ገዢዉ ፓርቲ ሰማያዊና አንድነት እንዲላተሙ ገዢዉ ፓርቲ ሰማያዊና አንድነት እንዲላተሙ ይፈልጋል ---- ናኦሚን በጋሻዉ ናኦሚን በጋሻዉ
ከፋሲካ/ትንሳኤ ቀን (ሚያዚያ 12) በስተቀር፣ ከመጋቢት 28 ጀምሮ ያሉ እሁዶችን ( መጋቢት 28 ፣ ሚያዚያ 5፣
ሚያዚያ 19 ቀን) የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ለማድረግ ቢያሳውቅም ከአስተዳደሩ እውቅና እስከአሁን ማግኘት
አልቻለም። አገዛዙ የአንድነትን ሰልፍ ለምን እንደፈራ አልገባኝም። አንድነት ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ያለው
እንደመሆኑ ሚሊዮኖች ይመጣሉ የሚል ጥርጣሬ ስላለም ሊሆን ይችላል።
በአንጻሩ ሌላ የፖለቲካ ድርጅት የሰማያዊ ፓርቲ፣ በመሃል ጣልቃ ገብቶ፣ አንድነት ባሳወቀበትና በቂ ጥበቃ
ማሰማራት አይቻልም በተባለበት፣ በሚያዚያ 19 ቀን፣ ሰልፍ እንደሚጠራ ለአስተዳደሩ አሳዉቆ ቅስቀሳዉን
ጀመሯል።
ገዢው ፓርቲ፣ ለአንድነት በሚያዚያ 19 ቀን እውቅና አልሰጥም ብሎ፣ ለሰማያዊ እውቅና ሳይሰጥ እንዳልቀረ፣
ካልሰጠ ደግሞ እንደሚሰጥ የሚናገሩ አንዳንድ ዘገባዎችንም እያነበብን ነው። ይህ የአገዛዙ ዉሳኔ፣ በሰማያዊና
በአንድነት መካከል ልዩነቶችን ለመፍጠር፣ «ተቃዋሚዎችን እርስ በርስ እየተጋጩ ነው» የሚል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ
በመርጨት ህዝቡን ለማደናገርና ተስፋ ለማስቆረጥ ሲባል፣ በተጠናና በተቀናበረ መልኩ የተወሰነ ጸረ-
ዴሞክራሲያዊና ሕግ ወጥ ዉሳኔ ለመሆኑ ብዙ አርቆ ማሰብ አይጠይቅም። በአጭሩ፣ አገዛዙ በተቃዋሚዎች
መካከል ትብብርን ማየት አይፈልግም። ተቃዋሚዎች እንዲላተሙና እንዲከፋፈሉ የማይቆፍረው ጉድጓድ፣
የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። በሰማያዊና በአንድነት መካከል የተፈጠረዉም ለአገዛዙ ትልቅ ገጸ በረከት ነው።
እርግጥ ነው አንድነት ሰልፍ ለማድረግ ከአስተዳደሩ ጋር እየተነጋገረ ባለበት ወቅት፣ ሰማያዊ ፓርቲ ጣልቃ
መግባቱ፣ በአንድነቶች ዘንድ በጥሩ አልታየለትም። እንደዉም ሕዝቡ ደስ የሚሰኘው፣ ሰማያዊ የአንድነትን ሰልፍ
ተቀላቅሎ በጋራ ሰልፉን ቢጥሩ እንደሆነ እየታወቀ፣ ሰማያዊ በተናጥል ጥንቃ መግባቱ ተገቢ አይ ደለም።
በተለይም ደግሞ ሚያዚያ 19 ቀን አንድነት ቀድሞ ጠይቆ፣ አገዛዙ ለሰማያዊ ፓርቲ እውቅና ለመስጠት መፈለጉ፣
በብዙዎች «ለምን? እንዴት? ሰማያዊ ከአንድነት በምን ተለይቶ ? …» የሚሉ ጥያቄዎች በሰማያዊ ላይ እንዲጠይቁ
በማድረግ ሰማያዊን ሊጎዱ የሚችሉ ናቸው።
ነገር ግን የአንድነት ፓርቲ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው፣ ጥያቄዎች በሕዝቡና በሜዲያው ተጠይቀው ምላሽ
እንዲያገኙ በመልቀቅ፣ ነገሮችን በእርጋታ መያዝ ያለበት ይመስለኛል። ብዙም ለኢቲቪ ፍጆታ የሚሆን ምልልስ፣
ከሰማያዊዎች ጋር አስፈላጊ አይደለም። ሕዝብ ያያል፣ ይታዘባል።ሁሉን ለሕዝብ ይተወዉ።
ግድ የለም ሰማያዊዎች በሚያዚያ 19 ሰልፍ ይውጡ። አንድ ሰልፍ ይሄን ያህል እንደትልቅ ነገር መቆጠር
የለበትም። መቅደም ነበር የፈለጉት፣ ደስ ይበላቸው ይቅደሙ። አንድነት በሳምንቱ፣ በሃያ ሶስቱም ወረዳዎች ያሉት
መዋቅሮች አደራጅቶ፣ የሕዝቡን ጥያቄዎች ይዞ ያኔ ደግሞ ይወጣል።
በሰማያዊ ዉስጥ ጥሩና ቅን ልብ ያላቸው፣ ከአንድነት ሆነ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብረው መስራት የሚፈልጉ፣
በርካታ በሳል አመራሮችና አባላት እንዳሉ ይታወቃል። ሰማያዊ እያደረገ ካለው ስህተት ተምሮ፣ ቅን አሳቢ
አመራሮች አይለው ወጥተው ከመጡ፣ ሰማያዊ አብሮ ለመስራት ፍቃደኝነት ካሳየ፣ አብሮ ከሰማያዊ ጋር
ለመስራት በሩን ሁልጊዜ ክፍት ያድርግ እላለሁ።
ከዚያ ዉጭ አንድነት እየሰራ ያለውን፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴዉን መቀጠል ነው ያለበት።
ገዢዉ ፓርቲ እያቀናበረ ያለውን ተንኮል ማክሸፍ የሚቻለው፣ ፊትን ከሰማያዊ ፓርቲ አዙሮ፣ ሥራ ሲሰራ ብቻ
ነው። ገዢዉ ፓርቲ ሰማያዊና አንድነት እንዲላተሙ ይፈልጋል። የሰማያዊ ወሳኝ የሆኑ ጥቂት አመራሮች
ከአንድነት ጋር መላተምን ይፈልጋሉ። አንድነት «ሽል» እያለ ማምለጥ ነው ያለበት። ከነርሱ ጋር ተያይዞ ወደ ታች
መጎተት የለበትም። በዚህ ረገድ ብስለትና ጥንቃቄ የሞላዉ የፖለቲካ አመራር ያስፈልጋል። ያንንም የአንድነት
አመራር አባልት ይሰጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ከአዲስ አበባዉ ሰልፍ በኋላ የነቀምቴ፣ የድሬደዋ፣ የአዋሳ፣ የደብረ ታቦር፣ የደብረ ማርቆስ ፣ የለገጣፎ፣ የጂንካ፣
የቁጫ፣ የአሶሳ፣ የአዳማ፣ የአብርሃ ጂራ፣ የመተማ፣ የጎንደር፣ የመቀሌ፣ የጊዶሎና የአምቦ ሕዝብ እየጠበቀ ነው።
እንቅስቃሴ ወደ ህዝቡ። ጉዞ ከሚሊዮኖች ጋር።

No comments:
Post a Comment