18 ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006
ፋክት፡- ከሀገር ከወጣህ ምን ያህል ጊዜ ሆነህ?
ታማኝ፡- እንደው ይሄን ነገር ባልጠየቅ ደስ ይለኝ ነበር።
ምክንያቱም የወጣሁበት ቀን በረዘመ ቁጥር፣ ሀገሬ ላይ በጣም
ክህደት የፈፀምኩ ያህል ይሰማኛል። የግድ ነው ካልከኝ ልናገር፤
አሁን እንግዲህ አስራ ስምንት አመት ገደማ ሊሆነኝ ነው።
ፋክት፡- በጣም ሩቅ ነው። አንተ ከወጣህ በኋላ ያን ጊዜ የነበረውን
ችግር የማያውቅ አዲስ የመጣ ትውልድ አለ ማለት ይቻላል፤ እናም
ለነርሱ ግልፅ እንዲሆንላቸው፣ ከሀገር የወጣህበት ትክክለኛ ምክንያት ምን
ነበር? ታስታውሰዋለህ?
ታማኝ፡- እንዴ! በጣም ነው እንጂ የማስታውሰው። እንግዲህ በፈረንጆቹ
አቆጣጠር ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ወደ አሜሪካ እየመጣሁ፣
ስራ እየሰራሁ እመለስ ነበር። በምሰራው የኪነ-ጥበብ ስራም የተነሳ አራት እና
አምስት ወራት እየቆየሁ፣ የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ስራዬን አቅርቤ እመለሳለሁ።
ይሄ ማለት እንግዲህ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1988 ዓ.ም. ማለት ይመስለኛል።
እናም ምንም እንኳ እንደ ችግር ባልቆጥረውም፣ በነዚህ ጊዜያት በተለያዩ ችግሮች
ውስጥ አልፌያለሁ። አሁን የሚገዛው የወያኔ ስርዓት ወደ ስልጣን ከመምጣቱ
በፊት የነሱን ፕሮግራም በሬዲዮ ስከታተል፣ ስለኢትዮጵያ ያላቸውን እቅድ
ሲናገሩ በፍፁም ከኔ እምነት ጋር የማይሄድ ስለነበር፣ ባገኘሁት አጋጣሚ
ሁሉ የተቃውሞ ሀሳቤን ገልጬያለሁ። በዚያ ምክንያትም የተለያዩ
ችግሮች ደርሰውብኛል። ያም ሆኖ ግን ሀገሬን እለቃለሁ የሚል
እምነት አልነበረኝም። ለዚህም ነበር እስከ 1988 ዓ.ም. ድረስ
ወደ ሀገርቤት እየተመላለስኩ የኖርኩት። በዚህ መሀል
እንግዲህ ሀገር ቤት መድረኩን ሳገኝ በአብዛኛው እምነቴን
ነበር የምገልፀው፤ ወደ ኋላ ላይ መድረክ የማጣት፣
የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም
ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ
ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት
(ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን
አምባገነንነት፣ ከፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይ
ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም
ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና፣ እስርና
ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል።
በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን
የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ
ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና
እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል
ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ
የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል።
በዚህም በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ
ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል።
አክትቪስት ታማኝ በየነ፣ ከተመስገን
ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለ-መጠይቅ
እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
“ከአሜሪካ በላይ፣
ራሳችን ተፅዕኖ መፍጠር አለብን”
ታማኝ በየነፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006 19
የመከልከል፣ የምሰራው ነገር ማጣት አልፎም
ግርፋት እና እስራት ይደረስብኝ ጀመር። ይሄን
ጉዳይ እንኳ ባልናገረው እመርጣለሁ፤ ምክንያቱም
ለነሱ የደስታ ስሜት የሚፈጥርላቸው ይመስለኛል።
በጊዜውም ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ
እንቅስቃሴዎች የተገደቡ ነበሩ። እናም ብቸኝነት
ተሰማኝ። የመስራት አቅሜም ሆነ የህልውናዬ ነገር
አደጋ ላይ ሲወድቅ ወጣሁኝ፤ በቃ ይኼው ነው
ነገሩ።
ፋክት፡- ከጥቂት ዓመታት በፊት ባሰራጨኸው
አንድ ሲዲ ላይ፣ የኢህአዴግ ሰራዊት አዲስ አበባ
እንደገባ ዕለቱኑ ፓርቲውን ተችተህ ለሲ.ኤን.ኤን
ቴሌቭዥን የሰጠኸው ቃለ-ምልልስ ነበር። ያ ወቅት
የቀድሞ ስርዓቱ ዋነኛ ሰዎች እንኳን ሀገር ጥለው
የተሰደዱበት ከመሆኑ አኳያ፣ አዲስ አበባ ተቀምጠህ
በድፍረት ስትተቻቸው ፍርሀት አልተሰማህም ነበር?
ታማኝ፡- እንዴ! የምን ፍርሃት ነው? እነርሱ እኮ
አዲስ አበባ ሳይገቡ፣ ገና አምቦን ሲቆጣጠሩ እኮ ነው
የደርግ ስርዓት ከሞላ ጐደል መፍረስ የጀመረው።
እናም አገሪቷን በአግባቡ እያስተዳደሯት እንዳልሆነ
ሁሉም የተረዳበት ጊዜ ነበር። ያም ቢሆን ዋና
ከተማዋን ሊቆጣጠሩ 23 ቀን ሲቀራቸው፣ አዲስ
አበባ ስታዲየም ውስጥ በርካታ ድምፃውያን
የተሳተፉበት ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት አዘጋጅተን
ነበር። ያን ጊዜ ታዲያ በራዲዮናቸው በተለይም
ሰንደቅ አላማን በጣም ያንቋሽሹ ነበር፣ የዘመናት
ታሪካችንንም በስድብ ያጠለሹ ነበር። ይኼ ደግሞ
በጣም ያበሳጨኝ ነበር። በዚህም የተነሳ ሁላችንም
ሰንደቅ አላማ ለብሰን ድምፃችንን እናሰማ ብለን
መጀመሪያ በብሄራዊ ትያትር ቤት፤ በሳምንቱ
ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም እነ ጥላሁን ገሠሠ፣
መሀሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ታምራት
ሞላ፣ መልካሙ ተበጀ፣ አረጋኽኝ ወራሽ፣ ንዋይ
ደበበ፣ ፀሀዬ ዮሀንስ፣ ፀጋዬ እሸቱ፣ ቴዎድሮስ
ታደሰ… እና ሌሎች በጣም በርካታ ድምፃውያን
የተሳተፉበት ‹የኢትዮጵያ አርቲስቶች ለኢትዮጵያ
አንድነት› የሚል ሾው አዘጋጅተን ነበር። ኮ/ል
መንግስቱም ስልጣን ላይ ነበሩ፤ እንዳልኩህ ሰዎቹ
23 ቀን ብቻ ነው የቀራቸው። በዚያች ሰዓትም
ቢሆን ባለችው ቀዳዳ የደርግን ድክመት
ለመጠቆም ሞክሬያለሁ። ያኔ ፍርሃት
ሳይሆን የሀገሬ ሁኔታ ነበር የሚያሳስበኝ፤
እዚሁ ሆኜ ነው የገቡት። ፍርሃት የሚባል
ነገር አልነበረም። ይህን የምለው አሁን
ዳር ሆኜ ለመናገር ብዬ ሳይሆን፤ በዛን
ጊዜ የቀደሙ አያቶቼ የተሰዉላት ሀገር፣ በዛ ደረጃ
እየተንቋሸሸች ሞትን እንደ ሞት የምቆጥርበት
እድሜና ሁኔታ ላይ አልነበርኩም ለማለት ነው።
እናም ፍርሃት አልነበረብኝም።
ፋክት፡- የመፍራቱን ጥያቄ ያነሳሁት፣ ወቅቱ በጣም
አስፈሪ ስለነበርና እነሱም ከመግደል የማያመነቱ
ስለነበር ነው?
ታማኝ፡- ልክ ነው! እንዲያውም እኮ ይገርማል።
አሁን ባነሳሁት ትርዒት ላይ፤ ያው ራዲዮናቸውን
በየጊዜው እከታተል ስለነበረ በየተለያየ ጊዜ
‹‹ይሄን ያህል ሰራዊት ገደልን››፣ ‹‹ይሄን ያህል
ሰራዊት ገደልን›› የሚሉትን ደምሬ፤ እንዴት ነው
ነገሩ?! እነዚህ ሰዎች በሚሉት ሂሳብ ከሄድን እኮ
ከሚመጣው ትውልድ ሁለት ሚሊየን ተበድረን
ሞተናል ማለት ነው! የሚል ቀልድ ሰርቼ ነበር።
በማግስቱ ታዲያ ጠዋት ከበረሀ የሚያሰራጩትን
ራዲዮናቸውን ስከፍት፤ እንደማስታውሰው ሴኮ
የሚባለው ሰው ድምፅ ይመስለኛል፣ ‹‹አቶ ታማኝ!
ሂሳቡን እዚያው አዲስ አበባ ስንመጣ እንተሳሰባለን››
ብሎኝ ቀልድ ሰርቶብኛል። በዕርግጥ ያ ወቅት
መጥፎ ጊዜ ቢሆንም፣ ፍርሃት አልነበርም። በኔ
ውስጥ የነበረው ነገር፣ ያ ሁሉ መስዋዕትነት
የተከፈለላት ሀገር በዚህ ደረጃ ስትዋረድ፣ ስትሰደብ
መስማት ያማል! እናም የሀገር ጉዳይ ለድርድር
የሚቀርብበት ሰዓት አይደለም የሚል ነበር።
ፋክት፡- ከሀገር ከመውጣትህ በፊት በወቅቱ
የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ
ቢሯቸው ጠርተው አስፈራርተውኻል ይባላል፤ ይሄ
ምን ያህል እውነት ነው?
ታማኝ፡- አይ አይደለም፤ ጠ/ሚኒስትር ታምራት
ላይኔ አላስፈራሩኝም። ግን ያው ታዛዥ አሽከሮች
በየጊዜው… እንዲህ አይነት ጉዳዮችን መናገር
ስለሚያናድደኝ ነው። ኤግዚቢሽን ማዕከል ትርዒት
ነበር። እሱን ለማሳየት ሄጄ፤ ሁለት የደህንነት
ሰዎችና አንዱ ደግሞ የቡና ቤት ባለቤት የሆነ ሰው
እየደበደቡ ሲወስዱኝ፣ አክሊሉ የሚባል የማዕበል
ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ‹‹ለምን ትደበድቡታላችሁ?
እርሱ ምን አደረገ?›› ብሎ በመጠየቁ፣ አፉ ውስጥ
ሽጉጥ ደግነው ይደበድቡት ነበር። እኔንም ‹‹ታምራት
ላይኔን እንዲህ አድርገህ ተሳደብክ›› እያሉ፣ በጣም
መጥፎ ስድብ ይሰዱቡኝ ነበር። እኔም የሚሰማኝን
አንድ ቀን ስልኬ ጠራና አንስቼ ‹‹ማን ልበል?›› ስል፣ ‹‹ታምራት ላይኔ ነኝ፤
በጌታ ስም ይቅር በለኝ፤ ይቅር ካላልከኝ አልቀመጥም!›› አሉኝ። ‹‹እኔ እኮ
ቀድሞ ነው ይቅር ያልኮት። ከእኔ ይልቅ በእርሶ ትዕዛዝ የተገደሉትና ወደእስር
የተወረወሩት እንዴት ነው ይቅር የሚሎት?›› ስላቸው፤ ‹‹ሁሉም በጊዜው
ይሆናል›› ብለውኝ እንድንገናኝ ቀጠሮ ያዝን 20 ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006
እውነት ነገርኳቸው። በሌላ ጊዜ ደግሞ አዲስ አበባ
ስታዲየም የኤርትራ እግር ኳስ ቡድን ከቡርንዲ
ጋር ሲጫወት ‹‹ለምን ቡርንዲን ደገፋችሁ›› ተብለን
ተይዝን ኮልፌ ወስደው አስረውናል፤ እኔንም
‹‹ታምራት ላይኔን እንዲህ ብለህ፣ ታምራት ላይኔን
እንዲህ ተናግረህ› እያሉ ብዙ አሽከሮቻቸው እየመጡ
ይሰድቡኝ ነበር። ጉዳዩ እንዲህ ነው እንጂ፤ ራሳቸው
ጠ/ሚኒስትር ታምራት ላይኔ አላስፈራሩኝም።
ፋክት፡- የቡና ቤቱ ባለቤት ታጋይ ነው? ማለት
አብሮ በትግል ውስጥ የመጣ ነው? ወይስ ጉዳዩ
የሚመለከተው ሆኖ ነው?
ታማኝ፡- አይደለም። መርማሪውን ስለሚያውቀውና
የአንድ ሰፈር ልጅ ስለሆኑ፣ ነው ገራፊ ሆኖ
የመጣው በተቀረ፣ ምንም ሊመለከተው የሚያስችል
ሥልጣን አልነበረውም፤ ነጋዴ ነው።
ፋክት፡- በ1988 ዓ.ም. የአድዋ ድል ሲከበር
መኢአድ፣ አንድ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ ነበር።
በዚያ ሰልፍ ላይ በህዝቡ ግፊት ወደ መድረክ ወጥተህ
ንግግር አድርገህ እንደነበር አስታውሳለሁ። ሆኖም
ከዚያን ዕለት በፊት እንዳትናገር ማዕቀብ ተጥሎብህ
እያለህ፣ አንተ ግን ያንን ሰብረህ በመውጣት ቀስቃሽ
ንግግር አድርገሀል፣ ትክክል ነኝ?
ታማኝ፡- አዎ! ትክክል ነህ። ህዝብ በተሰበሰበበት
ምንም አይነት መድረክ ላይ እንዳልናገር ከመከልከሌ
በተጨማሪ፣ ብሄራዊ ቴአትር ቤት እንኳን
እንዳልገባ ለተወሰነ ጊዜ ታግጄ ነበር። ትዕዛዙ
የተላለፈው በወቅቱ በነበሩት የባሕል ሚኒስትሩ
አቶ ልዑለስላሴ ቲማሞ ነበር። በገዛ ሀገሬ
ሰው በተሰበሰበበት እንዳልናገር መደረጌ በጣም
ያሳዝነኛል። በጊዜው ሙሉጌታ ወልደየስ የሚባል
ኳስ ተጫዋች ለብሔራዊ ቡድናችን ሲጫወት
እግሩን በመሰበሩ፣ በብሄራዊ ቴአትር ለሕክምና
የሚሆን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ሲደረግ
እኔ እንዳልኖር ታስቦ ነበር። ሆኖም ግን ዝግጅቱን
ፖስታ ቤት አድርገን በዚያ ተገኝቼያለሁ። የአድዋ
በዓል በሚከበርበት ዕለትም እስካሁን ያላነበብኩትን
የሀገሬን ታሪክ በእነእንድርያስ እሽቴ ‹‹ምኒልክ
ከውጊያው ፈርቶ ይሸሽ ነበር›› በማለት ድሉን
የአድዋ ነዋሪ ብቻ በማድረግና፤ ቀሪው የኢትዮጵያ
ህዝብ እንዳልተሳተፈበት ለማስመሰል የተሞከረበት
መንገድ በጣም አስገራሚ ነበር።
መቼም ያ ሁሉ ነገር አልፎ፣ ዛሬ ለማውራት
መቻሉ ራሱ ይደንቀኛል። እንደዚህ አይነት
ሁኔታዎች ስለነበሩ፣ የአድዋ ድል የሚከበረው ደግሞ
አድዋ ላይ ነው በማለት፤ ከአዲስ አበባ እንዲወጣ
የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ
ላይ ነው፤ እኔም እንደማንኛውም ዜጋ ስሜቴን
ለመግለፅ የተገኘሁት። ነገር ግን ከጐኔ የተቀመጡና
ያዩኝ ሰዎች ‹‹ታማኝ ይኸውና፣ ታማኝ ይናገር፣
ግባ ታማኝ›› እያሉ ሲሉኝ ወጣሁና ተናገርኩ።
ፋክት፡- ከሀገር ሳትወጣ ከሚያያዙ ጉዳዮች ጋር
የመጨረሻ አንድ ጥያቄ ላንሳ። ያኔ ከሀገርህ
ተገፍተህ ስትወጣ፣ ኢህአዴግ ይሄን ያህል ዘመን
በስልጣን ላይ ይቆያል የሚል እምነት ነበረህ?
ታማኝ፡- ረጅም ሳቅ… ኧረ! እንደውም በጭራሽ!
አሁንማ፣ እየቆዩ ሲሄዱ እኮ ለመድናቸው።
ፋክት፡- እዚያ ድምዳሜ ላይ ደርሰህ የነበረው፣
ጠንካራ ተቃዋሚ በመኖሩ ነበር? ወይስ ሌላ
የተማመንክበት ኃይል ነበር?
ታማኝ፡- አይ! በፍፁም አይደለም! ምንድነው
የሚባለው፣ ዘይትና ውሃ ይሉት ነገር የለም?
የኢትዮጵያ ህዝብና እነሱ ዘይትና ውሃ አይነት
ነበሩ እኮ። የተንሳፈፉ ነበሩ። አዲስ አበባ ስታዲየም
ኳስ ልናይ ስንገባ፣ እነሱ ያዘጋጁት አዲሱ ብሔራዊ
መዝሙር ሲዘመር፣ ሰዉ ተቃውሞውን ለማሰማት
የድሮውን መዝሙር ነበር የሚዘምረው። ኢትዮጵያዊ
የሚል መንፈስ በውስጣቸው ስለሌለ፣ የትኛውም
ባለስልጣን አዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ንግግር
ማድረግ እስከማይችልበት ደረጃ ድረስ ተደርሶ ነበር።
ከህዝቡም የተነጠሉ ነበሩ። በየትኛውም አቅጣጫ
ብትሄድ፣ ለምሳሌ ዘመን መለወጫ ሲከበር፣ ሰንደቅ
አላማ ይዞ የቆመ ሰው ከተገኘ ሰዉ እንደጉድ
ተነስቶ ይሸከመው ነበር። በሁሉም አቅጣጫ ህዝቡ
ይቃወማቸው ነበር። እንግዲህ ያንን አስተባብሮ
የሚመራ ሀይል ባለመኖሩ እንጂ፣ ኢህአዴግ ይህን
ያህል ዘመን ሊከርም አይችልም ነበር።
ፋክት፡- አሁን ወዳለህበት እንምጣና፤ በዲያስፖራው
በኩል በድጋፍም፣ በተቃውሞውም ያለውን ጎራ
እንዴት ትገልፀዋለህ?
ታማኝ፡- በዲያስፖራው በኩል አንድ መታወቅ
ያለበት ነገር፣ እዚህ ያለው የውጭ ሀገር ህይወት
እንደ ኢትዮጵያ አለመሆኑ ነው። ሁሉም ነገር
ከሰዓት ጋር የተያያዘ ነው። ኑሮ በሰዓት የተወጠረ
ነው። ቤተሰብ ካለ፣ ልጆች ካሉ ደግሞ የበለጠ ከባድ
ይሆናል። ምንም ፋታ የለህም። እንደ ቅዳሜና እሁድ
ያሉ የዕረፍት ቀንናት እንኳ፣ ይዘው የሚመጡት
የቤት ስራ አላቸው። በግልም ሆነ በማህበራዊ
ህይወት የምትወጠርበት ሁኔታ ነው ያለው። በዚህ
ውጥረት መሀል አዕምሮህ ይበልጥ የሚሰፋበት፤
ውሻና ድመት እንኳ መብታቸው የሚከበርበትን
ሁኔታ እያየህ፣ እንዴት ከውሻ ያነሰ ኑሮ እኖራለሁ?
በሚል ጥያቄ አዕምሮህ የሚፈተንበት ነው። እናም
ዲያስፖራው በዚህ ሁሉ ውጥረት መሀል እንቅልፍ
አጥቶ ሀገር ቤት ያለው ወገን ይህንን መብት
እንዲያገኝ እና ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሰረት
እንዲፈጠር ጥረት እያደርገ ነው። እንዳለመታደል
ሆኖ ግን፣ የመንግስት ደጋፊዎች የምትላቸው
እንዲህ አይነት ሀገር ውስጥ እየኖሩ፣ ኢትዮጵያ
በዘረኞችና በአምባገነኖች ስትመራ እያዩ፣ ልክ ነው
ብለው መደገፋቸው ግራ ከማጋባቱም በላይ በጣም
ያሳዝናል። ነፃ ሀገር ላይ ያለውን መመዘኛ እያዩ፣
በነፃነት የደረሱበትን የእድገት ደረጃ እየተመለከቱ፤
ለኢትዮጵያ ግን ይህንን ኋላቀር፣ ዘረኛ እና አፋኝ
ስርዓት ደግፈው ሲቆሙ ስታይ ግራ ይገባኻል።
በደጋፊና በተቃዋሚ መካከል ያለውን ልዩነት፣ እኔ
እንደዚህ ነው የማየው።
ፋክት፡- በዲያስፖራው ውስጥ ዘርን መሰረት ያደረገ
መከፋፈል አለ የሚለውን አባባል ትቀበለዋለህ?
ታማኝ፡- ምንም ጥያቄ የለውም። መሰረታችን
ኢትዮጵያ ነው። አንዳንዴ ወደ ሀገሩ ተመልሶ
ቤተሰቡን ጠይቆ መምጣት የሚፈልግ ሰው አለ።
ወደ ሀገር ቤት እንድትገባ ሲደረግ ደግሞ፣ ዘርህ
ከግምት ውስጥ ይገባል። ስለዚህ ነገሮችን በዚያ
መነፅር የሚመለከቱ አሁንም አሉ። ስለኢትዮጵያ
ተብሎ የልማት ጥሪ አትጠራም። የምትጠራው
የአማራ፣ የትግራይ፣ የጉራጌ፣ የደቡብ ተብሎ ነው።
ኤምባሲው እንኳ፣ በኢትዮጵያዊነት ለማሰባሰብ
የሚያስችል አቅም የለውም። ለምሳሌ በየአመቱ
ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት፤ ስደተኛው ራሱ
ያቋቋመው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አለ። እሱን
ለመቃረን ‹የትግራይ ፌስቲቫል፣ የኦሮሞ ፌስቲቫል›
የሚባሉ ተፈጥረዋል። ይሄ የሚያሳይህ ስርዓቱ
ያመጣብንን ችግር ነው። ቢሆንም ግን፣ አሁንም
በኢትዮጵያዊነታቸው ፀንተው የሚደክሙ፣ ፀንተው
እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሰዎች አሉ።
ፋክት፡- ስርዓቱ ካመጣው ተፅዕኖ ባሻገር፣
በዲያስፖራ ውስጥ የትግራይ ተወላጆችን ከስርዓቱ
ጋር አያይዞ ያለማመን ወይም የማግለል ሁኔታ
ይታያል፤ ይሄንን እንዴት ታየዋለህ?
ታማኝ፡- በበኩሌ ማግለል የሚለውን አላምንበትም።
ምን አቅም አለን ለማግለል? ኢትዮጵያ ውስጥ ብትሆን
ደህንነቱን፣ ፖሊሱን ተጠቅመህ ታገልላለህ። እዚህ
በምን ተጠቅመህ ታገልላለህ? ጥያቄው የተሰራውን
የመከፋፈያ ድልድይ ሰብሮ የመምጣት ጉዳይ ነው።
መንግስትን መቃወም ትግራይን እንደመቃወም
አድርገው የሚቆጥሩ አሉ። በቁጥር ብዙ ባይሆኑም
እንኳን በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ፣ ይሄን
ግንብ አፍርሰው የተቀላቀሉ የትግራይ ልጆች
አሉ። ስለዚህ ጥያቄው መዞር ያለበት፣ አሜሪካ
ውስጥ እየኖሩ የልዩነት ድልድይ ሰርተው፣ እኛ
እንደዚህ ነን ብለው ወደ ተቀመጡት ነው። ከዚህ
በቀር እኛ በምን አቅማችን ነው የምናገልላቸው?
ስርዓቱ ‹‹በዚህ በዚህ ልክ አይደለም›› ስትል፣ አይ
የትግራይን ህዝብ መቃወም ነው የሚሉ ካሉ፣ ይሄ
የነርሱ ችግር ነው የሚሆነው።
ፋክት፡- ከዚህ ቀደም በተቃውሞው ጎራ የነበሩ
አንዳንድ ግለሰቦች ወደ ኢህአዴግ ሲገቡ፤
‹‹የትግራይ ተወላጅ በመሆኔ ብቻ ተገፋሁ፣ ልታመን
አልቻልኩም፤ ትግሬ በመሆንህ ብቻ ብትቃወምም
የሚያምንህ የለም›› ሲሉ ይደመጣልና፤ ከዚህ አኳያ
ነው ጥያቄውን ያነሳሁት…
ታማኝ፡- እንዲህ ብለው የሚያምታቱ ሊኖሩ
ይችላሉ። ግን ስንት አመት ነው በዚህ ካርድ
መጫወት የሚቻለው? በዚህ ጉዳይ ላይ የሚጋጩ
ሁለት ነገሮችን ላንሳ። ይኼ መንግስት ራሱ
እንደሚያውጀው፤ መንግስታዊ አወቃቀሩ በብሄር-
ብሄረሰቦች መልካም ፈቃድ የተመሰረተ እስከሆነ
ድረስ፣ ለምንድነው የትግራይ ብቻ ተብሎ
የሚጠራው? በትግራዋይነቴ እንዲህ ተደረኩኝን
ምን አመጣው? እዚህ መንግስት ውስጥ ለምን
የሁሉም ብሄረሰቦች ድምፅ አይኖርም? ለምንድን
ነው ስለትግራይ ህዝብ ብቻ የሚባለው? ስለዚህ
ይሄን ጥያቄ የሚያነሱት እነሱ ብቻ ናቸው። እኔ
ተነስቼ በምናገረው ሀሳብ መጠየቅ ወይም መከሰስ
ያለብኝ በታማኝነቴ ነው። እኔ የተወለድኩበት
የጎንደር ህዝብ ሊጠየቅ ይችላል እንዴ? ለምንድን
ነው ይሄ ዓይነት አስተሳሰብ የሚመጣው? ስለዚህ
በጥቂት የብሄሩ ተወላጆች የተያዘ ቡድን ትክክል
ነው ብለው የሚከራከሩ እና እኛ ካልገዛን ብለው
የሚያምኑ ሰዎች አሉ፤ ስርዓቱን መቃወም
ከትግራይ ህዝብ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር
የለም። ስርዓቱ እንደ ስርዓት እኛን እየበደለን ነው
ስንል፣ በፀረ-ትግሬነት ይኮንኑሀል። ለምሳሌ የአስራ
አራት አመት ህፃን የገደለ ስርዓትን፣ ‹ለምንድን ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006 21
ነው ህፃናትን የምትገድለው?› ብለህ ስትጠይቅ፣
የትግራይን ህዝብ ስለምትጠላ ነው ብሎ መመለስ፣
ከጥያቄው ጋር እንዴት ሊገናኝ ይችላል? እንዲህ
እያሉ ማስፈራራት መቆም አለበት። አንተ ይሄን
ቃለ-መጠይቅ እስክታደርግልኝ ድረስ ይሄ ካርድ
ማስፈራሪያ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ባለፉት 23
አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ እንዲህ አይነት
ቃል ተናገረ የሚባል ሰው ሰምተህ ታውቃለህ?
በኦዲዮ፣ በቪዲዮ፣ በምስል ወይም በፅሁፍ የተነገረ
አንድም አታገኝም። በሥርዓቱ ድብቅ ሴራ ግን
ብዙ ገበሬዎች፣ ዘራቸውንና እድሜያቸውን መናገር
የማይችሉ ህፃናቶች ኢትዮጵያ ውስጥ አልተገፉም
እንዴ? ባለፈው ሳምንት የአማራ ክልል ም/
ፕሬዝዳንት በአደባባይ የአማራን ህዝብ ‹‹ለሀጫምና
ልጋጋም›› በሚል ፀያፍ ቃል አልተናገረም? እስቲ
ልክ እንደዚህ በትግራይ ህዝብ ላይ በዚህ ቀን፣
በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ነገር ብሏል የሚባል
ሰው ታመጣለህ? የለም! እንዲህ ዓይነቶቹን ነገሮች
የፕሮፓጋንዳ ማሽኑ የሚያነሳው፣ የተቃውሞው
ጎራ የሚጠይቀውን መሰረታዊ ጥያቄ ለመድፈን
እንዲያስችለው ነው። በእኔ በኩል፤ ሁላችንም ዘራችን
ሳይጠየቅ፣ በሕግ ፊት በእኩልነት የምንኖርበት
ሀገር ትምጣ እያሉ መጮህ፣ ለምን ፀረ-ትግራይነት
ተደርጎ እንደሚቆጠር መልስ የማላገኝለት ጥያቄ
ነው።
ፋክት፡- ይህንን ምክንያት የሚያነሱትን ሰዎች፣
የፖለቲካ ማጭበርበር የሚፈፅሙ አድርገን ማለፍ
እንችላለን?
ታማኝ፡- ምንም ጥያቄ የለውም። ለዚህም ነው
‹‹ስርዓቱን አትንኩት›› ሲሉን፤ የምንነካው በዚህ
በዚህ ምክንያት ነው ስንላቸው የሚያኮርፉት። እነሱ
ያለቻቸው ብቸኛ ካርድ ‹‹ትግራይ፣ ትግራይ…››
እያሉ መጮህ ብቻ ነው። ይኼ ምክንያት በቅጡ
መመርመር አለበት። ሰው ከመሬት ተነስቶ
ትግራይን የሚጠላበት ምክንያት ምንድን ነው?
በድህነት አብረን እኩል ተቸግረን ነው የኖርነው።
ታዲያ ከኢትዮጵያ ህዝብ በምን ስለተለዩ በተለየ
መንገድ ትጠላቸዋለህ? ሊጠሉበት የሚችሉበት
ምክንያት ነው ያልገባኝ! እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ
የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር
ችግሩን፣ መከራውን፣ ደስታና ሀዘኑን ተካፍሎ
ኖሯል። እንዴት ከ83 በኋላ በድንገት ጥላቻ ሊከሰት
ይችላል? ለዚህ ጥያቄ የሚያቀርቡት መልስ ‹ስልጣን
ስለያዝን ነው› የሚል ነው።
ከዚህ በተጨማሪም፤ እኛ ከዚህ በፊት ስልጣን
ይዘን ነበር፣ ከስልጣናችን ተባርረን የነበርን ሰዎች
ነን ይሉናል። ይኼ ሁሉ ተቃዋሚ በፀረ-ትግራይ
ስም ነው የሚንቀሳቀሰው ማለት ምን ማለት ነው?
ወይም በሳይንስ የተደገፈ ለተቃውሞው መነሻ
የሚሆን የተሰራ የላብራቶሪ ውጤት ካለ ይንገሩን።
ከዚህ ባለፈ ‹ዝም ማሰኘት የሚቻለው በዚህ መንገድ
ነው› ካልተባለ በስተቀር፣ ጥላቻን በፕሮግራም ፅፎ፣
አንድን ህዝብ እንደጠላት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለ፣
ከህወሓት በቀር ሌላ ድርጅት አላውቅም። እናም
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የህወሓትን ዕኩይ ተግባር
ለኛ መስጠት ከወንጀልም በላይ ወንጀል ነው።
ፋክት፡- አሁን በኢትዮጵያ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ
ትክክለኛ መረጃ አለኝ ብለህ ታስባለህ?
ታማኝ፡- ከናንተ በተሻለ መረጃ አለኝ ብዬ
አምናለሁ።
ፋክት፡- ጤፍ ስንት ብር የገባ ይመስልሀል?
ታማኝ፡- (ረ..ጅ…ም ሳቅ) እሱን ነው እንዴ መረጃ
የምትለው?
ፋክት፡- አገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ?
ታማኝ፡- ጤፍና እንቁላል እንኳ ስንት እንደገባ
አላውቅም። አንድ እርግጠኛ የምሆንበት ነገር
ግን፤ በጃንሆይ ጊዜ በኢትዮጵያ በአለባበሳቸው እና
በአኗኗራቸው የሚቀናው በመምህራን እንደነበር
አስታውሳለሁ። ዛሬ መምህራኑ ሆዳቸውን መሸፈን
እንዳልቻሉ ልነግርህ እችላለሁ። ስለዚህ ኑሮውን
በዚህ መለካት ትችላለህ።
ፋክት፡- ብዙው ኢትዮጵያዊ ከዚህ ቀደም
የሚያውቅህ ምርጥ አርቲስት እንደነበርክ ነው።
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ትንታግ አክቲቪስት (የመብት
ተሟጋች) ሆነሀል። ከጥበቡ ርቀሃል ማለት ይቻላል?
ታማኝ፡- አይ አልራቅሁም። በእርግጥ ምን መሰለህ፤
ጥያቄው በጣም ሰፊና በቃለ-መጠይቅ የሚያልቅ
አይነት አይደለም። በፅሁፍ ባብራራው ደስ ይለኝ
ነበር። የኪነ-ጥበብ ሰው ሀሳቡን ወደ ህዝቡ በተለያየ
መንገድ ያደርሳል፤ በዘፈን፣ በቀልድ፣ በግጥም፣
አልያም በትያትር ያደርሳል።
እኔም በንግግሬ እንደ ልቤ ሀሳቤን የማደርሰው
የጥበብ ችሎታዬን ተጠቅሜ ነው። ስለዚህ ከጥበብ
አልራቅሁም ማለት ነው። ምናልባት የራቅሁ
የሚያስመስለው በዘፈን ማለትም በኪነ-ጥበብ
ሙያ ተከፍሎኝ እሰራ የነበረውን ስራ ትቼ፣
በነፃ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ መድረኮችን እየፈለኩ
ስለምናገር ይሆናል። በተጨማሪም ሌላው እንደ
እሳት የሚፈራውን ፖለቲካ የሚባለውን ነገር ደፍሬ
ስለማደርገው ‹አይ ትቶታል› ተብሎ ካልሆነ በቀር፣
በውስጤ ያለው ችሎታና ፍቅር አሁንም እንዳለ
ነው። ምናልባት ችሎታ የሚለው ወደፊት ተፈትኜ
ሳልፍ የሚረጋገጥ ይሆን ይሆናል። ይህም ሆኖ፣
ጥበብን ለንግድ ባልጠቀምበትም፣ ለማምንበት ነገር
ግን እየተጠቀምኩበት ነው።
ፋክት፡- ሌሎች እንደ አንተ ያሉ አርቲስቶች በቀጥታ
ስርዓቱን ሲጋፈጡና ሲያጋልጡ አንመለከትም።
ምክንያታቸው ፍርሃት ብቻ ይመስልሃል?
ታማኝ፡- ፍርሃቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሌሎችም
ምክንያቶች ይኖራሉ። እውነት የምታስከፍለው
ዋጋ ይኖራል። ጋሊሊዮ የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን
ለዘመናት ያስተማረችውን የፀሀይን በመሬት ዙሪያ
መሽከርከር በሳይንሳዊ መንገድ ፈትኖ ተቃራኒውን
ሲያቀርብ፣ ራሱን ለመከራ መዳረጉን ከታሪክ
ድርሳናት መረዳት ይቻላል።
እናም በዚህ መልኩ ለእውነት መቆም የሚያመጣውን
በትር በመፍራት፤ ‹ጐመን በጤና› የሚለው ብሂል
የአርቲስቶቻችንም፣ የህዝቡም የህይወት መመሪያ
ሆኗል። ሁልጊዜ የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፤ በዚህ
ምድር ላይ ኖርን ለማለት የመጣን ሰዎች፣ አንዳች
ለውጥ ሳናመጣ እና ከራሳችን አሻግረን ለሌሎች
ሳንተርፍ፣ እንደእንስሳ ኖረን ማለፋችን ያሳዝነኛል።
ይሄ ማለት ራስን በልቶ ከማደር በላይ አለመመልከት
ነው። እናም የዝምታው ምክንያት ከፍርሃትም በላይ
ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት ይመስለኛል።
ፋክት፡- ከስርዓቱ ጋር እጅና ጓንት የሆኑትን
አርቲስቶች የጥበብ ስራ (ያውም አብዛኞቹ እንደ
አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ
እያተኮሩ) እየገዛ እነሱን የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ
የሚያደርገው፤ የሚጨቆነውና የሚረገጠው ህዝብ
ነው፤ አንተ በግልህ ይሄ ህዝብ ከስርዓቱ ጐን ቆመው
(ምንም እንኳ ሚዛኑ አናሳ ቢሆንም) የሚበድሉትን
አርቲስቶች በምን መልኩ መቃወም (Boycot)
ነበረበት ብለህ ታስባለህ?
ታማኝ፡- ትክክል ነው። ይሄ ጥያቄ ግን ወደ ብዙ
ነገር ይወስደናል። ከስርዓቱ ጋር ተባብረው ይህን
የሚያደርጉት የጥበብ ሰዎች ብቻ አይደሉም።
ለምሳሌ የሕግ ተማሪዎችን ብትወስድ፣ ስለሰው ልጅ
መብት ቅድሚያ ሰጥተው መሟገት እንዳለባቸው
ነበር የተማሩት፤ የምንመለከታቸው ግን በሀሰት
ከስሰው ሲያሳስሩ፣ ዐቃቤ-ሕግና ዳኛ ሆነው ሞት
ሲያስፈርዱ እና ሲፈርዱ ነው። እነዚህ እንግዲህ
የተማሩና የተመራመሩ የምንላቸው ናቸው። ህክምና
የተማሩትንም ስንመለከት፣ በቀላሉ ፈውስ ሊያገኝ
ለሚችለው በሽታ መፍትሄ ሲሰጡ አናይም። ይህን
የማያደርጉት የመንግስትን ፖሊሲ የሚቃወሙ
እየመሰላቸው ነው? የታማኝነት ጉድለትን በሁሉም
ሙያዎች ላይ እያየን ነው። ስለዚህ የብዙ ሙያ
ባለቤቶች የሆንነው ሁላችንም ለበደሉ መስፋፋት
አስተዋፅኦ እያደረግን ነው። እንደህዝብም
ማኩረፍ ስላቃተን ነው። ሕግ ተምረዋል
የሚባሉት የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ
‹‹በሽብርተኝነት ከተጠረጠረ ሰው ጋር የታየ
በሽብርተኝነት ይቀጣል›› ብለው ሲናገሩ በቴሌቪዥን
ተመልክቻለሁ። እኚህ ሰው እንግዲህ በሕግ ነው
የተመረቁት። እናም ይሄ ጥያቄ ለአንድ ቡድን ብቻ
የሚቀርብ አይሆንም።
ፋክት፡- አይ፣ የአርቲስቶች ግን ከዚህ ይለያል
ብዬ አስባለሁ። የጠቀስካቸው ሙያዎች በዚህም
አልን በዚያ፣ ወደ ስርዓቱ እንዲጠጉ ያስገድዳሉ
(በሹመትም ሊሆን ይችላል)። ጥበብ ግን ከዚህ
ለየት የሚል ይመስለኛል፤ የጥበብ ሰዎቻችን
እንቅስቃሴ በቀጥታ የህዝብን ተሳትፎ ስለሚጠይቅ
ወገንተኝነታቸው ወደ ህዝብ እንዲሆን ማድረግ
አይቻልም ወይ? ለማለት ፈልጌ ነው።
ታማኝ፡- ልክ ነው። መጀመሪያ ማኩረፍ መቻል
ራሱ ተፈጥሯዊ መብት መሆኑን ሁላችንም መረዳት
ይኖርብናል። ይሄንን ካመንን እነሱን ብቻ ሳይሆን
ሌላውንም ማስገዛት ይቻላል። የዚህን ስርዓት ቁልፍ
የንግድ ተቋማት እንቅስቃሴ ‹‹ቦይኮት›› ማድረግ
ይቻላል። ነገር ግን ማኩረፍ ብቻ እንኳን አቅቶን
ፈርተናል። ይህን ማድረግ ብንችል እኮ ማን ከማን
ጋር መቆሙን ለማወቅና፣ ለዚያም ተግባራዊ ምላሽ
ለመስጠት ይቻለን ነበር። ይሄ ከተቻለ ቀጣዩ ነገር
አያሳስብም፤ ምክንያቱም በሂደት ብዙ ነገሮችን
ማድረግ ይቻላል ብዬ አምናለሁ።
ፋክት፡- ያንተን የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ ለየት
የሚያደርገው በፊልሞች የሚቀነባበሩ መረጃዎችንም
አብረህ በማሰራጨትህ ነው። ለመሆኑ እነዚህን
መረጃዎች ከየት ነው የምታገኛቸው? ልምዱንስ
እንዴት ልታዳብረው ቻልክ?
ታማኝ፡- እንግዲህ… (ሳቅ)
ፋክት፡- መረጃዎቹን ከየት እንደምታገኝ ለመናገር
አትገደድም…
ታማኝ፡- ኧረ! ግድ የለም። መጀመሪያውኑ
ለምናገረው ነገር በቂ መልስ ከሌለኝ ለክርክርም
አልቀርብም። ድሮ በመድረክ ህይወቴ የሙያ
ባልደረቦቼ ‹‹አቶ ማስረጃ›› እያሉ ይቀልዱብኝ ነበር።
የወያኔ መንግስት በየቀኑ በአደባባይ ስለሚዋሽ
የመረጃ ችግር አይኖርም። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን
ለአንድ ጊዜ ካየህ ለአመት የሚበቃ መረጃ ይሰጥሃል።
በጣም ስለሚንቁን ነው መሰለኝ፣ የሚዋሹትን
እንኳን በአግባቡ አይዋሹም። በግሌ ግን፣ የማገኘውን
ነገር በሙሉ በማህደር የማስቀመጥ ልምድ አለኝ።
ለምሳሌ አንድ ሰው ተማረ እንኳ ቢባል 12 አመት
በትምህርት ቤት ከቆየ በኋላ፣ ለአራት አመት
ዲግሪው ደግሞ ዩኒቨርስቲ ይቆያል፤ የማስተርስና
የፒኤችዲውን ስንጨምር በአጠቃላይ ሃያ አመታት
ይፈጅበታል። እኔ ግን ከዚህ መንግስት የሃያ ሶስት
አመት ልምድ አለኝ። ስለዚህ እያንዳንዱን ነገር
ለማብራራት የዚህን ያህል ጊዜ ልምድ አለኝ ማለት
ነው።
አቶ መለስ በአንድ ወቅት
‹‹የስኳር ዋጋ የጨመረው፣
በስኳር የሚጠጣ ገበሬ ቁጥር
ስለጨመረ ነው›› ብለው
ነበር። አቶ ኃይለማርያምም
ስለጤፍ ዋጋ ሲጠየቁ፣
‹‹ጤፍ በልቶ የማያውቀው
ገበሬ፣ ጤፍ መብላት
በመጀመሩ ነው›› ሲሉ
መለሱ
ወደ ገፅ 24 ዞሯል
“ 24 ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006
ፋክት፡- የአቶ መለስን ሞት ስትሰማ ምን ተሰማህ?
ታማኝ፡- በወቅቱ ተናግሬ ነበር፤ ሁልጊዜም
በቴሌቪዥን የምታየውን ሰው ስታጣው እንደሰው
ያሳዝናል። እኔም በወቅቱ ደንግጬ ነበር። በኋላ
ላይ በማዘኔ እንኳን እንድቆጭ የሚያደርግ ነገር
በመንግስት ሲሰራ ተመልክቻለሁ። ሞተዋል ከመባሉ
ቀድሞ ነበር መረጃ የደረሰኝ። ግን በመንግስት
ሚዲያም ሲነገር ሀዘን ገብቶኝ ነበር። በቴሌቪዥን
ልጆቻቸውን ሳይ፣ አባት እንደነበሩ አስታውሼ አዝኜ
ነበር። በሳቸው ዘመን ኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን
መከራ ሳስብ ግን በጣም ይከፋኛል፤ ጥያቄው
‹‹በሞታቸው ምን ተሰማህ?›› ከሆነ ግን አዝኜያለሁ።
ፋክት፡- አቶ መለስን እንዴት ትገልፃቸዋለህ?
ይህን ጥያቄ ያነሳሁብህ ከሀገር ፍቅር አንፃር ነው።
ለምሳሌ መንግስቱ ኃይለማርያም አምባገነንነታቸው
ልክ አልነበረውም። ነገር ግን በሀገር ፍቅር ሲታሙ
አትሰማም። አቶ መለስ ግን ስማቸው በሁለቱም
ጉዳይ ሲብጠለጠል ስለምንሰማ ነው።
ታማኝ፡- እንደ አቶ መለስ በህዝብ ላይ ጥላቻ
ያለው ሰው ገጥሞኝ አያውቅም። በኢትዮጵያ ታሪክና
በኢትዮጵያ ቀደምት መሪዎች ላይ፣ እንዲሁም
በአማራ ህዝብ ላይ ይህን መሰል ጥላቻ ያለው ሰው
መፈጠሩንም አላውቅም። በዚያው ልክ ለኤርትራ
ያላቸው ፍቅር ወደር የለውም። ይህ የህትመት
ውጤት ሆነ እንጂ፣ በምስል ባስደግፈው ደስ ይለኝ
ነበር።
አዲስ አበባ በገቡ በሳምንቱ አቶ መለስን፣
ከጋሽ መስፍን ወ/ማሪያም፣ ዶ/ር መኮንን ቢሻው
እና እንድርያስ እሸቴ ጋር የሪፖርተሩ ጋዜጠኛ
አማረ አረጋዊ አወያይቷቸው ነበር። አንድ ቦታ
ላይ ጋሽ መስፍን ‹‹ይሄ መንግስት ስለኤርትራ
ጉዳይ ለመወሰን ምን ስልጣን (ማንዴት) አለው?››
ብለው ሲከራከሩ፣ አቶ መለስ ‹‹ማነው ማንዴት
የሚጠይቀን?›› በማለት እንዴት እንደተንቀጠቀጡ
አስታውሳለሁ። ከጣሊያን ወረራ በኋላ በስንት ልፋት
የተገነባን ሰራዊት፣ የነበረንን የሚያኮራ የአየር ኃይል
በአንድ ለሊት እንዴት አድርገው እንዳከሰሙት
ሳስብ ያበሳጨኛል። ወደፊት የሚኖረው ትውልድ
በጥላቻና በጥርጣሬ እንዲተያይ መርዝ ተክለው ነው
የሄዱት። ኒውዮርክ ላይ መጥተው ባደረጉት ንግግር፣
‹‹ለኤርትራ ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያዎቹ እኛ
ነን፤ በዚህ ደግሞ ኢትዮጵያውያኖች ይጠሉናል››
ብለው ተናግረዋል። ይህን ያሉበት ቪዲዮ አለኝ።
ዛሬ ደግሞ በግልባጩ እኛን ‹‹የኤርትራ ተላላኪ
ይሉናል››፤ ድሮ በስምንተኛው ሺህ የማይሆን ነገር
ይሆናል ሲባል እሰማ ነበር። ይኸው ዛሬ ኢትዮጵያን
ከሰባት አቅጣጫ የወጉ ሰው፣ ነጋሪት እየተጎሰመ
እንድንቀብራቸው ታውጇል። በአደባባይ ‹‹ቆሻሻ››፣
‹‹ወራዳ›› እና የመሳሰሉትን አስፀያፊ ስድቦች
የሚሳደብ መሪ ነው እንግዲህ ‹‹ባለራዕይ›› እየተባለ
ያለው። እናም እርሳቸውን የምገልፅበት ቃላት
የለኝም፡
ፋክት፡- ከመለስ ህልፈት በኋላ ያለችው ኢትዮጵያ
ምን ትመስላለች?
ታማኝ፡- ከዛ በኋላ ያለችውን ኢትዮጵያ፣ ግራ
የገባት ኢትዮጵያ ብላት የተሳሳትኩ አይመስለኝም።
ከርሳቸው በኋላ የተተኩት ሰው ብቻቸውን መምራት
ስለማይችሉ ሶስት ምክትሎች ተሰይመውላቸዋል።
እንደውም አንዳንዶች ‹‹ባጃጅ›› እያሉ ሲቀልዱባቸው
ሰምቼ ስቄያለሁ። መሄጃዋን የማታውቅ፣ በማዕበል
የምትንገላታ ሀገር መስላለች።
ፋክት፡- በቀጣዩ አመት 5ኛው ሀገር-አቀፍ ምርጫ
ይደረጋል። ያለፉትን ምርጫዎች ያሳለፍነው
ጉልበታማው አቶ መለስ እያሉ ነው። ቀጣዩ ግን
ያለ አቶ መለስ የሚካሄድ ነው። በአንተ አስተያየት፣
ምርጫው ከቀደሙት የተሻለ ወይስ የባሰ የሚሆን
ይመስልሀል?
ታማኝ፡- አቶ መለስን ብዙ ብወቅሳቸውም፣ በመካከል
የሚነሳላቸውም ነገር አለ። አቶ መለስ ዋሾ ናቸው።
እንደ አቶ መለስ ማን ነው አሰማምሮ የሚዋሸው?
ብዬ ሳስብ ግራ ይገባኛል። እኔ ኢትዮጵያን ከአሜሪካ
ጋር ማወዳደር አልፈልግም፤ ከኬኒያ ጋር ግን
አወዳድራታለሁ። በሀገሬም እነሱ ያላቸውን ነፃነት
ያህል የሚጠይቅ ህዝብ እንዳለም አውቃለሁ። እዚህ
ሀገር የማያቸው አንዳንድ ወጣት ኢትዮጵያውያን
አሉ። እነዚህ ወጣቶች፣ በተለያዩ የትምህርት
ዘርፎች ከማንም የተሻለ አቅም እንዳላቸው
አስመስክረዋል። ከሌሎች ሀገሮች ወጣቶች ጋር
ሆነው እየተወያዩ ፖለቲካ ሲነሳ ግራና ቀኝ ያያሉ።
ይሸማቀቃሉ። የሚገርመው፣ ፍርሃቱ አሁን ድረስ
አልለቀቃቸውም። ዋናው ጥያቄ፣ እንዲህ አይነት
ትውልድ እንዲኖረን ፈቅደናል ወይ? የሚለው
ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር በባህር ላይ መሞት
የሚል ትውልድ ለማፍራት ፍቃደኛ ሆነናል ወይ?
የሚለውም መነሳት አለበት። ይህ ከምርጫው በፊት
የሚነሳ ጥያቄ ነው። ይህን ለመመለስ ግን እያንዳንዱ
ዜጋ ራሱን መጠየቅ አለበት። እነርሱ የሚያዘጋጁልን
ምርጫ ይሄን አይመልሰውም።
በረዥም ርቀት ሩጫ እንደምንታወቀው ሁሉ፣
አሁን ደግሞ በተሸማቃቂነታችን እየታወቅን ነው።
ይሄ እስከ መቼ ይቀጥላል? በኤርፖርቶች አካባቢ
በሚኖሩ ረዣዥም ሰልፎች መሀል ኢትዮጵያዊውን
ትለየዋለህ። ሁሌም ሲደነብር ነው የምታየው።
ይህን መሸማቀቅ ለመታገስ ፍቃደኛ ነን ወይ?
ይሄን ለመመለስ የተዘጋጀ ዜጋ ካለ፣ ምርጫውንም
መጠበቅ አይጠበቅብንም። ይህ የህዝብ ውሳኔ ነው።
‹ወያኔ ስልጣን ይለቃል፤ ወይስ አይለቅም?› የሚለው
በእያንዳንዱ ዜጋ እንቅስቃሴ የሚመለስ ነው።
ፋክት፡- አይ! የእኔ ጥያቄ የአቶ መለስ መንግስት
የጨፈለቃቸውን መብቶች፣ የአቶ ኃይለማርያም
መንግስት ከምርጫው በፊት ሊመልሳቸው ይችላል
ወይ ብለህ ታስባለህ የሚል ነው?
ታማኝ፡- በመጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም ራሳቸው
ይህን ለማድረግ አቅም አላቸው ወይ? የሚለውን
ጥያቄ ማየት ያስፈልጋል። አሁን እኮ ተሰብስበው
የወሰኑትን ነው አቶ ኃይለማርያም ወጥተው
የሚነግሩን። የለውጡ ነገር ከራሳቸው ሰብዕና
ይመጣል ወይ? ለሚለው ጥያቄ፣ የእኔ ምላሽ
አይመስለኝም የሚል ነው። ሌላው ይቅርና በቃላት
ደረጃ እንኳን፣ አቶ መለስ ያሉትን የሚደግሙ
ሰው ናቸው’ኮ። አቶ መለስ በአንድ ወቅት ‹‹የስኳር
ዋጋ የጨመረው፣ በስኳር የሚጠጣ ገበሬ ቁጥር
ስለጨመረ ነው›› ብለው ነበር። አቶ ኃይለማርያምም
ስለጤፍ ዋጋ ሲጠየቁ፣ ‹‹ጤፍ በልቶ የማያውቀው
ገበሬ፣ ጤፍ መብላት በመጀመሩ ነው›› ሲሉ መለሱ።
ሶስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮችና አስራ ምናምን
አማካሪ ያላቸውን ሰው፣ እንዴት በራሳቸው ለመወሰን
የሚያስችል አቅም ይኖራቸዋል ብለን እንገምታለን?
የጨፈለቋቸውን መብቶች ለኢኮኖሚያዊ እርዳታ ሲል
ህወሓት ራሱ ማሻሻያ ሊያደርግ ይችላል እንጂ፤ ከአቶ
ኃይለማርያም ምንም ይመጣል ብዬ አልጠብቅም።
ፋክት፡- ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ፣ መሬት
ከኢትዮጵያ ተወስዶ ወደ ሱዳን ሊጠቃለል ነው
የሚል ዘገባ እየሰማን ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ አንተ
የምታውቀው መረጃ አለ?
ታማኝ፡- እዚህ ሀገር በተለያዩ ባለሙያዎች
የተዋቀረ ‹‹የድንበር ኮሚቴ›› የሚባል አለ። እነርሱ
የሚያወጡት መረጃ አለ። የሱዳን የመገናኛ ብዙሃንም
ያወጧቸውን ዘገባዎች ተከታትያለሁ። በዚያው
አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በስልክ ሲጠየቁ
የሰማሁት አለ። ከዚህ ሁሉ በፊት ግን የህወሓትን
ተፈጥሯዊ ባህሪይ ካየህ፣ መሬቱ የማይሰጥበት
ምንም ምክንያት አለመኖሩን ትረዳለህ። ያኔ ‹‹ባድመ
ተወረረች›› ብለው የዛን ሁሉ ኢትዮጵያዊ ደም
አፈሰሱ። ገፍቶ ሊሄድ ይችል የነበረው ሰራዊት፣
በአቶ መለስ ትዕዛዝ እንዲቆም ተደረገ። ጄንዳይ
ፍሬዘርም በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ቀርባ፣ ‹‹አቶ መለስ
ጄነራሎቹ ፊት ቆሞ፣ ጦርነቱን ያስቆመ ጀግና ነው››
ብላ ስትናገር ነበር። ከዚያም ወደ አልጀርስ ሄደው
ያለምንም ጠያቂ ተፈራረሙ። አንድም ኢትዮጵያዊ
ባለሙያ በሌለበት ፍርድ ቤት ተስማሙ። አቶ ስዩም
መስፍንም ‹‹ባድመም የእኛው ነች›› ብለው ነገሩን።
ይኸው እስከአሁን ድረስ ግን ባድመ የለችም።
ታዲያ እነዚህ ሰዎች በምን መለኪያ አያደርጉትም
ብለህ ታምናለህ? ስለአሰብ ወደብ ምን እንደሚሉ
ትሰማለህ? ‹‹የኤርትራን ሉዓላዊነት የሚቀናቀን ካለ
እኛም እንዋጋዋለን›› እያሉን ነው። ይህን ለመገመት
መማርና መመራመር አያስፈልግም።
ሰው እንዴት ሁልጊዜ
በአሸናፊነት ትዕቢት ውስጥ
ይኖራል? እናም፤ እስከመቼ
ነው እንዲህ እየሆናችሁ
የምትቀጥሉት? እስከመቼስ
ነው በዚህ ጥላቻ የምትኖሩት?
እስከመቼስ ጀግና ከእኛ ውጪ
የለም ብላችሁ ታስባላችሁ?
ያኔ አዲስ አበባ ስትገቡ
የነበራችሁ ጉልበት እንኳን ዛሬ
የለም። ከእድሜ ጋር ስኳርና
ደም ብዛትም ይመጣል።
“ከአሜሪካ በላይ፣...ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006 25
ፋክት፡- በቅርቡ የአሜሪካ ኮንግረስ “Bill 2014”
የሚባል ሕግ አፅድቋል። ይህ ውሳኔ የዲያስፖራው
እንቅስቃሴ ውጤት ነው ማለት ይቻላል?
ታማኝ፡- ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ ኮንግረሱን ሎቢ
(የሚወተውቱ) የሚያደርጉ ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን
ባለሙያዎች አሉ። በወርና በሁለት ወር ውስጥ
የሚሰራ ስራ አይደለም። ዋናው ነገር ግን ይሄ
አይደለም። የጉዳዩ ባለቤቶች እኛ ሆነን ሳለ፣ ከሌሎች
መጠበቃችን የሚያሳስብ ነው። አንድ መንግስት
አምባገነንም ሆነ ፋሽስት፣ አገር እንደአገር መቀጠሉን
በቅድሚያ ያያል። የትኞቹም መንግስታት ብሄራዊ
ጥቅም የሚሉት ጉዳይ አላቸው። ዴሞክራሲና
ሰብዓዊ መብት ከዚያ ቀጥሎ በሁለተኝነት የሚታይ
ነው። በእርግጥ በህጉ መፅደቅ ላይ የዲያስፖራው
ቀጥተኛ ተሳትፎ አለ። የዲፕሎማሲው ስራ ከዚህ
በፊት ሲሰራ ነበር፤ ወደፊትም ይሰራል። ግን
ከአሜሪካ ተፅዕኖ በላይ፣ እኛው ባለቤቶቹ ራሳችን
ተፅዕኖ መፍጠር አለብን የሚል እምነት አለኝ።
ፋክት፡- የህዳሴውን ግድብ በሚመለከት
የዲያስፖራው አቋም ምን እንደሚመስል ልትነግረን
ትችላለህ?
ታማኝ፡- ይኸውልህ፤ እዚህ ግራና ቀኙን
የምትመረምርበት እድል አለ። የምንኖረው
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን እያየንና የመንግስት
ፕሮፓጋንዳን ብቻ እየሰማን አይደለም።
እንደምራለንም፤ እንቀንሳለንም። በዙሪያ ባሉ
ጠላቶች በአይነ-ቁራኛ የሚታይ ይሄን መሰል
ፕሮጀክት መገንባት የነበረበት፣ የጠበቀ አንድነት
በፈጠረ ማህበረሰብ መካከል ነው። ከኢትዮጵያ
ህዝብ በተሻለ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ የሚገኘው
ዳያስፖራ፣ ይህን ግድብ ለመስራት ፈቃደኛ
ነው። ውጪ ያለውን ሰው በቀላሉ ልታታልለው
አትችልም። ሊታሰርበት የማይችልበት ቦታ
ስለሚኖር ሀሳቡን በነፃነት ይገልፃል። ከዚያ በፊት ግን
የሚስተካከሉ ጉዳዮች ሊኖሩ ይገባል። መጀመሪያ
አንድ ለአምስት የተቆለፈውን ህዝብ መፍታት፣
ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር ያስፈልጋል። ይህ
ከሆነ መንግስት ካሰበው በላይ ሊያደርግ የሚችል
አቅም ዲያስፖራው ዘንድ አለ። ይሄ መልስ ካላገኘ
ዲያስፖራው እድሜ ማራዘሚያ ሊሆን አይችልም።
በአባይም ጉዳይ ያለው ክርክር ይሄው ነው። የዜጎች
መብት በቅድሚያ መከበር አለበት። ስለኢትዮጵያ
ሲሉ የፃፉ፣ ስለኢትዮጵያ ሲሉ የታሰሩ መፍትሄ
ከተገኘላቸው፣ በአባይ ጉዳይ የማንስማማበት ምንም
ምክንያት የለም። ይሄ የዲያስፖራውም፣ የእኔም
አቋም ነው።
ፋክት፡- የአቶ ሌንጮ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ
በዲያስፖራው በኩል እንዴት እየታየ ነው?
ታማኝ፡- በእርግጥ ከዚህ በፊት ለውጥ እናመጣለን
በሚል ሀገር ቤት ከገቡ በኋላ፣ ለህወሓት እጅ የሰጡ
ብዙ እንዳሉ እናውቃለን። እኔ በግሌ፣ ራሴን ጨምሮ
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደሀገር ቤት መግባት
አለበት ብዬ አምናለሁ። ነገር ግን ማንም የኢቲቪ
የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ መሆንን አይፈልግም።
የሌንጮ መግባት በዲያስፖራው ፖለቲካ ላይ ያን
ያህል ተፅዕኖ ይፈጥራል ብዬ አላስብም።
ፋክት፡- ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን በአካል
አግኝተሀቸው ታውቃለህ? ካገኘሀቸውስ ምን
አውርታችኋል?
ታማኝ፡- አንዴ ከህዝብ ለህዝብ ስንመለስ አግኝቼ
ጨብጬያቸዋለሁ። ከዚያ ውጪ ጥላሁን ገሰሰ ታሞ
ደቡብ አፍሪካ ልጠይቀው በሄድኩ ጊዜ፣ ባጋጣሚ
ደውለው አለምፀሀይ ወዳጆንና ንዋይ ደበበን ካነጋገሩ
በኋላ እኔም አግኝቼያቸዋለሁ። ሳገኛቸውም፣
ለምን ያለፉበትን ታሪክ አይፅፉም ስላቸው፣ በ3
ቅፅ የሚወጣ መጽሐፍ እያዘጋጁ እንደነበር ያኔ
ነግረውኛል።
ፋክት፡- ከኢህአዴግ ባለስልጣናትስ ማንን አግኝተህ
ታውቃለህ?
ታማኝ፡- አቶ ታምራት ላይኔ ከእስር ተፈተው፣
ከሀገር ቤት ከወጡ በኋላ አግኝቼያቸዋለሁ። እኔ
በግሌ ብዙ መከራ ያየሁት ከርሳቸው ስም ጋር
በተያያዘ ነው። እንደው ብሄርተኛ ነህ እንዳልባል
እንጂ፣ እርሳቸው ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ
አማራ የሚባለው ህዝብ ብዙ መከራን አሳልፏል።
እና በእርሳቸው ላይ ጥያቄ ነበረኝ። ይሁንና ባንድ
አጋጣሚ አንድ ጓደኛዬ ቴዲ አፍሮን እስር ቤት
ሊጠይቀው ሄዶ፣ ‹‹ታምራት ላይኔን አየዃቸው።
ያሳዝናሉ፣ የሚጠይቃቸው ሰው የለም›› ሲለኝ፤
እንደው ባክህ ከቻልክ ገንዘብ ስጥልኝ አልኩት።
የነገርኩት ልጅ፣ ፈርቶ ነው መሰለኝ ብሩን ሳይሰጥ
ቀረ። እኚህ ሰው ስንት አመት ታግለው በራሳቸው
ሰዎች ታስረዋል። ይሄ ጭካኔ ነው።
ሆኖም እዚህ ሀገር እንደመጡ፣ አንድ ቀን ስልኬ
ጠራና አንስቼ ‹‹ማን ልበል?›› ስል፣ ‹‹ታምራት
ላይኔ ነኝ፤ በጌታ ስም ይቅር በለኝ፤ ይቅር ካላልከኝ
አልቀመጥም!›› አሉኝ። ‹‹እኔ እኮ ቀድሞ ነው ይቅር
ያልኮት። ከእኔ ይልቅ በእርሶ ትዕዛዝ የተገደሉትና
ወደእስር የተወረወሩት እንዴት ነው ይቅር
የሚሎት?›› ስላቸው፤ ‹‹ሁሉም በጊዜው ይሆናል››
ብለውኝ እንድንገናኝ ቀጠሮ ያዝን። ከዚያም ለቪኦኤ
ቀርበው፣ ለእኔ ከተናገሩት በተቃራኒው አወሩና
ቅሬታ ገባኝ። ከዛ በኋላ ተገናኝተንም፣ አውርተንም
አናውቅም።
ፋክት፡- በቀጠሮውስ አልተገናኛችሁም?
ታማኝ፡- ደውለውልኝ ነበር። እኔ ግን ፈቃደኛ
አልሆንኩም።
ፋክት፡- ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ምን
ትመክራቸዋለህ?
ታማኝ፡- አንድ ጊዜ አውራምባ ታይምስ የሚባል
ጋዜጣ ላይ ይህንኑ ጥሪ አቅርቤ ነበር።
ፋክት፡- እሺ! እዛ ላይ ከመለስከው ልንዘለው
እንችላለን።
ታማኝ፡- ኖ… ኖ… ኖ! ስለመለስኩት አይደለም።
ያኔ ካልኩት፣ አሁንም የምደግመው አለ። ስብሃትን
አንዳንዶች ‹‹አቦይ›› ይሏቸዋል፤ ይህ በትግራይ
ለሚከበር አባት የሚሰጥ ስያሜ ነው። የእርሳቸው
ንግግር ግን የሚያስከብር አይደለም። ቀድሜ እኔ
ልሞት ብችልም፣ ከእድሜ አንፃር ካየነው ግን
እርሳቸው ይቀርባሉ። ሌሎቹንም ብታያቸው
የጉርምስና እድሜያቸው በጫካ አልፏል። ነገር ግን
ዛሬም ድረስ በጥላቻ ውስጥ ናቸው። አንዳንዴ፣
እንዴት ለልጆቻቸው አያስቡም? ስል አስባለሁ።
ሰው እንዴት ሁልጊዜ በአሸናፊነት ትዕቢት
ውስጥ ይኖራል? እናም፤ እስከመቼ ነው እንዲህ
እየሆናችሁ የምትቀጥሉት? እስከመቼስ ነው በዚህ
ጥላቻ የምትኖሩት? እስከመቼስ ጀግና ከእኛ ውጪ
የለም ብላችሁ ታስባላችሁ? ያኔ አዲስ አበባ ስትገቡ
የነበራችሁ ጉልበት እንኳን ዛሬ የለም። ከእድሜ ጋር
ስኳርና ደም ብዛትም ይመጣል። ልጆቻችሁስ በሌላው
ህዝብ እየተወደዱ የሚኖሩ ናቸውን? ልጆቻችሁ
ከሌሎች ልጆች ጋር ተቀላቅለው መጫወት ይችላሉ
ወይ? ብዬ ልጠይቃቸው እፈልጋለሁ።
የእስክንድርና የሰርካለም ልጅ በእስር ቤት
ነው የተወለደው። በዚህ ላይ የአባትነት
ፍቅሩን ቀምታችሁ በለጋ እድሜው እንዲሰደድ
አድርጋችሁታል። የእነበቀለ ገርባ እና የእነውብሸት
ልጆችስ? ምን እያፈራችሁ ነው? በእያንዳንዷ
የሀገሪቱ ክፍል የሚቃትቱና፣ እህ… የሚሉ ህፃናት
በዝተዋል። በአንድ ወቅት ጋሽ መስፍን የተናገረውን
አስታውሳለሁ፤ ‹‹ይሄ መንግስት ከሶስት ትውልድ
ጋር የተጣላ ነው›› ብሎ ነበር። ከብርቱካን፣
ከብርቱካን እናት እና ከልጇ ጋር ተጣልቷል ለማለት
ፈልጎ ነው። ይታያችኋል ወይ? ጋዳፊን አላያችሁም
ወይ? ግዴላችሁም፣ ሌላውን ብትጠሉት እንኳን
ለልጆቻችሁ ስትሉ፣ እባካችሁ ይህን አድርጉ ነው
የምለው። ሰምተኸኛል?
ፋክት፡- አዎ! ሰምቻለሁ!
ታማኝ፡- ቄስ ሆንኩብህ እንዴ?
ፋክት፡- አይ በፍፁም! በፍፁም! እንቀጥል። ለረዥም
አመታት በአክቲቪስትነት ለሀገርህ ተጋድሎ
አድርገሃል። በዚህ ሂደት ውስጥ ስታልፍ ምን
አሳክቻለሁ? ምንስ አጥቻለሁ ብለህ ታስባለህ?
ታማኝ፡- ትርፍ ሲባል…?
ፋክት፡- የተነሳህለትን አላማ ከዳር ከማድረስ አኳያ
ማለቴ ነው፤
ታማኝ፡- አሁን እንግዲህ፣ እንዴት መሰለህ
ነገሩን የማየው? ይሄ ንግድ አይደለም። ይሄ
ኢትዮጵያዊነትን የያዘች ልብ እንዳትሞት የሚደረግ
ጥረት ነው። አለም እያየ የሞሶሎኒ ፓይለቶች
ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ ፈጅተዋል። ከነርሱ
ጋር መስዋዕትነት ሲነፃፀር የኔ ተግባር ቅንጦት
ነው። የምለውም ሀሳብ ውሸት እንዳልሆነ በአይኔ
እያየሁ ነው። በኪነ-ጥበብ ህይወቴ የተለያዩ አገራት
ዞሬያለሁ። የማከብራቸው የጥበብ ሰዎች እነ
ጥላሁን ገሰሰ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን እና ወጋየሁ
ንጋቱ የቆሙበት መድረክ ላይ ቆሜያለሁ። የህዝብ
ለህዝብ ጊዜ አገሬን ልክ እንደ ኳስ ተጫዋቾቹ፣
በማልችለው ቦታ ሁሉ ተሰልፌ የተሰጠኝ ተልዕኮ
አሳክቼ ተመልሼያለሁ። ለኔ በሙያ ደረጃ ይኼ
ትልቅ ስኬት ነው። አሁን በማደርገው ነገር ገንዘብ
ላላገኝ ወይም በምቾት ላልደሰት እችል ይሆናል።
ነገር ግን ሰው እኔን እንደ ትልቅ ሰው ቆጥሮ፣
በአክብሮት ከመቀመጫው ተነስቶ ሲቀበለኝ ሳይ፣
ለዓላማዬ ክብር እንዳለው ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸው
የሚቆረቆሩ ሰዎችን እንዳፈራው ያመላክተኛል።
የህዝብ አደራን መሸከም ከባድ ነው። መልሱ እንዲህ
በፍቅር ሲሆን እጅግ በጣም ያበረታል። ይህን በብር
አትገዛውም። ልጆቼ በኔ ምክንያት አይሸማቀቁም።
‹ሕግ ኢትዮጵያ ውስጥ ይስራ› ይል ነበር አባታችን
ማለታቸው አይቀርም።
ፋክት፡- በምታራምደው አቋም የተነሳ አጣሁት
የምትለው ነገር አለ?
ታማኝ፡- ገንዘብ ብቻ ነው ያጣሁት… (ሳቅ)
በተረጋጋች እና ሕግ በሚከበርባት ሀገር ማንኛውንም
ስራ ሰርቼ ገንዘብ ላገኝ እንደምችል እርግጠኛ ነኝ።
ፋክት፡- እኔ ጥያቄዎቼን ጨርሻለሁ። ቀረ የምትለው
ነገር ካለ እድሉን ልስጥህ?
ታማኝ፡- ብዙ ጊዜ ስለዲያስፖራው ሲነገር
የምሰማቸው ነገሮች አሉ። ‹‹ሰው ሊያስጨርሱ ነው››
እየተባለ ይወራል። ሰው በማለቁ ምን እናተርፋለን?
እኔ በህይወቴ ሙሉ የፓርላማ አባልም ሆነ
ሚኒስትር የመሆን ህልም ኖሮኝ አያውቅም። ሰው
ለማስጨረስ የሚሉት ሰዎች፣ እግረ መንገዳቸውን
ሰው የሚጨርስ መንግስት እንዳለን እየነገሩን
ነው። ዲያስፖራው እንደዚህ አይነት ሀሳብ በፍፁም
የለውም። በሌላ በኩል ማንም ትርፍ ጊዜ የለውም።
ዝም ብሎ ኖሮና ብር አጠራቅሞ፣ ወደ ኢትዮጵያ
በመሄድ በደንብ ተዝናንቶ መመለስ ይችላል። እኛ
ሰዎች በነፃነት ወደ ሀገራቸው መሄድ አለባቸው
ብለን ስለምናምን ነው ይሄን የምናደርገው። እዚህ
ሀገር ትንሹ ክፍያ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ሚኒስትር
የተሻለ ነው። የኢትዮጵያ ባለስልጣን መሆን
ምንድን ነው የሚያጓጓው? ‹ለስልጣን ነው እንዲህ
የሚሆኑት› የሚባለውም ስህተት ነው። በየጊዜው
መንግስት እንዲህ አደረገን ማለት እራሱ ይሰለቻል።
በሌሎች ሀገራት ዜጎች ፊት ያሸማቅቃል። ዋናው
ነገር ይሄን ለመለወጥ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት
ኢኮኖሚው አደገ ሲል፣ ለዕድገቱ ከቡናና ከጫት
ንግድ እኩል የዲያስፖራውም አስተዋፅኦ አለበት።
ፋክት፡- ፋክት መጽሔት አንተን ቃለ-መጠይቅ
ለማድረግ ደጋግማ ደውላ ፍቃደኛ ከሆንክ በኋላ፤
ስልኩን ዘግተህ ራስህ በመደወል የዚህን ያህል ሰፊ
ማብራሪያ ስለሰጠኸን፣ በመጽሔቷ አንባብያን ስም
እጅግ አድርጌ ላመሰግንህ እፈልጋለሁ።
ታማኝ፡- ኧረ እኔ ነኝ የማመሰግነው። እንግዲህ
ይታይህ! እኔ አሁን በእነሱ መለኪያ አዝማሪ
ነኝ። ታዲያ! አዝማሪ ለምን ይፈራሉ? ባለፉት
23 ዓመታት ውስጥ የማስታውሰው፣ የጥበብ
ስራዬን አንድ ጊዜ ብቻ ማሳየታቸውን ነው። እሱም
ስራዬን ለማንቋሸሽ ሲሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
በ1985 ዓ.ም. ያሳዩት ነው። ከዚህ ውጭ በእዚህ
ሁሉ ዓመታት ውስጥ አንድም ቀን በኢትዮጵያ
ቴሌቪዥንና ራዲዮ ስራዎቼ ቀርበው አያውቁም።
ይህን የምልህ አነሰኝ ብዬ አይደለም። የሕዝብ
ቴሌቪዥን ከፍተን ቤታቸው ድረስ ገብቼያለሁ።
በዚህ እደሰታለሁ። ግን ምን ዓይነት መንግስት ነው
ሀሳብ የሚፈራ? እነርሱ ሀሳብ ያስፈራቸዋል። እናም
ይህን እድል ሰጥታችሁኝ፣ ህዝቡን እንዳገኝና ሀሳቤን
እንድገልፅ ስላደረጋችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ። □
ፋክት፡- ከሀገር ከወጣህ ምን ያህል ጊዜ ሆነህ?
ታማኝ፡- እንደው ይሄን ነገር ባልጠየቅ ደስ ይለኝ ነበር።
ምክንያቱም የወጣሁበት ቀን በረዘመ ቁጥር፣ ሀገሬ ላይ በጣም
ክህደት የፈፀምኩ ያህል ይሰማኛል። የግድ ነው ካልከኝ ልናገር፤
አሁን እንግዲህ አስራ ስምንት አመት ገደማ ሊሆነኝ ነው።
ፋክት፡- በጣም ሩቅ ነው። አንተ ከወጣህ በኋላ ያን ጊዜ የነበረውን
ችግር የማያውቅ አዲስ የመጣ ትውልድ አለ ማለት ይቻላል፤ እናም
ለነርሱ ግልፅ እንዲሆንላቸው፣ ከሀገር የወጣህበት ትክክለኛ ምክንያት ምን
ነበር? ታስታውሰዋለህ?
ታማኝ፡- እንዴ! በጣም ነው እንጂ የማስታውሰው። እንግዲህ በፈረንጆቹ
አቆጣጠር ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ወደ አሜሪካ እየመጣሁ፣
ስራ እየሰራሁ እመለስ ነበር። በምሰራው የኪነ-ጥበብ ስራም የተነሳ አራት እና
አምስት ወራት እየቆየሁ፣ የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ስራዬን አቅርቤ እመለሳለሁ።
ይሄ ማለት እንግዲህ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1988 ዓ.ም. ማለት ይመስለኛል።
እናም ምንም እንኳ እንደ ችግር ባልቆጥረውም፣ በነዚህ ጊዜያት በተለያዩ ችግሮች
ውስጥ አልፌያለሁ። አሁን የሚገዛው የወያኔ ስርዓት ወደ ስልጣን ከመምጣቱ
በፊት የነሱን ፕሮግራም በሬዲዮ ስከታተል፣ ስለኢትዮጵያ ያላቸውን እቅድ
ሲናገሩ በፍፁም ከኔ እምነት ጋር የማይሄድ ስለነበር፣ ባገኘሁት አጋጣሚ
ሁሉ የተቃውሞ ሀሳቤን ገልጬያለሁ። በዚያ ምክንያትም የተለያዩ
ችግሮች ደርሰውብኛል። ያም ሆኖ ግን ሀገሬን እለቃለሁ የሚል
እምነት አልነበረኝም። ለዚህም ነበር እስከ 1988 ዓ.ም. ድረስ
ወደ ሀገርቤት እየተመላለስኩ የኖርኩት። በዚህ መሀል
እንግዲህ ሀገር ቤት መድረኩን ሳገኝ በአብዛኛው እምነቴን
ነበር የምገልፀው፤ ወደ ኋላ ላይ መድረክ የማጣት፣
የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም
ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ
ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት
(ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን
አምባገነንነት፣ ከፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይ
ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም
ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና፣ እስርና
ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል።
በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን
የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ
ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና
እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል
ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ
የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል።
በዚህም በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ
ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል።
አክትቪስት ታማኝ በየነ፣ ከተመስገን
ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለ-መጠይቅ
እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
“ከአሜሪካ በላይ፣
ራሳችን ተፅዕኖ መፍጠር አለብን”
ታማኝ በየነፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006 19
የመከልከል፣ የምሰራው ነገር ማጣት አልፎም
ግርፋት እና እስራት ይደረስብኝ ጀመር። ይሄን
ጉዳይ እንኳ ባልናገረው እመርጣለሁ፤ ምክንያቱም
ለነሱ የደስታ ስሜት የሚፈጥርላቸው ይመስለኛል።
በጊዜውም ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ
እንቅስቃሴዎች የተገደቡ ነበሩ። እናም ብቸኝነት
ተሰማኝ። የመስራት አቅሜም ሆነ የህልውናዬ ነገር
አደጋ ላይ ሲወድቅ ወጣሁኝ፤ በቃ ይኼው ነው
ነገሩ።
ፋክት፡- ከጥቂት ዓመታት በፊት ባሰራጨኸው
አንድ ሲዲ ላይ፣ የኢህአዴግ ሰራዊት አዲስ አበባ
እንደገባ ዕለቱኑ ፓርቲውን ተችተህ ለሲ.ኤን.ኤን
ቴሌቭዥን የሰጠኸው ቃለ-ምልልስ ነበር። ያ ወቅት
የቀድሞ ስርዓቱ ዋነኛ ሰዎች እንኳን ሀገር ጥለው
የተሰደዱበት ከመሆኑ አኳያ፣ አዲስ አበባ ተቀምጠህ
በድፍረት ስትተቻቸው ፍርሀት አልተሰማህም ነበር?
ታማኝ፡- እንዴ! የምን ፍርሃት ነው? እነርሱ እኮ
አዲስ አበባ ሳይገቡ፣ ገና አምቦን ሲቆጣጠሩ እኮ ነው
የደርግ ስርዓት ከሞላ ጐደል መፍረስ የጀመረው።
እናም አገሪቷን በአግባቡ እያስተዳደሯት እንዳልሆነ
ሁሉም የተረዳበት ጊዜ ነበር። ያም ቢሆን ዋና
ከተማዋን ሊቆጣጠሩ 23 ቀን ሲቀራቸው፣ አዲስ
አበባ ስታዲየም ውስጥ በርካታ ድምፃውያን
የተሳተፉበት ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት አዘጋጅተን
ነበር። ያን ጊዜ ታዲያ በራዲዮናቸው በተለይም
ሰንደቅ አላማን በጣም ያንቋሽሹ ነበር፣ የዘመናት
ታሪካችንንም በስድብ ያጠለሹ ነበር። ይኼ ደግሞ
በጣም ያበሳጨኝ ነበር። በዚህም የተነሳ ሁላችንም
ሰንደቅ አላማ ለብሰን ድምፃችንን እናሰማ ብለን
መጀመሪያ በብሄራዊ ትያትር ቤት፤ በሳምንቱ
ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም እነ ጥላሁን ገሠሠ፣
መሀሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ታምራት
ሞላ፣ መልካሙ ተበጀ፣ አረጋኽኝ ወራሽ፣ ንዋይ
ደበበ፣ ፀሀዬ ዮሀንስ፣ ፀጋዬ እሸቱ፣ ቴዎድሮስ
ታደሰ… እና ሌሎች በጣም በርካታ ድምፃውያን
የተሳተፉበት ‹የኢትዮጵያ አርቲስቶች ለኢትዮጵያ
አንድነት› የሚል ሾው አዘጋጅተን ነበር። ኮ/ል
መንግስቱም ስልጣን ላይ ነበሩ፤ እንዳልኩህ ሰዎቹ
23 ቀን ብቻ ነው የቀራቸው። በዚያች ሰዓትም
ቢሆን ባለችው ቀዳዳ የደርግን ድክመት
ለመጠቆም ሞክሬያለሁ። ያኔ ፍርሃት
ሳይሆን የሀገሬ ሁኔታ ነበር የሚያሳስበኝ፤
እዚሁ ሆኜ ነው የገቡት። ፍርሃት የሚባል
ነገር አልነበረም። ይህን የምለው አሁን
ዳር ሆኜ ለመናገር ብዬ ሳይሆን፤ በዛን
ጊዜ የቀደሙ አያቶቼ የተሰዉላት ሀገር፣ በዛ ደረጃ
እየተንቋሸሸች ሞትን እንደ ሞት የምቆጥርበት
እድሜና ሁኔታ ላይ አልነበርኩም ለማለት ነው።
እናም ፍርሃት አልነበረብኝም።
ፋክት፡- የመፍራቱን ጥያቄ ያነሳሁት፣ ወቅቱ በጣም
አስፈሪ ስለነበርና እነሱም ከመግደል የማያመነቱ
ስለነበር ነው?
ታማኝ፡- ልክ ነው! እንዲያውም እኮ ይገርማል።
አሁን ባነሳሁት ትርዒት ላይ፤ ያው ራዲዮናቸውን
በየጊዜው እከታተል ስለነበረ በየተለያየ ጊዜ
‹‹ይሄን ያህል ሰራዊት ገደልን››፣ ‹‹ይሄን ያህል
ሰራዊት ገደልን›› የሚሉትን ደምሬ፤ እንዴት ነው
ነገሩ?! እነዚህ ሰዎች በሚሉት ሂሳብ ከሄድን እኮ
ከሚመጣው ትውልድ ሁለት ሚሊየን ተበድረን
ሞተናል ማለት ነው! የሚል ቀልድ ሰርቼ ነበር።
በማግስቱ ታዲያ ጠዋት ከበረሀ የሚያሰራጩትን
ራዲዮናቸውን ስከፍት፤ እንደማስታውሰው ሴኮ
የሚባለው ሰው ድምፅ ይመስለኛል፣ ‹‹አቶ ታማኝ!
ሂሳቡን እዚያው አዲስ አበባ ስንመጣ እንተሳሰባለን››
ብሎኝ ቀልድ ሰርቶብኛል። በዕርግጥ ያ ወቅት
መጥፎ ጊዜ ቢሆንም፣ ፍርሃት አልነበርም። በኔ
ውስጥ የነበረው ነገር፣ ያ ሁሉ መስዋዕትነት
የተከፈለላት ሀገር በዚህ ደረጃ ስትዋረድ፣ ስትሰደብ
መስማት ያማል! እናም የሀገር ጉዳይ ለድርድር
የሚቀርብበት ሰዓት አይደለም የሚል ነበር።
ፋክት፡- ከሀገር ከመውጣትህ በፊት በወቅቱ
የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ
ቢሯቸው ጠርተው አስፈራርተውኻል ይባላል፤ ይሄ
ምን ያህል እውነት ነው?
ታማኝ፡- አይ አይደለም፤ ጠ/ሚኒስትር ታምራት
ላይኔ አላስፈራሩኝም። ግን ያው ታዛዥ አሽከሮች
በየጊዜው… እንዲህ አይነት ጉዳዮችን መናገር
ስለሚያናድደኝ ነው። ኤግዚቢሽን ማዕከል ትርዒት
ነበር። እሱን ለማሳየት ሄጄ፤ ሁለት የደህንነት
ሰዎችና አንዱ ደግሞ የቡና ቤት ባለቤት የሆነ ሰው
እየደበደቡ ሲወስዱኝ፣ አክሊሉ የሚባል የማዕበል
ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ‹‹ለምን ትደበድቡታላችሁ?
እርሱ ምን አደረገ?›› ብሎ በመጠየቁ፣ አፉ ውስጥ
ሽጉጥ ደግነው ይደበድቡት ነበር። እኔንም ‹‹ታምራት
ላይኔን እንዲህ አድርገህ ተሳደብክ›› እያሉ፣ በጣም
መጥፎ ስድብ ይሰዱቡኝ ነበር። እኔም የሚሰማኝን
አንድ ቀን ስልኬ ጠራና አንስቼ ‹‹ማን ልበል?›› ስል፣ ‹‹ታምራት ላይኔ ነኝ፤
በጌታ ስም ይቅር በለኝ፤ ይቅር ካላልከኝ አልቀመጥም!›› አሉኝ። ‹‹እኔ እኮ
ቀድሞ ነው ይቅር ያልኮት። ከእኔ ይልቅ በእርሶ ትዕዛዝ የተገደሉትና ወደእስር
የተወረወሩት እንዴት ነው ይቅር የሚሎት?›› ስላቸው፤ ‹‹ሁሉም በጊዜው
ይሆናል›› ብለውኝ እንድንገናኝ ቀጠሮ ያዝን 20 ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006
እውነት ነገርኳቸው። በሌላ ጊዜ ደግሞ አዲስ አበባ
ስታዲየም የኤርትራ እግር ኳስ ቡድን ከቡርንዲ
ጋር ሲጫወት ‹‹ለምን ቡርንዲን ደገፋችሁ›› ተብለን
ተይዝን ኮልፌ ወስደው አስረውናል፤ እኔንም
‹‹ታምራት ላይኔን እንዲህ ብለህ፣ ታምራት ላይኔን
እንዲህ ተናግረህ› እያሉ ብዙ አሽከሮቻቸው እየመጡ
ይሰድቡኝ ነበር። ጉዳዩ እንዲህ ነው እንጂ፤ ራሳቸው
ጠ/ሚኒስትር ታምራት ላይኔ አላስፈራሩኝም።
ፋክት፡- የቡና ቤቱ ባለቤት ታጋይ ነው? ማለት
አብሮ በትግል ውስጥ የመጣ ነው? ወይስ ጉዳዩ
የሚመለከተው ሆኖ ነው?
ታማኝ፡- አይደለም። መርማሪውን ስለሚያውቀውና
የአንድ ሰፈር ልጅ ስለሆኑ፣ ነው ገራፊ ሆኖ
የመጣው በተቀረ፣ ምንም ሊመለከተው የሚያስችል
ሥልጣን አልነበረውም፤ ነጋዴ ነው።
ፋክት፡- በ1988 ዓ.ም. የአድዋ ድል ሲከበር
መኢአድ፣ አንድ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ ነበር።
በዚያ ሰልፍ ላይ በህዝቡ ግፊት ወደ መድረክ ወጥተህ
ንግግር አድርገህ እንደነበር አስታውሳለሁ። ሆኖም
ከዚያን ዕለት በፊት እንዳትናገር ማዕቀብ ተጥሎብህ
እያለህ፣ አንተ ግን ያንን ሰብረህ በመውጣት ቀስቃሽ
ንግግር አድርገሀል፣ ትክክል ነኝ?
ታማኝ፡- አዎ! ትክክል ነህ። ህዝብ በተሰበሰበበት
ምንም አይነት መድረክ ላይ እንዳልናገር ከመከልከሌ
በተጨማሪ፣ ብሄራዊ ቴአትር ቤት እንኳን
እንዳልገባ ለተወሰነ ጊዜ ታግጄ ነበር። ትዕዛዙ
የተላለፈው በወቅቱ በነበሩት የባሕል ሚኒስትሩ
አቶ ልዑለስላሴ ቲማሞ ነበር። በገዛ ሀገሬ
ሰው በተሰበሰበበት እንዳልናገር መደረጌ በጣም
ያሳዝነኛል። በጊዜው ሙሉጌታ ወልደየስ የሚባል
ኳስ ተጫዋች ለብሔራዊ ቡድናችን ሲጫወት
እግሩን በመሰበሩ፣ በብሄራዊ ቴአትር ለሕክምና
የሚሆን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ሲደረግ
እኔ እንዳልኖር ታስቦ ነበር። ሆኖም ግን ዝግጅቱን
ፖስታ ቤት አድርገን በዚያ ተገኝቼያለሁ። የአድዋ
በዓል በሚከበርበት ዕለትም እስካሁን ያላነበብኩትን
የሀገሬን ታሪክ በእነእንድርያስ እሽቴ ‹‹ምኒልክ
ከውጊያው ፈርቶ ይሸሽ ነበር›› በማለት ድሉን
የአድዋ ነዋሪ ብቻ በማድረግና፤ ቀሪው የኢትዮጵያ
ህዝብ እንዳልተሳተፈበት ለማስመሰል የተሞከረበት
መንገድ በጣም አስገራሚ ነበር።
መቼም ያ ሁሉ ነገር አልፎ፣ ዛሬ ለማውራት
መቻሉ ራሱ ይደንቀኛል። እንደዚህ አይነት
ሁኔታዎች ስለነበሩ፣ የአድዋ ድል የሚከበረው ደግሞ
አድዋ ላይ ነው በማለት፤ ከአዲስ አበባ እንዲወጣ
የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ
ላይ ነው፤ እኔም እንደማንኛውም ዜጋ ስሜቴን
ለመግለፅ የተገኘሁት። ነገር ግን ከጐኔ የተቀመጡና
ያዩኝ ሰዎች ‹‹ታማኝ ይኸውና፣ ታማኝ ይናገር፣
ግባ ታማኝ›› እያሉ ሲሉኝ ወጣሁና ተናገርኩ።
ፋክት፡- ከሀገር ሳትወጣ ከሚያያዙ ጉዳዮች ጋር
የመጨረሻ አንድ ጥያቄ ላንሳ። ያኔ ከሀገርህ
ተገፍተህ ስትወጣ፣ ኢህአዴግ ይሄን ያህል ዘመን
በስልጣን ላይ ይቆያል የሚል እምነት ነበረህ?
ታማኝ፡- ረጅም ሳቅ… ኧረ! እንደውም በጭራሽ!
አሁንማ፣ እየቆዩ ሲሄዱ እኮ ለመድናቸው።
ፋክት፡- እዚያ ድምዳሜ ላይ ደርሰህ የነበረው፣
ጠንካራ ተቃዋሚ በመኖሩ ነበር? ወይስ ሌላ
የተማመንክበት ኃይል ነበር?
ታማኝ፡- አይ! በፍፁም አይደለም! ምንድነው
የሚባለው፣ ዘይትና ውሃ ይሉት ነገር የለም?
የኢትዮጵያ ህዝብና እነሱ ዘይትና ውሃ አይነት
ነበሩ እኮ። የተንሳፈፉ ነበሩ። አዲስ አበባ ስታዲየም
ኳስ ልናይ ስንገባ፣ እነሱ ያዘጋጁት አዲሱ ብሔራዊ
መዝሙር ሲዘመር፣ ሰዉ ተቃውሞውን ለማሰማት
የድሮውን መዝሙር ነበር የሚዘምረው። ኢትዮጵያዊ
የሚል መንፈስ በውስጣቸው ስለሌለ፣ የትኛውም
ባለስልጣን አዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ንግግር
ማድረግ እስከማይችልበት ደረጃ ድረስ ተደርሶ ነበር።
ከህዝቡም የተነጠሉ ነበሩ። በየትኛውም አቅጣጫ
ብትሄድ፣ ለምሳሌ ዘመን መለወጫ ሲከበር፣ ሰንደቅ
አላማ ይዞ የቆመ ሰው ከተገኘ ሰዉ እንደጉድ
ተነስቶ ይሸከመው ነበር። በሁሉም አቅጣጫ ህዝቡ
ይቃወማቸው ነበር። እንግዲህ ያንን አስተባብሮ
የሚመራ ሀይል ባለመኖሩ እንጂ፣ ኢህአዴግ ይህን
ያህል ዘመን ሊከርም አይችልም ነበር።
ፋክት፡- አሁን ወዳለህበት እንምጣና፤ በዲያስፖራው
በኩል በድጋፍም፣ በተቃውሞውም ያለውን ጎራ
እንዴት ትገልፀዋለህ?
ታማኝ፡- በዲያስፖራው በኩል አንድ መታወቅ
ያለበት ነገር፣ እዚህ ያለው የውጭ ሀገር ህይወት
እንደ ኢትዮጵያ አለመሆኑ ነው። ሁሉም ነገር
ከሰዓት ጋር የተያያዘ ነው። ኑሮ በሰዓት የተወጠረ
ነው። ቤተሰብ ካለ፣ ልጆች ካሉ ደግሞ የበለጠ ከባድ
ይሆናል። ምንም ፋታ የለህም። እንደ ቅዳሜና እሁድ
ያሉ የዕረፍት ቀንናት እንኳ፣ ይዘው የሚመጡት
የቤት ስራ አላቸው። በግልም ሆነ በማህበራዊ
ህይወት የምትወጠርበት ሁኔታ ነው ያለው። በዚህ
ውጥረት መሀል አዕምሮህ ይበልጥ የሚሰፋበት፤
ውሻና ድመት እንኳ መብታቸው የሚከበርበትን
ሁኔታ እያየህ፣ እንዴት ከውሻ ያነሰ ኑሮ እኖራለሁ?
በሚል ጥያቄ አዕምሮህ የሚፈተንበት ነው። እናም
ዲያስፖራው በዚህ ሁሉ ውጥረት መሀል እንቅልፍ
አጥቶ ሀገር ቤት ያለው ወገን ይህንን መብት
እንዲያገኝ እና ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሰረት
እንዲፈጠር ጥረት እያደርገ ነው። እንዳለመታደል
ሆኖ ግን፣ የመንግስት ደጋፊዎች የምትላቸው
እንዲህ አይነት ሀገር ውስጥ እየኖሩ፣ ኢትዮጵያ
በዘረኞችና በአምባገነኖች ስትመራ እያዩ፣ ልክ ነው
ብለው መደገፋቸው ግራ ከማጋባቱም በላይ በጣም
ያሳዝናል። ነፃ ሀገር ላይ ያለውን መመዘኛ እያዩ፣
በነፃነት የደረሱበትን የእድገት ደረጃ እየተመለከቱ፤
ለኢትዮጵያ ግን ይህንን ኋላቀር፣ ዘረኛ እና አፋኝ
ስርዓት ደግፈው ሲቆሙ ስታይ ግራ ይገባኻል።
በደጋፊና በተቃዋሚ መካከል ያለውን ልዩነት፣ እኔ
እንደዚህ ነው የማየው።
ፋክት፡- በዲያስፖራው ውስጥ ዘርን መሰረት ያደረገ
መከፋፈል አለ የሚለውን አባባል ትቀበለዋለህ?
ታማኝ፡- ምንም ጥያቄ የለውም። መሰረታችን
ኢትዮጵያ ነው። አንዳንዴ ወደ ሀገሩ ተመልሶ
ቤተሰቡን ጠይቆ መምጣት የሚፈልግ ሰው አለ።
ወደ ሀገር ቤት እንድትገባ ሲደረግ ደግሞ፣ ዘርህ
ከግምት ውስጥ ይገባል። ስለዚህ ነገሮችን በዚያ
መነፅር የሚመለከቱ አሁንም አሉ። ስለኢትዮጵያ
ተብሎ የልማት ጥሪ አትጠራም። የምትጠራው
የአማራ፣ የትግራይ፣ የጉራጌ፣ የደቡብ ተብሎ ነው።
ኤምባሲው እንኳ፣ በኢትዮጵያዊነት ለማሰባሰብ
የሚያስችል አቅም የለውም። ለምሳሌ በየአመቱ
ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት፤ ስደተኛው ራሱ
ያቋቋመው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አለ። እሱን
ለመቃረን ‹የትግራይ ፌስቲቫል፣ የኦሮሞ ፌስቲቫል›
የሚባሉ ተፈጥረዋል። ይሄ የሚያሳይህ ስርዓቱ
ያመጣብንን ችግር ነው። ቢሆንም ግን፣ አሁንም
በኢትዮጵያዊነታቸው ፀንተው የሚደክሙ፣ ፀንተው
እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሰዎች አሉ።
ፋክት፡- ስርዓቱ ካመጣው ተፅዕኖ ባሻገር፣
በዲያስፖራ ውስጥ የትግራይ ተወላጆችን ከስርዓቱ
ጋር አያይዞ ያለማመን ወይም የማግለል ሁኔታ
ይታያል፤ ይሄንን እንዴት ታየዋለህ?
ታማኝ፡- በበኩሌ ማግለል የሚለውን አላምንበትም።
ምን አቅም አለን ለማግለል? ኢትዮጵያ ውስጥ ብትሆን
ደህንነቱን፣ ፖሊሱን ተጠቅመህ ታገልላለህ። እዚህ
በምን ተጠቅመህ ታገልላለህ? ጥያቄው የተሰራውን
የመከፋፈያ ድልድይ ሰብሮ የመምጣት ጉዳይ ነው።
መንግስትን መቃወም ትግራይን እንደመቃወም
አድርገው የሚቆጥሩ አሉ። በቁጥር ብዙ ባይሆኑም
እንኳን በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ፣ ይሄን
ግንብ አፍርሰው የተቀላቀሉ የትግራይ ልጆች
አሉ። ስለዚህ ጥያቄው መዞር ያለበት፣ አሜሪካ
ውስጥ እየኖሩ የልዩነት ድልድይ ሰርተው፣ እኛ
እንደዚህ ነን ብለው ወደ ተቀመጡት ነው። ከዚህ
በቀር እኛ በምን አቅማችን ነው የምናገልላቸው?
ስርዓቱ ‹‹በዚህ በዚህ ልክ አይደለም›› ስትል፣ አይ
የትግራይን ህዝብ መቃወም ነው የሚሉ ካሉ፣ ይሄ
የነርሱ ችግር ነው የሚሆነው።
ፋክት፡- ከዚህ ቀደም በተቃውሞው ጎራ የነበሩ
አንዳንድ ግለሰቦች ወደ ኢህአዴግ ሲገቡ፤
‹‹የትግራይ ተወላጅ በመሆኔ ብቻ ተገፋሁ፣ ልታመን
አልቻልኩም፤ ትግሬ በመሆንህ ብቻ ብትቃወምም
የሚያምንህ የለም›› ሲሉ ይደመጣልና፤ ከዚህ አኳያ
ነው ጥያቄውን ያነሳሁት…
ታማኝ፡- እንዲህ ብለው የሚያምታቱ ሊኖሩ
ይችላሉ። ግን ስንት አመት ነው በዚህ ካርድ
መጫወት የሚቻለው? በዚህ ጉዳይ ላይ የሚጋጩ
ሁለት ነገሮችን ላንሳ። ይኼ መንግስት ራሱ
እንደሚያውጀው፤ መንግስታዊ አወቃቀሩ በብሄር-
ብሄረሰቦች መልካም ፈቃድ የተመሰረተ እስከሆነ
ድረስ፣ ለምንድነው የትግራይ ብቻ ተብሎ
የሚጠራው? በትግራዋይነቴ እንዲህ ተደረኩኝን
ምን አመጣው? እዚህ መንግስት ውስጥ ለምን
የሁሉም ብሄረሰቦች ድምፅ አይኖርም? ለምንድን
ነው ስለትግራይ ህዝብ ብቻ የሚባለው? ስለዚህ
ይሄን ጥያቄ የሚያነሱት እነሱ ብቻ ናቸው። እኔ
ተነስቼ በምናገረው ሀሳብ መጠየቅ ወይም መከሰስ
ያለብኝ በታማኝነቴ ነው። እኔ የተወለድኩበት
የጎንደር ህዝብ ሊጠየቅ ይችላል እንዴ? ለምንድን
ነው ይሄ ዓይነት አስተሳሰብ የሚመጣው? ስለዚህ
በጥቂት የብሄሩ ተወላጆች የተያዘ ቡድን ትክክል
ነው ብለው የሚከራከሩ እና እኛ ካልገዛን ብለው
የሚያምኑ ሰዎች አሉ፤ ስርዓቱን መቃወም
ከትግራይ ህዝብ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር
የለም። ስርዓቱ እንደ ስርዓት እኛን እየበደለን ነው
ስንል፣ በፀረ-ትግሬነት ይኮንኑሀል። ለምሳሌ የአስራ
አራት አመት ህፃን የገደለ ስርዓትን፣ ‹ለምንድን ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006 21
ነው ህፃናትን የምትገድለው?› ብለህ ስትጠይቅ፣
የትግራይን ህዝብ ስለምትጠላ ነው ብሎ መመለስ፣
ከጥያቄው ጋር እንዴት ሊገናኝ ይችላል? እንዲህ
እያሉ ማስፈራራት መቆም አለበት። አንተ ይሄን
ቃለ-መጠይቅ እስክታደርግልኝ ድረስ ይሄ ካርድ
ማስፈራሪያ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ባለፉት 23
አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ እንዲህ አይነት
ቃል ተናገረ የሚባል ሰው ሰምተህ ታውቃለህ?
በኦዲዮ፣ በቪዲዮ፣ በምስል ወይም በፅሁፍ የተነገረ
አንድም አታገኝም። በሥርዓቱ ድብቅ ሴራ ግን
ብዙ ገበሬዎች፣ ዘራቸውንና እድሜያቸውን መናገር
የማይችሉ ህፃናቶች ኢትዮጵያ ውስጥ አልተገፉም
እንዴ? ባለፈው ሳምንት የአማራ ክልል ም/
ፕሬዝዳንት በአደባባይ የአማራን ህዝብ ‹‹ለሀጫምና
ልጋጋም›› በሚል ፀያፍ ቃል አልተናገረም? እስቲ
ልክ እንደዚህ በትግራይ ህዝብ ላይ በዚህ ቀን፣
በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ነገር ብሏል የሚባል
ሰው ታመጣለህ? የለም! እንዲህ ዓይነቶቹን ነገሮች
የፕሮፓጋንዳ ማሽኑ የሚያነሳው፣ የተቃውሞው
ጎራ የሚጠይቀውን መሰረታዊ ጥያቄ ለመድፈን
እንዲያስችለው ነው። በእኔ በኩል፤ ሁላችንም ዘራችን
ሳይጠየቅ፣ በሕግ ፊት በእኩልነት የምንኖርበት
ሀገር ትምጣ እያሉ መጮህ፣ ለምን ፀረ-ትግራይነት
ተደርጎ እንደሚቆጠር መልስ የማላገኝለት ጥያቄ
ነው።
ፋክት፡- ይህንን ምክንያት የሚያነሱትን ሰዎች፣
የፖለቲካ ማጭበርበር የሚፈፅሙ አድርገን ማለፍ
እንችላለን?
ታማኝ፡- ምንም ጥያቄ የለውም። ለዚህም ነው
‹‹ስርዓቱን አትንኩት›› ሲሉን፤ የምንነካው በዚህ
በዚህ ምክንያት ነው ስንላቸው የሚያኮርፉት። እነሱ
ያለቻቸው ብቸኛ ካርድ ‹‹ትግራይ፣ ትግራይ…››
እያሉ መጮህ ብቻ ነው። ይኼ ምክንያት በቅጡ
መመርመር አለበት። ሰው ከመሬት ተነስቶ
ትግራይን የሚጠላበት ምክንያት ምንድን ነው?
በድህነት አብረን እኩል ተቸግረን ነው የኖርነው።
ታዲያ ከኢትዮጵያ ህዝብ በምን ስለተለዩ በተለየ
መንገድ ትጠላቸዋለህ? ሊጠሉበት የሚችሉበት
ምክንያት ነው ያልገባኝ! እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ
የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር
ችግሩን፣ መከራውን፣ ደስታና ሀዘኑን ተካፍሎ
ኖሯል። እንዴት ከ83 በኋላ በድንገት ጥላቻ ሊከሰት
ይችላል? ለዚህ ጥያቄ የሚያቀርቡት መልስ ‹ስልጣን
ስለያዝን ነው› የሚል ነው።
ከዚህ በተጨማሪም፤ እኛ ከዚህ በፊት ስልጣን
ይዘን ነበር፣ ከስልጣናችን ተባርረን የነበርን ሰዎች
ነን ይሉናል። ይኼ ሁሉ ተቃዋሚ በፀረ-ትግራይ
ስም ነው የሚንቀሳቀሰው ማለት ምን ማለት ነው?
ወይም በሳይንስ የተደገፈ ለተቃውሞው መነሻ
የሚሆን የተሰራ የላብራቶሪ ውጤት ካለ ይንገሩን።
ከዚህ ባለፈ ‹ዝም ማሰኘት የሚቻለው በዚህ መንገድ
ነው› ካልተባለ በስተቀር፣ ጥላቻን በፕሮግራም ፅፎ፣
አንድን ህዝብ እንደጠላት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለ፣
ከህወሓት በቀር ሌላ ድርጅት አላውቅም። እናም
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የህወሓትን ዕኩይ ተግባር
ለኛ መስጠት ከወንጀልም በላይ ወንጀል ነው።
ፋክት፡- አሁን በኢትዮጵያ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ
ትክክለኛ መረጃ አለኝ ብለህ ታስባለህ?
ታማኝ፡- ከናንተ በተሻለ መረጃ አለኝ ብዬ
አምናለሁ።
ፋክት፡- ጤፍ ስንት ብር የገባ ይመስልሀል?
ታማኝ፡- (ረ..ጅ…ም ሳቅ) እሱን ነው እንዴ መረጃ
የምትለው?
ፋክት፡- አገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ?
ታማኝ፡- ጤፍና እንቁላል እንኳ ስንት እንደገባ
አላውቅም። አንድ እርግጠኛ የምሆንበት ነገር
ግን፤ በጃንሆይ ጊዜ በኢትዮጵያ በአለባበሳቸው እና
በአኗኗራቸው የሚቀናው በመምህራን እንደነበር
አስታውሳለሁ። ዛሬ መምህራኑ ሆዳቸውን መሸፈን
እንዳልቻሉ ልነግርህ እችላለሁ። ስለዚህ ኑሮውን
በዚህ መለካት ትችላለህ።
ፋክት፡- ብዙው ኢትዮጵያዊ ከዚህ ቀደም
የሚያውቅህ ምርጥ አርቲስት እንደነበርክ ነው።
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ትንታግ አክቲቪስት (የመብት
ተሟጋች) ሆነሀል። ከጥበቡ ርቀሃል ማለት ይቻላል?
ታማኝ፡- አይ አልራቅሁም። በእርግጥ ምን መሰለህ፤
ጥያቄው በጣም ሰፊና በቃለ-መጠይቅ የሚያልቅ
አይነት አይደለም። በፅሁፍ ባብራራው ደስ ይለኝ
ነበር። የኪነ-ጥበብ ሰው ሀሳቡን ወደ ህዝቡ በተለያየ
መንገድ ያደርሳል፤ በዘፈን፣ በቀልድ፣ በግጥም፣
አልያም በትያትር ያደርሳል።
እኔም በንግግሬ እንደ ልቤ ሀሳቤን የማደርሰው
የጥበብ ችሎታዬን ተጠቅሜ ነው። ስለዚህ ከጥበብ
አልራቅሁም ማለት ነው። ምናልባት የራቅሁ
የሚያስመስለው በዘፈን ማለትም በኪነ-ጥበብ
ሙያ ተከፍሎኝ እሰራ የነበረውን ስራ ትቼ፣
በነፃ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ መድረኮችን እየፈለኩ
ስለምናገር ይሆናል። በተጨማሪም ሌላው እንደ
እሳት የሚፈራውን ፖለቲካ የሚባለውን ነገር ደፍሬ
ስለማደርገው ‹አይ ትቶታል› ተብሎ ካልሆነ በቀር፣
በውስጤ ያለው ችሎታና ፍቅር አሁንም እንዳለ
ነው። ምናልባት ችሎታ የሚለው ወደፊት ተፈትኜ
ሳልፍ የሚረጋገጥ ይሆን ይሆናል። ይህም ሆኖ፣
ጥበብን ለንግድ ባልጠቀምበትም፣ ለማምንበት ነገር
ግን እየተጠቀምኩበት ነው።
ፋክት፡- ሌሎች እንደ አንተ ያሉ አርቲስቶች በቀጥታ
ስርዓቱን ሲጋፈጡና ሲያጋልጡ አንመለከትም።
ምክንያታቸው ፍርሃት ብቻ ይመስልሃል?
ታማኝ፡- ፍርሃቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሌሎችም
ምክንያቶች ይኖራሉ። እውነት የምታስከፍለው
ዋጋ ይኖራል። ጋሊሊዮ የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን
ለዘመናት ያስተማረችውን የፀሀይን በመሬት ዙሪያ
መሽከርከር በሳይንሳዊ መንገድ ፈትኖ ተቃራኒውን
ሲያቀርብ፣ ራሱን ለመከራ መዳረጉን ከታሪክ
ድርሳናት መረዳት ይቻላል።
እናም በዚህ መልኩ ለእውነት መቆም የሚያመጣውን
በትር በመፍራት፤ ‹ጐመን በጤና› የሚለው ብሂል
የአርቲስቶቻችንም፣ የህዝቡም የህይወት መመሪያ
ሆኗል። ሁልጊዜ የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፤ በዚህ
ምድር ላይ ኖርን ለማለት የመጣን ሰዎች፣ አንዳች
ለውጥ ሳናመጣ እና ከራሳችን አሻግረን ለሌሎች
ሳንተርፍ፣ እንደእንስሳ ኖረን ማለፋችን ያሳዝነኛል።
ይሄ ማለት ራስን በልቶ ከማደር በላይ አለመመልከት
ነው። እናም የዝምታው ምክንያት ከፍርሃትም በላይ
ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት ይመስለኛል።
ፋክት፡- ከስርዓቱ ጋር እጅና ጓንት የሆኑትን
አርቲስቶች የጥበብ ስራ (ያውም አብዛኞቹ እንደ
አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ
እያተኮሩ) እየገዛ እነሱን የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ
የሚያደርገው፤ የሚጨቆነውና የሚረገጠው ህዝብ
ነው፤ አንተ በግልህ ይሄ ህዝብ ከስርዓቱ ጐን ቆመው
(ምንም እንኳ ሚዛኑ አናሳ ቢሆንም) የሚበድሉትን
አርቲስቶች በምን መልኩ መቃወም (Boycot)
ነበረበት ብለህ ታስባለህ?
ታማኝ፡- ትክክል ነው። ይሄ ጥያቄ ግን ወደ ብዙ
ነገር ይወስደናል። ከስርዓቱ ጋር ተባብረው ይህን
የሚያደርጉት የጥበብ ሰዎች ብቻ አይደሉም።
ለምሳሌ የሕግ ተማሪዎችን ብትወስድ፣ ስለሰው ልጅ
መብት ቅድሚያ ሰጥተው መሟገት እንዳለባቸው
ነበር የተማሩት፤ የምንመለከታቸው ግን በሀሰት
ከስሰው ሲያሳስሩ፣ ዐቃቤ-ሕግና ዳኛ ሆነው ሞት
ሲያስፈርዱ እና ሲፈርዱ ነው። እነዚህ እንግዲህ
የተማሩና የተመራመሩ የምንላቸው ናቸው። ህክምና
የተማሩትንም ስንመለከት፣ በቀላሉ ፈውስ ሊያገኝ
ለሚችለው በሽታ መፍትሄ ሲሰጡ አናይም። ይህን
የማያደርጉት የመንግስትን ፖሊሲ የሚቃወሙ
እየመሰላቸው ነው? የታማኝነት ጉድለትን በሁሉም
ሙያዎች ላይ እያየን ነው። ስለዚህ የብዙ ሙያ
ባለቤቶች የሆንነው ሁላችንም ለበደሉ መስፋፋት
አስተዋፅኦ እያደረግን ነው። እንደህዝብም
ማኩረፍ ስላቃተን ነው። ሕግ ተምረዋል
የሚባሉት የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ
‹‹በሽብርተኝነት ከተጠረጠረ ሰው ጋር የታየ
በሽብርተኝነት ይቀጣል›› ብለው ሲናገሩ በቴሌቪዥን
ተመልክቻለሁ። እኚህ ሰው እንግዲህ በሕግ ነው
የተመረቁት። እናም ይሄ ጥያቄ ለአንድ ቡድን ብቻ
የሚቀርብ አይሆንም።
ፋክት፡- አይ፣ የአርቲስቶች ግን ከዚህ ይለያል
ብዬ አስባለሁ። የጠቀስካቸው ሙያዎች በዚህም
አልን በዚያ፣ ወደ ስርዓቱ እንዲጠጉ ያስገድዳሉ
(በሹመትም ሊሆን ይችላል)። ጥበብ ግን ከዚህ
ለየት የሚል ይመስለኛል፤ የጥበብ ሰዎቻችን
እንቅስቃሴ በቀጥታ የህዝብን ተሳትፎ ስለሚጠይቅ
ወገንተኝነታቸው ወደ ህዝብ እንዲሆን ማድረግ
አይቻልም ወይ? ለማለት ፈልጌ ነው።
ታማኝ፡- ልክ ነው። መጀመሪያ ማኩረፍ መቻል
ራሱ ተፈጥሯዊ መብት መሆኑን ሁላችንም መረዳት
ይኖርብናል። ይሄንን ካመንን እነሱን ብቻ ሳይሆን
ሌላውንም ማስገዛት ይቻላል። የዚህን ስርዓት ቁልፍ
የንግድ ተቋማት እንቅስቃሴ ‹‹ቦይኮት›› ማድረግ
ይቻላል። ነገር ግን ማኩረፍ ብቻ እንኳን አቅቶን
ፈርተናል። ይህን ማድረግ ብንችል እኮ ማን ከማን
ጋር መቆሙን ለማወቅና፣ ለዚያም ተግባራዊ ምላሽ
ለመስጠት ይቻለን ነበር። ይሄ ከተቻለ ቀጣዩ ነገር
አያሳስብም፤ ምክንያቱም በሂደት ብዙ ነገሮችን
ማድረግ ይቻላል ብዬ አምናለሁ።
ፋክት፡- ያንተን የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ ለየት
የሚያደርገው በፊልሞች የሚቀነባበሩ መረጃዎችንም
አብረህ በማሰራጨትህ ነው። ለመሆኑ እነዚህን
መረጃዎች ከየት ነው የምታገኛቸው? ልምዱንስ
እንዴት ልታዳብረው ቻልክ?
ታማኝ፡- እንግዲህ… (ሳቅ)
ፋክት፡- መረጃዎቹን ከየት እንደምታገኝ ለመናገር
አትገደድም…
ታማኝ፡- ኧረ! ግድ የለም። መጀመሪያውኑ
ለምናገረው ነገር በቂ መልስ ከሌለኝ ለክርክርም
አልቀርብም። ድሮ በመድረክ ህይወቴ የሙያ
ባልደረቦቼ ‹‹አቶ ማስረጃ›› እያሉ ይቀልዱብኝ ነበር።
የወያኔ መንግስት በየቀኑ በአደባባይ ስለሚዋሽ
የመረጃ ችግር አይኖርም። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን
ለአንድ ጊዜ ካየህ ለአመት የሚበቃ መረጃ ይሰጥሃል።
በጣም ስለሚንቁን ነው መሰለኝ፣ የሚዋሹትን
እንኳን በአግባቡ አይዋሹም። በግሌ ግን፣ የማገኘውን
ነገር በሙሉ በማህደር የማስቀመጥ ልምድ አለኝ።
ለምሳሌ አንድ ሰው ተማረ እንኳ ቢባል 12 አመት
በትምህርት ቤት ከቆየ በኋላ፣ ለአራት አመት
ዲግሪው ደግሞ ዩኒቨርስቲ ይቆያል፤ የማስተርስና
የፒኤችዲውን ስንጨምር በአጠቃላይ ሃያ አመታት
ይፈጅበታል። እኔ ግን ከዚህ መንግስት የሃያ ሶስት
አመት ልምድ አለኝ። ስለዚህ እያንዳንዱን ነገር
ለማብራራት የዚህን ያህል ጊዜ ልምድ አለኝ ማለት
ነው።
አቶ መለስ በአንድ ወቅት
‹‹የስኳር ዋጋ የጨመረው፣
በስኳር የሚጠጣ ገበሬ ቁጥር
ስለጨመረ ነው›› ብለው
ነበር። አቶ ኃይለማርያምም
ስለጤፍ ዋጋ ሲጠየቁ፣
‹‹ጤፍ በልቶ የማያውቀው
ገበሬ፣ ጤፍ መብላት
በመጀመሩ ነው›› ሲሉ
መለሱ
ወደ ገፅ 24 ዞሯል
“ 24 ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006
ፋክት፡- የአቶ መለስን ሞት ስትሰማ ምን ተሰማህ?
ታማኝ፡- በወቅቱ ተናግሬ ነበር፤ ሁልጊዜም
በቴሌቪዥን የምታየውን ሰው ስታጣው እንደሰው
ያሳዝናል። እኔም በወቅቱ ደንግጬ ነበር። በኋላ
ላይ በማዘኔ እንኳን እንድቆጭ የሚያደርግ ነገር
በመንግስት ሲሰራ ተመልክቻለሁ። ሞተዋል ከመባሉ
ቀድሞ ነበር መረጃ የደረሰኝ። ግን በመንግስት
ሚዲያም ሲነገር ሀዘን ገብቶኝ ነበር። በቴሌቪዥን
ልጆቻቸውን ሳይ፣ አባት እንደነበሩ አስታውሼ አዝኜ
ነበር። በሳቸው ዘመን ኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን
መከራ ሳስብ ግን በጣም ይከፋኛል፤ ጥያቄው
‹‹በሞታቸው ምን ተሰማህ?›› ከሆነ ግን አዝኜያለሁ።
ፋክት፡- አቶ መለስን እንዴት ትገልፃቸዋለህ?
ይህን ጥያቄ ያነሳሁብህ ከሀገር ፍቅር አንፃር ነው።
ለምሳሌ መንግስቱ ኃይለማርያም አምባገነንነታቸው
ልክ አልነበረውም። ነገር ግን በሀገር ፍቅር ሲታሙ
አትሰማም። አቶ መለስ ግን ስማቸው በሁለቱም
ጉዳይ ሲብጠለጠል ስለምንሰማ ነው።
ታማኝ፡- እንደ አቶ መለስ በህዝብ ላይ ጥላቻ
ያለው ሰው ገጥሞኝ አያውቅም። በኢትዮጵያ ታሪክና
በኢትዮጵያ ቀደምት መሪዎች ላይ፣ እንዲሁም
በአማራ ህዝብ ላይ ይህን መሰል ጥላቻ ያለው ሰው
መፈጠሩንም አላውቅም። በዚያው ልክ ለኤርትራ
ያላቸው ፍቅር ወደር የለውም። ይህ የህትመት
ውጤት ሆነ እንጂ፣ በምስል ባስደግፈው ደስ ይለኝ
ነበር።
አዲስ አበባ በገቡ በሳምንቱ አቶ መለስን፣
ከጋሽ መስፍን ወ/ማሪያም፣ ዶ/ር መኮንን ቢሻው
እና እንድርያስ እሸቴ ጋር የሪፖርተሩ ጋዜጠኛ
አማረ አረጋዊ አወያይቷቸው ነበር። አንድ ቦታ
ላይ ጋሽ መስፍን ‹‹ይሄ መንግስት ስለኤርትራ
ጉዳይ ለመወሰን ምን ስልጣን (ማንዴት) አለው?››
ብለው ሲከራከሩ፣ አቶ መለስ ‹‹ማነው ማንዴት
የሚጠይቀን?›› በማለት እንዴት እንደተንቀጠቀጡ
አስታውሳለሁ። ከጣሊያን ወረራ በኋላ በስንት ልፋት
የተገነባን ሰራዊት፣ የነበረንን የሚያኮራ የአየር ኃይል
በአንድ ለሊት እንዴት አድርገው እንዳከሰሙት
ሳስብ ያበሳጨኛል። ወደፊት የሚኖረው ትውልድ
በጥላቻና በጥርጣሬ እንዲተያይ መርዝ ተክለው ነው
የሄዱት። ኒውዮርክ ላይ መጥተው ባደረጉት ንግግር፣
‹‹ለኤርትራ ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያዎቹ እኛ
ነን፤ በዚህ ደግሞ ኢትዮጵያውያኖች ይጠሉናል››
ብለው ተናግረዋል። ይህን ያሉበት ቪዲዮ አለኝ።
ዛሬ ደግሞ በግልባጩ እኛን ‹‹የኤርትራ ተላላኪ
ይሉናል››፤ ድሮ በስምንተኛው ሺህ የማይሆን ነገር
ይሆናል ሲባል እሰማ ነበር። ይኸው ዛሬ ኢትዮጵያን
ከሰባት አቅጣጫ የወጉ ሰው፣ ነጋሪት እየተጎሰመ
እንድንቀብራቸው ታውጇል። በአደባባይ ‹‹ቆሻሻ››፣
‹‹ወራዳ›› እና የመሳሰሉትን አስፀያፊ ስድቦች
የሚሳደብ መሪ ነው እንግዲህ ‹‹ባለራዕይ›› እየተባለ
ያለው። እናም እርሳቸውን የምገልፅበት ቃላት
የለኝም፡
ፋክት፡- ከመለስ ህልፈት በኋላ ያለችው ኢትዮጵያ
ምን ትመስላለች?
ታማኝ፡- ከዛ በኋላ ያለችውን ኢትዮጵያ፣ ግራ
የገባት ኢትዮጵያ ብላት የተሳሳትኩ አይመስለኝም።
ከርሳቸው በኋላ የተተኩት ሰው ብቻቸውን መምራት
ስለማይችሉ ሶስት ምክትሎች ተሰይመውላቸዋል።
እንደውም አንዳንዶች ‹‹ባጃጅ›› እያሉ ሲቀልዱባቸው
ሰምቼ ስቄያለሁ። መሄጃዋን የማታውቅ፣ በማዕበል
የምትንገላታ ሀገር መስላለች።
ፋክት፡- በቀጣዩ አመት 5ኛው ሀገር-አቀፍ ምርጫ
ይደረጋል። ያለፉትን ምርጫዎች ያሳለፍነው
ጉልበታማው አቶ መለስ እያሉ ነው። ቀጣዩ ግን
ያለ አቶ መለስ የሚካሄድ ነው። በአንተ አስተያየት፣
ምርጫው ከቀደሙት የተሻለ ወይስ የባሰ የሚሆን
ይመስልሀል?
ታማኝ፡- አቶ መለስን ብዙ ብወቅሳቸውም፣ በመካከል
የሚነሳላቸውም ነገር አለ። አቶ መለስ ዋሾ ናቸው።
እንደ አቶ መለስ ማን ነው አሰማምሮ የሚዋሸው?
ብዬ ሳስብ ግራ ይገባኛል። እኔ ኢትዮጵያን ከአሜሪካ
ጋር ማወዳደር አልፈልግም፤ ከኬኒያ ጋር ግን
አወዳድራታለሁ። በሀገሬም እነሱ ያላቸውን ነፃነት
ያህል የሚጠይቅ ህዝብ እንዳለም አውቃለሁ። እዚህ
ሀገር የማያቸው አንዳንድ ወጣት ኢትዮጵያውያን
አሉ። እነዚህ ወጣቶች፣ በተለያዩ የትምህርት
ዘርፎች ከማንም የተሻለ አቅም እንዳላቸው
አስመስክረዋል። ከሌሎች ሀገሮች ወጣቶች ጋር
ሆነው እየተወያዩ ፖለቲካ ሲነሳ ግራና ቀኝ ያያሉ።
ይሸማቀቃሉ። የሚገርመው፣ ፍርሃቱ አሁን ድረስ
አልለቀቃቸውም። ዋናው ጥያቄ፣ እንዲህ አይነት
ትውልድ እንዲኖረን ፈቅደናል ወይ? የሚለው
ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር በባህር ላይ መሞት
የሚል ትውልድ ለማፍራት ፍቃደኛ ሆነናል ወይ?
የሚለውም መነሳት አለበት። ይህ ከምርጫው በፊት
የሚነሳ ጥያቄ ነው። ይህን ለመመለስ ግን እያንዳንዱ
ዜጋ ራሱን መጠየቅ አለበት። እነርሱ የሚያዘጋጁልን
ምርጫ ይሄን አይመልሰውም።
በረዥም ርቀት ሩጫ እንደምንታወቀው ሁሉ፣
አሁን ደግሞ በተሸማቃቂነታችን እየታወቅን ነው።
ይሄ እስከ መቼ ይቀጥላል? በኤርፖርቶች አካባቢ
በሚኖሩ ረዣዥም ሰልፎች መሀል ኢትዮጵያዊውን
ትለየዋለህ። ሁሌም ሲደነብር ነው የምታየው።
ይህን መሸማቀቅ ለመታገስ ፍቃደኛ ነን ወይ?
ይሄን ለመመለስ የተዘጋጀ ዜጋ ካለ፣ ምርጫውንም
መጠበቅ አይጠበቅብንም። ይህ የህዝብ ውሳኔ ነው።
‹ወያኔ ስልጣን ይለቃል፤ ወይስ አይለቅም?› የሚለው
በእያንዳንዱ ዜጋ እንቅስቃሴ የሚመለስ ነው።
ፋክት፡- አይ! የእኔ ጥያቄ የአቶ መለስ መንግስት
የጨፈለቃቸውን መብቶች፣ የአቶ ኃይለማርያም
መንግስት ከምርጫው በፊት ሊመልሳቸው ይችላል
ወይ ብለህ ታስባለህ የሚል ነው?
ታማኝ፡- በመጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም ራሳቸው
ይህን ለማድረግ አቅም አላቸው ወይ? የሚለውን
ጥያቄ ማየት ያስፈልጋል። አሁን እኮ ተሰብስበው
የወሰኑትን ነው አቶ ኃይለማርያም ወጥተው
የሚነግሩን። የለውጡ ነገር ከራሳቸው ሰብዕና
ይመጣል ወይ? ለሚለው ጥያቄ፣ የእኔ ምላሽ
አይመስለኝም የሚል ነው። ሌላው ይቅርና በቃላት
ደረጃ እንኳን፣ አቶ መለስ ያሉትን የሚደግሙ
ሰው ናቸው’ኮ። አቶ መለስ በአንድ ወቅት ‹‹የስኳር
ዋጋ የጨመረው፣ በስኳር የሚጠጣ ገበሬ ቁጥር
ስለጨመረ ነው›› ብለው ነበር። አቶ ኃይለማርያምም
ስለጤፍ ዋጋ ሲጠየቁ፣ ‹‹ጤፍ በልቶ የማያውቀው
ገበሬ፣ ጤፍ መብላት በመጀመሩ ነው›› ሲሉ መለሱ።
ሶስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮችና አስራ ምናምን
አማካሪ ያላቸውን ሰው፣ እንዴት በራሳቸው ለመወሰን
የሚያስችል አቅም ይኖራቸዋል ብለን እንገምታለን?
የጨፈለቋቸውን መብቶች ለኢኮኖሚያዊ እርዳታ ሲል
ህወሓት ራሱ ማሻሻያ ሊያደርግ ይችላል እንጂ፤ ከአቶ
ኃይለማርያም ምንም ይመጣል ብዬ አልጠብቅም።
ፋክት፡- ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ፣ መሬት
ከኢትዮጵያ ተወስዶ ወደ ሱዳን ሊጠቃለል ነው
የሚል ዘገባ እየሰማን ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ አንተ
የምታውቀው መረጃ አለ?
ታማኝ፡- እዚህ ሀገር በተለያዩ ባለሙያዎች
የተዋቀረ ‹‹የድንበር ኮሚቴ›› የሚባል አለ። እነርሱ
የሚያወጡት መረጃ አለ። የሱዳን የመገናኛ ብዙሃንም
ያወጧቸውን ዘገባዎች ተከታትያለሁ። በዚያው
አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በስልክ ሲጠየቁ
የሰማሁት አለ። ከዚህ ሁሉ በፊት ግን የህወሓትን
ተፈጥሯዊ ባህሪይ ካየህ፣ መሬቱ የማይሰጥበት
ምንም ምክንያት አለመኖሩን ትረዳለህ። ያኔ ‹‹ባድመ
ተወረረች›› ብለው የዛን ሁሉ ኢትዮጵያዊ ደም
አፈሰሱ። ገፍቶ ሊሄድ ይችል የነበረው ሰራዊት፣
በአቶ መለስ ትዕዛዝ እንዲቆም ተደረገ። ጄንዳይ
ፍሬዘርም በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ቀርባ፣ ‹‹አቶ መለስ
ጄነራሎቹ ፊት ቆሞ፣ ጦርነቱን ያስቆመ ጀግና ነው››
ብላ ስትናገር ነበር። ከዚያም ወደ አልጀርስ ሄደው
ያለምንም ጠያቂ ተፈራረሙ። አንድም ኢትዮጵያዊ
ባለሙያ በሌለበት ፍርድ ቤት ተስማሙ። አቶ ስዩም
መስፍንም ‹‹ባድመም የእኛው ነች›› ብለው ነገሩን።
ይኸው እስከአሁን ድረስ ግን ባድመ የለችም።
ታዲያ እነዚህ ሰዎች በምን መለኪያ አያደርጉትም
ብለህ ታምናለህ? ስለአሰብ ወደብ ምን እንደሚሉ
ትሰማለህ? ‹‹የኤርትራን ሉዓላዊነት የሚቀናቀን ካለ
እኛም እንዋጋዋለን›› እያሉን ነው። ይህን ለመገመት
መማርና መመራመር አያስፈልግም።
ሰው እንዴት ሁልጊዜ
በአሸናፊነት ትዕቢት ውስጥ
ይኖራል? እናም፤ እስከመቼ
ነው እንዲህ እየሆናችሁ
የምትቀጥሉት? እስከመቼስ
ነው በዚህ ጥላቻ የምትኖሩት?
እስከመቼስ ጀግና ከእኛ ውጪ
የለም ብላችሁ ታስባላችሁ?
ያኔ አዲስ አበባ ስትገቡ
የነበራችሁ ጉልበት እንኳን ዛሬ
የለም። ከእድሜ ጋር ስኳርና
ደም ብዛትም ይመጣል።
“ከአሜሪካ በላይ፣...ፋክት ቁጥር 33 የካቲት 2006 25
ፋክት፡- በቅርቡ የአሜሪካ ኮንግረስ “Bill 2014”
የሚባል ሕግ አፅድቋል። ይህ ውሳኔ የዲያስፖራው
እንቅስቃሴ ውጤት ነው ማለት ይቻላል?
ታማኝ፡- ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ ኮንግረሱን ሎቢ
(የሚወተውቱ) የሚያደርጉ ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን
ባለሙያዎች አሉ። በወርና በሁለት ወር ውስጥ
የሚሰራ ስራ አይደለም። ዋናው ነገር ግን ይሄ
አይደለም። የጉዳዩ ባለቤቶች እኛ ሆነን ሳለ፣ ከሌሎች
መጠበቃችን የሚያሳስብ ነው። አንድ መንግስት
አምባገነንም ሆነ ፋሽስት፣ አገር እንደአገር መቀጠሉን
በቅድሚያ ያያል። የትኞቹም መንግስታት ብሄራዊ
ጥቅም የሚሉት ጉዳይ አላቸው። ዴሞክራሲና
ሰብዓዊ መብት ከዚያ ቀጥሎ በሁለተኝነት የሚታይ
ነው። በእርግጥ በህጉ መፅደቅ ላይ የዲያስፖራው
ቀጥተኛ ተሳትፎ አለ። የዲፕሎማሲው ስራ ከዚህ
በፊት ሲሰራ ነበር፤ ወደፊትም ይሰራል። ግን
ከአሜሪካ ተፅዕኖ በላይ፣ እኛው ባለቤቶቹ ራሳችን
ተፅዕኖ መፍጠር አለብን የሚል እምነት አለኝ።
ፋክት፡- የህዳሴውን ግድብ በሚመለከት
የዲያስፖራው አቋም ምን እንደሚመስል ልትነግረን
ትችላለህ?
ታማኝ፡- ይኸውልህ፤ እዚህ ግራና ቀኙን
የምትመረምርበት እድል አለ። የምንኖረው
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን እያየንና የመንግስት
ፕሮፓጋንዳን ብቻ እየሰማን አይደለም።
እንደምራለንም፤ እንቀንሳለንም። በዙሪያ ባሉ
ጠላቶች በአይነ-ቁራኛ የሚታይ ይሄን መሰል
ፕሮጀክት መገንባት የነበረበት፣ የጠበቀ አንድነት
በፈጠረ ማህበረሰብ መካከል ነው። ከኢትዮጵያ
ህዝብ በተሻለ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ የሚገኘው
ዳያስፖራ፣ ይህን ግድብ ለመስራት ፈቃደኛ
ነው። ውጪ ያለውን ሰው በቀላሉ ልታታልለው
አትችልም። ሊታሰርበት የማይችልበት ቦታ
ስለሚኖር ሀሳቡን በነፃነት ይገልፃል። ከዚያ በፊት ግን
የሚስተካከሉ ጉዳዮች ሊኖሩ ይገባል። መጀመሪያ
አንድ ለአምስት የተቆለፈውን ህዝብ መፍታት፣
ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር ያስፈልጋል። ይህ
ከሆነ መንግስት ካሰበው በላይ ሊያደርግ የሚችል
አቅም ዲያስፖራው ዘንድ አለ። ይሄ መልስ ካላገኘ
ዲያስፖራው እድሜ ማራዘሚያ ሊሆን አይችልም።
በአባይም ጉዳይ ያለው ክርክር ይሄው ነው። የዜጎች
መብት በቅድሚያ መከበር አለበት። ስለኢትዮጵያ
ሲሉ የፃፉ፣ ስለኢትዮጵያ ሲሉ የታሰሩ መፍትሄ
ከተገኘላቸው፣ በአባይ ጉዳይ የማንስማማበት ምንም
ምክንያት የለም። ይሄ የዲያስፖራውም፣ የእኔም
አቋም ነው።
ፋክት፡- የአቶ ሌንጮ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ
በዲያስፖራው በኩል እንዴት እየታየ ነው?
ታማኝ፡- በእርግጥ ከዚህ በፊት ለውጥ እናመጣለን
በሚል ሀገር ቤት ከገቡ በኋላ፣ ለህወሓት እጅ የሰጡ
ብዙ እንዳሉ እናውቃለን። እኔ በግሌ፣ ራሴን ጨምሮ
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደሀገር ቤት መግባት
አለበት ብዬ አምናለሁ። ነገር ግን ማንም የኢቲቪ
የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ መሆንን አይፈልግም።
የሌንጮ መግባት በዲያስፖራው ፖለቲካ ላይ ያን
ያህል ተፅዕኖ ይፈጥራል ብዬ አላስብም።
ፋክት፡- ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን በአካል
አግኝተሀቸው ታውቃለህ? ካገኘሀቸውስ ምን
አውርታችኋል?
ታማኝ፡- አንዴ ከህዝብ ለህዝብ ስንመለስ አግኝቼ
ጨብጬያቸዋለሁ። ከዚያ ውጪ ጥላሁን ገሰሰ ታሞ
ደቡብ አፍሪካ ልጠይቀው በሄድኩ ጊዜ፣ ባጋጣሚ
ደውለው አለምፀሀይ ወዳጆንና ንዋይ ደበበን ካነጋገሩ
በኋላ እኔም አግኝቼያቸዋለሁ። ሳገኛቸውም፣
ለምን ያለፉበትን ታሪክ አይፅፉም ስላቸው፣ በ3
ቅፅ የሚወጣ መጽሐፍ እያዘጋጁ እንደነበር ያኔ
ነግረውኛል።
ፋክት፡- ከኢህአዴግ ባለስልጣናትስ ማንን አግኝተህ
ታውቃለህ?
ታማኝ፡- አቶ ታምራት ላይኔ ከእስር ተፈተው፣
ከሀገር ቤት ከወጡ በኋላ አግኝቼያቸዋለሁ። እኔ
በግሌ ብዙ መከራ ያየሁት ከርሳቸው ስም ጋር
በተያያዘ ነው። እንደው ብሄርተኛ ነህ እንዳልባል
እንጂ፣ እርሳቸው ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ
አማራ የሚባለው ህዝብ ብዙ መከራን አሳልፏል።
እና በእርሳቸው ላይ ጥያቄ ነበረኝ። ይሁንና ባንድ
አጋጣሚ አንድ ጓደኛዬ ቴዲ አፍሮን እስር ቤት
ሊጠይቀው ሄዶ፣ ‹‹ታምራት ላይኔን አየዃቸው።
ያሳዝናሉ፣ የሚጠይቃቸው ሰው የለም›› ሲለኝ፤
እንደው ባክህ ከቻልክ ገንዘብ ስጥልኝ አልኩት።
የነገርኩት ልጅ፣ ፈርቶ ነው መሰለኝ ብሩን ሳይሰጥ
ቀረ። እኚህ ሰው ስንት አመት ታግለው በራሳቸው
ሰዎች ታስረዋል። ይሄ ጭካኔ ነው።
ሆኖም እዚህ ሀገር እንደመጡ፣ አንድ ቀን ስልኬ
ጠራና አንስቼ ‹‹ማን ልበል?›› ስል፣ ‹‹ታምራት
ላይኔ ነኝ፤ በጌታ ስም ይቅር በለኝ፤ ይቅር ካላልከኝ
አልቀመጥም!›› አሉኝ። ‹‹እኔ እኮ ቀድሞ ነው ይቅር
ያልኮት። ከእኔ ይልቅ በእርሶ ትዕዛዝ የተገደሉትና
ወደእስር የተወረወሩት እንዴት ነው ይቅር
የሚሎት?›› ስላቸው፤ ‹‹ሁሉም በጊዜው ይሆናል››
ብለውኝ እንድንገናኝ ቀጠሮ ያዝን። ከዚያም ለቪኦኤ
ቀርበው፣ ለእኔ ከተናገሩት በተቃራኒው አወሩና
ቅሬታ ገባኝ። ከዛ በኋላ ተገናኝተንም፣ አውርተንም
አናውቅም።
ፋክት፡- በቀጠሮውስ አልተገናኛችሁም?
ታማኝ፡- ደውለውልኝ ነበር። እኔ ግን ፈቃደኛ
አልሆንኩም።
ፋክት፡- ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ምን
ትመክራቸዋለህ?
ታማኝ፡- አንድ ጊዜ አውራምባ ታይምስ የሚባል
ጋዜጣ ላይ ይህንኑ ጥሪ አቅርቤ ነበር።
ፋክት፡- እሺ! እዛ ላይ ከመለስከው ልንዘለው
እንችላለን።
ታማኝ፡- ኖ… ኖ… ኖ! ስለመለስኩት አይደለም።
ያኔ ካልኩት፣ አሁንም የምደግመው አለ። ስብሃትን
አንዳንዶች ‹‹አቦይ›› ይሏቸዋል፤ ይህ በትግራይ
ለሚከበር አባት የሚሰጥ ስያሜ ነው። የእርሳቸው
ንግግር ግን የሚያስከብር አይደለም። ቀድሜ እኔ
ልሞት ብችልም፣ ከእድሜ አንፃር ካየነው ግን
እርሳቸው ይቀርባሉ። ሌሎቹንም ብታያቸው
የጉርምስና እድሜያቸው በጫካ አልፏል። ነገር ግን
ዛሬም ድረስ በጥላቻ ውስጥ ናቸው። አንዳንዴ፣
እንዴት ለልጆቻቸው አያስቡም? ስል አስባለሁ።
ሰው እንዴት ሁልጊዜ በአሸናፊነት ትዕቢት
ውስጥ ይኖራል? እናም፤ እስከመቼ ነው እንዲህ
እየሆናችሁ የምትቀጥሉት? እስከመቼስ ነው በዚህ
ጥላቻ የምትኖሩት? እስከመቼስ ጀግና ከእኛ ውጪ
የለም ብላችሁ ታስባላችሁ? ያኔ አዲስ አበባ ስትገቡ
የነበራችሁ ጉልበት እንኳን ዛሬ የለም። ከእድሜ ጋር
ስኳርና ደም ብዛትም ይመጣል። ልጆቻችሁስ በሌላው
ህዝብ እየተወደዱ የሚኖሩ ናቸውን? ልጆቻችሁ
ከሌሎች ልጆች ጋር ተቀላቅለው መጫወት ይችላሉ
ወይ? ብዬ ልጠይቃቸው እፈልጋለሁ።
የእስክንድርና የሰርካለም ልጅ በእስር ቤት
ነው የተወለደው። በዚህ ላይ የአባትነት
ፍቅሩን ቀምታችሁ በለጋ እድሜው እንዲሰደድ
አድርጋችሁታል። የእነበቀለ ገርባ እና የእነውብሸት
ልጆችስ? ምን እያፈራችሁ ነው? በእያንዳንዷ
የሀገሪቱ ክፍል የሚቃትቱና፣ እህ… የሚሉ ህፃናት
በዝተዋል። በአንድ ወቅት ጋሽ መስፍን የተናገረውን
አስታውሳለሁ፤ ‹‹ይሄ መንግስት ከሶስት ትውልድ
ጋር የተጣላ ነው›› ብሎ ነበር። ከብርቱካን፣
ከብርቱካን እናት እና ከልጇ ጋር ተጣልቷል ለማለት
ፈልጎ ነው። ይታያችኋል ወይ? ጋዳፊን አላያችሁም
ወይ? ግዴላችሁም፣ ሌላውን ብትጠሉት እንኳን
ለልጆቻችሁ ስትሉ፣ እባካችሁ ይህን አድርጉ ነው
የምለው። ሰምተኸኛል?
ፋክት፡- አዎ! ሰምቻለሁ!
ታማኝ፡- ቄስ ሆንኩብህ እንዴ?
ፋክት፡- አይ በፍፁም! በፍፁም! እንቀጥል። ለረዥም
አመታት በአክቲቪስትነት ለሀገርህ ተጋድሎ
አድርገሃል። በዚህ ሂደት ውስጥ ስታልፍ ምን
አሳክቻለሁ? ምንስ አጥቻለሁ ብለህ ታስባለህ?
ታማኝ፡- ትርፍ ሲባል…?
ፋክት፡- የተነሳህለትን አላማ ከዳር ከማድረስ አኳያ
ማለቴ ነው፤
ታማኝ፡- አሁን እንግዲህ፣ እንዴት መሰለህ
ነገሩን የማየው? ይሄ ንግድ አይደለም። ይሄ
ኢትዮጵያዊነትን የያዘች ልብ እንዳትሞት የሚደረግ
ጥረት ነው። አለም እያየ የሞሶሎኒ ፓይለቶች
ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ ፈጅተዋል። ከነርሱ
ጋር መስዋዕትነት ሲነፃፀር የኔ ተግባር ቅንጦት
ነው። የምለውም ሀሳብ ውሸት እንዳልሆነ በአይኔ
እያየሁ ነው። በኪነ-ጥበብ ህይወቴ የተለያዩ አገራት
ዞሬያለሁ። የማከብራቸው የጥበብ ሰዎች እነ
ጥላሁን ገሰሰ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን እና ወጋየሁ
ንጋቱ የቆሙበት መድረክ ላይ ቆሜያለሁ። የህዝብ
ለህዝብ ጊዜ አገሬን ልክ እንደ ኳስ ተጫዋቾቹ፣
በማልችለው ቦታ ሁሉ ተሰልፌ የተሰጠኝ ተልዕኮ
አሳክቼ ተመልሼያለሁ። ለኔ በሙያ ደረጃ ይኼ
ትልቅ ስኬት ነው። አሁን በማደርገው ነገር ገንዘብ
ላላገኝ ወይም በምቾት ላልደሰት እችል ይሆናል።
ነገር ግን ሰው እኔን እንደ ትልቅ ሰው ቆጥሮ፣
በአክብሮት ከመቀመጫው ተነስቶ ሲቀበለኝ ሳይ፣
ለዓላማዬ ክብር እንዳለው ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸው
የሚቆረቆሩ ሰዎችን እንዳፈራው ያመላክተኛል።
የህዝብ አደራን መሸከም ከባድ ነው። መልሱ እንዲህ
በፍቅር ሲሆን እጅግ በጣም ያበረታል። ይህን በብር
አትገዛውም። ልጆቼ በኔ ምክንያት አይሸማቀቁም።
‹ሕግ ኢትዮጵያ ውስጥ ይስራ› ይል ነበር አባታችን
ማለታቸው አይቀርም።
ፋክት፡- በምታራምደው አቋም የተነሳ አጣሁት
የምትለው ነገር አለ?
ታማኝ፡- ገንዘብ ብቻ ነው ያጣሁት… (ሳቅ)
በተረጋጋች እና ሕግ በሚከበርባት ሀገር ማንኛውንም
ስራ ሰርቼ ገንዘብ ላገኝ እንደምችል እርግጠኛ ነኝ።
ፋክት፡- እኔ ጥያቄዎቼን ጨርሻለሁ። ቀረ የምትለው
ነገር ካለ እድሉን ልስጥህ?
ታማኝ፡- ብዙ ጊዜ ስለዲያስፖራው ሲነገር
የምሰማቸው ነገሮች አሉ። ‹‹ሰው ሊያስጨርሱ ነው››
እየተባለ ይወራል። ሰው በማለቁ ምን እናተርፋለን?
እኔ በህይወቴ ሙሉ የፓርላማ አባልም ሆነ
ሚኒስትር የመሆን ህልም ኖሮኝ አያውቅም። ሰው
ለማስጨረስ የሚሉት ሰዎች፣ እግረ መንገዳቸውን
ሰው የሚጨርስ መንግስት እንዳለን እየነገሩን
ነው። ዲያስፖራው እንደዚህ አይነት ሀሳብ በፍፁም
የለውም። በሌላ በኩል ማንም ትርፍ ጊዜ የለውም።
ዝም ብሎ ኖሮና ብር አጠራቅሞ፣ ወደ ኢትዮጵያ
በመሄድ በደንብ ተዝናንቶ መመለስ ይችላል። እኛ
ሰዎች በነፃነት ወደ ሀገራቸው መሄድ አለባቸው
ብለን ስለምናምን ነው ይሄን የምናደርገው። እዚህ
ሀገር ትንሹ ክፍያ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ሚኒስትር
የተሻለ ነው። የኢትዮጵያ ባለስልጣን መሆን
ምንድን ነው የሚያጓጓው? ‹ለስልጣን ነው እንዲህ
የሚሆኑት› የሚባለውም ስህተት ነው። በየጊዜው
መንግስት እንዲህ አደረገን ማለት እራሱ ይሰለቻል።
በሌሎች ሀገራት ዜጎች ፊት ያሸማቅቃል። ዋናው
ነገር ይሄን ለመለወጥ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት
ኢኮኖሚው አደገ ሲል፣ ለዕድገቱ ከቡናና ከጫት
ንግድ እኩል የዲያስፖራውም አስተዋፅኦ አለበት።
ፋክት፡- ፋክት መጽሔት አንተን ቃለ-መጠይቅ
ለማድረግ ደጋግማ ደውላ ፍቃደኛ ከሆንክ በኋላ፤
ስልኩን ዘግተህ ራስህ በመደወል የዚህን ያህል ሰፊ
ማብራሪያ ስለሰጠኸን፣ በመጽሔቷ አንባብያን ስም
እጅግ አድርጌ ላመሰግንህ እፈልጋለሁ።
ታማኝ፡- ኧረ እኔ ነኝ የማመሰግነው። እንግዲህ
ይታይህ! እኔ አሁን በእነሱ መለኪያ አዝማሪ
ነኝ። ታዲያ! አዝማሪ ለምን ይፈራሉ? ባለፉት
23 ዓመታት ውስጥ የማስታውሰው፣ የጥበብ
ስራዬን አንድ ጊዜ ብቻ ማሳየታቸውን ነው። እሱም
ስራዬን ለማንቋሸሽ ሲሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
በ1985 ዓ.ም. ያሳዩት ነው። ከዚህ ውጭ በእዚህ
ሁሉ ዓመታት ውስጥ አንድም ቀን በኢትዮጵያ
ቴሌቪዥንና ራዲዮ ስራዎቼ ቀርበው አያውቁም።
ይህን የምልህ አነሰኝ ብዬ አይደለም። የሕዝብ
ቴሌቪዥን ከፍተን ቤታቸው ድረስ ገብቼያለሁ።
በዚህ እደሰታለሁ። ግን ምን ዓይነት መንግስት ነው
ሀሳብ የሚፈራ? እነርሱ ሀሳብ ያስፈራቸዋል። እናም
ይህን እድል ሰጥታችሁኝ፣ ህዝቡን እንዳገኝና ሀሳቤን
እንድገልፅ ስላደረጋችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ። □
No comments:
Post a Comment