Sunday, September 14, 2014

ተቃዋሚዎችና ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ ዘመን ተመኙ

        የተቃዋሚ ፓርቲዎች አዲሱ ዓመት ዲሞክራሲያዊ ስርአት የሚያብብበት፣ የህግ የበላይነት የሚረጋገጥበትና የፖለቲካ ምህዳር የሚሰፋበት ዓመት እንዲሆን በመመኘት፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመልካም ዘመን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡የኢትዮጵያ ዲሞክራሲውያን ፓርቲ (ኢዴፓ) ለአዲስ አድማስ በላከው የመልካም ምኞት መግለጫ፤ መጭው ዘመን የመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርአት የሚጠናከርበት፣ የጥላቻና የኩርፊያ ፖለቲካ ታሪክ የሚሆንበት፣ የመቻቻልና የመከባበር ፖለቲካ የሚጎለብትበት፣ የጭፍን ተቃውሞና ድጋፍ በአማራጭ የፖለቲካ ሃሳብ የሚተካበት እንዲሁም፣ ምክንያታዊ ፖለቲካ የሚያብብበት እንዲሆን ተመኝቷል፡፡
ህዝቡ በመጭው አገራዊ ምርጫ በተሳትፎው ስልጡን መሆኑን ዳግም የሚያረጋግጥበትና የፖለቲካ ምህዳሩ ሁሉንም አሳታፊ በሆነ መልኩ የበለጠ የሚሰፋበት እንዲሆን የተመኘው ኢዴፓ፣ የሀገር ዳር ድንበር በማስከበር ስራ ላይ ለተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ለህግ ታራሚዎች እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ ብሏል፡፡
ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (ቅንጅት) በበኩሉ፤ ለ2007 ምርጫ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቁሞ አዲሱ ዓመት የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት ያለገደብ የሚከበርበት፣ ድህነት ተወግዶ ብልፅግና የሚመጣበት እንዲሁም ዜጎችን እኩል የሚያደርግ ዲሞክራሲዊ ስርአት የሚሰፍንበትና በህዝብ ለህዝብ” የቆመ መንግስት የሚመሰረትበት ይሆን ዘንድ ተመኝቷል፡፡ የኢህአዴግ አንዳንድ ካድሬዎች በቅንጅት አባላት ላይ ወከባ እየፈፀሙ ነው ያለው ቅንጅት፤ ነፃነትን ገድቦ የምርጫ በእንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ተገቢ ባለመሆኑ፣ ኢህአዴግ በአዲስ ዓመት ጉዳዩን በአንክሮ ሊያስብበት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)፤ በበርካታ የሃገሪቱ ከተሞች ህዝባዊና ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከ97 ዓ.ም ወዲህ በህብረተሰቡ ውስጥ የሰረፀውን ፍርሃት ፖለቲካ ድባብ በማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን የጠቆሙት የፓርቲው ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ፤ የአባላት እስርና እንግልትን ጨምሮ በርካታ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም አላማውን አሳክቷል ብለዋል፡፡
ፓርቲው ከመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጋር ውህደት ለመፈፀም ከጫፍ ላይ ደርሶ እንደነበር አቶ ስዩም አስታውሰው፤ ሂደቱ ቢሳካ ኖሮ 2006 ዓ.ም ይበልጥ ስኬታማ ዓመት ይሆንልን ነበር ብለዋል፡፡ ውህደቱም በአዲሱ ዓመት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሳካል ብለን እናምናለን ሲሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡ ቀጣዩ አመትም ሰብአዊና ዲሞክራሲዊ መብቶች እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የሚከበሩበት፣ ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነበት፣ እንዲሆን ከመንግስት በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቁ ጠቁመው፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤናና መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡ አገሪቱ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት የምትመች፣ ዜጐች ስደትን የማይመርጡባት አገር እንድትሆንም አንድነት ተመኝቷል፡፡ የኢህአዴግ የህዝብ ተሳትፎ አደረጃጀት ፅ/ቤት ኃላፊና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ደስታ ተስፋው በበኩላቸው፤ ያለፈው ዓመት ኢህአዴግ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ተግባራዊ በማድረግ በርካታ ውጤት እያስመዘገበ ያሳለፈበት ዓመት መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ ከድህነት ለመውጣት እየተደረገ ያለው ርብርብ አይቻልም የሚለውን መንፈስ የሰበረ ነው፡፡
2007 ዓ.ም የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ የመጨረሻ ዓመት በመሆኑ ከምንጊዜውም በላይ ለላቀ ውጤት የምንነሳበትና የምንረባረብበት ዓመት ነው” ያሉት አቶ ደስታ፤ በዚህ ዓመት ምርጫ እንደሚካሄድ አስታውሰው፤ ህዝቡ ህገ-መንግስቱ የሰጠውን መብት ተግባራዊ የሚያደርግበት ዓመት ነው ብለዋል፡፡ ለኢህአዴግ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ዓመት መሆኑን የገለፁት አቶ ደስታ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የሰላም፣ የብልፅግናና የእድገት ዓመት እንዲሆን፣ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ እየፈቱ፣ በሃገራዊ መግባባት እጅ ለእጅ ተያይዘን ሃገራችንን ለላቀ ውጤት የምናበቃበት ዓመት ይሁን ሲሉ ተመኝተዋል፡፡ ያለፈው ዓመት ለመኢአድ አባላት ከባድ ጊዜ እንደነበር አስታውሰው ፓትሪውንም የተለያዩ አካላት ለማፍረስ ጥረት ያደረጉበት አመት ነበር ብለዋል፡፡ አክለውም የዲሞክራሲው ሂደት ወደ ኋላ እንጂ ወደፊት የሚሄዱበት ዓመት አልነበረም ብለዋል፡፡
“የ2007 ዓ.ም ደግሞ ህዝቡ በንቃት መሪዎቹን የሚመርጥበት ዓመት ይሁን፣ መንግስትና ምርጫ ቦርድ ቦታ ከሰጡን ለመወዳደር እንዘጋጀለን፤ ካልሰጡን ይቀራል” ያሉት አቶ አበባው፤ ዓመቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰላምና የብልፅግና እንዲሆን በፓርቲያቸው ስም መልካም ሞኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን እንደሻው በበኩላቸው፤ መድረክ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የብልፅግናና የጤና ዓመት እንዲሆን ተመኝተው በሃገሪቱ ያለው የፖለቲካ ምህዳር ችግር በሰላማዊ ውይይት ተፈትቶ ህዝቡ የስልጣን ባለቤት ለመሆን በፍትሃዊ ምርጫ ድምፁን የሚጥበት አመት ይሆን ዘንድ ተመኝተዋል፡፡
Rate this item
(1 Vote)
back to top
ስፖርት አድማስየዋልያዎቹ የሞሮኮ ጉዞ አጠያያቂ ሆነ
የዋልያዎቹ የሞሮኮ ጉዞ አጠያያቂ ሆነ
       የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2015 እኤአ ሞሮኮ ላይ ለሚስተናግደው 30ኛው አፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍበት ዕድል ተመናመነ፡፡ ባለፈው ሳምንት በተደረጉ

 
 
 


ነፃ አስተያየትአገሪቱን ወደኋላ ሲጎትቱ የኖሩት ወገኛ ሃሳቦች
Written by ዮሐንስ ሰ.
           ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ሌሎችን ለመርዳት የሚችሉ ስኬታማ ሃብት ፈጣሪዎችን በማፈላለግ ልምድ ከማቃመስና በአርአያነታቸው ከማነቃቃት ይልቅ፤ የሚስኪኖችን ጓዳ ጎድጓዳ እያነፈነፈና እንባ እያራጨ በሬዲዮ ወይም በቲቪ ለአደባባይ
ህብረተሰብአዲስ አመት ሲመጣ ከአሮጌ ማንነት እንውጣ!
አዲስ አመት ሲመጣ ከአሮጌ ማንነት እንውጣ!
(እስቲ እውነት እውነቱን እናውራ)    ሰው መሬት መንገሻው ሰማይ መናፈሻው ተደርገው የታነፁለት ንጉስ ነው፡፡ ስለሆነም ልቡን ስሎ፣ አዕምሮውን አብስሎ ሲተጋና ጥበብን ሲሻ በመሬት የተተከሉ፣ በሰማይ የተሰቀሉ እንዲሁም መሀል ላይ የሚንቀዋለሉ ፍጥረታት
ርዕሰ አንቀፅ“በአንድ ጊዜ ከላሟ፤ ሥጋዋንም፣ ወተቷንም፣ ጥጃዋንም ማግኘት አይቻልም!”
የራሺያው መሪ ስታሊን ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ አደረገ አሉ፡፡ ሰዉን ስብሰባ ጠርቷል፡፡ ተሰብሳቢው ፀጥ ብሎ ያዳምጣል፡፡ከተሰብሳቢው መካከል ድንገት አንድ ሰው አስነጠሰው፡፡ ስታሊን ንግግር ከሚያደርግበት ምስማክ ቀና ብሎ፤ በቁጣ፣ ኮስተር ባለው
ከአለም ዙሪያየጋዛ ጦርነት በገንዘብ ሲሰላ…
የጋዛ ጦርነት በገንዘብ ሲሰላ…
*    ጋዛን መልሶ ለመገንባት 6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል*    እስራኤል ለጦርነቱ 2. 3 ቢሊዮን ዶላር አውጥታለችለሰባት ሳምንታት ያህል ከወደ እስራኤል ቀን ከሌት ሲሰነዘርባት በቆየው አሰቃቂ ድብደባ አሳር መከራዋን ስታይ የቆየችው የፍልስጤሟ
ባህልየዘመን መለወጫና አፄ ቴዎድሮስ
የዘመን መለወጫና አፄ ቴዎድሮስ
“ይማሯል እንደ አካልዬ! ይዋጉዋል እንደ ገብርዬ!”          ይህን የተናገሩት ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው፡፡ በዘመናቸው የነበሩ ካህናትና የእስልምና መሪዎች “እኔ እበልጣለሁ ሊቁም እኔ ነኝ” እየተባባሉ ያስቸገሩ ነበርና ሁለቱን ወገኖች
ኪነ-ጥበባዊ ዜና“የክረምት ፊደላት” የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ለ3ኛ ጊዜ ተካሄደ
እናት ማስታወቂያ እና አጋ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከጀርመን የባህል ማእከል፣ ከሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያና ከካፒታል ሆቴልና ስፓ

&coopy; 2013

No comments:

Post a Comment