የሰላማዊ ትግል እድገታችን - ግርማ ሞገስ
የዚህ ጽሑፍ ግብ የሰላማዊ ትግል እድገት ከኢትዮጵያ ውጭ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጋቸውን እድገቶች ታሪክ
ማጥናት ነው።
(ሀ) ከኢትዮጵያ ውጭ፥
(1) ከክርስቶስ መወለድ ቀደም ብሎ
ጥንታዊ ሮማውያን ከክርስቶስ ልደት 509 አመቶች ግድም ቀደም ብሎ የነበረውን ፍጹም አምባገነናዊ የዙፋን
አገዛዝ አፍርሰው ረፓብሊክ የፖለቲካ ስርዓት መሰረቱ። ይህ አዲስ ህብረተሰብ ፓትሪሳን (Patrician) እና
ፕሌቢያን (Plebeian) በሚባሉ ሁለት መደቦች የተከፈለ ነበር። ፓትሪሳን የሚባለው መደብ በቀድሞው ንጉሳዊ
ስርዓት የነገስታት እና የባላባት ዝርያዎችን የነበሩትን ያካተተ የገዢዎች መደብ ነበር። ፕሌቢያን (Plebeian)
የተባለው መደብ አናጺውን፣ ብረታ ብረት አቅላጩን፣ መንገድ እና ህንጻ ሰራተኛውን፣ አራሹን፣ ነጋዴውን፣ ምግብ
አብሳዩን፣ በወታደርነት አገልጋዩን እና የመሳሰለውን የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ መደብ ነበር።
በረፓብሊክ የፖለቲካ ስርዓት ህዝብ አስተዳዳሪዎቹን ይመርጣል። ይሁን እንጂ በጥንታዊት ሮማውያን ረፓብሊክ
ጅማሬ ግድም የመምረጥ እና የመመረጥ መብት የነበራቸው ፓትሪሳኖች ብቻ ነበሩ። ፕሌቢያኖች መምረጥም ሆነ
መመረጥ አይችሉም ነበር። የሰራተኛው መደብ የፖለቲካ ነፃነት አልነበረውም ማለት ነው። (እንደ
ህውሃት/ኢህአዴግ አይነቶቹ የዘመናችን አምባገነኖች ደግሞ ከምዕራቡ ዓለም ህጋዊነት ለማግኘት ሲሉ ምርጫ
ይፈቀዱ እና የምርጫውን ኮሮጆ ይቆጣጠራሉ። በሰላማዊ ትግል የምርጫውን ኮሮጆ አምባገነኖች
እንዳይቆጣጠሩት ካልተደረገ ውጤቱ እንደ ሮማዎቹ መሆኑ ነው። ህዝብ ነፃነት የለውም።)
የሆነው ሆኖ ፓትሪሳኖች የሚያስተዳድሩባቸውን ህንጻዎች ሆነ የሚኖሩባቸውን ቤቶች የሚሰሩት ፕሌቢያኖች
ናቸው። ፓትሪሳኖች የሚገለገሉባቸውን የቤት እቃዎች፣ ምግብ ነክ ሸቀጦች፣ የከተማ መንገዶች እና የከተማ ጽዳት
የመሳሰሉትን ሁሉ የሚሰሩት ፕሌቢያኖች ናቸው። ግብር ከፋዮቹም እነሱው ፕሌቢያኖች ናቸው። ለጦርነት
የሚያስፈልጉ ተዋጊ ወታደሮችም ሆነ የከተማ ጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች የሚመለመሉት ከፕሌቢያኖች ነው።
ስለዚህ ይህን ሁሉ ትብብር ፕሌቢያኖች በመለገሳቸው ነው አዲስቱ ረፓብሊክ እንደ ህብረተሰብ መቆም
የቻለችው። ይህን ሁሉ ትብብር በመለገሳቸው ነው ፓትሪሳኖች የመንግስት ስልጣን ባለቤቶች መሆን የቻሉት።
ፕሌቢያኖች የለገሱትን ትብብር ቢነፍጉ ፓትሪሳኖች የሚገዙት ህዝብ ቀርቶ የሚቀምስቱ ምግብ እንኳን
እንደማይኖራቸው ግልጽ ነው። ፕሌቢያኖች እሺ ብለው ካልተገዙ የፓትሪሳኖች መንግስት ሊኖር አይችልም።
ይህን ሁሉ ያስተዋሉ ፕሌቢያኖች ውስጥ ውስጡን የፖለቲካ ነፃነት ውይይት እና ቅስቀሳ ጀመሩ። የጀመሩት
የፖለቲካ እንቅስቃሴ ግብ የፖለቲካ ነፃነት ሲሆን ወደ ሚፈልጉት ነፃነት የሚያደርሳቸው መንገድ ደግሞ
ለፓትሪሳኖች የለገሱትን ትብብር በቀጣይነት መንፈግ እንደሆነ ፕሌቢያኖች ተረድተዋል። ትብብር ለመንፈግ ደግሞ
ወታደር አደራጅተው ከፓትሪሳኖች ጋር የእርስ በርስ ጦርነት ማድረግ እንደማያስፈልጋቸው ፕሌቢያኖች
ተገንዝበዋል። ትብብር ለመንፈግ እንኳን ጦርነት ክፉ ቃል መለዋወጥ እና ጠብ መፍጠር እንደማያስፈልጋቸው
የተገነዘቡት ፕሌቢያኖች የመረጡት የትግል ስልት ሰላማዊ (Non-violent) የፖለቲካ ትግል ነበር። ፕሌቢያኖች ነፃ
የሚያወጣቸው ቡድንም አልፈለጉም። ሰላማዊ የትግል ስልት የራሳቸው ነፃ አውጪዎች አደረጋቸው።
ስለዚህ የፕሌቢያኖች ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የራሳቸውን ህብረተሰብ በመመስረት ለፓትሪሳኖች
ይለግሱዋቸው የነበረውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ወታደራዊ እና የከተማ ጸጥታ ማስከበር ትብብር
በቀጣይነት ለመንፈግ መወሰኑን ይፋ አድርጎ ውሳኔውን መፈጸም ጀመረ። ካለፕሌቢያኖች ትብብር ቀጣይነት
ፓትሪሳኖች የሚመሩት መንግስት ሊኖር እንደማችል ለመረዳት ብዙም አልፈጀባቸውም። የፕሌቢያኖችን የፖለቲካ
ነፃነት ተጨባጭ በሆነ መንገድ በማወቅ እራሳቸውን ከውድቀት አተረፉ። ፕሌቢያኖች የራሳቸውን የአስተዳደር
ተቋሞች መሰረቱ። የፓትሪሳኖች እና የፕሌቢያኖች አስተዳደር ተቋሞች በህብረት ረፓብሊኩን ማስተዳደር ጀመሩ።
ይኽ የሆነው ከክርስቶስ መወለድ 494 አመቶች ቀደም ብሎ ነበር። ከዚህ አጭር ታሪክ ከክርስቶስ መወለድ ቀደም ብሎ ሳይቀር የሰው ልጅ ስኬታማ ሰላማዊ ትግል ማድረጉን
እንገነዘባለን። ሰላማዊ ትግል ግብታዊ መሆን የለበትም። የፕሌቢያውያን ሰላማዊ ትግል ድንገት በግለሰብ የተነሳ
ወይንም ፓትሪሳኖች በአንድ ግለሰብ ላይ በፈጸሙት በደል ህዝብ ድንገት ተቆጥቶ ያደረገው አልነበረም። ግብታዊ
ወይንም ካለበቂ ዝግጅት ወይንም ካለፕላን የሚፈጸም ሰላማዊ ትግል ሊሸነፍ ይችላል። ሰላማዊው ትግል
የተሸነፈበት ምክንያት ግን ትግሉ ሰላማዊ በመሆኑ ሳይሆን በትክክል አለመራቱ ነው። የሆነው ሆኖ ከክርስቶስ
ልደት ወዲህም ስከታማም ስኬታማ ያልሆኑም ብዙ ሰላማዊ ትግሎች ተደርገዋል። ለጥቀን ሰላማዊ ትግል በተለያዩ
ዘመኖች ያደረጋቸውን ንድፈ አሳባዊ እድገቶች እና በአለም ውስጥ የተፈጸሙ ስኬታማ ሰላማዊ ትግሎችን
ለመገንዘብ የሚያስችሉ ጥቂት ታሪኮችን ባጭር ባጭሩ እናጠናለን።
(2) ከክርስቶስ ልደት ወዲህ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ
ከፈረንሳይ አብዮት (1789-1799) ቀደም ብሎ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1500 ዓ.ም. ኤትኔ ዴላ ቧቴይ
[Etienne dela Boetie] የተባለ ወጣት ፈረንሳዊ ፈላስፋ እድሜው ገና 18 ሳለ በጻፈው መጽሐፍ፣ አምባገነን ገዢ
ግለሰብ ህዝብን እንደፈለገው የሚገዛበት የፖለቲካ ኃይሉ (ስልጣኑ) ከግለሰቡ ጋር አብሮ የተወለደ ሳይሆን
ተገዢው ህዝብ የሰጠው (የለገሰው) ነው በማለት አጥብቆ ይከራከር እንደነበር ጂን ሻርፕ የሰላማዊ ትግል ፖለቲካ
በሚለው መጽሐፉ ክፍል 1 ገጽ 10-11 ያመለክታል። ይህ የቧቴይ [Boetie] የክርክር አሳብ ፍሬ እንደሚከተለው
ባጭሩ ሊቀርብ ይችላል፥
“አግባብነት በጎደለው መንገድ አዋርዶ የሚገዛችሁ አምባገነን ግለሰብ ያሉት ሁለት አይኖች፣ ሁለት
እጆች፣ አንድ ሰውነት ብቻ ብቻ ሆኖ ሳለ እናንተ ተገዢዎቹ ግን ያሉዋችሁ አይኖች፣ እጆች እና ሰውነት
ተቆጥረው አያልቁም። ስለዚህ እናንተ ባትተባበሩት ኖሮ አንድ ግለሰብ ብቻውን አዋርዶ ሊገዛችሁ
ባልቻለ ነበር።”
ቧቴይ [Boetie] ክርክሩን በመቀጠል፣ በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነን ገዢዎችን ከስልጣን ለማውረድ ወይንም
ስልጣናቸውን ለመቆጣጠር (ለመገደብ) መፍትሄው ትብብር መንፈግ ነው ማለቱን ጂን ሻርፕ የሰላማዊ ትግል
ፖለቲካ በሚለው መጽሐፍ ክፍል 1 ገጽ 34-35 የገለጸው የቧቴይ [Boetie] ፍሬ አሳብ እንደሚከተለው ሊቀርብ
ይችላል፥
“ስሮቹ አፈር ውስጥ ያልተቀበረ እና ውሃ ያልተሰጠው ዛፍ (ችግኝ) የሚጠጣው ውሃ አጥቶ ደርቆ
(ተርቦ) እንደሚሞት ሁሉ በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖችም የሚታዘዝላቸው፣ የሚተባበራቸው እና
እርዳታ የሚለግሳቸው ህዝብ ባይኖር ኖሮ ልክ እንደዛፉ ተርበው ይሞቱ ነበር። ተርበው እንዲሞቱ
ለማድረግ ደግሞ ኃይል (violence) መጠቀም ቀርቶ ክፉ ቃል፣ ቁጣ እና ጸብ አያስፈልግም።
የተለገሳቸውን ተገዢነት፣ ትብብር እና እርዳታ በሰላማዊ መንገድ በመንፈግ የፖለቲካ ኃይል ምንጫቸውን
አድርቆ በረሃብ እንዲሞቱ ማድረግ ይቻላል።”
እንደ ቧቴይ [Boetie] አሳብ፣ አምባገነኖች ሊበቅሉ፣ ሊለመልሙ፣ ሊያብቡ እና አቅም አግኝተው ህዝብን ሊገዙ
የሚችሉት እራሱ ተገዢው ህዝብ በፍራቻ ወይንም በፈቃደኛነት ከሚለግሳቸው ተገዢነት፣ ትብብር፣ እርዳታ፣
የአገር ተፈጥሮ ሃብት እና ኢኮኖሚ ባለቤትነት የመሳሰሉ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች የሚፈስለትን ምግብ
በመቀለብ ሲሆን ከአምባገነኖች ነፃ ለመውጣት መድሃኒቱ በሰላማዊ ትግል አንድም እነዚህን የፖለቲካ ኃይል
ምንጮች ሙሉ በሙሉ ማድረቅ አሊያም ምንጮቹን በመቆጣጠር ለአምባገነኖች የሚፈሰውን ምግብ መቀነስ
(መገደብ) ነው። በሰላማዊ ትግል የእንግሊዝ አምባገነን ንጉሶች ስልጣን እንደተገደበ ወደፊት ከቦታው ስንደርስ
እናነባለን። እንግዲህ በ16ኛው ክፍለ ዘመን እንኳን የሰላማዊ ትግል ንድፈ አሳብ እድገት እዚህ ደረጃ ደርሶ ነበር
ማለት ነው።
ቧቴይ የ16ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የ18 አመት ልጅ መሆኑን ስንገነዘብ በፈረንሳይ ዘመናዊ (Secular)
ትምህርት መቼ እንደጀመረ እራሳችንን መጠየቃችን አይቀርም። ቀደም ብለን እንዳነበብነው የፓሪስ ዩንቨርስቲ
የተከፈተው በ1100 ዓ.ም. ነበር። ስለዚህ ከ1100 እስከ ባቴይ የመጣበት 1500 ድረስ 400 አመቶች አሉ። ስለዚህ
ዘመናዊ (Secular) ትምህረት የፈረሳይን ህዝብ አስተሳሰብ ማሳደጉን መገንዘብ አያዳግትም። ኢትዮጵያ ለዘመናዊ
(Secular) ትምህርት በሯን የከፈተችው ባፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት በ1942 (እ.አ.አ. 1950) እንደነበር ቀደም
ብለን አንብበናል።
(3) በ18ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ
ከፍ ብለን በፈረንሳይ እንዳየነው ዘመናዊ (Secular) ትምህርት በእንግሊዝ ህዝብም ዘንድ ከፍተኛ የባህል እና
ያስተሳሰብ ለውጥ አስከትሏል። እነ ቧቴይ በፈረንሳይ ስለ ሰላማዊ ትግል ሲጽፉ እና ሲሰብኩ በእንግሊዝም
ተመሳሳይ የፖለቲካ ለውጥ መንገድ የሚጽፉ እና የሚሰብኩ ምሁራን ነበሩ። ስለዚህ በእንግሊዝ የተለያዩ ሰላማዊ
ተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ለፓርላማ መወለድ ምክንያት ሆኑ። ከዚያ ፓርላማው በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበረውን
አምባገነን ንጉስ ስልጣን የሚገድብ ህግ በመደንገግ በ1713 ዓ.ም. እንግሊዝ የመጀመሪያውን ጠቅላይ ምኒስቴር
መረጠች። እንግሊዝ በዘመናዊ የህዝብ መንግስት መተዳደር ጀመረች። ዘውዳዊው መንግስት ኋላቀር አምባገነን
መንግስት ሲሆን አዲስ የተፈጠረው መንግስት ዘመናዊ መንግስት ነው። ዘመናዊ መንግስት መፈጠሩ
ለኢንዱስትሪው አብዮት ተጨማሪ ምቹ ሁኔታ ፈጠረ። በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ ባፄ ባካፋ መተዳደር ላይ ነበረች።
ከፊት ይጠብቃት የነበረው ደግሞ ዘመነ መሳፍንት ነበር።
(4) በ19-20ኛ ክፍለ ዘመን በሩሲያ
በዚህ ዘመን ለሰላማዊ ትግል ፍልስፍና እድገት አስተዋጾ ካደረጉ ታላላቅ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ ፈላስፎች
ውስጥ ሩሲያዊው ሊዮ ቶልስቶይ [Leo Tolstoy] (1828-1910) አንዱ ነበር። ጋንዲ ስለ ራሱ ህይወት ታሪክ
በጻፈው መጽሐፍ ውስጥ “በዘመኑ አለም ያፈራችው ታላቅ የሰላማዊ ትግል ሐዋሪያ ነበር” በማለት ቶልስቶይን
አድንቆ ጽፏል።
“ጦርነት እና ሰላም” (‘War and Peace’) የተሰኘው ልብ ወለድ መጽሐፉ ለሊዮ ቶልስቶይ አለም-አቀፍ ታዋቂነትን
እና ታላቅነትን ካተረፉለት መጽሐፍቶቹ ውስጥ ውናኛው ሳይሆን አይቀርም።
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1908 ዓ.ም. ደግሞ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የህንድ ህዝብ በሺዎች በሚቆጠሩ
እንግሊዞች ቅኝ መገዛቱን አስመልክቶ ከጻፈው ውስጥ ወስዶ ጂን ሻርፕ የሰላማዊ ትግል ፖለቲካ በሚለው
መጽሐፉ ክፍል 1 ገጽ 30 አስፍሯል። በጅን ሻርፕ መጽሐፍ የቀረበው የቶልስቶይ ፍሬ አሳብ እንደሚከተለው
ባጭሩ ሊቀርብ ይችላል፥
“30 ሺ እንግሊዞች የሚያንቀሳቅሱት የንግድ ኩባንያ (ድርጅት) ከ200 ሚሊዮን ህንዶች ላይ አገራቸውን
ነጥቆ ረግጦ እየገዛቸው ነው የሚለው ዜና ለሰሚ ግራ ያጋባል። ማመን ያዳግታል። ከማንኛውም አይነት
አጎል አምልኮት እና ጥንቆላ ነፃ ለሆነ ግለሰብ ይህን ወሬ ወስደህ ብትነግረው ለማመን ይቸገራል።
ለመሆኑ፣ 30 ሺ ሰዎች 200 ሚሊዮን ሰዎችን አሜን ብለው እንዲገዙላቸው አደረጉ ማለት እራሱ ምን
ማለት ነው? ይህ እንዴት ያለ ህንዶች ትብብር ሊፈጸም ይችላል? የህንዶች ትብብር ስለመኖሩ 30 ሺ እና
200 ሚሊዮን የሚሉት ቁጥሮች በግልጽ አይናገሩምን? 200 ሚሊዮን ህንዶች እንዴት በ30ሺ እንግሊዞች
ለመገዛት እንደበቁ እና እንዴት ነፃ ሊወጡ እንደሚችሉ ለመረዳት የእንግሊዞችን ወታደራዊ ኃያልነት
ብቻ ሳይሆን የህንድን ህዝብ የመተባበር እና የመታዘዝ ልማድ እና ባህል ጨምሮ መመርመር
ያስፈልጋል።”
የቶልስቶይ አሳብ፣ የ30 ሺ እንግሊዞች ወታደራዊ ኃያልነት የፈለገው ደረጃ ቢሆንም የ200 ሚሊዮን ህንዶች
የመተባበር እና የመታዘዝ ልማድ ባይኖር ኖሮ የእንግሊዞች ገዢነት ከቶ አይታሰብም የሚል ነው። ይኽ የቶልስቶይ
አሳብ ከፍ ብለን ካነበብነው የፈረንሳዩ ቧቴይ [Boetie] አሳብ ጋር ተመሳሳይ ነው።
በ1909 ዓመተ ምህረት ከላይ የተጠቀሰው የቶልስቶይ ጽሁፍ በእንግሊዝ አገር በህግ ሙያ ሰልጥኖ በደቡብ አፍሪካ
የህግ ጠበቃነት ስራ ላይ ተሰማርቶ እግረ መንገዱን የሰላማዊ ትግልን ፍልስፍና በመፈተን ላይ በነበረው ወጣት
ጋንዲ እጅ ገባ። ጋንዲ ከመደነቁ የተነሳ ጽሑፍን የጻፈው ታዋቂው ቶልስቶይ መሆኑን ለማረጋገጥ ለቶልስቶይ
ደብዳቤ ጻፈ። ቶልስቶይ በ1910 ዓመተ ምህረት ከዚህ አለም በሞት እስከተለየበት ጊዜ ድረስ ከጋንዲ ጋር ደብዳቤ
ይለዋወጡ ነበር።
(5) በ20ኛው ክፍለ ዘመን በህንድ
ጋንዲ (1869-1948) ሰላማዊ ትግልን መጀመሪያ የፈተነው በህግ ጠበቃነት ደቡብ አፍሪካ እየሰራ ሳለ ነበር።
በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የህንዶች ማህበረሰብ ላይ ይፈጸም የነበረውን የዘር አድልዎ በመቃወም በፍርድ ቤት
ጨምሮ። ጋንዲ በተለያዩ በርካታ ጊዚያት በደቡብ አፍሪካ ታስሯል። በሰላማዊ ትግል ፍልስፍና ላይ እምነቱን
ከገነባ እና ስለ ሰላማዊ ትግል አፈጻጸም አሳቡን ካዳበረ በኋላ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1915 ዓ.ም. ወደ ህንድ
ተመለሰ። ወደ ህንድ ሲመለስ የሰላማዊ ትግል ዘዴ እና ባህል በደቡብ አፍሪካም ተሰራጭቶ ነበር።
ጋንዲ ወደ ህንድ ሲመለስ የመጀመሪያው ጥያቄ “እንዴት ሰላማዊ ትግል መጀመር?” የሚለው ነበር። ማንኛውንም
አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመጀመር በአንድ በኩል እንግሊዞችን በከፍተኛ ደረጃ የማያስቆጡ በሌላ ደግሞ
በፍራቻም ይሁን በፈቃደኛነት ትብብር ለግሰው የሚኖሩትን ህንዶች ድጋፍ በቀላሉ ሊያገኙ የሚችሉ ጥያቄዎችን
መቅረጽ የግድ ነው። ስለዚህ ጋንዲ ህንድ እንደተመለሰ ገበሬዎችን፣ የእርሻ ሰራተኞችን፣ የከተማ የቀን ሰራተኞችን
አደራጅቶ እንግሊዞች የጫኑባቸውን የመሬት ግብር እና የዘር አድልዎ በመቃወም ሰላማዊ እንቅስቃሴ በመጀመር
እንዲሰራጭ በማድረግ የሰላማዊ ትግሉን አቅም ለመገንባት ፕላን ነደፈ። አይኑን ከነፃነት ላይ ሳይነቅል!
ስለ ሰላማዊ ትግል ቀደም ሲል የፈረንሳዩ ቧቴይ [Boetie] እና የሩሲያው ቶልስቶይ [Tolstoy] ከጻፉት ጋር
የሚመሳሰል አሳብ ጋንዲ እንደነበረው በ1920 ዓ.ም. ጋንዲ ከጻፈው ውስጥ የጅን ሻርፕ ባልደረባ ሮበርት ሄልቬይ
(Robert L. Helvey) ‘ስትራተጂያዊ ሰላማዊ ትግል ገጽ 96’ በሚለው የምርምር ጽሑፉ ያመለክታል። በሮበርት
ሄልቬይ ጽሑፍ የተጠቀሰው የጋንዲ ፍሬ አሳብ እንደሚከተለው በአጭሩ ሊቀርብ ይችላል፥
“ለህንዶች ባእድ የሆነው የእንግሊዝ ቅኝ ገዥ መንግስትም ሆነ ማንኛውም አይነት አምባገነን መንግስት
ካለ ተገዢው ህዝብ ትብብር ሊገዛ አይችልም።”
ጋንዲ ለነፃነት እና ለዲሞክራሲ ያደረገው ሰላማዊ ትግል ዓብይ ስትራተጂ የመነጨው ከዚህ ስለ መንግስት
ከነበረው ትክክለኛ ግንዛቤ እንደነበር ጂን ሻርፕ የሰላማዊ ትግል ፖለቲካ በሚለው መጽሐፉ ክፍል 1 ገጽ 84 ላይ
ያመለክታል። ስለዚህ ነፃ ለመውጣት ስትራተጂው ትብብር መንፈግ ነው ማለት ነው። እንደ ጋንዲ እምነት፣
በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ቅኝ ገዢም ይሁን ያገር ተወላጅ፣ በስልጣን ላይ ሊቆይ የሚችለው ተገዢው ህዝብ
ለገዢው ቡድን የለገሰውን ትብብር (Cooperation)፣ ታዛዥነት (Obedience) እና አሜን ብሎ መገዛት
(Submission) ሲቀጥል ነው። ተገዢ ህዝብ ለገዢው የለገሰውን ትብብር (Cooperation)፣ ታዛዥነት
(Obedience) እና አሜን ብሎ መገዛት (Submission) በቀጣይነት ከነፈገው ገዢው በስልጣን ላይ መቆየት
አይችልም ማለት ነው።
ስለዚህ መንግስት ካለህዝብ ትብብር በስልጣን ላይ ሊቆይ ስለማይችል እና ትብብር ለመንፈግ ደግሞ ምንም
አይነት ኃይል እና ጭቅጭቅ ስለማያስፈልግ በድስፕሊን በታነጸ ቀጣይነት ባለው ሰላማዊ ትግል የህንድ ህዝብ ነፃ
ሊወጣ ይችላል ማለት ነው። ጋንዲ የመራውም የነፃነት ትግል ይህን አይነት ትግል ነበር። ሰላማዊ ትግል የህንድን
ህዝብ የራሱ ነፃ አውጭ አደረገው ማለት ነው።
ጋንዲ ምኞቱ ወይንም ግቡ ነፃነት ነበር። ግቡን የሚገልጽ ፕሮግራም ጻፈ። ፕሮግራሙን ተፈጻሚ በማድረግ ወደ
ነፃነት የሚያደርሰውን ስትራጂ ከፍ ብለን እንዳየነው ቀየሰ። አያይዞም የትግል ዚደውን መረጠ። ሰላማዊ ትግል
ማለት፥ “(1) አረመኔ የሆኑ ህጎችን ካለፍራቻ መቃወም፣ (2) በራስ ላይ እምነት ማሳደር እና የግል ክብርን
ማስጠበቅ፣ (3) እንግሊዞችን ሆነ የሚተባበሩዋቸውን ህንዳውያን (ፖሊስ፣ ደህንነት እና የጦር ኃይል) መግደል
ተቀባይነት እንደማይኖረው፣ (4) ትግሉ ከስርዓቱ ጋር እንጂ ከግለሰቦች ጋር መሆን እንደሌለበት፣ (5) ቅኝ
ገዢዎችም ሆኑ የሚተባበሩዋቸው ህንዶች ካለ ህንድ ህዝብ ትብብር ስልጣን ላይ ሊቆዩ እንደማይችለ ተገንዝበው
ሰላማዊ እንቅስቃሴውን እንዲቀላቀሉ ማድረግ እና የመሳሰሉ ናቸው” የሚል ትርጉም ሰጠ ለሰላማዊ ትግል ጋንዲ።
ስለ ትብብር እና ድርጅት አስፈላጊነት፣ ስለሴቶች ተሳትፎ አስፈላጊነት፣ ስትራተጂውን ተፈጻሚ ለማድረግ
ዘመቻዎች ስለማስፈለጋቸው ሁሉ ፃፈ ጋንዲ።
ከፍ ብለን እንዳየነው የመሬት ግብር በመቃወም የጀመረው ሰላማዊ ህዝባዊ ተቃውሞ እንቅስቃሴ (ዘመቻ) ቀሰ
በቀስ የቅኝ ገዢውን መንግስት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች በማድረቅ ነፃ ማውጣት የሚያስችሉ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትብብር መንፈግ እንዲሁም ጣልቃ መግባት ሰላማዊ ዘመቻዎች ተሸጋገረ። የህንድ ህዝብ
በመጨረሻ ነፃ ወጣ በሰላማዊ ትግል።
በዚህ አይነት ጋንዲ ሰላማዊ ትግልን ከፍተኛ ደረጃ አደረሰው። የሰላማዊ ትግልን ኃያልነት ለአለም ህዝብ በገሃድ
አሳየ። የብዙ ፖለቲካ ፈላስፎችን እና ተመራማሪዎችን አእምሮ ማረከ። ከእነዚህ ውስጥ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣
ዲዝማንድ ቱቱ እና ጂን ሻርፕ ጥቂቶቹ ናቸው።
ለኒልሰን ማንዴላ (1918-2013) ታላቅነትን ያስገኘለት ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ በሰላማዊ መንገድ የዘር እኩል
አለመሆንን (አፓርታይድ) በማስወገዱ ነው። በቀብሩ ስነ ስርዓት ሰሞንም የውጭ አገር መሪዎች እና ያገሩ
ተወላጆች ባደረጉዋቸው የመታወሻ እና ስንብት ትግግሮች ይህንን ሲያረጋግጡ ነበር። ኒልሰን ማንዴላ እስር ቤት
ሳለ “ጦርነት እና ሰላም” (‘War and Peace’) የተባለውን የቶልስቶይ መጽሐፍ ለማንበብ ፈልጎ ከውጭ
እንዲገባለት የእስር ቤቱን አስተዳዳሪዎች ጥይቆ እንደነበር በማንዴላ እስር ቤት ታሪክ ውስጥ ተዘግቧል።
ለጥቀን ጅን ሻርፕ (Gene Sharp) ለሰላማዊ ትግል ንድፈ አሳብ እና አፈጻጸም እድገት ያደረገውን አስተዋጽዎ እና
ከ20ኛው ከፍለ ዘመን መገባደጃ ወዲህ እና በምንገኝበት 21ኛው ክፍለ ዘመን በአለም ውስጥ ለነፃነት እና
ለዴሞክራሲ የተደረጉ ትግሎችን ስኬታማነት በማገዝ እና በመገዳደል የሚፈጸሙ የፖለቲካ ለውጦችን መጠን ዝቅ
በማድረግ ያደረገውን ተጽዕኖ እናጠናለን።
(6) በ20ኛው መገባደጃ እና ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን በአልበርት አነስታይን ተቋም
ባለንበት ዘመን በአለም ውስጥ በርካታ ታዋቂ የሰላማዊ ትግል ተመራማሪዎች እና ጸሐፊዎች አሉ። ይሁን እንጂ
ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ በሰላማዊ ትግል አምባገነኖችን ከመንግስት ስልጣን በማስወገድ ረገድ
ለተሳኩ ሰላማዊ ትግሎች ቀጥተኛ ጥናታዊ ጽሑፎች በማተም እና ምክሮችን በስልጠና መልክ በመለገስ ረገድ ግን
ቦስተን ከተማ የሚገኘው የአልበር አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም ጎልቶ ወጥቷል። የዚህ ተቋም
ተቀዳሚ ትኩረት የሰው ልጅ ባለንበት ክፍለ ዘመን እንዴት በሰላማዊ ትግል ከአምባገነኖች ነፃ ሊወጣ እና ድሉን
ከቅልበሳ ጠብቆ ወደ አስተማማኝ ዴሞክራሲ መሸጋገር ይችላል? የሚል ሲሆን ሁለተኛው ተዛማጅ ትኩረቱ ደግሞ
በአለም ወስጥ እርስ በርስም ይሁን በአገሮች መካከል የሚፈጠሩ ጦርነቶችን ተቃዋሚ የነበረውን ታዋቂ የፊዚክስ
ሊቅ የአልበርት አነስታይን (1879-1955) ምኞት ተመታሰብ ነው።
ለምን አልበርት አነስታይን የሚል ስያሜ ተሰጠው ተቋሙ? ዝርዝር ውስጥ ሳልገባ ባጭሩ የአቶሚክ ቦንብ
የተፈጠረው በ1905 ዓ.ም. አልበርት አነስታይን ስለ ኢነርጂ (Energy) የቀመረውን ፎርሙላ በመተቀም በመሆኑ
እና አልበር አነስታይን ግን ፎርሙላውን የቀመረው ለአቶሚክ ቦንብ መፈጠር ብሎ ሳይሆን ለሌሎች ሰላማዊ
የሰው ልጅ ኢነርጂ (Energy) ፍጆታዎች ብሎ ነበር። ስለዚህ አለበር አነስታይን ከ1929 ዓ.ም. ወዲህ ጀምሮ
በአለም ውስጥ በአገሮች መካከል ጦርነት ቢነሳ ምንም አይነት ወታደራዊ ግልጋሎት እንደማይሰጥ እና የማንኛውም
አይነት ጦርነት ተቃዋሚ መሆኑን በህትምት ለአለም ህዝብ አሳውቆ ነበር። የፈራው አልቀረም በሁለተኛው አለም
ጦርነት አሜሪካ ፎርሙላውን በመጠቀም አቶሚክ ቦንብ ሰርታ በ1945 ዓ.ም. ሂሮሽማ እና ናጋሳኪ የተባሉ ሁለት
የጃፓን ከተሞችን በአቶሚክ ቦንብ በመምታት ሁለቱ ከተሞች ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ እንዲቀልጥ አድርጋ ጃፓንን
ማሸነፍ ቻለች። ዛሬምም ድረስ በአካባቢው የሚወለዱ ሰዎች የሚዘገንን የአእምሮ እና የአካል ጉድለቶች
አሉዋቸው። ከቦንቡ መሰራት ጀምሮ ጦርነቱን አልበርት አነስታይን ተቃውሟል። አለበር አነስታይን የሰላማዊ
ትግል አማኝ ነበር። ተቋሙ የአልበር አነስታይን መታሰቢያ ተባለው በዚህ ምክንያት ነው።
ተቋሙን የመሰረተው በሃርቫርድ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆነው ጅን ሻርፕ (Gene Sharp)።
ተቋሙ የሚሰራው ለትርፍ አይደለም። ጅን ሻርፕ በ1928 ዓ.ም. ምህረት በኦሃዮ ክፍለ አገር (Ohio State)
ተወልዶ የመጀመሪያ ድግሪዎቹን ከሰራ በኋላ ዶክትሬቱን በኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ ሰራ። የመመረቂያ ወረቀቶቹም
በሰላማዊ ትግል ጥናት እና ምርምር ላይ ያተኮሩ ናቸው። ስለዚህ ጋንዲ በብዙ የዘመናችን የሰላማዊ ትግል
ተመራማሪዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ጅን ሻርፕንም አልማረም ነበር። ጅን ሻርምን የእድሜ ልክ የሰላማዊ ትግል
ተማሪ፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሆን አድርጎታል።
ጅን ሻርፕ የጋንዲን እና አለማችን ከጋንዲ ቀደም ብላ ያፈራቻቸው የሰላማዊ ትግል ፈላስፎች እና አራማጆች ለሰው
ዘር ያበረከቱትን እውቀት አሰባስቦ እና የራሱንም ምርምር ጨምሮ በንደፈ አሳብ እና በአፈጻጸም ሰላማዊ ትግልን
ከፍተኛ ደረጃ አድርሶታል። ብዙ የሰላማዊ ትግል ተመራማሪዎችም አፍርቷል። በዩንቨርስቲም ሆነ በመጽሐፎቹ የሚያስተምረው ሰላማዊ ትግል ነው። የመሰረተው ተቋምም በዘመናችን የሰላማዊ ትግልን መሰረታዊ አሳብ
በተለያዩ የአለም ቋንቋዎች በማሰራጨት አለም አቀፍ እውቅናን አግኝቷል።
የጅን ሻርፕ ስራዎች በከፊሉ የሚከተሉትን ያካትታሉ፥ (1) ከርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የሰው ልጅ ለነፃነት
ያደረጋቸውን ሰላማዊ ትግሎች ታሪክ በማሰባሰብ ረገድ ጅን ሻርፕ ብዙ ጠቃሚ ስራዎች ሰርቷል። (2) ሰለ ሰላማዊ
ትግል ንድፈ አሳብ እና አፈጻጸም ዘመናዊ የሆኑ በርካታ መጽሐፍቶች ጽፏል። ከአምባገነን ወደ ዴሞክራሲ
የሚለው መጽሐፉ በአምባገነን አገሮች ስለሚደረጉ ሰላማዊ ትግሎች ያሉትን አሳቦች ጨምቆ ያቀርባል።
የጅን ሻርፕ እና የባልደረቦቹ ሰላማዊ ትግል ስራዎች በምስራቅ አውሮፓ፣ በላቲን አሜሪካ፣ አሁን በቅርቡ ደግሞ
በግብጽ፣ በየመን፣ በቱኒሲያ እና በቀሩት አረብ አገሮች ህዝቡ የራሱ ነፃ አውጪ በመሆን አምባገነኖችን ከስልጣን
ማስወገድ እና ወደ ዴሞክራሲ መሸጋገር እንዲችል በማድረግ ትልቅ አስተዋጾ አድርጓል። እርግጥ በግብጽ እና
በመሳሰሉት አገሮች ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው ሽግግር አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ምክንያቱ ግን ሰላማዊው ትግል
እና ሰላማዊ ትግል ለውጥ የሚያመጣባቻው ሶስቱ መንገዶች ባለመስራታቸው ሳይሆን የሰላማዊ ትግል መሪዎች
እውቀት ማነስ እና የዝግጅት እጥረት ነው።
የፖለቲካ ኃይል ምንጮች፣ የፖለቲካ ድጋፍ ምሶሶዎች፣ የሰላም ትግል መሳሪያዎች (200 ግድም ደርሰዋል)፣
የሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጫ መንገዶች፣ ህዝብን የራሱ ነፃ አውጭ ማድረግ፣ የሰላማዊ ትግል አቅም መገንባት፣
ሰላማዊ ትግልን ፕላን ማድረግ (ግብታዊ እንዳይሆን)፣ የትጥቅ ትግልን ቆሻሻነት፣ ሰላማዊ ትግል እና መለዮ ለባሽ፣
ሰላማዊ ትግል እና ከተሞች፣ ሰላማዊ ትግል እና ምርጫ (ለምርጫ ፓርቲዎች)፣ ሰላማዊ ትግል እና መፈንቅለ
መንግስት የሚሉት ቁልፍ ጽንሰ አሳቦች በሙሉ ግልጽ በሆነ መንገድ ተተንትነው የተሰራጩት በአልበርት
አነስታይን ተቋም ባልደረባ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ነው። ከስልጠና ክፍል ሁለት ጀምረን እነዚህን ጽንሰ
አሳቦች በሰፊው እናጠናለን።
አንድ ህዝብ ሰላማዊ ትግል እና ምርጫ በመጠቀም የራሱ ነፃ አውጪ ለመሆን የሚሻ ከሆነ የፖለቲካ ኃይል
ምንጮችን ለይቶ ማወቅ እና የፖለቲካ ምንጮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም መገንባት እንደሚያስፈልገው
የሚቀጥለው የሰርቢያ ህዝብ የነፃነት እና የዴሞክራሲ አጭር ታሪክ ያስረዳል፥
በ1990ዎቹ ሰርቢያዎች የአምባገነኑን የሞልሶቪች መንግስት በመቃዋም አጥንት የሚሰብር የክረምት ብርድ
ሳይበግራቸው ሰላማዊ ሰልፎች ያደርጉ ነበር። ይሁን እንጂ በሰላማዊ ሰልፍ ብቻ የሞልሶቪችን መንግስት ከስልጣን
ማስወገድ እንደማይችሉ በመረዳታቸው በሰላማዊ ትግል የሞልሲቪችን መንግስት መጣል የሚያስችላቸው
ተጨማሪ አሳብ ያፈላልጉ ነበር። በዚህን ጊዜ ነበር የሰርቢያ ሰላማዊ ትግል ጎበዝ ስትራተጂስት ስርድጃ ፖፖቪች
(Srdja Popovic) የጂን ሻርፕ ባልደረባ ሄልቬይ (Helvey) ቡዳፔስት (ሃንጋሪ) ውስጥ ሰላማዊ ትግል ስልጠና
በመስጠት ላይ ሳለ የተገናኘው። ስትራተጂስቱ ስርድጃ ፖፖቪች (Srdja Popovic) ለሄልቬይ (Helvey)
ፍላጎቱን ከገለጸለት በኋላ በምላሹ ሄልቤይ (Helvey) የራሱን የስልጠና ስራ ከአምባገነን ወደ ዴሞክራሲ እና የሰላማዊ
ትግል ፖለቲካ (The Politics of Nonviolent Action) ከሚሉትን የጅን ሻርፕን ስራዎች ጋር ጨምሮ እንዲያነብ
መክሮት እና መጽሐፍቶቹን ሰጥቶት ይለያያሉ።
ስርድጃ ፖፖቪች (Srdja Popovic) የተባለውን ካደረገ በኋላ “ጅን ሻርፕ ህዝብን በሰላማዊ ትግል የራሱ ነፃ
አውጭ በማድረግ አምባገነን መንግስትን ማስወገድ የሚያስችል አስደናቂ ስራ ለግሷል።” ይላል። “አስደናቂ
ስራዎች” የሚለው ጅን ሻርፕ የተነተናቸውን 6 የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ምንነት ጨምሮ ማለቱ ነው። ከዚያ
ስርድጃ ፖፖቪች (Srdja Popovic) እና ጉዋደኛዎቹ በጅን ሻርፕ መጽሐፍ ውስጥ በተዘረዘሩት 6 የፖለቲካ
ኃይል ምንጮች ላይ ያተኩራሉ። በመጨረሻም በ2000 ዓ.ም. የተደረግውን ምርጫ ተከትሎ ሞልሶቪች
እንደተለመደው ድምጽ በመስረቅ ምርጫውን ማሸነፉን ቢገልጽም ህዝብ የገዢነት መብት፣ አገር ለማስተዳደር
ከህዝብ የሚያገኛቸውን ትብብር እና ድጋፍ (የሲቪል ሰርቫንቱን ትብብር)፣ የአገር ተፈጥሮ እና ኢኮኖሚ ሃብት
ባለቤትነት የተባሉትን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች በመንፈግ ድምጹን አስከበረ። የኢኮኖሚ ሃብት ባለቤትነቱን
በማጣቱ ለመለዮ ለባሹ የወር አበል መክፈል እንደማችል ግልጽ ሲሆን መለዮ ለባሹ ሞልሶቪችን ከድቶ ህዝብን
ተቀላቀለ። ታማኝነቱን እና ታዛዥነቱን በምርጫ ላሸነፉት ፓርቲዎች መሪ ለገሰ። ሞሊሶቪች ከስልጣን ወረደ።
እነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ህዝብ በፈቃደኛነት፣ ወይንም በፍራቻ፣ ወይንም በግዴለሽነት ለአምባገነኖች
የሚለግሳቸው ናቸው። ስለዚህ ህዝብ የለገሰውን 6 የፖለቲካ ኃይል ምንጮች እንዲነፍግ ለማድረግ የርስ በርስ
ጦርነት (ትጥቅ ትግል) ማወጅ እና ከምስኪኑ መለዮ ለባሽ ጋር ደም መፋሰስ ትክክል አይደለም። እንደ ኢትዮጵያ አይነቱ አገር ውስጥ አብዛኛው ዝቅተኛ ማዕረግ መለዮ ለባሽ እና ተራ ወታደር ወታደርነት የሚቀጠረው እራሱን
ለመመገብ፣ ደሃ እናቱን ለመርዳት እና ልጆቹን ለመመገብ እና ለማስተማር ሲል መሆኑ መታወቅ አለበት።
ለስልጣን ሲባል ከማንም የኢትዮጵያ ጠላት መንደር በተሰበሰበ እርዳታ የኢትዮጵያን ምስኪን ተራ ወታደር ደም
ማፍሰስ ኢሞራል (Immoral) ነው። አምባገነኖችን ከስልጣን ለማስወገድ እንኳን ቦምብ ማፈንዳት፣ ክፉ ቃል
መለዋወጥ እና ጠብ መፍጠር አያስፈልግም። ከ6ቱ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ውስጥ ዋናዎቹን በሰላማዊ ትግል
በመቆጣጠር እና በመንፈግ አምባገነኖችን ከስልጣን ማስወገድ ይቻላል። 6ቱን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ወደፊት
ከቦታው ስንደርስ እናነባቸዋለን። አምባገነኖች አለን ብለው የሚነግሩዋችሁን ያህል አቅም የላቸውም።
(ለ) የሰላማዊ ትግል እድገት በኢትዮጵያ
በዚህ ክፍል በኢትዮጵያ የሰላማዊ ትግልን ታሪክ እና ሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ያደረገውን ትግል እናጠናለን።
(1) በ17ኛው ክፍለ ዘመን የታላቁ እያሱ (ዐፄ እያሱ አንደኛ) ሰላማዊ ትግል
ዐፄ ሠርፀ ድንግል (1556-1590) ወራሪዊቹን ቱርኮች ከምጽዋ ቢያባርር እና ምጽዋን ነፃ ቢያወጣም በኢትዮጵያ
የጦር መሳሪያ ኋላቀርነት እና በተለይም ካፄ ሠርፀ ወዲህ በኢትዮጵያ ለስልጣን የሚደረገው የእርስ በርስ ጦርነት
ስለተባባሰ ቱርኮች ከምጽዋ አልፈው እስከ ድባርዋ ድረስ ተጠናክረው መያዛቸው እና ከድባርዋ እንዲወጡ
ቢደረግም ጣሊያን በ1877 ዓ.ም. በጦር እስከያዘቻት ጊዜ ድረስ ምጽዋ ለ300 መቶ አመቶች ያህል ዘመን በቱርኮች
ስር መቆየቷ ይታወቃል።
ስለዚህ በኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ላይ ቱርኮች የጋረጡትን እንቅፋት ለማስወገድ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ህዝቡ
ታላቁ እያሱ (1674-1698/9) ብሎ የሚጠራው ተወዳጅ ንጉሰ ነገስት በታሪካችን ሰላማዊ ትግል አድርጓል።
ከእያሱ ሰላማዊ ትግል የምንማረው በሰላማዊ ትግል ፍልስፍና እምነት በመመራት ብቻ ሳይሆን የአቅም ጉዳይም
ሰላማዊ ትግል እንድንመር ሊያስገድደን እንደሚችል ነው። ጭንቅላቱ ካለ ማለት ነው! እያሱ ብልህ ሰው ነበር።
የምጽዋን ወደብ በመያዛቸው ቱርኮች ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ቀረጥ እየጨመሩ የኢትዮጵያ ነጋዴ
እንዲጎዳ እና የኢትዮጵያ ውስጥ ንግድ እንዲዳከም አደረጉ። (1) በምጽዋ ያሉት ቱርኮች የሚበሉትን እና
የሚጠጡትን በሙሉ የሚገዙት ከኢትዮጵያ ነጋዴዎች እንደሆነ ታላቁ እያሱ ያውቃል። (2) ቱርኮች ምግብ እና
መጠጣቸውን በጦርነት ማረጋገጥ ከፈለጉ ደግሞ ጦርነት ለማድረግ ሜዳ ወዳለበት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ገባ
ማለት አለባቸው። ቱርኮች መድፍ እና የመሳሰሉት በወቅቱ ዘመናዊ የሚባሉት የጦር መሳሪያዎች ቢኖሩዋቸውም
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ተዋጊ ፈረሰኞች በፈረሰኛ ጋልበው ቱርኮች መካከል እየገቡ ጦርነቱን ወደ ጨበጣ ውጊያ
እየለወጡባቸው ቱርኮችን ደጋግመው ስላሸነፉዋቸው ቱርኮች በኢትዮጵያ ሜዳ ላይ ከኢትዮጵያውያን ጋር መዋጋት
አይፈልጉም። ታላቁ እያሱ እነዚህን ሁለት ሃቆች ያውቃል። ስለዚህ ታላቁ እያሱ ጦሩን ቀደም ብሎ አኩስም እና
ሃሜሴን ላይ አስፍሮ ከትግሬዎች እና ሃማሴኖች ጋር ከመከረ በኋላ ከኢትዮጵያ ወደ ምጽዋ ወደብ ምንም አይነት
ምግብ ነክ ሸቀጥ እንዳይሄድ ዐዋጅ አስነገረ። ቱርኮች የምግብ ምንጫቸው ተዘጋ። በዚህ አይነት ቱርኮችን በአዋጅ
እንዲራቡ በማድረግ ቱርኮችም በተራቸው ከወደቡ የሚያገኙት ጠቀሜታ ዝቅ እንዲል አደረገ። ታላቁ እያሱ
በዐዋጅ የንግድ ልውውጥ እገዳ አደረገ ማለት ነው። ቱርኮች የሚበሉት ተቸገሩ። በደረሰባቸው ችግር ተገደው ወደ
ድርድር መጡ። ከዚህ በፊት የዘረፉትን ሸቀጥ መለሱ። የጫኑትን ቀረጥ አንሱ። በዘመናችንም የዚህ አይነት የንግድ
እቀባ በመንግስታት መካከል የሚደረግ የሰላም ትግል እንደሆነ እናውቃለን። የሰላም ትግል በሚል ባይፈርጀውም
የተደረገውን ዝርዝር ሁኔታ ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ “የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ካፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ”
በሚለው መጽሐፍ ገጽ 179 ላይ በሰፊው ይተርካል። ባጭሩ እንመልከት።
ናይብ ሙሳ የተባለው በምጽዋ እና በአርኪቆ የነበረው የቱርኮች ሹም ብዙ ሸቀጥ እየነጠቀ እና ቀረጥ
እያበረከተ የምጽዋ እና የሐማሴን ህዝብ ንግድ እንዳይነግድ አደረገ። በዚህን ጊዜ ንጉሱ ወዲያው ወደ ሐማሴን
አውራጃ ገዢዎች እና ባላባቶች መልክተኛ ልኮ፥
“ቅቤ፣ ማር፣ እህል ይዞ ከሐማሴን ወደ ምጽዋ ለንግድ ማንም እንዳይሄድ፣ የሄደ ግን ብርቱ ቅጣት ያገኘዋል”
ሲሉ ዐዋጅ ነገረ። በዚህ ዐዋጅ ቱርኮች ታላቅ ችግር ላይ ወደቁ። የአርኪቆ ገዥ ናይብ ሙሳም ወታደራዊ ዘመቻ አድርጎ ዐዋጁን
በኃይል እንዳያስፈርስ ያፄ እያሱ ጦር ሰራዊት ቀደም ብሎ በአክሱም እና በሐማሴን መስፈሩን አስተውሏል።
ምንም እንኳን በመድፉ ቢተማመንም ጦርነት በኢትዮጵያ ምድር ቢጀምር ኢትዮጵያውያን የሽምጥ በፈረስ
ጋልበው በመደፉ መካከል በመግባት ውጊያውን ወደ ጨበጣ ውጊያ እንደሚቀይሩበት ያውቃል። ስለዚህ
ናይብ ሙሳ በቀረጥ ምክንያት የዘረፈውን ሸቀጥ ይዞ ንጉሱ የነበረበት አክሱም ድረስ መጣ። የጨመረውን
ቀረጥ እንደሚያነሳ ቃል ገብቶ ከንጉሱ ጋር እርቅ አደረገ። የዘረፈውን ሸቀጥ ለንጉሱ አስረከበ። ከዚህ በኋላ
የሐማሴን ህዝብ ወደ ምጽዋ፣ የምጽዋ ህዝብም ወደ ሐማሴንም ወደ ትግራይም እየመጣ እንደቀድሞው
እንዲነግድ ስምምነት አደረጉ። ከስምምነቱ በኋላ ናይብ ባሻ ወደ ስፍራው ንጉሱም ወደ ጎንደር ተመለሱ።
እርግጥ ይኽ በታላቁ እያሱ የተደረገው የሰላም ትግል በኢትዮጵያ የተደረገ የመጀመሪያ የሰላም ትግል ነው ከሚል
ድምዳሜ አያደርሰንም። ነገር ግን በኢትዮጵያ የሰላም ትግል መደረጉን ያረጋግጥልናል።
(2) በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ግድም የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን ሰላማዊ ትግል
እነ ነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ (1886-1919) እና የቀሩት በዚያን ዘመን በራሳቸው አነሳችነት
ከሚሲዮናውያን እና ከጎብኚዎች ጋር እየተወዳጁ ውጭ አገር እየሄዱ ተምረው ወደ አገራቸው የተመለሱት
ምሁራን የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ ምሁራን መሆናቸውን ባህሩ ዘውዴ ያመለክታል።
እነዚህ ምሁራን ውጭ አገር ተምረው ሲመለሱ ክብረ ነገስት (The Glory of Kings) የተባለውን መጽሐፍ የዳቦ
ቅርጫት እያለ የሚጠራት አገራቸው የነበረችበት ድህነት እና ኋላቀርነት ደረጃ እጅግ ይጸጽታቸው ነበር።
ኢትዮጵያን እንደ ጃፓን ማድረግ አለብን ይሉ ነበር። ጃፓንን እንደ ሞዴል የመረጡበት ምክንያት ጃፓንም እንደ
ኢትዮጵያ በንጉሰ ነገስ የምትገዛ ደሃ እና ኋላቀር አገር ስለነበረች እና በፍጥነት የምዕራቡን አለም ስልጣኔ ወርሳ
እድገት በማድረጓ ነበር። ይኽን ምኞታቸውን ተፈጻሚ ለማድረግ የሞከሩት በሰላማዊ መንገድ እንጂ በትጥቅ ትግል
አልነበረም። አገሪቱ በዙፋናዊ ገዢዎች እጅ ስለነበረች የመረጡት ሰላማዊ መንገድ የወጣት ሉዑላንን እና
መስፍኖችን አስተሳሰብ በመለወጥ አገሪቱን ወደ ስልጣኔ እና ብልጽግና እንዲወስዷት ማድረግ ነበር። በዚያን ዘመን
ትኩረታቸው በልጅ እያሱ እና በራስ ተፈሪ ላይ ነበር። በራስ ተፈሪ ላይ የሰሩት የመለወጥ ስራ የፈለጉትን ያህል
ለውጥ ባያመጣም በዘመናዊ (Secular) ትምህርት ላይ ለዘመናት ተዘግቶ የነበረውን በር በመጠኑም ቢሆን
በመክፈት ረገድ ውጤት አምጥቷል።
(3) ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ማለቂያ ወዲህ የምርጫ ፓርቲዎች ሰላማዊ ትግል
እንደሚታወቀው ለመደነስ ሁለት ሰው እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለስልጣን የእርስ በርስ ጦርነት ለማድረግም
በጦርነት ማድረግ የሚስማሙ ገዢ እና ተገዢ ፓርቲዎች ያስፈልጋሉ። ዛሬ እንደምናየው ግን በኢትዮጵያችን
ሰላማዊ ትግልን የሚያራምዱ በርካታ ተቃዋሚ የምርጫ ፓርቲዎች አሉን። ይህ የሚያሳየው ለዘመናት ኢትዮጵያን
እጅና እግሯን ተብትቦ የኋሊት ሲጎትታት የነበረው የመገዳደል የመንግስት ሽግግር ባህላችንን ቢያንስ ቢያንስ 50
ከመቶ ያህል ወድቅ ማድረጋችንን ነው። የኋሊት ጎታቹን ጸረ-እድገትና ጸረ-አንድነት የርስ በርስ ጦርነት ለመላቀቅ
እና የስልጣኔን መንገድ ለመጀመር ቢያንስ ቢያንስ ጀምረናል ማለት እንችላለን። እነዚህን የምርጫ ፓርቲዎች
ስናስተውል ኢትዮጵያችን የሰላማዊ ትግል ፍልስፍና እና ባህልን በተቋም ደረጃ መደገፏን እናጤናለን። ይህ
የምስራች የሚያሰኝ ነው። ብዙ ስራ ግን ይቀራል።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ትናንት አምባገነኑ ህውሃት/ኢህአዴግ እንዳደረገው ከጫካ ጠበንጃ አንግቦ ዘው ብሎ
የመንግስት ስልጣን ባለቤት መሆን አይቻልም። ያን ማድረግ ለኢትዮጵያችን የትናንት ታሪክ ሆኗል ብዬ አፌን
መልቼ እናገራለሁ። በአገር ውስጥ ያሉት የምርጫ ፓርቲዎች በአንድ ለሊት ህዝባዊ መከላከል (People’s
Resistance) ሊጠሩ ይችላሉ። ህዝቡም የራሱ ነፃ አውጭ የመሆን ባህል እየገነባ ነው።
በተጨማሪ የሰላም ትግል መሪዎቹን እነ ጋንዲን፣ እነ ማርቲን ሉተር ኪንግን እና እነ ሮሳ ፓርክስን እንደ አርአያ
የወሰዱ በርካታ የኢትዮጵያ ወጣቶች አገራቸውን በሰላማዊ ትግል ለመለወጥ በመታገል ተገቢውን መስዋትነት
መክፈል ጀምረዋል። የአልበርት አነስታይን ተቋም ምርምር ስራዎችንም መተዋወቅ የጀመሩ ኢትዮጵያውያን
ወጣቶች ቁጥራቸው ትንሽ አይደለም። ይህ ሁል ተስፋ ይሰጠናል። ይሁን እንጂ የሰላማዊ ትግል እውቀት ይበልጥ
በህዝባችን ዘንድ እንዲታወቅ ለማድረግ ብዙ መስራት አለብን። በተረፈ የተጫናትን አምባገነን ቡድን በሰላማዊ
ትግል እውቀት እና አቅም ትገነባለች እንጂ ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ኋላቀሩ እርስ በርስ ጦርነት አትመልስም።

No comments:
Post a Comment