Wednesday, April 16, 2014

አባይን ለመንከባከብ የጎሰኛነት አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መተካት አለበት

Page | 1

 አባይን ለመንከባከብ የጎሰኛነት አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መተካት አለበት
 አክሎግ ቢራራ (ዶር)
 ክፍል አንድ
“ለምንወደው ለዛሬው ሕዝባችንም ሆነ፤ ከዘመን ወደ ዘመን ለሚከተለው ትውልድም ጭምር፤ የዓባይን የውሃ ሃብት ለሕይወቱ
ደህንነትና ለፍላጎቱ ማርኪያ እንዲውል ማድረግ፤ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ግምት የምትሰጠውና በቅድሚያ የሚያሳስባት ጉዳይ ነው።
አምላካችን ያበረከተላትን ይህን ሃብቷን ለሕዝባቸው ህይወትና ደህንነት በማዋል እንዲጠቀሙበት ከጎረቤት ወዳጅ አገሮች ጋር
በለጋስነት በጋራ ለመካፈል ዝግጁ ብንሆንም፤ ይህን የውሃ ንብረቷን በቁጥር እየጨመረ ለሚሄደው ሕዝቧና በማደግ ላይ ላለው
ኢኮኖሚ ጥቅም እንዲውል ማድረግ የኢትዮጵያ ተቀዳሚና የተቀደሰ ግዴታዋ ነው።”
 ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ ጥቅምት 1957 ዓም
“ወንዞችን በጋራ ፈሰስ የሚጋሩ አገሮች ሁሉ ውሃውን አግባብ፤ ፍትሃዊ፤ ለሁሉም ጠቃሚ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብትና ግዴታ
አለባቸው። ይህን ሲያደርጉ በተቻለ መጠን ለጋራ ጥቅም በመመካከርና አንዱ ሌላውን ሳይጎዳ፤ ውሃውንና አካባቢውን ዘላቂነት ባለው
መንገድ በመንከባከብ ይሆናል።”
Convention on the Law of the Non-navigational Uses of International Watercourses, UN General Assembly
resolution 43/52 of December 1994.
አባይን የመጠቀም ጥያቄ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከላይ ከተናገሩት በበለጠ ደረጃ ዛሬ ወሳኝ ሆኗል። ባሁኑ ወቅት በዓለም አከራካሪ፤ አሳሳቢና
ጦርነትን ፈጣሪ ከሆኑ አንኳር ጉዳዮች አንዱ ውሃንና ወንዞችን የመጠቀም መብት ነው። ከፍተኛ ሽሚያና ሴራ አለ። ጉዳዩን ያጠኑ
ግለሰቦችና ተቋሞች እንዲህ ይላሉ። “የዛሬ አስራ ስድስት ዓመት (2030) የዓለም ሕዝብ ብዛት እየጨመረ፤ ፍላጎት እያደገ፤ ከተሜነትና
ልማት እየተስፋፋ ስለሚሄድ፤ አራት ቢሊዮን ሕዝብ የውሓ እጥረት ያጋጥመዋል። ከዚህ ውስጥ ብዙ መቶ ሚሊዮን የሚገመተው
በአፍሪካ ቀንድ፤ በሰሜን አፍሪካ፤ በሳሄል አገሮች ይገኛል።” ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ሕዝብ ዛሬ አንድ ነጥብ አንድ
ቢሊዮን ሲገመት፤ በተባበሩት መንግሥታት ስሌት፤ በ2050 ይህ ቁጥር ወደ ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ከፍ ይላል። የውሃ ተፋሰስ
ተፎካካሪ ወደ ሆኑት ግብጽና ኢትዮጵያ ብናተኩር የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ዛሬ ካለው እጥፍ ይሆንና ቢያንስ መቶ ሰማንያ አምስት
ሚሊዮን ይደርሳል። ቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ከገመተው ዝቅ ብሏል ማለት ነው። በአንፃሩ፤ የግብፅ ሕዝብ ብዛት መቶ ሃያ
አምስት ሚሊዮን ይሆናል። ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ግብፅን በስድሳ ሚሊዮን ሕዝብ ትበልጣለች ማለት ነው። ሆኖም፤ ከግብፅ ጋር
ለመወዳደር፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ አንድነት፤ የመላዊ ሕዝቧን ኢትዮጵያውይነት መቀበል ወሳኝ ነው። በተጨማሪ ሁሉም
ኢትዮጵውያን የሚሳተፉበትና ክፍጹም ድህነት የሚላቀቁበትን ዘላቂና ፍትሃዊ ኢኮኖሚ መመስረት ያስፈልጋ። ማንኛውም አገር
በአፈና፤ በጎሰኛንትና በስደት በተበከለ አገዛዝ ጠንካራ ሕብረተሰብና ጥንካራ አገር ለመመስረት አይችልም። ኢትዮጵያ ታሪክ ያላት፤
መነሻና መድረሻ ያላት፤ ታላቅ ለመሆን የምትችል፤ የብዙ ብሄር/ብሄረሰብ ደሴት መሆኗን ተቀብለን ከልዩነቶች በላይ የሚገልጻት ዋናው
እሴት ኢትዮጵያ አንድ አገር መሆኗን መቀበል፤ ዜግነት ኢትዮጵያዊ እንጅ ጎሳዊ አለመሆኑን በማንኛውም ግንኙነት ማስተጋባት የወቅቱ
ጥያቄዎች ናቸው እላለሁ። ይኼን የተቀደሰ መርህ እንደዋዛ ካየነው፤ ኢትዮጵያን ለሌሎች (ጥቂት ተጠቃሚዎችና ለፈረንጆች)
እንደምናስተላልፋት በአይናችን እያየን ነው። ዛሬ ኢትዮጵያውያን በጎሳ ስለተከፋፈሉ፤ መብታቸውና ነጻነታቸው ስለታፈነ በሃገራቸው
የተፈጥሮ ሃብት፤ በቤታቸው፤ በመሬታቸው፤ ብህይዎታቸ፤ በሃብታቸው፤ ለማዘዝ አይችሉም። ለመጀመሪያ ጊዜ ፈረንጆች
ከኢትዮጵያዊን የበለጠ ተሰሚነትና መብት አላቸው። አስደናቂውና የሚያኮራው የመሰረታዊ ለውጥ ምልክት ወጣቱ ትውልድ “መብት
ይጠየቃል፤ አይለመንም፤ ፍርሃት አልወለደንም፤ በህሊናየ አታዝም” እያለ በደሴ፤ በሃህር ዳር፤ በጎንደር፤ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች
የሚያሰማው ድምፅ ነው። ሌሎቻችን እጆቻችን አጣጥፈን የምንመለከት ጊዜ ያለፈ ይመስለኛል።
ከሁሉም በላይ አስጠቂ፤ ከፋፋይ፤ የውጭ ኃይሎች መግቢያ ወንፊት የሆነውን የጎሳ ክልል ስርአት ለመለወጥ ድፍረት ያለው ሕብረ-
ብሄር ተቃዋሚና ዓመራር፤ እውነተኛ ለውጥን የሚፈልግና ለዚህ መስዋት ለመሆን የተዘጋጀ ትውልድ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ
ከጎሰኛነት ፖለቲካና ማንነት አደረጃጀት ራሱን አጽድቶ ለጋራ አገር፤ ለጋራ ፍትሃዊ ልማት፤ ለእውነተኛ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ በፍጥነትና
በቆራጥነት ለመስራት ካልወሰነ በሚኮራባት አገሩ ድሃ፤ ፈሪ፤ አጎብዳጅ፤ ራሱን ወዳድ፤ በህይወቱ ለማዘዝ የማይችል፤ ከቤቱና መሬቱ
ውጣ ሲባል ሳያመናምን “መቸ” የሚል ይሆናል። ፍትህ፤ መብት፤ እኩልነት፤ ነጻነት በልመና እንደማይገኝ ባለፉት አርባ ዓመታት
አይተናል። አዲስ አበባ የሚደረገው የቤትና ሌላ ሕንጻዎች ስራ የሚያሳየው ይኼን ነው። ነዋሪዎች ከቤታቸውና ከመሬታቸው
እንዲወጡ ተደርጓል። ወደፊትም ይደረጋል። ኢትዮጵያውያን የነበራቸውን የእርስ በርስ ትሥሥር (Social fabric) አስወግደው
እንዲበታተኑ እየተደረገ ነው። ለማን ጥቅም፤ ወደየት ለማምራት፤ ማንን ለመተካት፤ ማንን ለማክበር ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች ነገ
ሳይሆን ዛሬ መጠየቅ አለባቸው። እነዚህና ተመሳሳይ የማህበረሰብ ጥያቄዎች ካልተጠየቁና ሕዝቡ ራሱ ለእነዚህ መልስ ካልሰጠ ከፊቱ
ተደቅኖ የሚታየውን አደጋ ለመከላከል ያስቸግረዋል። አንድ ታዛቢ በቅርቡ ባደረገው ዘገባ ሕዝቡ ነቅቶ ለሃገሩና ለራሱ መብት ካልተነሳ
“እትዮጵያ የሚለው አገርና ኢትዮጵያዊ የሚለው ሕዝብ ያከትማል።” ከፅንሱ፤ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኢትዮጵያን Page | 2

እንዳልነበረች አድርጎ እውቅናዋን መናድ፤ ጎሰኛነትን አጠንክሮ በማስተማር ስርአታዊ ማድረግ፤ የኢኮኖሚ፤ የማህበረሰብና የፖቲክላ
የበላይነት ጥቅሙን በማያሻማ መሰረት ተቋማዊ አድርጎ አገር ወዳድ የሆኑ ተቀናቃኞችን በኢትዮጵያ ጉዳዮች ድምፅ እንዳይኖራቸው
ማፈንና ማሳደድ፤ እንዲደኸዪ ማድረግ ነበር። ይህ ቀድሞ የታሰበበት ስትራተጂ በራሳችን መከፋፈልና ፍርሃት ጭምር ስኬታማ ሆኗል።
ለምሳሌ፤ የአማራው ብሄረሰብ ለኢትዮጵያ የሚኮራ አስተዋጽዖ እንዳላደረገ፤ “ጨቋኝ፤ ወራሪ፤ ቅኝ ገዢ፤ ነፍጠኛ” ወዘተ እየተባለ
ሲነገር፤ በገደል ሲወረወር፤ ከያለበት ውጣ ተብሎ በሃገሩ በጂምላ ስደተኛ ሲሆን፤ የረባ የተፈጥሮ ኃብት እንዳይኖረው ሲደረግ፤ ፈቅደን
በአይናችን እያየን “አማራና ወንጀል ተመሳሳይ አይደሉም” ብለን የተነሳን ጥቂቶች ነን። የጋምቤላ (በመሬት ነጠቅ)፤ የሶማሌንና የኦሮሞ
(በሽብርተኛነት፤ የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ (በመሬት ነጠቃና በዘመናዊነት)፤ አማራውን “በመጢነት ወዘተ። እነዚህ ሁሉ
የህወሓት/ኢህአዴግ ኢላማ የሆኑት ሕገ-መንግሥቱን በመጣስ ነው። የእነዚህ ኢትዮጵያውያን፤ በተለያዩ ወቅቶች፤ የሰብእነት ክብራቸው
ሲገፈፍ፤ እልቂት ሲደርስባቸው፤ አቤቱታቸውን ለዓለም ሕዝብ ያሰሙላቸው የውጭ አገር የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ናቸው።
የተማረና ኃብት ያለው በስደት ዓለም የሚኖርና የሚሰራ ኢትዮጵያዊ ስለሌለ አይደለም። ስለተከፋፈልን፤ ራስ ወዳድ ስልሆንና በፍርሃት
ዓለም ውስጥ ስለምንኖር ጭምር ነው።
የውሓ አምባ በሆነችው ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ሕዝብ በየጊዜው ውሃ አያገኝም፤ በእፍኝ ከሚቆጠሩ በስተቀር አብዛኛው ሕዝብ ንፁህ
ውሃ አያገኝም። ሰማንያ ሲስት በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ መብራት የለው፤ ዘመናዊ መገናኛ ህልም ነው ወዘተ።
የህወሓት መስራቾች ከጅምሩ በአዲስ አበባ ሆነ በሌላ ከተማ ፍጹም የፖለቲካ፤ የማህበረሰብና፤ በተለይ፤ የኢኮኖሚ የበላይነት መያዝ
ለተፈለገው “የመቶ ዓመታት” ገዢነት ያገለግላል በሚል ፈለግ ይመራሉ። በቅርቡ አገር ጎብኝቶ የተመለሰ ለህሊናው ተገዢ የሆነ ታዛቢ
“ከዓይን ምስክር” በሚል አርእስት፤ ትዝብት ቁ 22, መጋቢት 28, 2006 ዓም ባወጣው የስርአቱን የአገዛዝ ዘዴ አመልካች ጽሁፍ
እንዲህ ብሏል። “በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ የስስትና የራስ ወዳድነት ባህርይ እየተጎለበተ ነው።” ይህ ስሥታምነትና ራስ ወዳድነት ሆነ
ተብሎ ኢትዮጵያዊ ስሜት እንዳይኖር፤ ራስን ማገልገል አገር ወዳድነትን፤ መተሳሰብን፤ አብሮ መኖርን፤ መረዳዳትን ወዘተ እንዲተካ
የሚያባብል የአገዛዝ ዘዴ ነው። ብዙ ስደተኞች (ዲያስፖራ) የዚህ ዘመናዊ ጥበብ ምርኮኛ ሆነዋል። አንዲት በቤተሰቧ ስም መሬት
ተከራይታ፤ በዶላር ከፍላ “በዲይስፖራ ግቢ” ዘመናዊ ቤት የሰራች ኢትዮጵያዊ-አሜሪካን ስትመለስ ለጓደኞቿ ያወራችው
በዲያስፖራውን በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለውን የኑሮና የአስተሳሰብ ልዩነት ያመለክታል። “አዲስ አበባ የጎጆ ቤት
የሚባል ነገር የለም፤ ርሃብተኛነት ፈጽሞ ጠፍቷል። ለማኝ የለም። በመንገድ የሚተኛ ሰው አላየሁም። እድገቱ በጣም አስደናቂ ነው”
ወዘተ። ታዲያ እድገቱ አስደናቂና ፍትሃዊ ከሆነ ህወሓት/ኢህአዴግ ሰላማዊ ሰልፍ ምን አስፈራው? ተቃዋሚ ፓርቲዎች አገር አቀፍ
በህኖነ ደረጃ ተንቀሳቅሰው እንዲወዳደሩ ምን አስፈራው? ተተኪ የሚሆኑ አገር ወዳድ፤ ለፍትህ የቆሙ፤ ችሎታ ያላቸውን የወደፊት
መሪዎችን ለምን ይስራል፤ ከአገር ያባርራል? የቱሪስቷ አባባል ያስደነቀውና በቅርቡ አዲስ አበባንና ወጣ ብሎ የገጠሩን ሕዝብ ኑሮ ያየ
ግለሰብ እንዲህ ብሎ ጠየቃት “ለመሆኑ አዲስ አበባን ዙረሽ አይተሻል፤ ሰማንያ ሰባት በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖርበትን የገጠር
ኑሮ ዞር ብለሽ አይተሺዋል? አንች ያየሺው የምታርፊበትንና የምትዝናኝበት ቦሌን፤ የዲያስፖራን ሰፈር መሰለኝ።”
ኢኮኖሚስት የኢትዮጵያ “የብልጭልጭ እድገት” ብሎ ሰይሞ መሰረታዊ ለውጥ ገና አይታይም። አገር ወለድ ልማት አይካሄድም። የግሉ
ክፍል አላደገም። ፋብሪካ የለም። ሌላ ቀርቶ ፎቅ ተሰርቶ (ፎቁን ማን በባለቤትነት እንደያዘው ነዋሪው ሕዝብ ይውቃል፤ ባዶውን
ተቀምጧል፤ ተከራይ የለም ባለው ተመሳሳይነት፤ የ “ዓይን ምስክር” ጸሃፊው ድርሰት እንዲህ ሲል አስቀምጦታል። “ብዙ ህንጻዎች
ተሰርተዋል። አብዛኛዎቹ ሆቴሎች ናቸው….ያላለቁና ከነጭራሻቸው የቆሙ ሕንጻዎች ብዙ ናቸው።” ችግሩ ሕንጻዎች መሰራታቸው
አይደለም። ከተሜነትና ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መስራት የዘመናዊነት አመልካች ነው። ጥያቄው ሕንጻዎቹ የማን ናቸው፤ እንዴት ተሰሩ፤
ማንን ይጠቅማሉ/ያከብራሉ፤ ማንን ያገለግላሉ፤ ማንን ያከስራሉ/ያደኼያሉ፤ ገንቢዎች የማንን መሬት ይነጥቃሉ፤ የማንን ቤት ያፈርሳሉ፤
ማን ከቀዩ እየተወገደ ማን እየተተካ ነው፤ ለምን? ወዘተ የሚሉት የማህበረሰብ፤ የኢትዮጵያ ዜግነት ጥያቄዎች ናቸው። ደራሲው በሚገባ
አስቀምጦታል “የወያኔ ባለስልጣናትና የሪያል ስቴት (የመሬትና የቤት ደላላዎች ማለቱ ነው) ባለቤቶች የውጭ ከረንሲ (ምንዛሬ ማለቱ
ነው) ምንጭ የሆነው ዲያስፖራው ስለሆነ የሚገዛውን ቤትና ቦታ በአሜሪካ ዶላር እንዲከፍል ይጠየቃል።” አሜሪካ ያለው የውጭ
ምንዛሬውን ውጭ እንዲከፍል ይደረጋል። ቤቱን ስለሚፈልግ ሕግ ቢጣስ ባይጣስ፤ አገሪቱ ብትጎዳ ባትጎዳ፤ ሕብረተሰቡ በድህነት
ቢሰቃይ ባይሰቃይ፤ የስራ እድል ቢኖር ባይኖር ደንታ የለውም። ስርአቱ ከላይ በአድልዎ፤ በጉቦና በሙስና የገማ፤ በሕግ የማይገዛ
መሆኑን ሁሉም አውቆት የሚፍጨረጨረው የራሱን ጥቅም ለማገልገል ነው። የቤት ዋጋ ወደ ጨረቃ የሚበር ይመስላል። ጥሮ ግሮ
የሚኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋጋውን አይችለውም። የእድገት አድናቂ እየሆነ ይኖራል ማለት ነው። “ነዋሪው ተገዶ፤ ቤቱ ፈርሶ፤
መሬቱ ተነጥቆ” የት እንደሚደርስ ባይታወቅም፤ “ኮንዶሚኒየም ይገባል” የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ከዋናው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣ
ብሎ የሚሰራው “ሑለት መኝታ ቤት ያለው ኮንዶ ሃያ ሰባት ሺህ ዶላር፤ ሶስት ክፍል ያለው ሰላሳ አምስት ሺህ ዶላር” ወዘተ ከሆነ የኔ
ቢጤው በህልሙም ቢመኘው፤ የዲያስፖራ ቅርብ ዘመድ ከሌላው፤ ሊገዛው አይችልም። ከየት አምጥቶ። የማይካደው ገዢው አዲስ
ባለጸጋና፤ አገሩ አስተምራው ተሰዶ ሃኪም፤ የሕግ ባለሞያ፤ አስተማሪ፤ ታክሲ ነጂ፤ ቤት ጠራጊ፤ የፈረንጆች ሕፃናት ሞግዚት ሰራተኛና
ሌላ ሆኖ የሚሰራ ሁሉ የመግዛት አቅሙ ሰርቶ አደር ከሆነው ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ነው።
ሌላ በውጭ ምንዛሬ ለመከራየት የሚችል በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ አለ፤ በእርዳታ፤ በበጎ ስራ አገልግሎት፤ በኢንቬስትመንት፤
በልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ በኃይማኖት፤ በስለላ፤ በሚሊታሪ አገልግሎትና ሌሎች ተቋሞች ወዘተ ስራ የተሰማራ ፈረንጅ።
ከዓምስት ዓመታት በፊት አዲስ አበባ የሚሰራ ወዳጀ በሰበሰበው ማስረጃ ቢያንስ ሃያ ሺህ የውጭ ድርጅቶች፤ አብዛኛዎቹ የመንግሥት
ያልሆኑ ነበሩ። የእነዚህ ቁጥር እንደጨመረ እገምታለሁ። ከላይ የጠቀስኩት ጸሃፊ “ባለስልጣኖች በአርባ ዓመት ውስጥ አዲስ አበባን Page | 3

እንደአውሮፓ ከተማ እናደርጋለን ብለው ተነስተዋል” ብሏል። ይህ ራእይ፤ ሌሎች አገሮች እንደሚደረገው (ቻይና፤ ሕንድ፤ ናይጀሪያ፤
ጋና፤ ሳንቲያጎ/ችሌ፤ ሳይጎን/ቬትናም፤ ባንግኮክ/ታይላንድ ወዘተ፤ ቢያንስ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የመካከለኛው መደብ አካል
ሆነው፤ የሚኮሩባት፤ በባለቤትነት መሬትና ቤት እንዳቅማቸው ገዝተው የሚደሰቱባት፤ ከጎረቤቶቻቸው ጋር ማህበርና ቡና
የሚጠጡባት ወዘተ አዲስ አበባ ብትሆን እሰይ ያስብላል። ከተማይቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ርእሰ ብሄር ከተማ፤ የወደፊቱን አመልካች ናት
ለማለት ይቻል ነበር። የከተማይቱ እድገት ልክ እንደሌላው እድገት ሆኗል፤ አብዛኝው ድሃ፤ ጥቂቶች ሃብታም የሆኑባት። የተፈጥሮ
ኃብት (የከተማና የገጠር መሬት፤ ወንዝና ውሃ፤ ማእደን ወዘተ) የጥቂቶች መክበሪያና መዝናኛ እየሆነ ከሄደ ቆይቷል። ይህ የኢትዮጵያን
ሕዝብ በእድገት ስም ከባለቤትነት ማግለልና ማስወገድ ዙሮ ዙሮ አንድ ቀን አደጋን መውለዱ የማይቀር ይመሰለኛል። ጸሃፌው
“የስስትና የራስ ወዳድነት ባህርይ እየተጎለበተ ነው” ያለው ለዚህ ነው። ይኼን ከስርአቱ የመጣ አዲስ የስስትና የራስ ወዳድነት ባህርይ
“ድርጂታዊ ምዝበራ” በተባለው መጽሃፌ አሳይቻለሁ።
የአባይ “ታላቁ የተሃድሶ ግድብ” ከዚህ ጋር ምን አገናኘው? መሰረተ ልማት ትርጉም የሚኖረው የማህበረሰቡን ህይወት ስያሻሺል ነው።
ግድብ ሆነ ሌላ መሰረተ ልማት ድህነትን ለመቀነስ፤ ቀስ በቀስ ፈጽሞ ለማጥፋት፤ የመፍጠርና የማምረት ለማጎልመስ፤ ብዙ ሚሊዮን
ኢትዮጵያዊያን በተለይ ወጣቱ ትውልድ (ከአርባ ዓምስት እድሜ በታች ያለውን ማለቴ ነው) ወደ ስደት ዓለም ከመጓዝ ይልቅ
በሃገራቸው ኮርተው፤ የስራና የባለቤትነት እድል አግኝተው እንደሌሎች በፍጥነት ሃብታም እንደሆኑ አገሮች (ኮሪያ፤ ታይዋን፤
ሲንጋፖር፤ ታይላንድ፤ ቻይና፤ ቦትስዋና፤ ሞሪሺየስ ወዘተ) ወደ መካከለኛ ገቢ ሲሸጋገሩ ነው። ይህ ምኞት አይደለም፤ ይቻላል። ሆኖም
ሁሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ራሱ ተባብሮና ታግሎ ስኬታማ ማድረግ ግዴታው ነው፤ ፈረንጆችና ጎሰኞች ሊያደርጉለት
አይችሉም። ከተባበሩ፤ ስስታምነትንና ራስ ወዳድነትን ወደ ጎን ትተው ለማህበረሰባዊ እድገት አብረው ከቆሙ፤ ኢትዮጵያዊያን ሌሎች
ከደረሱበት የማይደርሱበት ምንም ምክንያት አይኖርም የሚል እምነት አለኝ።
የማይካደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ፤ ከተሜነት ሲስፋፋ፤ የአገሩቱ እኮኖሚ ዘመናዊ ሲሆን ያለውን የውሃ ሃብት
በእቅድና በዘዴ መጠቅም ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጨማሪ ውሃ፤ ተጨማሪ ምግብ፤ ተጨማሪ የስራ እድል ወዘተ ያስፈገዋል።
የዚህ ለወጣቱ ትውልድ የቀረበ ትንተና መሰረተ ሃሳብ ሁለት ነው።
አንድ፤ ከላይ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከአርባ ሰባት ዓመታት በፊት እንዳስቀመጡት፤ ኢትዮጵያ አባይንና ሌሎች ወንዞቿን ለሕዝቧ ኑሮ
መሻሻል፤ የመስኖ እርሻ አስፋፍቶ የምግብ ዋስትናን ስኬታማ ለማድረግ፤ ለዘመናዊ ኢንዱስትሪ መመስረትና በኩራዝ፤ በእንጨት፤
በኩበትና በሌላ ዘላቂነት በሌለው የማብሰያና የመብራት ኃይል ለሚኖረው ሰማንያ ሶስት በመቶ ለሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ
የመብራት አገልግሎት ለመዘርጋት የመጠቀም መብት አላት የሚል ነው። ስድሳ ሰባት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ መብራት
አገልጎሎት የላቸውም። ስለሆነም፤ የአባይ ግድብ የጎሰኞች ባለፀጋነት ማጠናከሪያ፤ የስልጣናችው ማቆያ፤ የተወዳጅነት መነገጃ ሊሆን
አይችልም። እኔ ግድቡን የማየው ከኢትዮጵያ ጥንካሬና፤ ከሕዝቧ ኑሮ መሻሻል ጋር ነው። የጥቂቶች ስልጣን ማቆያና ጥቅም መገልገያ
መሆን የለበትም። ዓባይን የመጠቀም አስኳል መብት ግብጾችና ሌሎች ደጋፊ የአረብ መንግሥታት ለኢትዮጵያና ለሌሎች የዓባይ ወንዝ
ተፋሰስ አገሮች ሊከለክሉ አይችሉም። ኢትዮጵያ ከዓባይ ወንዝ ሰማንያ ስድስት በመቶ የሚሆነውን ውሃ መጋቢ ወይንም አበርካች አገር
መሆኗ ከፈርዖኖች አገዛዝ ዘመን በፊት የታወቀ ነው። ይኼን ያስተዋሉ ተመራማሪዎች፤ “ግብፅ የናየል (አባይ) ገፀ በረከት ናት ይላሉ፤
እውነት ነው። ግብጽ ያልተቀበለችው ግን አባይ የኢትዮጵያ ገፀ በረከት መሆኑን ነው። አንድ ሰው ገፀ በረከት ሲሰጥ ራሱን ድሃ አድርጎ
አይደለም፤ ይህ ሞኝነት ነው። የኦክስፎርድ ዩኒቪርስቲው ሃሪ ቬርሆኢቭን እንዲህ ሲል አስቀምጦታል። “It is high time for Egypt
to appreciate that the Nile is not Egyptin, but an Afrcan River. Egypt should not issue empty threats of war, but
endorse Ethiopia’s dam programme and work with Sudan and South Sudan to ensure its full potential is realized.”
ባጭሩ፤ “ግብፅ ከዱሮው አቋሟ ወጥታ የአባይ ወንዝ የግብፅ ሃብት ሳይሆን የአፍሪካዊያን ወንዝ መሆኑን መቀበል አለባት…ወደ ጦርነት
እሄዳለሁ የሚለው ዛቻ አያዋጣትም፤ የሚያዋጣት ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ጋር በመተባበር የወንዙን እምቅ ጥቅም ለሁሉም አገሮች
በሚጠቅም ሁኔታ ማልማት ነው።” የምጨምረው ለግብፅና ለኢትዮጵያም የሚያዋጣቸው በሰላምና በመተሳሰብ ይህን ታላቅ ወንዝ
ተመዛዛኝ ጥቅም እንዲሰጥ በመጣር ነው።
Harry Verhoeven, “Why a ‘water war’ over the Nile won’t happen,” June 13, 2013 እንዲህ ብሏል። “ኢትዮጵያ መብቷን
አስጠብቃ፤ በአባይ ሸለቆ ግድብ እሰራለሁ ብላ ስታስታውቅ በጣም ደስ አለኝ፤ የግብፅ መንግሥት ግድቡን፤ የጦር ኃይል ተጠቅሜ
አፈርሳለሁ ሲል አሳሰበኝ።” የስታንፈርድ ዩኒቬርስቲ የህግ ትምኅርት ቤት ዲን ቻፕማን ሰፊ ጥናት አድርጓል። በዓለም ሕግና ደንብ
በኩል ያለውን የይገባኛል መብት የሕግ ተማሪዎችና በማስረጃ የደረሱበት ድምዳሜ የሚከተለው ነው። “የዓለም አቀፍ ሕግ፤ ከላይና
ከታች ያሉ የተፋሰስ አገሮች ሚዛናዊ ግልጋሎት እንዲያገኙ ግዴታ አለባቸው።” ግብፅ በራሷ ውሳኔ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን
የወጡትን የዓለም መንግሥታት ውሎች አሻፈረኝ ልትል አትችልም ማለት ነው። የህግ ባለሞያዎቹ “ኢትዮጵያ የተሃድሶን ግድብ
ለመገንባት መብት አላት ወይንስ የላትም” ለሚለው ጥያቄ “ይህ መብት ምንም አያከራክርም፤ የዓለም የፍትህ ፍርድ ቤት የተቋቋመው
እንደዚህ ያሉ አከራካሪ ጉዳዮችን ለማስተናገድ ነው፤ ጉዳዩ ለፍርድ ቢቀርብ ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ያሸንፋሉ” ብለዋል።
የዓለም ውሎች የአፍሪካን ተፋሰስ አገሮች መብት የሚደግፉ ከሆኑ ግብፆች ከሕግ በላይ ናቸው ማለት ነው? በእኔ ግምት ከዓለም ሕግ
በላይ አይደሉም። በግድቡ ምክንይት ውሃው ይቀንስ አይቀንስ፤ ከግድቡ የሚገኘው ጥቅም ከጉዳቱ ከፍተኛ ይሁን አይሁን ገና
አይታወቅም። ሁለቱ መንግሥታት የተለያዩ ማስረጃዎች ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የግድቡ ማህበራዊ ጥቅም ምን እንደሆነ፤ Page | 4

አካባቢውንና ነዋሪዎችን እንዴት በዘላቂነት እንደሚጠቅም/እንደማይጎዳ፤ የመብራት ኃይሉን ሽጦ የሚያገኘውን የወጭ ምንዛሬ የት ላይ
እንደሚያውል ወዘተ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በግልፅና በአስቸኳ ማስረዳት አለበት። ማስታወስ ያለብን፤ ግብጾችና ሱዳኒሶች ከእንግሊዞች
ጋር በመተባበር የአባይን ወንዝ ለልማታቸው ሲገድቡ( አስዋንና ሮዘሪስ) ማንንም የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች ጥቅምና ፍላጎት ዋጋ
አልሰጡትም። ግድቦቹ የጥቁር አፍሪካ አገር ሕዝቦችን ይጎዳል፤ አይጎዳም ብሎ የጠየቀ ታዛቢ አልነበረም። ከዚህ ባሻገር፤ ኢትዮጵያ
በግዛቷ ውስጥ ግደብ መስራቷ ለግብፆች ስነ-ልቦና፤ ጉራና የታላቅነት መለያ፤ ማለትም፤ አባይን በበላይነት መቆጣጠር የለመዱት ባህል
ይናዳል የሚል ስሜት አለ። ድሃ፤ ኋላ ቀር፤ ድምፅ የለሽ፤ ጥገኛ ወዘተ የነበሩ የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች ወንዞችን የመጠቀም
መብት አለን ብለው በጋራ ሲቆሙ፤ ግብጾች ይህ ሂደት የማይቆም ጉዳይ መሆኑን አይተው፤ አፍሪካ እየተለወጠች መሄዷን
አልተቀበሉትም። ኢትዮጵያና ሌሎች የጥቁር አፍሪካ አገሮች ኢኮኖሚዎች ያድጋሉ ብሎ የገመተ ግብጻዊ የለም። በአብዛኛው የግብፅ
መሪዎች ለጥቁር ሕዝቦች ንቅት ያሳያሉ ማለት ነው። ትህትና፤ ይሉኝታ፤ እኩልነት ወዘተ አሳይተው አያውቁም። በአፍሪካ አህጉር
ተቀምጠው አፍሪካዊ ነን ብለው አያውቁም። ይኼን ዶሓ አይቸዋለሁ። ምንም እንኳን “መለስ እኛ አረቦች ነን” ቢልም፤ በዚህ በኩል
እኛም ኢትዮጵያዊያን ጥቁር አፍሪካዊያን ሆነን ከጥቁር አፊርካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አልመሰረትንም። ለራሳችንና ለሃገራችን ስንል፤
የአባይን መብት ለማስጠበቅ ጭምር፤ የጠበቀ ሁለ-ገብ ግንኙነት መመስረት ግዴታ ነው።
የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች መብታቸውን በግልፅ ለዓለም ሕዝብ ተናግረዋል፡፡ የኡ(ዩ) ጋንዳ ፕሬዝደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ የተናገሩት
አግባብ አለው። “እኛ አፍሪካዊያን ግብፅ በተከታታይ ጥቁር አፍሪካን እየጎዳች እንድትቀጥል አንፈቅድም።” የሙሴቬኒን መንግሥትና
አመራር ብንቀበል ባንቀበል (ውሳኔው የዩጋንዳ ሕዝብ ብቻ ነው) የቆሙበት አፍሪካዊ አቋም ጠንካራና የምጋራው ነው። በተመሳሳይ፤
ሁለት የምስራቅ አፍሪካ መንግሥታት፤ ታንዛኒያና ኬንያ አቋም ወስደዋል። በ2003, የታንዛኒያ መንግሥት ግብጽ የምትከተለውን
የበላይነት አመራር አልቀበልም ብሎ፤ በቪክቶሪያ ሃይቅ ዙሪያ ለሚኖሩ አራት መቶ ሽህ ነዋሪዎች የመስኖ እርሻ እንዲጠቀሙ ቧምቧ
ዘርግቷል። ግብፅ ቦምብ አላደረገችውም። የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በ2004 ዓም አባይን በሚመለከት ስብሰባ እንዲህ ብለዋል።
“ለብዙ ዘመን በዝምታ ስንሰቃይ ኖረናልና የጋራ ንብረታችን የሆነውን ሃብት ለመጠቀም እንድንችል ውሳኔ የመውሰጃው ጊዜ አሁን
ነው።” ይኼ አሁን ሌሎች የጥቁር አፍሪካ የተፋሰስ አገሮች በድርጊት የሚያሳዩት፤ ኢትዮጵያን ሲያስጠቃ፤ ሆኖም ተከታታይ የኢትዮጵያ
መንግሥታት በአቅማቸው የአገራቸውን ብሄራዊ መብት ለማስከበር ሲዋጉበትና ሲሟገቱበት የቆየ ጉዳይ ነው። የታወቀው ምሁር ሃጋይ
ኤርሊች The Cross and the River: Ethiopia, Egypt and the Nile, በተባለው መፅሃፉ ኢንዲህ ብሏል። ግብጾች የአባይን “ወንዝ
ለመቆጣጠር” በኢትዮጵያ ላይ ያልጫሩት ጦርነት የለም። “ግብጽ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና አባይን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር
ከይፋትና አዳል ጦርነት ጀምሮ እስከ ከዲብ ኢስማኤል መንግሥት የጦር ዘመቻ፤ ከዚያም በአፍሪካ ቅኝ ገዥ ሆና የአባይን ፈሰስ ተከትላ
በወንዙ ዙሪያ ያሉትን መሬቶች ሁሉ ‘ለመቆጣጠር’ ፤ ከዚያም አረቦች ያቀዱትንና በቁሳቁስ የደገፉትን የኦጋዴንና የኤርትራን ጦርነቶች
በወሳኝነት ደግፋለች። ግብጽ በኢትዮጵያ ያልጫረችው ጦርነት የለም… በኢትዮጵያውያና አመለካከት፤ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማጥፋት፤
ቢያንስ ለመቆጣጠር፤ ቢቻል በኃይማኖት ዙሪያ ግዛት ለማድረግ ያልሞከረችው ነገር የለም …ከአጼ ላሊበላና አጼ ዘረ ያእቆብ እስከ
ጠቅላይ ሚኒስተር አክሊሉ ሃብተወልድ ድረስ።” ኤርሊች አምባሳደር ዓማኑኢል አብራሃምንና ፕሮፌሰር ውንድሙ ጥላሁንን ጠቅሶ
“የአህመድ ግራኝ ጭካኔ የነበረበት ወረራ ያሳየው፤ በተከታታይ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚደረግ ሴራ ሁሉ የሚጠነሰሰው ካይሮ ነው”
ያሉትን አስምሮበታል። በዚህ ጸሃፊ አመለካከት፤ ኢትዮጵያንና ግብፅን የሚያዋጣቸው ተወያይተውና ተስማምተው ሁለቱንም አገሮች
የሚጠቅም፤ አግባብ ያለው፤ የተመጣጠነና ፍትሃዊ የሆነ፤ የጋራ ልማትንና እድገትን የሚያስተጋባ ስምምነት ላይ መድረስ ነው።
ኤርሊች ያቀረበው ገንቢ አማራጭ መሆኑን፤ በራሳቸው ጥረትና ፍላጎት፤ የአፍሪካ ተፋሰስ አገሮች አምነውበት ከግብፅና ከሱዳን ጋር
ስምምነት ላይ ለመድረስ ሞክረዋል። ይህ አማራጭ ለሁሉም ጠቃሚና ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ (The Diplomacy Option)
የሚረዳ ነበር። የዓባይ ተፋሰስ ትብብር መርሃ ግብር (The Nile Basin Initiative (NBI) 1999) የተባለው አማራጭ በሰፊ ጥናቶች
ተደግፎ በአፍሪካ የውሃና የተፈጥሮ ልማት ሚኒስትሮች ውይይት ዳረ ሰላም፤ ታንዛኒያ እውቅና ያገኘና ተስፋ የሰጠ ራእይና ፕሮግራም
ነው። ከዚያም በኋላ አብዛኛዎቹ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የተፋሰስ አገሮች “የኢንቴቢ ውል” የተባለውን ፈርመዋል። ከላይ የጠቅስኩትን
መርሃ ግብር ዓለም ባንክ፤ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጂትና ሌሎች ለጋስ ድርጂቶች በቴክኒክና በገንዘብ የደገፉት የመጀመሪያ
የጋራ ጥረት ራእይ እንዲህ ይላል “ይህ ታሪካዊ የሆነ አስር መንግሥታት የተሳተፉበት የጋራ ራእይ “ዘላቂነት ያለው የማህበረሰብና
የኢኮኖሚ ልማትን “ተመዛዛኝ በሆነ መንገድ የተፋሰስ አገሮችን ጥቅም ለማጠናከር” የሚደረግ ጥረት ነው (In an historic effort, the
ten countries of the Nile have come together within The Nile Basin Initiative to realize a shared vision to achieve
sustainable socio-econmic development through the equitable utilization of, and benefit from, the common Nile
Basin water resources.” መርሃ ግብሩ የሚከተሉትን ሰባት ሁለ-ገብ የሆኑ ዓላማዎች ያመለክታል፤
አንድ፤ የጋራ ዳር/ድንበር የሚመለከት የአካባቢ እንክብካቤ
ሁለት፤ የወንዙ የመብራት ኃይል ንግድና አጠቃቀም
ሶስት፤ የእርሻ ምርትን ለማሳደግ ውሃውን ሃላፊነት ባለውና በቁጠባ መጠቀም
አራት፤ የውሃ ሃብት እቅድና አስተዳደር
አምስት፤ እርስ በርስ መተማመንን ማጠናከር፤ አግባብ ያላቸውን ሁሉ ማሳተፍ (መገናኛ) Page | 5

ስድት፤ ትምህርትና ስልጣኔ
ሰባት፤ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ልማት ማጠናከር፤ ጥቅምን/ትርፍን በጋራ ማደላደል/ ሚዛናዊና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማሰራጨት።
(The Nile Basin Initiative, Shared Vision Programs, 7 Volumes, 2001, Entebbe, Uganda).
በአጠቃላይ ሲታይ፤ ይህ መርሃ ግብር ካለፈው የአባይ አጠቃቀም እጂግ የተለየ፤ በተፋሰስ አገሮች የጋራ ጥቅምና ሃላፊነት ላይ ያተኮረ፤
ግጭትን የሚያስወግድ፤ ወንዙ በዘላቂነት ለሁሉም አገሮች እንዲያገለግል የተፀነሰ፤ ውሃን እንደማይተካ የተፈጥሮ ሃብት ለመንከባከብ
የሚያስችል ነው። አምባሳደር ኃይሉ ወልደ ጊወርጊስ ከላይ በተጠቀሰው መፅሃፉ እንዳስቀመጠው “የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች
አስሩም የዓባይ ተጋሪ አገሮች፤ በጋራ ባላቸው ራዕይ በመመራት፤ የውሃ ኃብታቸውን በተሻለ መንገድ ለማስተዳደርና ድህነትን
ተባብረው ለማሸነፍ ነው…. በመርሃ ግብሩ መሰረት የአባይ ተፋሰስ አገሮች በጋራ የሚወስዷቸው እርምጃዎች ሲሆኑ ዋና ግባቸው
የተፋሰሱን ውሃ ሃብት በሚዛናዊ ግልጋሎት አካባቢውን የሚጠቅም ዘላቂ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ማዳበር ነው።” ሆኖም ይህ
የተቀደሰ የጋራ ልማት ራእይና ተባባሪ የሆነ ፕሮግራም አልተሳካም። ከ1999 ጀምሮ የተባበሩት መንግሥታት፤ የአፍሪካ አንድነት
ድርጂት፤ ዓለም ባንክና ሌሎች መርሃ ግብሩ ስኬታም እንዲሆን ብዙ ጥረት አድርገዋል። ዓለም ባንክ ለዚህ ጉዳይ ስኬታማነት በሚል
ባጀት መድቦ ልዩ ቡድንና መስሪያ ቤት አቋቁሞ ይከታተል ነበር። ይህ የዓለም ሕብረተሰብ ተስፋ የጣለበት ራእይና ፕሮግራም ለምን
እንዳልተሳካ ከዚህ በታች ባጭሩ እንይ።
የግብፅ “ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ የባለንብረትነት መብት”
ግብጾች ከላይ እንዳቀረብኩት አንድ የማይበገር መርህ አላቸው። የአባይን ወንዝ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር። ለዚህ አቢይ ተባባሪ
መሳሪያ የተጠቀሙትና አሁንም ለመጠቀም የወሰኑት ኢትዮጵያን መከፋፈል፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት መሞከር፤ የውስጥ
ተቃዋሚዎችን በገንዘብ፤ በጦር በመሳሪያ፤ በዲፖሎማሲ መደገፍና ልክ ኤርትራ እንደሆነው አንድ አንድ ለእነሱ የሚረዱ የአገሪቱ
ክፍሎች ነጻ እንዲሆኑ ማድረግ፤ ኢትዮጵያን በወኪል ወረራ ወዘተ ማድከም፤ ድሃና ደካማ ሆና እንድትቆይ ማድረግ፤ የአባይን ወንዝ
እንዳትገድብ አበዳሪ ለጋስ መንግሥታትና ድርጂቶችን መጫንና ማስፈራራት፤ የአረብ መንግሥታትን በማባበል በኢትዮጵያ ላይ
የቃላትና የዲፕሎማሲ ጦርነት ማካሄድ ወዘተ። ከአረብ መንግሥታት ጋር በሰላምና በመከባበር ለመኖር የተደረገውን ጥረት ሁሉ እንደ
ደማካነት አይተውታል። ሳዳም ሁሴን በስልጣን ላይ ሳለ የኤርትራን ነጻ አውጭ ግንባር ደግፎ “የቀይ ባኅር አረብ እንጂ አፍሪካዊ
አይደለም” ብሎ ፎክሮ ነበር። ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፤ የአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት
አመራር፤ ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ አካል እንድትሆንና የአረብ አገሮች ከኢትዮጱያ ጋር ያላቸው ከታሪክና ከአገሪቱ አቀማመጥ
የመጣ የተፈጥሮ ግንኙነት ማጠንከር አስፈላጊ ነው የሚል ነበር። በዚህ የተነሳ ዓለም ባንክ፤ የአለም ፋይናንስ ድርጂትና ሌሎች
ኢትዮጵያን የመካከለኛው ምስራቅ አካል አድርገዋት ነበር። ይህ ብልሃት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት የትም አላደረሳትም። የአረብ
መንግሥታት የኤርትራን መገንጠል በከፍተኛ ደረጃ ደግፈዋል። አሁን በበላይነት ለሚገዛው ህወሓት ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥተዋል።
የህወሓት መስራቾችና መሪዎች ፀረ-ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አቅም ባይወስዱ ኖሮ የተም አይደርሱም ነበር። በ 1970ዎቹ፤ የንግድ
ባንክ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኘና አገሬን ወክየ ምስራቅ ጀርመን፤ ሩማኒያ፤ ሃንገሪ፤ አሜሪካና ኩባ በሄድኩበት ሁሉ የተነገረኝና
የተጠየቅሁት የአረብና የምእራብ መንግሥታት “መንግስቱ ኃይለማሪያምን ለመጣል” እንደወሰኑ፤ “ለሻቢያና ለህወሓት ነጻ አውጭ
ግንባሮች መረጃና ርዳታ እንደሚሰጡ” ነበር። ግብጾች፤ ሶሪያዎች፤ ኢራኮች፤ አሜሪካኖች፤ እንግሊዞች ወዘተ ይጠቀሱ ነበር።
ቀይ ባህርን ሙሉ በሙሉ የአረብ ባህር አደርጋለሁ ያለው ሳዳም የተመኘውን አግኝቷል። የአረብ አገሮች አጋር ቡድን አግኝተው
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የባህር በሯ ተዘግቷል። መዘጋቱ ኢትዮጵያን ደካማ አድርጓታል፡፡ ኤርትራም ጭምር ድሃና ኋላቀር
እንድትሆን አድርጓል። የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል የጎዳው ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የኤርትራን ሕዝብ ጭምር ነው። ከኢትዮጵያ
አንጻር ሲታይ፤ ደህንነቷን አድክሞታል። “አስደናቂ እድገት” አለ ተብሎ ቢነገርም፤ የኢኮኖሚ እንስቃሴዋን በሚፈለገው ፍጥነትና ደረጃ
እንዲያድግ ማነቆ ሆኗል፤ በተለይ የንግዷን ዋጋ ከፍ አድርጎታል። አንድ ጥናት እንዳመለከተው፤ በሌሎች አገሮች ወደቦች ጥገኛ
የሆነችው ኢትዮጵያ ከሌሎች ወደብ ካላቸው አገሮች ጋር ስትወዳደር የምትሸምተውና ወደ ውጭ የምትልከው እቃ የመጓጓዣ ዋጋ
ቢያንስ ሶስት እጅ ወደላይ ከፍ ብሏል። አንድ መርከብ ላይ የሚጫን ሳጥን (container) ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ ወደ
ብራዚል ከሚላከው ጋር ሲነጻፀር ሶስት እጅ ከፍ ይላል። ይህ ሁኔታ፤ የአገሪቱን ተወዳዳሪነት ይቀንሰዋል። ይህ የህወሓት መንግሥት
ኤርትራን ሆነ ብሎና ፈቅዶ እንድትገነጠል በማድረግ፤ ለኢትዮጵያ ያበረከተው የአሁኑና ተከታታይ ትውልድ ሊረሳው የማይችል ግፍና
ክህደት ነው። (መለስ ዜንዊ፤ “የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወደየት።” ግብጾችና ሌሎች የቀይ ባህርን በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ
ይመኙ የነበሩ መንግሥታት ሁሉ ሳይዋጉ ያገኙት ድል በህወሓት መሪዎች አማካኝነት ስጦታተ ነው።
ጥናቶች የሚያመለክቱት ሱዳንና ግብፅ ለሻቢያ፤ ለህወሓትና ለሌሎች የጎሳ ስብስቦችና ነጻ አውጭ ግንባሮች የኋላ ምሽግ መሆናቸውን
ነው። የግብጽና ሌሎች የአረብ አገሮች ኤርሊች እንደሚለው መቻቻልን፤ መከባበርን ቢፈልጉና፤ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሉአላዊነት፤ ግዛታዊ
አንድነት፤ ጥቅምና ደህንነት ቢያከብሩ ኖሮ፤ እትዮጵያና የአረብ አገሮች የሚደጋገፍ፤ ለሁሉም የሚጠቅም የኢኮኖሚ፤ በተለይ የንግድ
ትሥስር ለመመስረት ይችሉ ነበር። ለምሳሌ፤ አረቦች ምግብ ስለሚሸምቱ ለኢትዮጵያ የእርሻ ውጤት ገበያ ሊሆኑ ይችላሉ። ኢትዮጵያ
ለጊዜው ዘይት ስለሌላት ለዘይታቸው ገበያ አቅርቦት ልትሆን ትችላለች። እስካሁን የሚታየው ሚዛናዊ ያልሆነ የተዛባ ግንኙነት ነው።
አንዱ የበላይ አንዱ የበታች። ዓለም አቀፋዊ (Globalization) የንግድ ግንኙነት የሚጎዳው ለዚህ ነው። ያዋጥል ብሎ ይኼን ሁኔታ
ያጠናከረው የህወሓት ዓመራር ነው። Page | 6

ለዚህ ነው፤ ኢትዮጵያ ሁኔታው እስከሚለወጥ ድረስ፤ የራሷን ጥቅም ለማስከበር ኢኮኖሚዋን ፍትሃዊና ዘላቂነት ባለው መንገድ ማሳደግ
አለባት የሚለውን ሃሳብ የማቀርበው። ይህ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው የእድገት መርህ የመላውን ሕዝብ ተሳትፎ፤ በሕግ ፊት የሁሉም
ኢትዮጵያውያን እኩልነት መከበርን ወዘተ ይጠይቃል። የህወሓት ዓመራር ይህን ወሳኝ የአገዛዝ ስልት ዋጋ-ቢስ አድርጎታል። የተሳሰረ
ማህበረሰብ (Ntional cohesion)፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በተፈጥሮ ሃብታቸው የመገልገል መብት ከአባይ ግድብ በላይ አስፈላጊ ነው።
ኢትዮጵያን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያቆያት ይህ በገንዘብ የማገዛ እሴት ነው። ይህን ትሥስር እንዳልነበር ማድረግ ኢትዮጵያን በቀጥታ
ማድከም ነው። በአባይ ግድብ ሆነ በሌላ የብሄራዊ ዓመራር ወሳኙ ጎሰኛነት ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ነው እላለሁ።
የመላው ሕዝብ ተሳትፎ በስራ ላይ ቢውል አገሪቱ በፍጥነት እንድታድግ፤ የሕዝቡ ኑሮ እንዲሻሻል፤ ስደት እንዲቆም፤ ቢያንስ እንዲቀንስ
ይረዳል። በውጭ ግንኙነት በኩል፤ በተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም (ዓባይ)፤ በአካባቢ የኢኮኖሚ፤ የንግድ፤ የመጓጓዣና ሌሎች ትብብሮች
(Regional Integration) የአፍሪካ አንድነት ድርጂት መስራችና መዲና የሆነችው ኢትዮጵያ መተባበርና መቀራረብ የሚኖርባት
ከሚንቋትና ከሚያደክሟት ጋር ሳይሆን ከጥቁር አፍሪካ ጋር ይሁን እላለሁ። በተለይ በምስራቅ አፍሪካና በአፍሪካ ቀንድ ከሚገኙ
የጎረቤት አገሮች ጋር፤ ኤርትራን ጭምሮ። የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝብ የማይካድ ለብዙ ሽህ ዓመታት የቆየ የታሪክ፤ የባህል፤
የኃይማኖት፤ የንግድ፤ የጅኦግራፊና ሌሎች የሚያገናኙት እሴቶችና ባህሎች አሉት። ይህ ወሳኝ ግንኙነት በጥቂት ጎሰኞችና ራስን
አገልጋዮች መወሰን የለበትም። የሁለቱም ወጣት ትውልድ ከስደትና ውርደት ይልቅ አብሮ መኖሮን መምረጥ አለበት። ህወሓትና ሻቢያ
ይህን እድል የመወሰን መብት የላቸውም። አብሮ መኖር፤ አብሮ ህይወትን ማሻሻል ብልሃት ነው፤ ጥላቻ ድንቁርና ነው። የሳሃራ በታች
አገሮች የንግድና የኢንቤስትመንት ግንኙነታቸው እያደገ የሄደው በፍጥነት የዓለምን ኢኮኖሚ ግንኙነት ከለወጡትና ከሚለውጡት፤
ብሪክስ (ብራዚል፤ ራሽያ፤ ሕንድ፤ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ) ግንኙነታቸውን ስላጠናከሩ ነው። ቻይና ዛሬ በአፍሪካ አገሮችና
በመካከላቸው የሚታየውን የመሰረተ ልማት ኋላ ቀርነት (መንገድ፤ ሃዲድ ወዘተ) ለማሻሻል ጥረት እያደረገች ነው። ለራሷም ንግድ
ስለሚጠቅም። የአፍሪካ አገሮች እያደጉ ለመሄድ፤ በመካከላቸው ያለው የተፈጥሮ፤ የባህል፤ የፖለቲካና ሌላ ማነቆዎች ማስወገድ
አለባቸው (Eliminate physical and other barriers that keep them poor and weak). የልማት ሊቃውንት የሚናገሩትና
የሚተነብዩት ከሳሃራ በታች ያሉ አገሮች ጥሩ መንግሥታትና አመራር ካላቸው ፈጣን እድገት እነደሚያሳዩ፤ በመካከላቸው ጠንካራ
ግንኙነት እንደሚፈጥሩ፤ የተፈጥሮ ሃብታቸውን ለሕዝቦቻቸው ልማት ለመጠቀም ብቃት እንደሚኖራቸ ነው።
የአባይን ግድብ የማህበራዊ ጥቅም ከጥርጣሬ ውስጥ ያስገባው፤ ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን ዓለም
ያደነቀውን፤ ኢትዮጵያን ከውጭ ወረራ የታደጋትን የመወያየት፤ የመነጋገር፤ የመመካከር፤ እውቀትን የመሽመት፤ የመንቀሳቀስና የትም
የመስራት/የመኖር መብት ወዘተ ባህል ስለናደው ነው። ዛሬ ህወሓት ከፈቀደላቸው ታማኞች ውጭ፤ ኢትዮጵያዊያን የትም ለመኖር
አይችሉም። የዜግነት መብት ተንዷል። የአፍሪካ አንድነት ድርጂት እንደ አውሮፓ የጋራ ማህበር የሚደራጂበት ጊዜ ሩቅ አይደለም
የሚለውን መርህ ብጋራም፤ በራሱ አገር እንደ ልብ የመንቀሳቀስን መብቶ ያገበ መንግሥት ከሌሎች አገሮች ጋር ህብረት እፈልጋለሁ
ቢል ተቀባይነት አያገኝም። ጥሩ ቤቱን እያፈረሰ (ኢትዮጵያ) ሌላ ትልቅ ቤት እሰራለሁ ማለት (የአፍሪካ የጋራ ማህበር) የፖለቲካ
ቲያትር ነው። የሁሉም ቤት የሆነችት ኢትዮጵያ ከሌሎች ጋር ለመደራደር አቅም ይኖራታል። ከዚህ በፊት አሳይታለች።
ከታላላቅ ግድቦች የሚገኝ የመብራት ኃይል ስርጭት፤ የሃዲድና ሌሎች መገናኛዎች ለዚህ የአፍሪካ ተደጋገፈ የንግድና የኢኮኖሚ
ግንኙነት ወሳኝ ናቸው። ለዚህ ነው ቻይናዎች በመሰረተ ልማት ላይ ተወዳዳሪ የሌለው ሚና ይጫወታሉ ተብሎ በሰፊው
የሚነገርላቸው። አንድ አህጉር የምትመሰለው አሜሪካ የለማችው አገር አቀፍ መገናኛን በመዘርጋት ነው፤ ቻይናም የምታደርገው
ተመሳሳይ ነው። የኢትዮጵያና የሌሎች ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአባይ ተፋሰስ አገሮች ጥንካሬ ቁልፍ ነው የምልበት ዋና ምክንያት
የወደፊቱን የአፍሪካዊያንን የራሳቸውን የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የሚያደርጉትን የእድገት ስሌት በማጤን፤ የዓባይ ግድብ ለኢትዮጵያ
ጥቅም የሚሰጥ መሆኑን በመገንዘብ ጭምር ነው። ቀደም ሲል እንዳሳሰብኩት፤ ይህ ጥቅም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ መሻሻል ሊውል
የሚችለው ሕዝቡ በአንድነት አስቀድሞ መብቴና ጥቅሜ ይከበር ሲል ብቻ ነው። አልያ፤ ህወሓት አሁን እንደሚያደርገው የኢኮኖሚች
ጮሌነት ዓመራር “ አይዟችሁ፤ ዕኔ የማደርገው ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ነው” ማለቱ አይቀርም። ሕዝቡ ከአሁኑ ለመብቱ መነሳት
አለበት የምለው ለዚህ ነው።
ዓባይ ለኢትዮጵያና ለሌሎች ተፋሰስ አገሮች ወሳኝ ነው። ግብፅ በመተባበር ፋንታ፤ የአፍሪካ ተፋሰስ አገሮች እንዲከፋፈሉ ሞክራለች።
አሁን ከተፋሰሱ አገሮች መካከል ከኤርትራ መንግሥት ውጭ ግብፅን በይፋ የሚደግፍ የለም። የሱዳን መንግሥት የኢትዮጵያን አቋም
ሲደግፍ ኢሳይያስ አፈወርቂ እንደተለመደው ግብፅን ደግፏል። ይኼን ሲያደርግ የጎዳው የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የኤርትራን
ሕዝብ ጭምር ነው። ቀድሞ ወዳጁ የነበረውን፤ የህወሓትን መንግሥት በመጥላት ብቻ የሚጎዳው የራሱንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው።
አቋሙ ኤርትራን ከተፋሰስ አገሮች ለይቷታል። በመለየቱ ከአረብ መንግሥታት ጋር አብሮ ቆሟል ማለት ነው።
የሱዳን መንግሥት ጥንት የነበረውን አቋም (በልዩ ልዩ ምክንያቶች) ለውጦ የተፋሰስ አገሮች ተመጣጣኝ የሆነ ጥቅም የማግኘት
መብታቸውን ይደግፋል። የኢትዮጵያን የተሃድሶ ግድብ ጭምር። ባለፈው ዓመት በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የጦፈ የዲፕሎማቲክ
“ጦርነት” ሲካሄድና የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ከሱዳን ጋር መለስ ዜናዊ የጀመረውን የድንበር ድርድር ‘በምስጢር’ ሲያካሂድ፤ የፕሬዝደንት
አል ባሺር መንግሥት እንዲህ ብሏል። “ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ ውሃ ፈሰስ” ግብፅንና ሱዳንን በሚጎዳ መጠን “እስካልቀነሰች ድረስ
የዓባይን ወንዝ የመገደብ መብት አላት። ሱዳን ታላቁን የተሃድሶ ግድብ አትቃወምም፤ “የግብፅን መንግሥት የምናሳስበው ይህ ግድብ
የመብራት ኃይል በማቅረብ፤ ከፀሃይ ሙቀት የሚባክነውን ውሃ በመቀነስ አንጻር መደገፍ አለበት” ብሏል። ይህ የሱዳን ውሳኔ ግብፅ
ብቸኛ ተቀናቃይ እንድትሆን አድርጓታል። ሆኖም፤ አሳሳቢ የሚሆነው የሱዳን አቋም ዘላቂነት ነው። በአንድ በኩል የኢትዮጵያን መሬት Page | 7

በምስጢር ተደራድሮ መውሰድና በኢትዮጵያና በሱዳን ሕዝብ መካከል የቆየውን ተከባብሮ መኖር ማኮላሸት፤ በሌላ በኩል ወዳጁ
ለሆነው ለህወሓት ጎሰኛና ብሄርተኛ ቡድን ታይቶ የማይታወቅ እውቅና መስጠት ግራ የሚያጋባ አቋም ነው። ነገ ጎሰኛው የህወሓት
ቡድን በሕዝብ ዓመጽ ከስልጣን ቢወገድ የሱዳኑ መንግሥት አቋም ምን ይሆን ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ፤
የባህር በሯ እንዲዘጋና የሱዳን፤ ወይንም የሌላ ወደብ ያለው አገር ጥገኛ እንድትሆን ያደረገ መንግሥት፤ የኢትዮጵያን ቁልፍ ተቋሞችና
እሴቶች አጥፍቶ አገሪቱን ለአደጋ ያጋለጠ አገዛዝ ሊታመን ይችላል? የአባይን ግድብ መገንባቱ ብቻ ያጠበባትን አገር፤ ያጠፋውን እሴትና
ሃብት ይተካል? ወጣቱ ትውልድ ሁልጊዜ የህወሓት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ መሆን የለበትም። ለፍትህ-ርትዕ መቆምና፤ ለራሱ የወደፊት እድል
መታገል ይኖርበታል። ካላደረገ በተከታታይ ለስደት ይዳረጋል። ተሰዶም በአገሩም እየኖረ ይዋረዳል። የገዢው ፓርቲ ቡድን
በተደጋጋሚ ያሳየው ለጊዚያዊ ጥቅም ቅድሚያ መስጠትን ነው። ይህን ሲያደርግ በውሸት፤ በጉራ፤ በማስፈራራት፤ ድርጂቶችን ሰርስሮ
በመግባት፤ በስለላ፤ በማፈን፤ በትምክሕተኛነት ወዘተ ባህርዮችና ስራዎች ነው። የባሽር መንግሥትም ተመሳሳይ የሆኑ ባህርዮች ያሳያል።
ሕዝቡ አያምነውም። አሁንም “አረብ ያልሆኑ ሱዳኒሶችን (ዳርፉር)” ያሰቃያል፤ ይገድላል፤ ያሳድዳል። በሕዝብ ጭፍጨፋ (Genocide)
ተከሷል። የህወሓትም የበላይ ዓመራር በተመሳሳይ ጭፍጨፋ ክስ ቀርቦበታል (ጋምቤላ)።
የህወሓት ጠባብ ጎሰኛ ቡድን የፈጠረው ኢትዮጵያን እንዳልነበረች የማፈራረስ የፖለቲካ አወቃቀር ግልጽ መሆኑ አይካድም። ሆኖም፤
“The Nile (ዓባይ) River is African and Ethiopia is its hub” በተባለው ትንተናየ ባለፈው ዓመት ያቀርብኩት የፖሊሲ ሃሳብ
እንዳለ እደግፈዋለሁ። ገዢውን ፓርቲ ከኢትዮጵያ ሉአላዊነትና ዘላቂ ጥቅም እለያለሁ። የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችና ምሁራን
የህወሓትን ጎሰኛና አምባገነናዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ መብት፤ ከመላው ሕዝቧ ዘላቂ ጥቅም መለየት ግዴታቸው ነው።
አብዛኛዎቻችን የምንለው ይህ ጎሰኛ ቡድን ራሱን አገልጋይ እንጂ መላውን ሕዝብ ወካይ፤ ለአገሪቱ ግዛታዊ አንድነት ተቆርቋሪ፤ ለጋራና
ፍትሃዊ እድገት፤ ላልተዛባ የስራ፤ የገቢና የሃብት ስርጭት የቆመ አይደለም ነው። ይህ አያከራክርም። በአባይ ግድብ ዙሪያ ገዢውን
ፓርቲ መጠራጠር የመጣው በዚህ ምክንያት ነው። ግብጾች ለስድሳ ዓመታት የጨቆናቸውን፤ ሙሰኛውን ሙባረክን በሕዝብ አመጽ
አስወግደው ሞርሲን መረጡ፤ ሞርሲን አስወግደው የጦር ኃይሎችን መረብ እንደገና ዘረጉ። የግብፅ የጦር ኃይል ከሁሉ በላይ አገር
ወዳድ ነው። ስለሆነም፤ ይህ ወታደራዊ አገዛዝ የአባይን ይገባኛልነት አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ይደግፋል። ግብፅ የውስጥ እርጋታ
ባይኖራትም፤ ያልተለወጠውና ግብጾች የሚጋሩት የፖሊሲ ዓመራር የአባይን የበላይነት ይዞ መቆየት ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን
መንግሥት ቢቀያየርም የኢትዮጵያን ብሄራዊ አንድነት፤ በተፈጥሮ ሃብቷ ላይ ሊኖራት የሚገባትን ሉአላዊነት በመንግሥት ጥላቻ የተነሳ
መቃወም በታሪክ ፊት ያስጠይቀናል። የሚጠቅመው የግብፅን መንግስት፤ የሚጎዳው የጥቁር ተፋሰስ አገሮች ነው። በእኔ ግምት፤
የኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ከፖለቲካ፤ ከጎሳ፤ ከኃይማኖት ወዘተ ልዩነቶች በላይ ነው። ከጥላቻ በላይ ነው። የአባይን ግድብ ለመገደብ
ቢችሉ ኖሮ አጼ ኃይለ ሥላሴም ደርግም ይገነቡት እንደነበር ምንም አልጠራጠርም።
በአንድ ወቅት የታወቁት የውጭ ግንኙነትና ሌላ ባለሞያ ደጃዝማች (ዶር) ዘውዴ ገብረ ሥላሴ በዓባይ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን
የባለቤትነት መብት ካርታ ተጠቅመው፤ ታሪክን ተመርኩዘው፤ “ይህ የአባይ ወንዝ መነሻ ነው፤ እንዚህ ጅረቶቹ ናቸው፤ ይህ የጣና
ሓይቅ ነው፤ ይህ የአባይ ጎርጂ ነው፤ አሜሪካኖች አጥንተው ግድቦች ከዚህ ከዚህ ላይ ቢሰሩ ይጠቅማል ብለዋል” እያሉ የኢትዮጵያን
ብሄራዊ መብት ደግፈው በስሜት ሲናገሩ አስታውሳለሁ። ስለዚህ፤ የኢትዮጵያ መብት አያከራክርም። በአጼ ኃይለ ሥላሴና በደርግ ጊዜ
የዓባይ ግድብ ተገደበ ብለን የምንቃወም አይመስለኝም። አብዛኛዎቻችን የፖለቲካ ዓመራራቸውን ባንቀበልም፤ የኢትዮጵያን ዘላቂ
ጥቅም፤ ሉአላዊነትና የሕዝቧን ኑሮ መሻሻል የምንቃወም አይመስለኝም። እንዲያውም ደስ ብሎን ባይሆን “ይኼን ሰሩ፤ የማይረሳ
ሃውልት ነው” እንል ነበር የሚል ግምት አለኝ። የሳይድ ባሬ መንግሥት ኢትዮጵያን ሲወር፤ የኤርትራ መንግሥት ባድሜን ሲወር፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥቱንና መለስን ስለሚቃወም “አገሬ ትወረር፤ አያገባኝም” አላለም። ሴቱም፤ ወንዱም፤ ወጣቱም፤ የሁሉም
የኃይማኖት ተከታዮች፤ ድሃውም፤ ሃብታሙም ወዘተ በአንድ ላይ ተነስቷል። በባድሜ ላይ እውቀቴ የተወሰነ ነው፤ በሶማሌ ወራራ
መጠነኛ እውቀት አለኝ፤ አገሬን አገለግል ነበር። የየንግድ ባንክ ዋና ስራ አስኪያጂ በነበርኩበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ በሶማሌ ጦር
ስትወረር፤ የታወቁት አገር ወዳድ ነጋዴ ከዲር ኢባ ሩብ ሚሊዮን ብር ለአገራቸው እንደሠጡ አስታውሳለሁ። “እኔም ለሃገሬ” ብለው
ወደ ቢሮየ መጥተው የነገሩኝ ትዝ ይለኛል።
የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነትና የተፈጥሮ ሃብቷን የመጠቀም ሉአላዊነትና መብት በማንኛውም መንግሥት የማንቃወም ከሆነ ዛሬ
በምን መስፈርት እንቃወማለን የሚል ጥያቄ አግባብ አለው። የአጼ ኃይለ ሥላሴና የደርግ መንግሥታት እንደተለወጡ ሁሉ፤
የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥትም ይለወጣል። ይህን አልጠራጠርም። ሕዝቡ በመተባበር ከተነሳ ወይንም ገዢው ፓርቲ ነጻና ፍትሃዊ
ምርጫ እንዲካሄድ ከፈቀደ መለወጡ አይቀርም። የማይለወጠው ሃውልትና ጥሪት አባይና በአባይ ላይ የሚሰራ ማንኛውም ግድብ
ነው። የህወሓት የበላዮች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያመጡት ወይንም በችሎታችው የፈጠሩት አንድም ነገር የለም። ህወሓት በውጭ እርዳታ፤
በመዝረፍ፤ ስልጣን ከያዘ በኋላ በኪራይ ሰብሳቦነት ከድኅነት ወደ ሃብታምነት የተሸጋገረ ጎሰኛ ፓርቲ ነው። በበኩሌ የምገምተው
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘረፋውንም በሚገባ ያውቃል፤ ሆኖም ግድቡን ይደግፋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ገዢውን ፓርቲ ግድብ፤
መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶች በመስራቱ ብቻ አመኔታና አድናቆት የሚሰጠው አይመስለኝም። እምነቴ በኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በተለይ
በወጣቱ ትውልድ ስለሆነ፤ ዛሬ ሕዝቡ ዝም ብሎ ህወሓትን የፈለገውን አድርግ የሚል አይመስለኝም። የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን ካለበት
አፈና ለመላቀቅ፤ ኮርቶና በሃገሩ ተከብሮ እንዲኖር ለሰብአዊ መብቱ፤ ለተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነቱ ተባብርሮ መነሳት ይኖርበታል።
እየተነሳም ነው። ለማንኛውም፤ “በእድገት ስም ግርዶሽ” እንዳይሆን፤ ግድቡንና የግብፅን ዛቻ ተጠቅሞ ይሁን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ
ከግድቡ ባሻገር ሁለት ማነቆዎችን አጣምሮ የመወጣት ግዴታ አለበት። Page | 8

አንድ፤ ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝና ሌሎች ወንዞችን በጥናት በተደገፈ፤ አካባቢውን የሚንከባከብ፤ ሕብረተሰቡን የሚያገለግል፤ የምግብ
ዋስትናን የሚያመቻች፤ የስራ እድልን የሚፈጥር፤ የአካቢውን ነዋሪዎች ጥቅም የሚያጎለምስ፤ በልማት ስም ነዋሪዎችን ከመሬታቸው
የማያስወግድ፤ ከተወገዱ ቢያንስ ተመጣጣኝ ካሳ የሚከፍል፤ የኢንዱስትሪ ልማትን መሰረት የሚጥል፤ ዛሬ በጨለማ የሚኖረውን
(የመብራት አገልግሎት የሌለውን ስድሳ ሰባት ሚሊዮን ሕዝብ) የመብራት አገልግሎት ፍላጎት የሚያቃልል ወዘተ እንዲሆን ድምፅን
ማሰማት፤ ነጻና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ እንዲካሄድ መታገል፤ በተቻለ መጠን ወደ ግብፅና ሱዳን የሚፈሰው ውሃ እንዳይቀንስ መንግሥት
ጥረት እንዲያደርግ ምክር መለገስ ተገቢ ነው፤
ሁለት፤ በእኔ ግምት፤ ህወሓትና ሌልች ተባባሪ የጎሳ ፖለቲካ ድርጂቶች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይወያይበት፤ ጥቅሙንና ጉዳቱን
ሳያመዛዝኑበት የፈጠሩት አፓርታይድን የመሰለ የግዛት አወቃቀር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከስሩ አናግቶታል። ባለፉት ሃያ ሶስት
ዓመታት የታየው ክስተት፤ ይህ ለህወሓት ጎሰኞች ታይቶ የመይታወቅ የፖለቲካ፤ የማህበረሰብና የኢኮኖሚ ስልጣን፤ ገቢና ኃብት
የፖለቲካ ቁንጮውን ለሚያሽከረክሩት የጎሰኛ ቡድኖች ያሸጋገረ አገዛዝ ከመቶው ዘጠና የሚሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በድህነት፤
በጥገኝነት፤ በስደት፤ በተስፋ መቁረጥ፤ በዋጋ ግሽበት ወዘተ አዙሪኝ ውስጥ አስገብቶታል። ቢል ኢስተርሊ ስለጎሰኞች አመራር አደጋ
እንዲህ ብሏል፤ “በጎሰኝነት በተከፋፈሉ አገሮች የፖለቲካ መሪዎች የጎሳ ቅንጂት እየፈጠሩ፤ የጎሳ ልዩነቶችንና ግጭቶችን የሚያባብሱት
ዋና ምክንያት ሆነ ብለው ለራሳቸው የፖለቲካ የበላይነትና የኢኮኖሚ ጥቅም፤ ማለትም የግልና የቤተሰብ የኃብት ማካበቻ (ኪራይ
ሰብሳቢነት የሚባለው) ዘዴ ለማስተናገድ ነው። In many ethnically divided countries today, politicians exploit ethnic
animosities to build a coalition that seeks to redistribute income.”The Whiteman’s Burden. በገቢና በኑሮ ያለውን
አለመመጣጠን ወደጎን ትተን በክልሎች መካከል እንዴት የተዛባ እድገት ተከሰተ ብለን እንጠይቅ። ምርምር ያደረጉ የውጭ ድርጂቶች
እንዲህ ይላሉ “የፌደራል መንግሥቱን በበላይነት የሚቆጣጠረው ህወሓት፤ የፖሊሲ አመራር፤ የኢንቬስትሜንት (የባጀትና የውጭ
እርዳታ፤ የውጭ መዋእለ-ንዋይ ፈሰስና ስርጭት ወዘተ ይወስናል። ሲወስን፤ ሕዝቡን በዜግነቱ ሳይሆን ተባባሪ የሆኑ የጎሳ የበላዮችን
ብቻ ያሳትፋል። የፌደራሉ መንግሥት የበላይ ያልገባበት ውሳኔ አይደረግም። ሰማንያ በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን ገቢና ባጀት
በበላይነት የሚቆጣጠረው ይኼው ቡድን ነው። አካባቢዎችና ክልሎች የሚመኩበት ገንዘብ ከፌደራሉ መንግሥት የሚመጣውን ነው።
ይህን ሲያደርጉ ጎሳ (ethnic affiliation) ከፍተኛና ማእከላዊ ቦታ ይይዛል።“ ተባባሪዎች ይጠቀማሉ፤ ተቃዋሚዎች ይቀጣሉ ማለት
ነው። ተደማጭነት ያለው፤ የውጭ ምንዛሬ የሚለግሰው ያድጋል፤ የሌለው በድህነቱና በኋላ ቀርነቱ ይቀጥላል። International Crisis
Group, Ethiopia: ethnic-federalism and its dicontents, Human Rights Watch, Development without Freedom.
Indian Ocean Newsletter.
የአሁኑ የጎሰኛና የጎጠኛ ስብስብ ሕብረተሰቡን ለአስከፊ የኑሮ ሁኔታ፤ ወጣቱን ትውልድ ለተከታታይ ስደት የዳረገ መሆኑ አያከራክርም።
የጎሳ አድልዎ፤ የጉቦ፤ የሙስናና ከሕግ ውጭ ለግል ጥቅም ከድሃው ሕዝብ እየተዘረፈ፤ በተፈጥሮ ሃብት፤ በከተማ መሬትና ቤት ስራ
እየተሰበሰበ ወዘተ የሸሸውና የሚሸሸው ከሃያ አምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመተው ሃብት ብቻ ይገልጸዋል፡፡ ይህ በግልጽ
የሚካሄድበት አንዱ ዋና ምክንያት ነጻ የሆኑ ብሄርዊ ተቋሞች ስለተናዱና ስለተወገዱ፤ ጠንካራ ሕብረ-ብሄር ተቃዋሚ ፓርቲ ስለሌለ፤
የሲቪክ ድርጂቶች ድምጥማጣቸው ስለጠፋ፤ የነጻ መገናኛ ብዙሃን ስለሌለ ወዘተ ነው። በክልል የተዛባ እድገት፤ በገቢና ሃብት ክምችት
ወዘተ ብናሰላው ለሃገሪቱና ለሕብረተሰቡ ፍትህ ተቆርቋሪ እንደሌለ ያሳያል። ሕብረተሰቡ የነጻነት ጮራ አንግቦ ተቃዋሚውን
ሲመርጥም የህወሓት የበላዮች ልዩ ልዩ ዘዴዎች ፈጥረው ቀልብሰውታል። ሕዝብ ለመንግሥት ያለውን እምነት አውድመውታል።
የታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የአጼ ኃይለ ሥላሴን፤ የደርግንና የህወሓትን መንግሥታት “እኛና እነርሱ” በሚል ትንተና
እያወዳደረ እንዲህ ብሏል “አጼው “ከተራማጅነት ወደ ቀልባሽነት” ሲሻገሩ ሃገሪቱን ወደ ደም ውቅያኖስ ገፍተዋት አለፈዋል።
የወታደሮች ስብስብም በበኩሉ የአደራ ሸክምን በኃላፊነት መፍታት ባለመቻሉ ኤርትራን አሳጥቶን፤ በህብረ-ብሄራዊው ልሂቃን
መቃብር ላይ ለገነኑ ብሄርተኛ ኃይሎች አሳልፎ ሰጥቶን ወድቋል። ከኃይለማሪያም ደሳለኝ ጀርባ ያለው ገዥ ቡድንም በተራው፤ ልክ
እንደ አንድ በሳጠራ የተገነባ ቤት እነ-ሲ አይ ኤ እና ሌሎች ምእራባዊ ተቋሞች ሃገሪቱ የምትፈርስበትን ቀን ቀጠሮ ( እ አ አ 2030 ዓም
ድረስ ማለታቸው ልብ ይላል) እስኪሰጡን ድረስ የመበታተን ጥርጊያ መንግገዱን ከማበጀት አልሰነፈም።” ምንም እንኳን ሶስቱን
መንግሥታት በማነጻጸሩ ላይ ልዩነቶች ቢኖሩኝም፤ ለምሳሌ የውጭ መንግሥታት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያደረጉት ሴራ---ሁሉም
አምባገነኖች መሆናቸው አያከራክርም። ዋናው ቁም ነገር፤ ህወሓት በፍጹም የበላይነት የሚመራው መንግሥት (ተመስገን “ከጀርባ
ያለው ገዥ ቡድን” ያለው) ኢትዮጵያን በቀረጸው የጎሳ (ክልል) ፌደራሊዝም እየበታተናት ይታያል። ሕገ-መንግሥቱን ለማፈራረስ
ጸንሶና ከስራ ላይ አውሎ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ቁሚያለሁ ለማለት የሞራል ብቃት የለውም።
የሰላም ተቋም ኢትዮጵያ “በመውደቅ ላይ ካሉ አገሮች አስራ ሰባተኛ ናት” ሲል፤ የአሜሪክ የስለላ ድርጅቶችና ምሁራን አሜሪካ
የሚደግፈውን መንግሥት ደካማ ጎን አይተው የዛሬ አስራ ስድስት ዓመት “አገሪቱ ትፈራርሳለች” ብለው “ሲጠነቁሉ” እንዴት ከዚህ
ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አበቃቸው ብለን መጠየቅ አግባብ አለው። የመግዛት አቅም ስላለው፤ እንደ ቱሪስት ኢትዮጵያ የሚመላለሰው፤
የመጦሪያ ቤት የገዛው ስደተኛ የማያውቀውን እነሱ ያውቃሉ ማለት ነው። የዲያስፖራው ቱሪስት የሚለው አገሪቱ “አስደናቂ በሆነ
ደረጃ እያደገች ነው:: ርሃብና የስራ እጥረት የለም። የአዲስ አበባ ሕዝብ ቢያንስ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ይኖራል። የጭቃ ቤት የሚባል
ነገር የለም፤ ድህነት እየጠፋ ነው” ወዘተ ነው። ሁሉም በልቶ፤ ጠጥቶ፤ መኖሪያ ቤት ኑሮት፤ መብቱ ተጠብቆለት እንደልቡ በሰላም
በሃገሩ ከኖረ ኢትዮጵያ አትፈራርስም። ወጣቱ ትውልድ አይሰደድም፤ ተሰዶ በሳውዲ አረቢያ፤ በክዌትና ሌሎች አገሮች ክብሩ
አይገፈፍም። መቶ ሽህ ወገኖቻችን ከሳውዲ አረቢያ አይባረሩም። በአዲስ አበባ ብቻ መቶ ሽህ ወጣቶች በየቀኑ በርሃብ አለንጋ
አየሰቃዩም። አገሪቱ የምትፈራርስ ከሆነ የአገዛዝ ግፍ አለ፤ የወደፊቱ አስተማማኝ አይደለም ማለት ነው። Page | 9

አስተማማኝ ሁኔታን የሌለ መሆኑን ለማወቅ ቦሌ ደርሶ፤ በቦሌ ወይንም በዲያስፖራ ሰፈር ቆይቶ፤ ሸራቶን ተዝናንቶ መመለስ በቂ
አይደለም። የአብዛኛውን ሕዝብ ኑሮ ማጤን፤ የሰብአዊ መብቶች መታፈን ያስከተለውን ቀውስ መመርመር፤ ከማያውቁት ሰው ጋር
ለመማርና ለማወቅ መነጋገር፤ የገጠሩን ሕዝብ ኑሮ ወጣ ብሎ መቃኘት ወዘተ አስፈላጊ ነው። ቱሪስት ስደተኞች የሚኖሩበትና
የሚጎበኙት ዓለም “የትግራይ ጀኔራልችና ሌሎች አዲስ ባለ ፀጋዎች ሰፈር” ተብሎ የሚጠራውን ቦሌ ነው የሚሉ ብዙ ለህሊናቸው
ተገዢ የሆኑ የፈረንጅ ታዛቢቅዎች አሉ። ቢል ኢስተርሊ ኒው ዮርክ ቁጭ ብሎ ስለ ኢትዮጵያ አልጻፈም። ጎብኝቶ ያየውን አመዛዝኖ
ጽፏል። ዘጠና በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድሃ መሆኑን አል-ጀዚራ በዚህ ዓመት ባደረገው ዘገባ አቅርቦታል። በአዲስ አበባ
ብቻ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የረባ መጠለያ እንደሌላቸው፤ መቶ ሽህ የሚሆኑ ወጣቶች በርሃብ እንደሚሰቃዩ፤ በያመቱ ብዙ
ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች እንደሚሰደዱ፤ ብዙዎቹ በመንገድ እንደሚሞቱ፤ ስድሳ ሰባት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የመብራት
አገልግሎት እንደሌላቸው፤ ዘመናዊ የመገናኛ አገልግሎት (modern teleicommunications technology) በሌሎች አገሮች (ኬንያ፣
ባንግላደሽ) የድሃ ሕዝቦችን ኑሮ ሲያሻሺል “ከኃይለማሪያም ደሳለኝ ጀርባ አገሪቱን የሚቆጣጠረው ህወሓት” ይህን መብት መከልከሉን
አለማወቅ ለህሊና ይቀፋል። ህወሓት ይህን ቴክኖሎጅ የሚጠቀምበት ድህነትን ለመቀነሰ አይደለም። ተቃዋሚውን በያለበት
ለመቆጣጠር ነው። በኢንተርኔት ስርጭት ያለውን ሃቅ ማየት ይጠቅማል። ሞሮኮ በአፍሪካ ከፍተኛውን ደረጃ ይዛለች። ግብፅ
ሁለተኛውን፤ ኬንያ ሶስተኛውን። በኢንተርኔትና በፌስቡክ ስርጭት፤ ኢትዮጵያ የመጨረሻ ናት። በኢንተርኔት ከመቶ አንድ፤ በፌስቡክ
ከመቶ ዚሮ ነጥብ ዘጠኝ፤ በመንግሥት የመገናኛ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከመቶ ሃያ ናት። ህወሓት ነጻ ፕሬስና የዘመናዊ መገናኛ ስርጭት
ይፈራል ማለት ነው። የመገናኛ ነጻነት የሌለው ሕብረተሰብ ለመብቱ ለመታገል ያስቸግረዋል። ወጣቱ ትውልድ ይህ መብት የሚገባው
መሆኑን ተረድቶ መታገል አለበት። አልያ፤ እውቀቱ ስለታፈነ ከሌላው ዓለም ጋር ለመወዳደር፤ ለመብቱ ለመታገል አይችልም።
የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ የግብፅና የኬንያ ወጣት ትውልድ የደረሰው ቴክኖሎጂ ለሱም መብቱ መሆኑን መጠየቅ ይችላል።
በተመሳሳይ በውጭ የሚገኘው፤ የደህንነት መብቱ የተደፈረ ስደተኛ የህወሓትን መንግሥት መሪዎች ልክ እንግሊዝ አገርና ሌሎች
እንደሆነው ክስ ሊመሰርትባቸው መድፈር አለበት።
በዛሬዋ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያውያን የበለጠ እውቅናና መብት ያላቸው የውጭ አግሮችና ዜጎቻቸው መሆናቸውን ከላይ ባጭሩ
አቅርቤዋለሁ። ህወሓት አገር ወዳዶችን አጥፍቶ በምትካቸው ፈረነጆችን ተክቷል፤ አስተማሪዎችን ከአዲስ አበባ ዩንቤርስቲ አባሮ
በፈረንጆች ተክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን አባሮ ችሎታ በሌላቸው ታማኞችና በፈረንጆች ተክቷል ወዘተ። እንደዚህ
ባለ ብሄራዊ ክፍተት ሰላይ ድርጅቶች፤ መንግሥታት፤ ሊቃውንት (ኤክስፐርቶች) እንደፈለጉ፤ ሰብአዊ አገልግሎትና እርዳታ እነሰጣለን
በሚል ዘይቤ ከፍተኛ ደሞዝና አበል እየተከፈላቸው፤ የህወሓት ጀኔራሎች፤ የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎቻቸው ከባንክ ተበድረው
የሰሯቸውን ሕንጻዎች፤ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በከፍተኛ ኪራይ እየተከራዩ አገሪቱን ጥገኛ አድርገዋታል። ሚናቸው ጥልቀት ያለውና እኛ
የማናውቀውን እውቀት ሰጥቷቸዋል። በእርዳታ ስም ሁለመናችን፤ ገመናችን ለማወቅ አስችሏቸዋል። የተማረ የሰው ኃይል ስለሌን
አይደለም። በሃገራችን እድል ለመሳተፍ ስላልቻልን ነው። ለዚህ ነው፤ ፈረንጆች እኛ አስደናቂ እድገት አለ እያልን፤ አገሪቱ ልትፈራርስ
ትችላለች ብለው ለመተንበይ የሚችሉት። አገሪቱ ልክ እንደ ዩጎስላቢያ ብትከፋፈል የውጭ መንግሥታት የእነሱን ጥቅም የሚያገለግል
ተገንጣይ አገርና ዓመራር እስካገኙ ድረስ ምንም ቅር አይላቸውም። እነሱ ልክ እንደ ገዢው ፓርቲ የሚፈልጉትን ያውቃሉ። እኛ
ኢትዮጵያውያን ስለተከፋፈልንና ስለተናናቅን፤ ሌላው ቀርቶ አንዱ የሚለውን ሌላው ጠቅሶ አይናገርም። ጎሰኛው ህወሓት በፈቃዳችን፤
የእውቀት ሽባና ድሃ አድርጎናል። ኢትዮጵያዊው ቱሪስት የማያውቀውን ፈረንጆች ያውቃሉ። የእኛን የወደፊት እድል አሳልፈን ሰጥተናል
ለማለት እደፍራለሁ። አገሪቱ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ባለው መልክ እያደገች ከሆነ፤ ፈረንጆች ለምን ትፈራርሳለች ይላሉ? ፍትሃዊ፤
ያልተዛባና ዘላቂነት ያለው እድገት ካለ ለምን “የተገንጣይ እንቅስቃሴዎች” ብዛት ቢያንስ ወደ ሰባት አደገ ይላሉ።
የገዢው ቡድን የተከሰተውን አደጋ ካወቀ ለምን ብሄራዊ ተቋሞችንና አሴቶችን አሁንም ያፈርሳል? ለምን ነዋሪዎች ሲባረሩ ይህ አደገኛ
ነው፤ ከሕግ ውጭ ነው፤ መቆም አለበት፤ ካልቆመ ድርጊቱን የፈጸመ ሁሉ ይቀጣል፤ ይታሰራል የማይለው። ይኼን ለማድረግ ፍላጎት
የለውም። ምክንያቱም፤ ስርአቱ የተፈጠረው አንዱን ብሄረሰብ ከሌላው ጋር በማጋጨትና ሰብአዊ መብቶችን ፍጹም በሆነ ደረጃ
በማፈን ነው። ሰላምና እርጋታ ከተፈጠረ እንደልብ ለመዝረፍ አይቻልም። ስለሆነም ሌሎቻችን ለማወቅ የተሳነን ጎሰኛው የገዢው
ቡድን የበላይነት ይዞ ለመቆየት የቻለው ጥቂቶችን በማክበር፤ ጠላቶቹን በማግለል፤ ሃብት እንዳይኖራቸው በማድረግ፤ በማሳደድ፤
በማሰር፤ ከአገር በማስወጣት፤ በማድኽየት፤ በመግደል፤ በድንቁርና እንዲኖሩ በማረግ፤ በመደለል፤ በማስፋራራት፤ በስለላ መረብ ወዘተ
ነው። ቡድኑ የሚሰራውን ያውቃል። የምንሰራውን በሚገባና በጥልቀት የማናውቀው አገር ወዳድና ለፍትህ የቆምነው ነን። ለምሳሌ፤
አገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያሉ ተቃዋሚዎች አሁንም፤ እርስ በርሳቸው የሚያደርጉት መጠላለፍ፤ መወቃቀስ፤ መበታተን ለገዢው
ፓርቲ የማይገኝ ጡንቻ ሰጥቶታል። ገዢው ቡድን ለራሱ ጠባብ ጥቅም ሲል የጎሳ ፌደራሊዝም ፈጠረ። አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ የመገንጠል
መብትን ሕጋዊ እንዲያድረግ እውቅና ሰጠ። የዚህ አንጋፋ ተጠቃሚ ሆኗል። ስለሆነም፤ ቢያንስ ሰባት ተገንጣይ እንቅስቃሴዎች
እንዲፈጠሩ የአገዛዝ ድክመቶች አሳይቷል፤ ለምሳሌ ችግሮችን በውይይትና በማሳተፍ ባለመፍታቱ። ለጭቁን ሕዝቦት የተመሰረተው
የጎሳ ፌደራል ስርአት አልሰራም ማለት ነው። አለመስራቱን ካወቅን ሌሎቻችን አሁንም በህይወት እያለን የሩቅ ተመልካች፤ እርስ
በርሳችን የምንጠላለፍና የምንጣላ የሆንንበት ምክንያት ግልፅ አይደለም። ፍርሃት፤ የግል ጥቅም፤ የተቃዋሚዎች መከፋፈል፤ ያለፈው
የፖለቲካ ታሪክ ሰለባነት ይሆን ? አገራችን ከፊታችን እየተናደች፤ እየተከፋፈለች እያየን ለምን የሩቅ ተመልካች፤ የወሬ አቀባይ ወዘተ
ሆንን?
 Page | 10

ተመስገን ደሳለኝ የአገሪቱን ሁኔታ ከእኔ የበለጠ ያውቃል። በግልፅ የሚታየውን የመፈራረስ ችግር ተወጥቶ ታላቋን ኢትዮጵያን፤ ታላቅ
ሊሆን የሚችለውን ሕብረተሰቧን ለመገንባት ከተፈለገ፤ ለጥቂት ጎሰኞች አገልጋይ የሆነውን የጎሳ ፌደራሊዝም መለወጥ አስፈላጊ
ሆኗል። ስርአቱ “የሃገሪቱን ህልውና ወደ ከፋ መዳረሻ የገፋ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህም እኒህን ሃገረ-መንግስታዊ ክስረቶች ተሻግሮ
ለማሰንበት እና የተሻለ ለማድረግ የተጣሱ የመሰሉንን ምልከቶች በአንድ አቅፎ፤ በዜግነት ላይ ብቻ የሚቆም ማእከላዊ መንግሥት
የሚያበጅልን ሆደ-ሰፊ፤ ከሴራ የነፃ፤ ከጥላቻ የተፋታ፤ ከቂም በቀል የራቀና አቻችሎ የተጋረጠውን አደጋ የሚያሻግር መሪ
ያስፈልገናል….ከተወሰኑ የፖለቲካ ፍላጎቶች በዘለለ፤ ከትላንት የፖለቲካ ታሪክ የታረቀ….ሀገረ-መንግሥቱን በማሻሻል የሚገነባ መሪን
ከመናፈቅ የተሻለ ምርጫ ያለን አይመስለኝም” ብሏል። እኔም በሕዝብ ድምፅ የተመረጠ፤ ለሕዝብ ጥቅም ብቻ የሚገዛ የመንግሥት
ስርአት ያስፈልጋል የምለው ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። ሆኖም፤ ይህ በምኞት አይገኝም። ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ጥሩ ምኞት
ያለን ሁሉ በአንድ ላይ መረባረብ አለብን። ሕዝቡ፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ለራሱ ጥቅምና ክብር ሲል ፍርሃትን አስወግዶ ለመብቱ
ከአንድ ላይ አገር አቀፍ በሆነ ደረጃ ድምፅጹን ማሰማት ይኖርበታል። አንዳንድ ቦታ የሚታየው የሕዝብ ድምፅ አገር አቀፍ ቢሆን
የበለጠ ውጤት ያሳያል የሚል ግምት አለኝ። የአባይ ግድብ ከሕዝብ መብትና ጥቅም ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ ውጭ ዋጋ ቢስ
ይሆናል። ግድቡ ለጥቂቶች ዝናና ጥቅም ከሆነ የሚታደገውም ኃይል አይኖርም የሚል ፍርሃት አለኝ። የተካፋፈለ ሕብረተሰብ የአገሩን
ብሄራዊ ህልውናና ዘላቂ ጥቅም ለማስከበር አቅም አይኖረውም። መብቱ ተከብሮ በኢትዮጵያዊነቱ ከአንድ ላይ ከቆመ ማንም የውጭ
ኃይል ሊያሸንፈው አይችልም።
የጎሰኛነት የበላይነት አገዛዝ ጎጅነቱ ለአሁኑ ትውልድ ብቻ አይደለም። ተከታታይ ትውልድ ይበክላል። ለምሳሌ፤ የህወሓትና ተባባሪ የጎሳ
የበላዮች፤ በተለይ የህወሓት፤ ወጣት ልጆቻቸውን፤ ታማኝ መሰል ደጋፊዎቻቸውን በምርጥ ትምኅርት ቤቶች፤ በመንግሥት ባጀት አገር
ውስጥና ከአገር ውጭ (ቻይና፤ ሕንድ አገር ወዘተ) ያስተምራሉ። እነዚህ ወጣቶች ከአገር በወጣ ኃብት ይደገፋሉ፤ የወደፊት እድላቸው
አገር ቤትና ውጭ ተደላድሏል ማለት ነው። የወደፊት ወሳኝና አስተማማኝ የሆነ እድል ፈጠሩ ማለት ነው። በአንጻሩ፤ በአገር ቤት
የሚኖረው ወጣት ትውልድ እንዲደነዝዝ፤ ተስፋ እንዲቆርጥ፤ ለአገሩ ፍቅር፤ ለተራው ሕዝብ አክብሮት እንዳይኖረው፤ ህወሓት አገሪቱን
ለውጭ ባህል ክፍት አድርጓታል። ወጣቱ ትውልድ የዘመኑ ዓለም-አቀፍነት (Globalization) ስለባ እንዲሆን ተደርጓል። ለአገሩ ባህል፤
ለአገሩ እሴቶች፤ ለአገሩ የጥንት ባህሎች እንዳይቆረቆር ብዙ ጫና ይደረግበታል። “ስሥታምነት፤ ራስ ወዳድነት፤ በአጭር ጎዳና ሰርቆም፤
ዋሽቶም፤ ጉቦ ሰጥቶ ሃብት ሰብሳቢነት፤ ሙስና፤ አድልዎ፤ አጎብዳጅነት፤ ገንዘብ ከሃገር ማሸሽ፤ በሱስ መበከል ወዘተ እንደ ዘመናዊይነት
እንዲቀበለው አድርጎታል። ገዢው ፓርቲ የጎሳ ልዩነትና ጥላቻ ተቀባይነት እንዳለው በትምሕርት ቤት፤ በየስብሰባውና በመገናኛ ብዙሃን
ይለፈልፍለታል። የአስራ ስድስት ዓመት ወጣት ሆኘ የድርሰት ውድድር (The Challenges My Country Faces in Today’s World
አሸንፌ አሜሪካ በመጣሁበት ወቅት በየቦታው የተገናኘኋቸው በትምሕርት ገበታ ላይ የነበሩ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን
ለፈረንጆች የሚያስተዋውቁት “እኔ ከኢትዮጵያ ነኝ፤ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” በሚል ግልፅ በሆነ በሚያኮራ መታወቂያ ነበር። ምንም እንኳን
አገራችን ድሃና ኋላ ቀር ብትሆን፤ እትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚያኮሩ መታወቂያዎች እንደነበሩ አስታውሳለሁ። በወቅቱ ሁሉም
ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰው በጋራ አገራቸውን ሌሎች ዘመናዊ የሆኑ አገሮች ወደደረሱበት ለማሸጋገር ስሜትና ፍላጎት
ነበር። “ለእኔ ሃብታምነት፤ ለእኔ ኑሮ፤ ለእኔ ጎሳ የበላይነት” የሚል አላስታውስም። የአሁኑ ትውልድ ከቀድሞው የሚለይበት አንዱ
ለውጥ “እኔ ከኢትዮጵያ ነኝ፤ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ እኔ አገሬንና መላውን ሕብረተሰቧን ለማገልገል እፈልጋለሁ። የሁሉም
ኢትዮጵያውያን ኑሮ ከተሻሻለ የእኔም ኑሮ ይሻሻላል” የሚሉ እሴቶች በመጥፋት ላይ ናቸው። ስግብግብነት፤ ጮሌነት፤ “እኔ ከሞትኩ
ሰርዶ አይበቀልነት…” እንደ አሸን ፈልተዋል። ባጭሩ፤ የኢትዮጵያዊያን መታወቂያና መለያ የነበሩ የባህልና የማህበረሰብ ምሰሶዎች (the
cultural and social fabric and glues) ሆነ ተብሎ በተቀረፀ የጎሰኞች የበላይነት ተንደዋል።
መለስ ያለው ትዝ ይለኛል፤ “ሌብነት የጉብዝና ምልክት ነው። ሌባው እስካልተያዘ ድረስ።” የህወሓትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት
ከትውልድ ወደ ትውልድ ያስተላልፋሉ ተብሎ በትምኃርትና በስልጠና ላይ የሚገኙ “የወደፊት መሪዎች” አእምሮን ከሚያደነዝዙ
የውጭና አገር ወለድ ባህሎች ተከልለዋል። ከፍተኛ የአእምሮና የአካል ጉልመሳ ይደረግላቸዋል። ታሪካቸው አኩሪ እንደሆነ
ይነገራቸዋል። የአእምሮና የአካል እንክብካቤ የሚደረግለት ትውልድ የወደፊቱን የፖለቲካ፤ የማህበራዊና የኢኮኖሚ የበላይነት ይይዛል
(ይወርሳል) የሚለው የህወሓት የበላዮች ስሌት በስራ ላይ ይታያል። ህወሓት ይኼን የሚያደርገው በጥበብ ነው። ሌላውን ወጣት
ትውልድ በመጥፎ ባህል እንዲበከል በማድረግ፤ የስራ እድል በመከልከል--የኦሮሞው፤ የአማራው፤ የደቡቡ፤ የጋምቤላው፤ የኦጋዴኑ፤
የአፋሩ ወዘተ ወጣት በገፍ ከአገር እንዲወጣ ሁኔታዎችን በማመቻቸት። ይህ ሲሆን ተወዳዳሪና ተቀናቃይ ትውልድ አይኖርም።
ቢኖርም አቅም አይኖረውም የሚል ግምት በማስተጋባት ይመስላል። በጎጂ ባህል (መጠጥ፤ የእንግሊዞችን የኳስ ጨዋታ አዘውትሮ እያዩ
“ይህ የኔ ቡድን፤ ያ የአንተ ቡድን” እያሉ መወዳደር፤ በሴቶች ላይ ብልግና መፈፀም፤ ጫት መቃም ማዘውተር፤ ሌላም ሌላም) እንደተራ
ነገርና እንደ ስልጣኔ ተቆጥሯል። ወጣቱ ትውልድ በሚያፍነው ስርአት ላይ በማተኮር ፋንታ፤ አእምሮውን በሚስብ አማራጭ ላይ
ትኩረት እንዲያደርግ ሆነ ተብሎ የሚሰራ የአገዛዝ ስልት አካል ነው። “በአገዛዝ አፈና ላይ እስካላተኮርክ ድረስ ማንኛውንም ነገር
ለማድረግ ትችላለህ” የተባለ ትውልድ ይመስላል። በፍጥነት ዘመናዊ በሆኑ በደቡብ ኮሪያ፤ በታይዋን፤ በሲንጋፖር፤ በጥንታዊዋ ጃፓን፤
በቬትናም ወዘተ የማይታሰበው በኢትዮጵያ “ዘመናዊነት” ሆኑል። እነዚህ አገሮች ወጣቱ ትውልድ ዘመናዊነትን ከባህሉ፤ ከታሪኩ፤
ከልምዱ፤ ከብሄራዊ ቅርሱ ወዘተ ጋር አብሮ እንዲንከባከብ አድርግዋል።
ጎሰኞች ሆነ ብለው ኢትዮጵያዊነትን ለመገርሰስ ወጣቱ ትውልድ የአገሩን ባህል እንዲጠላ አስገድደውታል። ገንቢ የሆነ የሁሉንም
ብሄር፤ ብሄረሰብ ባህል፤ ወግና ማእረግ፤ ልምድና ታሪክ የሚያንፀባርቅ አማራጭ አውጥቶ ትውልድን ለማነጽ ይቻል ነበር። አሁንም
ፈቃደኛነትካለ፤ ይሕ ገንቢ አማራጭ ስራ ላይ ሊውል ይችላል። ለፖለቲካ ስልጣን መቆያ፤ ለግልና ለቤተሰብ የኢኮኖሚ ጥቅም Page | 11

ማጠናከሪያ የኢትዮጵያውያንን ባህሎች ማጥፋት ዙሮ ዙሮ በታሪክ አስጠያቂ ነው። አገሪቱን ለጥቃት እየዳረጋት ነው። እኛ ራሳችን
የሚያኮራውን ታሪክ፤ ባህልና ልምድ ወደ ጎን ትተን በሁሉም ነገር “ፈረንጅና የፈረንጅ ባህል አምላኩ” ስንሆን ማንነታችን እንደሚጠፋ
አልጠራጠርም። በሚሊዮኖች የምንቆጠረው የኢኮኖሚ ስደተኞች የመንፈስ ስደተኞች መሆን የለብንም። አርመኖች፤ አይሁዶች፤
አይሪሾች፤ ዩክራኒያኖች ወዘተ ለሰብአዊ መብቶችና ለሌሎች ማህበረሰብአዊ ጉዳዮች የሚያደርጉትን የሃገር አስተዋጽዖ እኛም ለማድረግ
እንችላለን። የትም ቢኖር የአሁንና ተከታታይ ትውልድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተቆርቋሪ ሆኖ በራሱ አገር ባህል መኩራትና በስራ ላይ
ማዋል የማህበራዊ ጥንክርና ይሰጠዋል። በማንኛውም ዓለም ይከበራል።
የባህል ማጥፋት ሂደቱ በወጣቱ ትውልድ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በዘመናዊነት ሳቢያ ኢትዮጵያ ልትንከባከባቸው የሚገባት የልዩ ልዩ
ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ባህል እየጠፉ ነው። የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ የአፋር፤ የጋምቤላ፤ የኦሞ ሸለቆ ወጣት እንደ ህወሓት የበላዮች
ልጆችና የቅርብ ዘመዶች ተመሳሳይ የትምሕርት እድል የለውም። ትምኅርት ከሌለው ባህሉን፤ ወግ ማእረጉን፤ ልምዱን፤ ታሪኩን የኑሮ
ዘዴውን፤ የተፈጥሮ ሃብቱን ለመንከባከብ አይችልም። በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ካለበት ድህነት ነጻ ወጥቶ፤ በኢትዮጵያዊነቱ
ቢያንስ በሃገር ደረጃ ለመወዳደር አይችልም። የውጭ ታዛቢዎች የመሬት ነጠቃን ሰፊ ጉዳት በመገንዘብ በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረው
ወጣት ትውልድ እንኳን በሃገር ደረጃ በራሱም ክልል የመወሰን፤ ሃብት የመያዝ ወዘተ እድል አይኖረውም ይላሉ። ገዢው ፓርቲ የዚህን
አግላይነት አደጋ አላየውም። ማንም ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነው ሰብአዊ መብቱ ተከብሮ፤ የተፈጥሮ ሃብቱ ባለቤት መሆኑ
በሕግ ታውቆለት ኑሮውን ለማሻሻል ሲችል፤ ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ብሩህ የሆነ የወደፊት እድል ሲኖራቸው ነው። መሬቱን ነጥቆ
“ኢትዮጵያዊ ነህ” ማለት የፖለቲካ ጨዋታ ነው።
የፍልስፍና ኋላ ቀርነት
የጎሰኛነት ፍልስፍና አገር ከመግንባት (Nation Building) እና ከዘመናዊነት ጋር አብረው አይሄዱም። የታወቀው ኢትዮጵያዊ ሊቅ
ፕሮፌሰር መስፍን ወልድ ማሪያም “የጎሰኛነት አጭር ትርጉም ዓለምን በራሱ ጠባብ ኢምንትነት የሚለካ ሰው ነው። መለኪያው (ራሱ)
ለኪው ነው” ብሏል። ይህን ትርጉም እጋራለሁ። በእድገት፤ በገቢ፤ በከፍተኛ ትምኃርት፤ በተፈጥሮ ሃብት ቁጥጥርና ሌሎች መለኪያዎች
የፖለቲካ፤ የወታደር፤ የስለላ፤ የዳኝነት ወዘተ ውሳኔዎች ስልጣን ያልያዘው ክፍል አያገባውም ማለት ነው። ራሱን ለማሻሻል የሚችለው
በጎሰኛው ቡድን ፈቃድ እንጅ በኢትዮጵያዊነት በመብቱ አይደለም። መብቱ የተካደ ሕዝብ ሁል ጊዜ “እቫካችሁ መብቴን ስጡኝ፤
አክብሩልኝ” ሲል አይኖርም። በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ነግሶ ሳለ፤ ዘረኛው መንግሥት (ዘረኛነትና ጎሰኛነት አባትና ልጅ ናቸው)፤
ሕዝቦችን ከፋፍሎ፤ ነጮች ከፍተኛውን የገንዘብ፤ የምርትና የተፈጥሮ ሃብት እንዲይዙ፤ ድብልቆች (Colord) መካከለኛውን፤ ጥቁሮች
ርፍራፊውን እንዲይዙ የሚል ዓመራር ነበረው። የትምሕርትና የስልጠና እድል የሚወሰነው በተመሳሳይ ነበር። የጎሰኛው ገዢ ፓርቲም
ፍልስፍና ተመሳሳይ ነው። የበላይ ጎሰኞች የትም ቦታ ለመኖር፤ ሃብት ለመያዝ ወዘተ ይችላሉ። የፖለቲካ ስልጣን ስላላቸው ብቻ።
ለምሳሌ፤ የአማራውን ብሄረሰብ በጅምላ አውግዞ ጠላት ነው የሚል ፍልስፍና አካሄዷል። አኟኩን “ለራስህ ስልጣኔ ከመሬትህ መወገድ
አለብህ” አለብህ ይላል። እምቢ ሲል ኢ-ሰብአዊ የሆነ በደል ይደርስበታል። ይህ ሁኔታ አሁንም ይካሄዳል። ሆነ ተብሎ፤ በአማራው ላይ
የሚደረገው ግፍ በምንም አይነት የሚቆም አይመስልም። በዋና “ጠላትነት” ስለተፈረደበት። የሸዋ አማራ ገዢዎች ወዘተ ጭቆና፤
ትግራይን የማደሕየት ታሪክ የሚለው የኩነና ሽፋን ነው። ከዚያ ወዲህ በድርጊት የታየው የፍልስፍናው ዋጋ ከፋይ አማራው በጅምላ
ነው። በተለይ የገጠሩ ድሃ--በጉራ ፈርዳ፤ በተለያዩ የኦሮሞ ክልል ክፍሎች፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ወዘተ። እነዚህ ሰርቶ አደሮች እንዴት
የትግራይ ወይንም የሌላ ብሄር “ጠላት” እንደሆኑ ማንም ማስረጃ ለማቅረብ አይችልም። የሩዋንዳን እልቂት ሃያኛ ዓመት ስናስታውስ
ጎሰኞች “የሚያደርጉት አፈና ተመሳሳይ እልቂት የሚጋብዝ ይሆናል” የሚሉ ታዛቢዎች አሉ። ተስፋ የማደርግው የኢትዮጵያውያንን
ጨዋነነት ከተመሳሳይ አደጋ ይታደጋታል በሚል ስሌት ተማምኘ ነው። የጎሰኛነት ፍልስፍና ዳር ድንበር የለውም። ማንንም አይምርም።
ለጭቁን ብሄረሰቦች ቆሜያለሁ የሚለው ህወሓት/ኢህአዴግ በኦሞ ሸለቆ፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዶን፤ በአፋርና በሌሎች ክልሎች
የሚያካሂደው የሰብአዊ መብቶች አፈናና እርግጫ ለሃገሪቱ አለመረጋጋት መጋቢ ሆኗል። ባጭሩ አገዛዙ አገርንና ሕብረተሰብን
ያደማል፤ ያደክማል፤ ያፈራርሳል።
ጎሰኛው ቡድን ታሪክን ዋሺቶ ይከልሳል። ሕዝብን ለይቶ ለእልቂት ይዳርጋል። ለዚህ ዋና ዋቢ ለስምንት መቶ ሺሕ ሕዝብ እልቂት
የሆነው በሩዋንዳ የተካሄደው የጎሳ ጥላቻ ያስከተለው ወንጀል ነው። ከማኛውም አቅጣጫ ይምጣ፤ ጎሰኛነት ጥላቻን ፈጣሪና አጠናካሪ፤
ሌላውን አግላይ ነው። በዛሬዋ ኢትዮጵያ የህወሓትና የኦነግ ጎሰኞች በጥላቻ ተክነዋል። ያልነበረ ታሪክ ጨምረው እየፈጠሩ ኢትዮጵያን
አድክመዋል። ሕብረተሰቧን ከፋፍለዋል። እርጋታን በክለዋል። የታወቀው ኢትዮጵያዊ ሊቅ፤ ዶር ኃይለ ማሪያም ላሬቦ፤ በጎሰኞች
የተፈጠረውን ጥላቻና አደጋ በማየት “ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ” በሚል አርእስት “አጤ ምኒልክ የሚጠሉበት
ኢትዮጵያን በጦር ኃይል መልሰው አንድ ማድረጋቸው ከሆነ ማንም መንግሥት አዲስም ሆነ ፈራርሶ የነበረው አንድም ሳይቀር በሙሉ
የተፈጠረው በጦር ኃይል ነው። በሕዝብ ስምምነትና ፍቅር የተቋቋመ መንግሥት በታሪክ የለም። ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም።
አለ የሚል ካለ በቅዠት ዓለም የሚኖር ብቻ ነው….ምኒልክ ከተራ ሰው የሚለዩት ባስተዋይነታቸው አርቆ በማየታቸው ነው።”
ማለትም፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅነት በማሰብ። “መንግሥታት የተቋቋሙ ደግሞ እንደሳቸው ባሉት አሻግሮና አርቆ
ማየት ችሎታ ባላቸው ሰዎች ነው።” ቻይና፤ ተርኪ፤ ኢታሊ፤ ጀርመኒ፤ አሜሪካ፤ ናይጀሪያ ወዘተ። “እስራኤል በቅዱስ መጽሃፍ ታሪክ
ተመስርታ ነው ከፈረሰች በሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ ነው የተፈጠረችው። ጀርመን ሶስት ሺህ ከሚያክሉና እርስ በርስ ከሚፋጁ የጎሳ
ባላባቶች በፈረንጅ አቆጣጠር በ 1871 ዓም አንድ አገር የሆነችው…ምኒልክ ግን አንድነቷ” የተናደውን ኢትዮጵያን ከሁሉም
ብሄር/ብሄረሰቦች የተወጣጣ ጦር አዝምተው መልሰው “አዋህደዋል።” በተመሳሳይ፤ ጣሊያን ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለማድረግ ሲሞክር Page | 12

ሕዝቧን አደራጅተው፤ ብሄር/ብሄረሰብ፤ ድሃ/ሃብታም/ወጣት/ሺማግሌ/ሴት/ወንድ፤ ክርስቲያን/እስላም ወዘተ ሳይለዩ መርተው የአድዋን
ድል ተጎናጽፈዋል። ለኢትዮጵያና ለመላው የጥቁር ሕዝብ መለያ ጥሪት ትተውልን አልፈዋል። ይህ ሲሆን ችግሮች አልነበሩም፤ የተጎዳ
የለም ለማለት አይቻልም። የታሪክ ሂደት ነው።
ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን የታሪክ ሂደት፤ ያለፈውንና በህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የሚካሄደውን ጥፋት ለማመዛን የሚችሉት
በጥላቻና በጎሰኞች የፖለቲካ ውሳኔ አይደለም። ኢትዮጵያዊያን የሚወያዩበት መድረክ አስፈላጊ ነው። የሰላምና የእርቅ ኮሚሺን
አቋቁመው ሃቁን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሊመረምሩና ጥፋቶች ወደፊት እንዳይደገሙ ለማድረግ ይችላሉ። ጎሰኞች ይህን አማራጭ
አይፈልጉም። ጥቅማቸውን ይጻረራል። ጎሰኛነት በጥላቻ ግርዶሽ ስለተበከለ ለሕዝቡ ሰላምና እርቅ፤ ለአገሪቱ ዘላቂ ጥቅምና ሕልውና
አደጋ እየፈጠረ ነው። የጥላቻው ፖለቲካ ለጎሰኞች እንደሚያገለግል አስቀድመው አውቀውት ነበር።
መለስ ዜናዊ “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ወይንም ለደቡብ ሕዝብ ምኑ ነው” ሲል የፈጠረውና የለገሰው አጥፊ ፍልስፍና አለ።
የአክሱም፤ የጎንደር፤ የሃረር፤ የላሊበላ ወይንም ሌላ ሃውልትና ቅርስ ከጎሳው ውጭ ለሌላው ምኑም አይደለም ሲባል፤ ኢትዮጵያውያን
የሚጋሩት አንድም ነገር የለም ማለት ነው። የሚጋሩት ከሌለ አብረው ለመኖር፤ አብረው ድህነትን ለማጥፋት፤ አብረው ለማደግ፤
አብረው የተፈጥሮ ሃብትን በኢትዮጵያዊነታቸው ባለቤት ለማድረግ፤ አብረው የአባይን “የተሃድሶ ግድብ” በጋራ ለመጠቀም
የሚያስተሳስራቸው ምሰሶ (ምሰሶዎች) የለም ማለት ነው።
ለዚህ ነው፤ ጎሰኞች ይሉኝታ በሌለው መንገድ ራሳቸውን አክብረው ሌላውን ያገለሉት። የእድገትን ጥቅም የሚያዩት በ”ጎሰኛነት
መነጽር” ነው። ህወሓት “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው….ምኑ ነው” የሚል ፍልስፍና አሁንም ከተከተለ፤ “የተሃድሶ ግድብ” ለአፋሩ፤
ለጋምቤላው፤ ለኦሞ ሸለቆው፤ ለኦጋዴኑ ሕዝብ ወዘተ ምኑ ነው? የዓባይና የሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች ግንባታዎች ግልፅነትና ሃላፊነት
በሚያሳይ መንገድ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ኑሮ መሻሻል መዋል አለባቸው። ይህን ለማድረግና የግድቡን ዘላቂ ደህነነት ለማረጋገጥ
የጎሰኛነት ፍልስፍናና አገዛዝ መወገድ አለበት።
ይቀጥላል

















 Page | 13









No comments:

Post a Comment