻ እየተብከነከኑ
ከሆነ ስህተት መፈጸም ባህሪያቸው ቢሆንም በዚህ ነጥብ ላይ ደግሞ እጅግ ተሳስተዋል። “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ” ይባል የለም
እንዴ!? ስለሆነም አንጎላቸን እንጅ አልተኛንም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም ስትነሱት እኛም የናንተን ሰላም ማደፍረስ የግድ ስለሚለንና
እስከ ወዲያኛው ሄዳችሁ አገር እፎይ እስከሚል ድረስ በፍጹም በሰላም ማደር አትችሉም። ግብረ-በላውም የሆድ ጉዳይ ሆኖበት ሌላ
መተዳደሪያ አጥቶ እንጅ ህወሃትንና ሹምባሾቹን አምኖ አለመሰለፉን ልታውቁት ይገባችኋል። እውነት እላችኋለሁ ክፉ ቀን እየመጣና
ጥቁር ሞት የእያንዳንዳችሁን በር ሊያንኳኳ እየተጠጋ መምጣቱን ተቀበሉኝ። ምርጫው የእናንተ ቢሆንም እጃችሁን ከህዝብ ትካሻ ላይ
ማንሳት ወይም በጀመራችሁት የጥፋት መንገድ መቀጠልና የሚከተለውን ማየት እንደቀራችሁ ማመን ይገባችኋል። በተለይም የግንባሩን
መስራቾች የማታውቁ የድል አጥቢያ አርበኞች በሙያችሁ አገርን ማገልገል ሲገባ የህወሃት ጀሌ በመሆን የምትወሻክቱት የኢትዮጵያን
ህዝብ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻችሁንም አንገት የሚያስደፋ ስለሆነ ይህን ቅሌታችሁን ብታቆሙ ይሻላችኋል። በተለይ አሁን የትምህርት
ሚንስትር የሆነው ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩና ሽመልስ ከማል ጌቶቻችሁን ለማስደሰት የምታደርጉት የመታመኛ ቅዥት ህወሃት እንደ ሎሚ
መጦ እንደሚጥላችሁና ህወሃት አዲስ ናፋቂ መሆኑን ካለመረዳታችሁም በላይ ። ለሀገር ጥቅም ባታውሉትም ኢትዮጵያ ከድኻው ህዝብ
የጤና ታክስ፤ የንግድ ሥራ ግብር፤የመሬትና የእርሻ ሥራ ግብር …ወዘተ እየተባለ በተከፈለ ገንዘብ የተማራችሁ ስለሆነ ምነው በ23 ዓመት
ውስጥ የህወሃት ሴራ ሊገባችሁ ያልቻለው? ለምንስ ከኑግ ጋር የተገኘች ሰሊጥ የምትሆኑት? የኢትዮጵያን ህዝብ በአንድነቱ ገባችሁበት ፤
በእምነቱ ገባችሁበት ፤ መሬቱን ሀብት ንብረቱን ዘረፋችሁት ፤ሠርቶ ሀብት እንዳያፈራና ራሱን እንዳይችል መሬት ጦም እያደረች ስንዴና
ዘይት ለመቀበል ሰልፍ ላይ እንዲወጣ ዳረጋችሁት ምነው ጃል! ፍጡር መሆኑን ረሳችሁት እንዴ? ደስ አይበላችሁና እነዚህን ሁሉ ችግሮች
ተሸክሞ ሊጠርጋችሁ ተነስቷል። በተለይ በውጭ የሚኖረው ያሰደዳችሁት ኢትዮጵያዊ በተለያዩ ሁኔታዎች ከህዝብ ጎን የቆመበት ሰአት
ነው ቀላል አይምሰላችሁ። አቶ በረከት በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የተተኮሰ ጥይት ስለሆነ እዛ ላይ አናተኩርም ብሎ ነበር። ነገሩ ግን
በተገላቢጦሹ ነው ለዓባይ ግድብ ግን የገንዘብ ምንጩ ተደርጎ የተሰላው ይኸው የተተኮሰ ጥይት ማሳሌ የሆነው ዲያፖራው ነበር።
በተለይም በደርግ አገዛዝ
ተወልዶ ያደገ ፤ የህወሃትን የ23 ዓመታት በጎሳ ማናከስ ችግር ሳይበግረው ዘወር በሉልኝ ጊዜው የኔ ነው የሚል ወጣት ትውልድ ስለ እናት
አገሩ የሚቆረቆር ትውልድ ለመደራጀትና የራሱን እጣ ፈንታ በራሱ መለኪያ ሊያበጅ መነሳሳቱ በጣም የምሥራች የሚያስብል ነው
ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል። እኔ በግሌ በአሁኑ ሰአት እሠራለሁ ዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት በሰፈነበት አገር
እኖራለሁ ላባደር ስለሆንኩ የላባደሩን ኑሮ እየኖርኩ ነኝ።ነገር ግን ሰላም የለኝም ምክንያቱም በየቀኑ ብዙ የምዳስሣቸው የሀገር ቤት
ጉዳዮች ስለአሉ እረፍት የለኝም። በተለይ አርባ ዓመት የሞላው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ቀውስና ተተኪው ትውልድ በዚህ ወቅት ምን አይነት
ታሪክና ኢትዮጵያን ነው የምናስረክበው በማለት እጨነቃለሁ። ዳሩ ግን እግዚአብሔር የሚወዳትና የባረካት ኢትዮጵያ የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላት ቢፈታተናትም ጠላቶቿን ድል ማድረጓ የማይቀር መሆኑን ከወጣቶቹ እንቅስቃሴ ለመረዳት በመቻሌ ምስጋና
ለእግዚአብሔር እያቀርብኩ ነው።
ከዚህ ቀደም “እሜቴ እውይ አሉ እኔም እውይ” ልበል አለች እንዲሉ እኔም እንደ ማንኛውም ሰው የተለያየ ርእስ ያላቸው
ጹሑፎችን(ጦማሮችን) በመጻፍ በድረ-ገጽ ላይ እንዲነበቡ ማድረጌ ይታወቃል።ነገር ግን በብእር ስም ( nike name ) የተጻፉ ስለነበር
የአንባቢዎቼን ትችት (እርምት) እንዳገኝ ወይም በርታበት የሚል ደጋፊን ለማግኘት የሚያስችል እማኝ የሚሆን የኢ.ሜይል አድራሻ ስለ
አልነበራቸው የሁለቱንም ወገን ማየት አልቻልኩም። በተለያዩ ስሞች (መጠሪያዎች)የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራው ላይ የተፈጸመውንና
እየተፈጸመ ካለው በመነሳት፤የመከላከያ ሠራዊቱ ከሕዝብ መነጠሉንና የገዥው ቡድን መሣሪያ መሆኑን በሕዝብ ላይ ያነጣጠረ
መሣሪያውን አፈሙዝ እንዲያነሳ፤ እንኳን እስራት ሞትም ይምጣ ለሱዳን በተሰጠው መሬታችን ላይ የሚከተለውን አደጋ በማስመልከት፤
አባጣለው ገብሬ፤ፎቁንና መንገዱንማ ጣሊያንም ሠርቶት ነበር ልማታዊ መንግሥት ተብየው የማልማት ተፈጥሮ እንደሌለው ማሳያ፤
ህወሃት ማን ነው?የህወሃትን መነሻና መድረሻ ያመላከተ ፤ ሳይኖሩ መሞት በደርግም ይሁን በነዚህ የትግራይ ወራሪ ወንበዴዎች ዘመን
የኢትዮጵያ ሕዝብ ኖሮን ሳይኖር የሚሞትበትን ውስጣዊ ሁኔታዎች ያመላከተ …ወዘተ ጹሑፎችን የሚያካትቱ ነበሩ።ሁሉም ጹሑፎቼ
ጠብ አጫሪውና ጐሰኛውን(የትግራይ ወንበዴዎች ቡድን) የየወቅቱን እንቅስቃሴ በመከታተል የምዘግባቸው ነበሩ ወደፊትም ይህን
“የቀለም አብዮት” እያሉ ህወሃቶች የሚቀልዱበትን ቃል ሌላ የሚናፍቁት“የጥይት አብዮት” እስከሚመጣላቸው ድረስ ተውሸ ልበለውና
የቀለም አብዮቱ ወይም የህወሃትን ፀረ-ሕዝብና ፋሽስታዊ ባሕሪይ በማጋለጥ እቀጥልበታለሁ ። ወደ ነጥቤ ልመለስና ማስተላለፍ
የፈለኩትን መልዕክት እንደሚከተለው ላካፍላችሁ ወደድኩ።
የተለያዩ ፀሐፊዎች የብዕር ስምን የሚጠቀሙበት ለምንድን እንደሆነ ምክንያቱ ግልጽ ነው። ህወሃትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ያልፈለጉ
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ወይም ከኢትዮጵያ አጎራባች አገሮች በስደት የሚኖሩ በብዕር ስም ቢጠቀሙ አይፈረድባቸውም። እንደ እባብ
የሚቀጠቅጥ የመከላከያ ኃይልና የአጋዚ ሠራዊትን የተማመነ ፤ ጓዳ ገብቶ የሚሰልል ደህንነትን ተማምኖ ራሱን ከሕግ በላይ ላደረገ ባለ ጊዜ
የተለያዩ የትግል ስልቶችን መጠቀሙ አግባብ ያለው ነገር ነው።በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራው)ግን ስሙን ለማስቀመጥ
የሚፈራው ለምንድን ነው የሚለውን ስንመለከት 1ኛው/ ዝም ብሎ ፍርሃት ነው። የሥርአቱ የጥቅም ተካፋይ ከሆነ ወይም በጉልበቱ
ንብረት ያፈራ ነገር ግን ሥርአቱን የጠላ ወደ አደባባይ ብቅ ብል ንብረቴን ይወርሱኛል የሚል ሊኖር ይችላል መፍትሔው ግን ተደብቆ
በመተኮስ አይመጣም ሊታገል የቆረጠ ልብ ሕይወት ንብረትን መሰዋትን እንደሚያስከፍል መርሳት አይገባውም።የኔ ቢጤ ንጣታም ድኻ
የሚኮሳ ደሮ የሌለው ግን ምኑ ይወረሳል? ማንስ አሜሪካ አውሮፓና ካናዳ መጥቶ አፍኖ እንዳልወሰደው ነው? በቅርቡ አንድ ወንድሜ
አንድ ጨዋታ አጫወተኝ -- የዘመኑ ሰው መስታዎት መሆን ሲገባው መነጽር እየሆነ መጥቷል አለኝና መጀመሪያ ሁለቱን በመጠን አይቸ
በማነስና በመተለቅ መልስ ስሠጠው እሱ ግን ሌላ መልስ ነበረው። “” መነጽር ሌላውን ብቻ የምትመለከትበት ነው መስታዎት ግን ራስህን
የምታይበት ነው”” ብሎ አብራራልኝ። እናም ሌላውን ከማሔስ ወይም ከመተቸት ቀድመን ራሳችን እንገምግም። የጠብ ከፋፍሎ የለም።
ህወሃት መወገድ ያለበት ፋሽስት ድርጅት ነው ብሎ የሚያምን ተቃዋሚ ከማን ጋር እንደሚታገልና እንዴት እንደሚታገል ማየት ይገባዋል።
«ተደብቆ መተኮሱ ባይለመድ መልካም ነው። አብርሃ ደስታ ከትግራይ ተመስገን ደሳለኝና ፕሮ/ መስፍን ግርማ ሰይፉ እዛው ህወሃት
አፍንጫ ስር ሆነው እየታገሉ አይደለም እንዴ?ድርጅቶችን ሳንጨምር :: 2ኛው/ ፍርሃት ኢትዮጵያ ስሄድ ያስሩኛል፤ ቤቴን ድርጅቴን
ይወርሱብኛል ቤተሰቤን ያሰቃዩብኛል የሚባል ምክንያት ነው። ኧረ ማን ነው የሥርአቱ ደጋፊ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ወትቶ
ገብቶ የሚያድረው? በርግጥ ይህ አይነቱ ድርጊት የህወሃት ዋና ባህሪው እንደሆነ ይታወቃል ነገር ግን እስከ መቼ ? እንዲህ ዓይነቱ ሰው
ከፍርሃት በቀቀን ራሱን ማላቀቅ ወይም አርፎ መቀመጡ ይመረጣል የድረ-ገጽ ባለቤቶችን ሥራም የሚያቃልለው ይመስለኛል።
ምክንያቱም አልጨከነም ልቡ አልቆረጠለትም ማለት ነው። ትግሉ ሀገርን በማዳንና በማጥፋት ፤ ተተኪ ትውልድ በመተካትና ባለመተካት
፤ የሀገርን ታሪክ ጠብቆ በማቆየትና ህወሃት በያዘው መንገድ ቀጥሎ እንዲገታና በህወሃት መሪነት ከባዶው የሚጀምር ታሪክ የህወሃት ታሪክ
ለመፍጠር በሚደረግ ፤ የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበርና በማስደፈር …ወዘተ ላይ የመጡ ፈተናዎችን የማለፍና ያለማለፍ ጉዳይ ነው።
በአንድነት ላይ ያነጣጠረ ነጣጥሎ አዳክሞ አገር የማጥፋት ዘመቻ ነው።
ለማጠቃለል በአሁኑ ሰአት የሚፈራና ሲርድ የሚያድር የህወሃት ግብረ-በላ ፤ ጋሻ ጃግሬና ህወሃት ናቸው እንጅ የመከራ ቀንበር ከትካሻው
የማይወርድለት ምስኪን ኢትዮጵያዊማ ሳይሞት የሞተ አይደለም እንዴ? ለምኑ ይፈራል ? አንዴ ገላውን ለህወሃት ነብሰ ገዳይ ቡድን
የሰጠ ስለሆነ “ደም ተቀብቶ ዝምብ አይፈሩ” እንዲሉ ከደሙ ንጹሕ በመሆኑ የሚፈራበት ምክንያት የለውም ። ድንጉጦችን
ሲያስባትታቸውና አተኩሮ ያያቸውን ሁሉ ወደ ዘብጥያ የሚያወርዱት ሞራለቢሶችን ከሚያስፈራው ምክንያት በጥቂቱ- በዝርፊያ የከበሩ
እነሱ፤የተመቻቸ ኑሮ የሚኖሩ እነሱ፤አገር የሚገዙ እነሱ ሁሉ ነገር መሬትም የነሱ፤ ገዳይ እነሱ፤ አሳሪ እነሱ፤ፈራጅ እነሱ፤ በወንጀል
የተጨማለቁ እነሱ፤ሳዳጆች እነሱ፤የጥፋት መልዕክተኞች እነሱ፤ ትውልድ ያመከኑ እነሱ፤ ለዘመናት የቆየን ተከብሮ የኖረን የዋልድባ ገዳም
የመነኮሳትን አጽም በዶዘርና ግሪደር እያረሱ ስኳር እናመራታልን በሚል ሰበብ የተዳፈሩ ታሪክ ይቅርታ የማያደረግላቸው እነሱ ፤
በየገዳማቱና አብያተ ቤተክርስትያናት ርኩስ ተግባር የፈጸሙ እነሱ፤ የራሳቸው ታጋይ የነበረን ዐይንህ ላማረንም በማለት ገድለው የጨረሱ
እነሱ፡ታሪክን የካዱ እነሱ ናቸውና። ስለዚህ አናሳዎቹን አስወግዶ በሕዝብ ይሁንታ የሚገነባ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማምጣት
የቻልነውን ሁሉ ልናደርግ ኃላፊነትና ታሪካዊ ግዴታ አለብን እንነሳ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም ትኑር!!!
e.mail:- fgetachew@gmail.com

No comments:
Post a Comment