Monday, January 27, 2014

መቼ ነው

መቼ ነው?
መቼ ነው ይሄ ቀን - ከኛ ቤት ’ሚያልፈው
ለመኖር መደፋት - ተረት የሚሆነው?
መቼ ነው ወገኔ - መኖር የሚችለው
እንደሰው ለመኖር - ሰውን እሚመስለው?
መቼ ነው ረሃቡ - ተረታሁ የሚለው
እሳቱ እሳት ሁኖ - ኑሮን ’ሚያበስለው?
መቼ ነው ይሄ ቀን - ተረት እሚሆነው
መኖር አለመኖር - መሆኑ እሚያከትመው?
 (አበራ ለማ)


No comments:

Post a Comment