Saturday, March 8, 2014

የድንቁርና ፈላስፎች።

የድንቁርና ፈላስፎች።
የመፅሃፍ ውበቱ፣
ቢሆን ኖሮ ውፍረቱ፣
ይህን የደንቆሮዎች መድበል፣
ይህን የድንቁርና ማህደር፣
እንል ነበር ውብ ነው፣ ሳንፈራ ሳናፍር፣
እንል ነበር።

ደግነቱ፣
የመፅሃፍ ውበቱ፣
ሁሌም ነው እንጂ ይዘቱ።

ኣምሃ ኣስፋው
የካቲት 18 ቀን 2006 ኣም

ባለፈው ሳምንት ´የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶችª የተሰኘ 660 ገፆች ያሉት መፅሃፍ ኣነበብኩ፤ ኣንብቤም ኣዘንኩ።
ìምን ታደርጊዋለሽ?î ብየ ላልፈው ኣስቤ ነበር። ነገር ግን፣ ሙሉ መፅሃፉን የመገምገም ፍላጎቱ ባይኖረኝም፣ መድረኩን
ለነዚህ ኣእምሮ ቢስ ጎሰኞች ብቻ መተው ተገቢ መስሎ ኣልታይህ ኣለኝ።
ፅሁፌ የሚናገረው ስለኣራት ሰዎች ብቻ ነው፤ በጅምላ የመጥላትም ሆነ የመውደድ ባህል ካለው ጎሳ ኣልተወለድኩምና።
ንብረት እንክዋን ካባት ወደልጅ መተላለፍ ካቆመ 40 ኣመት ሊሞላው ነው። እነዚህ እብዶች ግን የተፀናወታቸውን የጥላቻ
በሽታ ለልጆቻቸው ለማስተላለፍ፣ የማይፅፉት ውሸት የለም። እብደት መሆን ኣለበት እንጂ፣ ድንቁርና ብቻውን ይህን ያህል
እብለት ከየት ያመጣል?
እሩቅ ከመሄዴ በፊት የነዚህን ኣራት ìሰዎችî ስም ልግለፅ። የመፅሃፉ ደራሲ ኣቶ ታቦር ዋሚ፣ ምስክሮቻቸው ታደሰ በሪሶ
(ረ/ፕሮፌሰር)፣ ብርሃኑ ለሜሶ (ረ/ፕሮፌሰር) እና ተሰማ ታኣ(ፕሮፌሰር) ናቸው። ìየኣይጥ ምስክርዋ ድንቢጥî ልል
ኣሰብኩና፣ ኣይጥና ድንቢጥን ከእንዚህ እርኩሶች ጋር ማወዳደሩ ነውር ነው ብዬ ተውኩት።
እንግዴህ፣ ኣቶ ታቦር ለኣማርኛ ቋንቋ ያላቸውን ጥላቻ ኣስመርኩዤ ትችቴን ልጀምር።
ኣቶ ታቦር ኦሮምኛን እያሞገሱ፣ ቁቤ ብለው የሚጠሩትን የፊደል ስርኣት እያገነኑ፣ በኣንፃሩ ኣማርኛን እያንክዋሰሱ፣
የኣማርኛን ፊደል (እሳቸው ሳባ ነው የሚሉት) እያቃለሉ፣ እያንግዋጠጡ ብዙ ፅፈዋል። ኦሮምኛ ለመናገር ውብ የሆነ ቋንቋ
እንደሆነ፣ የኣማርኛ ፊደል እንኳንስ ኦሮምኛን ራሱን ኣማርኛን የመፃፍ ችሎታ እንደሌለው፣ የሚጠብቁና የሚላሉ ፊደሎችን
ምሳሌ እየሰጡ ያስረዱናል።
ኦሮምኛ ጣፋጭ ቋንቋ እንደሆነ ከኣቶ ታቦር ሳይሆን ኦሮምኛ ከሚናገሩ ዘመዶቼ (ወዴት ከፍ ከፍ እንዳይሉኝ ዘመዶቼ
ኣማሮች ናቸው) ከሰማሁ 50 ኣመታት ኣልፈዋል። ስለዚህ በኦሮምኛ ውበት ላይ ጥርጣሬ የለኝም፤ ቢኖረኝ ኦሮሞኛን
ለመፃፍ ከኢትዮጵያው ፊደል ይልቅ እንግሊዝኛው መመቸቱ ላይ ነው። ለማኛውም ኣንድ ቋንቋ የሚያድገው ሲፃፍበት
ነው። ታዲያ ኣቶ ታቦር 660 ገፅ ያለው መፅሃፍ በሚወዱትና በሚያደንቁት ኦሮምኛ ሳይሆን፣ በሚንቁትና ኋላ-ቀር ነው
በሚሉት ኣማርኛና በኣማርኛ ፊደል መፃፋቸው ለምን ይሆን?
የተለያዩ ምክንያቶች መስጠት ይቻላል።
1. ኣማርኛ ተናጋሪዎች መፅሃፉን ኣንብበው ኦሮሞዎችን እንዲጠሉ።
2. ደራሲው በኦሮምኛ በተለይም በቁቤ የመፃፍ ችሎታ ስለሌላቸው። 3. ኦሮምኛን ስለሚንቁ ወይም ለኣማርኛ ውስጣዊ የሆነ ስነልቡናዊ ኣክብሮት ስላላቸው።
4. ገንዘብ ማግኛ ዘዴ ስለሆነና በኣማርኛ ያልተፃፈ መፅሃፍ ስለማይሸጥ።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ፣ ከላይ እንደገለፅኩት ኣማሮች በጅምላ ሰው የመውደድም ሆነ የመጥላት ባህል
የላቸውም። ኣማሮች እዚህ የስነ ልቡና ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ መቶ ኣመታት ፈጅቶባቸዋል። ለዚህም ነው ኣማሮችን
በቀላሉ ማስተባበርም ሆነ ማሳደም የሚያስቸግረው። ለዚህም ነው ኣማሮች ከማንም ጎሳ ጋር መጋባትና ኣብሮ መኖር
የሚችሉት። ስለዚህ ፅሁፍዎን እንብበው ኦሮሞዎችን ባጠቃላይ የሚጠሉ ኣማሮች ማግኘት ከባድ ይመስለኛል።
ስነ ፍጥረታዊ ጥናት (ስይንሳዊ - ሰየነሰ ከሚለው ግስ ከወጣ) እደግፋለሁ፤ ስለሚሉ ከላይ የጠቀስኩትን ሃሳብ ለመደገፍ
ትንሽ ሙከራ እናካሂድ። ከተለያዩ 10 ጎሳዎች 10 ሰዎች ይምረጡና የሚከተለውን መመሪያ እና ምርጫ ይስጥዋቸው።
ለኣንድ ወር ያህል፣ መሳሪያ ሳትይዙ፣ ከተማ ሳትረግጡ፣ በእግራችሁ ከኢትዮጵያ ባንዱ ክፍለ ሃገር (ለእርሶ ክልል)
ትዘዋወራላችሁ። የራሳችሁ ጎሳ የሚኖርበትን ክፍለ ሃገር መምረጥም ሆነ የራሳችሁ ጎሳ በሚኖርበት ቀበሌ ውስጥ መጓዝ
ኣትችሉም። ካሉ በኋላ ያችን ኣንድ ወር የሚያሳልፉበትን ክፍለ ሃገር እንዲወስኑ ምርጫ ይስጥዋቸው። የትኛውን ክፍለ ሃገር
የሚመርጡ ይመስልወታል?
ሁለተኛው ጥርጣሬየን በተመለከተ ብዙ ኦሮሞዎች ሲያማርሩ የሰማሁት ነገር ነው። ቋንቋውን በደንብ እንደሚናግሩ
ባምንም፣ በቁቤ መፃፍ መቻልዎን ግን እጠራጠራለሁ። የእርስዎ ጥፋት ኣይደለም፤ ኣራትና ኣምስት ኣናባቢዎች
የሚደረደሩበት የፅህፈት ስርኣት በጣም ኣስቸጋሪ ነው። የኣማርኛን ፊደሎች መጠቀም እንደማይመችዎ ለማስረዳት
ደጋግመው የሚያቀርቡት ማስረጃ፣ እማርኛ የማጥብቂያ ምልክቶች የሉትም የሚለውን ስሞታ ነው። መልሱን ከፕሮፌሰር
ባዬ ይማም ፅሁፎች ውስጥ እንጅ ከፖል ሄንዜ መፅሃፍ ውስጥ ኣያገኙትም። ìሃሬî፣ ìሬî ሲጠብቅ ìኣህያî ìሬî ሲላላ ደግሞ
ìኣጠበî ማለት ነው ብለውናል። በመጀመሪያ የሚፅፉት ለፈረንጆች ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣ ìሸቀጡን በìሃሬî ጭኜ ወደ
ገበያ ወጣሁî፣ ብየ ብፅፍ፣ (በኦሮምኛ) ìሬîን ሳያጠብቅ የሚያነብ ኦሮምኛ ተናግሪ ይኖራል? ባዬ ይማም ግን ማንኛውም
የሚጠብቅ ፊደል ሳድሱን ያስቀድማል ይላሉ።(ባዬና ቲም 1989) ìሬîን ኣጥብቀው ìሃሬî ሲሉ የሚፈጠሩትን ድምፆች ልብ
ብለው ያዳምጥዋቸው። ሃ-ር-ሬ ወይም ታህታይ ቅርፁን ከፃፉት ህ-ኣ-ርር-ኤ ነው። ይታይዎታል የሚጠብቀው ፊደል
ተናባቢ ሁለቴ ሲደግም? ከኔ ይውጣ ብየ ነው እንጂ፣ ድንጋይ ላይ ውሃ እንደማፈስ ይገባኛል።
የሶስተኛውን ነጥብ መልስ የሚያውቁት ራስዎ ነዎትና ልተውልዎት።
ዋናው ሚስጥር ያለው ግን ኣራተኛው ነጥብ ውስጥ ሳይሆን ኣይቀርም። ባለፉት 10 ኣመታት ውስጥ ኣራቴ ኢትዮጵያን
ጎብኝቻለሁ። ብዙ መፅሃፎች ስለምገዛ የመፅሃፍ መደብሮችን ኣዘወትራለሁ። በመጀመሪያው ጉዞየ ብዙ የኦሮምኛና የትግርኛ
መፅሃፎች ተደርድረው ኣይቼ ነበር። የኦሮምኛ መፅሃፎቹ ለትምህርት ቤት መማሪያ የተመደቡ የሂሳብና የስነ ፍጥረት
መፅሃፎች ነበሩ። ይህም ማለት፣ በግለ ሰብ ፍላጎት ሳይሆን በመንግስት ትእዛዝ የተፃፉና የታተሙ ነበሩ፣ ማለት ነው።
በሚቀጥለው ጉዞየ ከጥቂት የትግርኛ መፅሃፎች በስተቀር የኦሮምኛዎቹ ጠፉ። ኣገር ቅጠሉ ሁሉ የኣማርኛ መፅሃፍ ሆነ።
ምናልባት ኣማርኛ ባለፉት 20 ኣመታት ያሳያው እድገት በሌላው ዘመን ካደረገው እድገት የበለጠ ሳይሆን ኣይቀርም።
ኣማሮች በጉልበታቸው ኣሳደጉት ኣይባል፣ እንኳን ሌላውን ለማስገደድ ህይወታቸውን ለማዳን የሚበቃ ሃይል የላቸውም።
ባለፉት 200 ኣመታት የነበሩት ነገስታት፣ ትግሬዎቹና ኦሮሞዎቹን ጨምሮ ኣማርኛን የቤተ መንግስት ቋንቋ ማድረጋቸው
ኣማርኛን ኣልጠቀመውም ብየ ኣልከራከርም። ግን ኣማርኛ ባለንበት ዘመን የሚያሳየው ከፍተኛ እድገት ውንጀላዎ ስሜታዊ
ፈጠራ እንጂ ታሪካዊ እውነት እንዳልሆነ ያመለክታል።
እንግዴህ፣ ኣቶ ታቦር ለምንድነው በኣማርኛ የሚፅፉት? ለሚለው ጥያቄ ፣ በኣብላጫው ለገንዘብ ሲሉ ነው፤ የሚል መልስ
ካገኘንለት ወደሌላ ጉዳይ እንሸጋገር።
ኣማርኛ በጨቋኝ ስርኣት ስር እንክዋን የሚያድግበት ምክንያት ምንድን ነው?
1. ኣማርኛ ከሌሎች የኢትዮጵያና የውጭ ቋንቋወች ቃላትም ሆነ ሰዋስዋዊ ስርኣቶችን ወስዶ የራሱ የማድረግ ጠባይ
ኣለው። ለምሳሌ፣ ìùኛîን በመጨመር ሌሎች ቃላትን መፍጠር የተወረሰው ከኦሮምኛ ነው። ፈረስ ብለን ፈረሰኛ፤ ከፍታ ብለን ከፍተኛ ማለት የቻልነው ከኦሮምኛ ተምረን ነው። (የባዬ ይማምን የኣማርኛ ሰዋስው 2000
ይመልከቱ) ባዬ ይማም በዚህ ኣላቆሙም። እንደ ìሽ፣ ች፣ ጅ . . . ì ያሉት የላንቃ ድምፆችን እና በባለቤት ጀምሮ
በግስ የመጨረስ ባህርይውን የተቀናጀው የኩሽ ቋንቋዎች ባሳደሩበት ተፅእኖ እንደሆነ ይነግሩናል። ለዚህም ነው
የእጅ ስራቸው ስላለበት፣ ኣማርኛ ለኦሮሞዎች የራሳቸው እንጅ የባእድ ቋንቋ ኣይደለም የምንለው። ኣቶ ታቦር
ከሌሎች ወስዶ የሚያድግ ቋንቋ የማይረባ ይመስላቸዋል። ኣማርኛ ከኦሮምኛ የወሰዳቸውን ቃላት ይዘረዝራሉ።
ከሌሎች ወስዶ የራሱ ማድረግ ግን የትልቅ ቋንቋ ምልክት መሆኑ ኣልገባቸውም፤ የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር
ባህርይ ኣለመሆኑም ኣልታያቸውም። በነገራችን ላይ፣ ካንድ ቦታ፣ ኣማርኛ ከኦሮምኛ የተዋሳቸው ቃሎች ብለው
ይዘረዝራሉ። መዋስን ምን ኣመጣው? መል-ልሱ ሊሉን ፈለጉ እንዴ?
2. ሂሳባዊ ስርኣት የሚከተል ቋንቋ የለም። ኣማርኛ ግን ለሂሳባዊነት የተጠጋ ቋንቋ ነው። ቀደም ስል፣ ìሳይንስî
የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ያነሳሁት በኣማርኛ ሊጠቀሙበት ከፈለጉ፣ ìሰየነሰî ከሚለው ግስ ተነስተው ìስይንስî
የሚል ስም የሚሰጥወት የሰዋስው ህግ ኣለ፤ ልልዎት ፈልጌ ነው። ፊደሎቻቸው ከሁለት የሚበልጡ የኣማርኛ
ግሶችን ከሚፈጥሩ ቅርፆች ኣንዱ በìùî የሚናበቡ ፊደሎች ሲደረደሩ ነው። ስለዚህ፣ ìሳይንስî የሚለው
የእንግሊዝኛ ቃል የኣማርኛ ግስ ቢኖረው ìሰየነሰî ይሆን ነበር። ግሱ ከታወቀ ስም ከሚሰጡን ህጎች ኣንዱ
እያንዳንዱን ፊደል ወደ ሳድስ መቀየር ነው። ይህንን ሂሳባዊ ህግ በመከተል ìስይንስîን እናገኛለን። ይታይወታል?
ኣማርኛ ከሌሎች መለቃቀም ሳይሆን ከሌሎች የወሰደውን የራሱ የሚያደርግበት ስልት እንዳለው፣ ይታይወታል?
ኣቶ ታቦር! እየደከመኝ ነው። ሳልሄድ በፊት ስለ ኣባ ባህርይ ትንሽ ልበል። የፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌን ኣባ ባህርይ
ኣንብበውታል። ማንበብ ብቻም ኣይደል ኣንብበው ጠልተውታል። ኣባ ባህርይ ግን ባለውለታዎ ናቸው። የሚኮሩበትን የገዳ
ስርኣት በወሬ ሳይሆን በውስጡ ኖረው፣ እንደተረት ሳይሆን በምሁራዊ ኣስተያይት ፅፈው ያቆዩልዎ ሊቅ ናችው። እሳቸው
ባይፅፉት ኖሮ ከተራ ተረት ያለፈ ዋጋ ኣይኖረውም ነበር። በተለይ ረ/ፕሮፌሰር ታደስ በሪሶ ኣባ ባህርይን ሊያከብሩ
ይገባቸዋል፤ ኣባ ባህርይ፣ ከቀዳሚዎቹ የኣለም ስነ-ሰብእ (Anthropology) ሊቃውንት ኣንዱ ናቸውና።
ከኣባ ባህርይ ልትማሩ የሚገባችሁ ነገር ካለ፣ መፃፍን ነው። ካልተፃፈ ቋንቋ ኣያድግም። ባዬ ይማም፣ ìያልተፃፈና ስርኣቱ
በወጉ ያልታወቀ ቋንቋ ተቆፍሮ ሊወጣ የሚችል ኣፅም የለውምî፤ ይላሉ። እኔ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በሙሉ እንዲያድጉ
ከሚፈልጉት ሰዎች ኣንዱ ነኝ። ኣማርኛ ባካባቢው ያገኛቸውንም ሆነ ከሩቅ የመጡትን ቋንቋዎችን የሚመገብ ሆዳም በሬ
ነው። ሌሎች ቋንቋዎች ሲያድጉ ይጠቀማል እንጂ ኣይጎዳም። ከሌሎች ቃል ወስዶ፣ በራሱ ህግ መሰረት ሲያረባቸው
የሚፈጠሩት ቃላት የሚሰጡት ትርጉምና ሃሳብ፣ ቃላቱ የተወሰዱበት ቋንቋ ውስጥ እንኳን ኣይገኙም። (የፕሮፌሰር መስፍን
ኣረጋን ሰገላዊ ኣማሮምኛ ይመልከቱ)። እኔ የማውቃቸው የኦሮምኛ ቃላት ኣራት ናቸው፤ ቶኮ፣ ለመ፣ ሰዲ እና ኣፉር።
ባቅሜ፣ እንዚህን ቃሎች ለኣማርኛ እንደሚከተለው መግብያቸዋለሁ።
ቶኮያዊ እኩልታዎች = Linear Equations ፣ ኢቶኮያዊ እኩልታዎች = Non Linear Equations፣ X-ለመ = X-Squared ፣
X-ሰዲ = X- Cubed ፣ X-ኣፉር = X4 ወይም X to the 4th power ወይም X የተሰኘው ፍሩቅ (Variable የሚለዋወጥ፣
የሚፈራረቅ) በኣራት ሲታየል . . . ።

እንግዴህ ይብቃኝ። ነገር ቢበዛ በ ìሃሬî ኣይጫንም። ነገር ቢበዛ በìኣጠበî ኣይጫንም ብለው እንደማይተረጉሙት ተስፋ
ኣደርጋለሁ። ኣደራ የምልዎት ግን (የኔን ኣደራ እንኳን ከቁቅም የሚቆጥሯት ኣይመስለኝም) በኦሮምኛ እንዲፅፉ ነው። ግን፣
ኦሮምኛ እንዳያድግ ወደኋላ የሚጎትተው ይሄ ቁቤ የሚሉት ነገር ነው። በኢትዮጵያ ፊደል ቢፃፍ ኖሮ፣ ኦሮምኛ ባለፉት ሃያ
ኣመታት ውስጥ ትልቅ እድገት ያሳይ ነበር። ከስሜታዊነትና ከጥላቻ ላንድ ኣፍታ ይገለሉና ልቦናዎን ላንድምታዊ ኣስተሳሰብ
ከፈት ያድርጉት።
የምንቻቻልበትን፣ የምንከባበርበትን እና ይቅር የምንባባልበትን ጊዜ ያምጣልን።
ኣምሃ ኣስፋው። 

No comments:

Post a Comment