የኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰላማዊ ትግል መንገድ እየተዘጋ ነዉ አለ፦ ህዝቡን ወደ ትጥቅ ትግል እንዳይወስድ እንደሚሰጋ አስጠነቀቀም።
ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ ይከተላል ያለውን አደገኛ አካሄድም በጥብቅ አወገዘ ። የመድረክ አመራር አባላት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢህአዲግ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን በመዝጋቱ ፣ በሰላማዊ ትግሉ ላይ አሉታዊ ጥላ እንዳጠላበት አስታውቀዋል ። ህዝቡ ይህን እንዲገነዘብ ያሳሰቡት የአመራር አባሉቱ ከፓርቲው ጎን በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል ።
.dw.de
No comments:
Post a Comment