አሁንም ዳግም የአይደርን ጭፍጨፋ ለመዘንጋት እንደፍር ይሆን?
(ዮሐንስ ወልደገብርኤል፣ ሪፖርተር ጋዜጣ)
በ1990 ዓ.ም. የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት መቐለ በሚገኘው የአይደር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ክላስተር ቦምብ ያዘነበው
ኤርትራዊው የተዋጊ ጄት ፓይለት በቅርቡ ወደ ጂቡቲ በመክዳት የፖለቲካ ጥገኝነት እንደጠየቀ በርካታ የሚዲያ ዘገባዎች አጋልጠዋል፡፡
ይህ ከአንድ ደርዘን በላይ የሆኑ ሕፃናትን ጨምሮ በ60 ንፁኃን ሲቪል ዜጎች ላይ በፈጸመው ግድያና በሌሎች 168 ሰዎች ላይ ባደረሰው
ከባድ የአካል መጉደል በፈጸመው ጀብዱ፣ በአገሩ መንግሥት እንደ ብሔራዊ ጀግና የሚቆጠረው ሰው ስሙ ሀብቶም ካህሳይ ይባላል፡፡
ሀብቶም ዛሬ እየኖረ ያለው ከኢትዮጵያ ጋር የወንጀለኞች ልውውጥ የሁለትዮሽ ስምምነት ከፈረመችውና በዚሁ ስምምነት መሠረት በርካታ
በሰው ልጆች ላይ ወንጀሎችን በመፈጸማቸው ይከሰሱ ዘንድ ተመልሰው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ባደረገችው አገር ጂቡቲ ውስጥ ነው፡፡
ሀብቶም ወደ ኢትዮጵያ እንዲተላለፍ ለመፍቀድ አሁን ያለው የሕግ ድባብ ከማናቸውም ሳንካ ነፃ ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ በአይደር
ጨቅላ ሕፃናት ላይ የተፈጸመው የአረመኔያዊው ድርጊት ስቃይ አሁንም በተጎጂ ዘመዶች ልቦናና ህሊና ትኩስ ሆኖ ይገኛል፡፡
ያም ሆኖ ግን ሀብቶም ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ ለፍትሕ እንዲቀርብ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ጥሪም ሆነ ጥረቶች አልተሰሙም፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሰብዓዊ መብት ቡድኖች፣ ምሁራንና ሌሎች የዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት
የተፈጸመው አስደንጋጩ ጭካኔ ከሁላችንም የጋራ ትዝታ ወጥቶ እንደተረሳ ሙሉ ለሙሉ ልሳናቸው ተዘግቷል፡፡
በተግባር ለመንቀሳቀስ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ለንፁኃን ተጎጂዎች ፍትሕ ለመጠየቅና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተግባር ጊዜው አሁን
ነው፡፡ ለሰብዓዊ ፍጥረት ላለን የክብር ስሜት ጠንካራ መግለጫ በመስጠት በትምህርት ቤት ሕፃናት ላይ የተፈጸመ የጅምላ ጭፍጨፋ
የጀግንነት ሳይሆን፣ የትም ቢሆን በሕግ ሊያስከስስ የሚገባ ጨካኝ የጦር ወንጀል መሆኑን በተግባር ለማሳየት ወቅቱ አሁን ነው!
ሀብቶም ካህሳይ ለፍትሕ እንዲቀርብ ወደ አገራችን እንዲተላለፍ ጥሪ ለማድረግ ወቅቱ አሁን ነው!
ከታኅሣሥ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያዊያንና የኤርትራዊያን ኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች በሀብቶም ወደ ጂቡቲ የመክዳት ዜና
ተጥለቅልቀው ቆይተዋል፡፡ ይህ ዜና በቅድሚያ የተለቀቀው አፍሪካን ኤክስፕረስ በተሰኘ የወሬ ምንጭ ሲሆን፣ ሌሎች የወሬ ምንጮች
ይህንኑ በመቀባበል አስተላልፈውታል፡፡ የወሬ ምንጩ እንዳጋለጠው ቢያንስ ካለፉት 15 ዓመታት በላይ የኤርትራ አየር ኃይል ፓይለት
መሆኑን የምናውቀው ሀብቶም፣ የአገሩን የአየር ክልል በማለፍ በቦምብ ጣይ አውሮፕላኑ ወደ ጂቡቲ በመብረር ወደ ሌላ አገር የፖለቲካ
ጥገኝነት ለመጠየቅ ዕቅድ እንዳለው ተወስቷል፡፡
በሌላም በኩል ሀብቶም በኢትዮጵያ ላይ ጦርነቱ እንደተነሳ ግንቦት 4 ቀን 1998 ዓ.ም. በትግራይ መቐለ ከተማ በሚገኘው በአይደር
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ቦምብ የመጣል ተልዕኮ ተሰጥቶት ግዳጁን በሚገባ የፈጸመ ፓይለት መሆኑ ተጋልጧል፡፡ ፓይለቱ
በጣለው የክላሰተር ቦምብ ምክንያት አንድ የሦስት ወራት ጨቅላ ሕፃንን ጨምሮ ሰባት ከአንድ ዓመት አስከ አራት ዓመት ዕድሜ ያላቸው
ሕፃናት፣ 18 ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱ ልጆችን ጨምሮ 53 ሰዎች ወዲያውኑ ተገድለዋል፡፡
የሀብቶም መክዳት ወሬ ከተዘገበ ጀምሮ እነሆ ሁለት ሳምንታት ያለፉ ሲሆን፣ አስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ መንግሥት ዘንድ በይፋ የተሰጠ አስተያየትም ሆነ ዕርምጃ የለም፡፡
የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሆነ የፍትሕ ሚኒስቴር ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ በዚህ እጅግ ጠቃሚና አልፎ አልፎ በሚፈጸም
ክስተት ላይ መንግሥት ሊወስደው እያሰበ ስላለው ዕርምጃ የሚጠቅሱ ወይም ጠቋሚ ፍንጮች የሉም፡፡ በበኩሌ በመንግሥት፣
በደጋፊዎቹ፣ በሲቪል ማኅበረሰቡና በአገሪቱ የሕግ ሙያተኞች ዘንድ ያለው ፍፁም የሆነ ዝምታ ሙሉ ለሙሉ ግራ የሚያጋባ ሆኖብኛል፡፡
የሰብዓዊ መብት ቡድኖችም ቢሆን በጉዳዩ ላይ ፈዝዘዋል፡፡ በሲቪል ዜጎቻችን ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ የፈጸመው ተጠርጣሪ የፖለቲካ
ጥገኝነት ጥያቄ በማቅረብ የሕግ ጥበቃ እየጠየቀ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ እንደምን አድርጎ የአምነሲቲ ኢንተርናሽል ዕርምጃን ላያነሳሳ ሳይችል
ቀረ?
የካቲት 24 ቀን 1991 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግሥታት መካከል የነበረው ጦርነት ለመገባደድ እየተቃረበበት በነበረበት ጊዜ
አጠቃላይ ድሉ በኢትዮጵያ ኃይሎች እጅ መሆኑ መታየት ሲጀምር፣ ‹‹አይደርን ለመዘንጋት እንደፍር ይሆን?›› በሚል በሪፖርተር
የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ‹‹ጆን ወ›› በተሰኘው የብዕር ስሜ አንድ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚህ ጽሑፌ ላይ በአይደር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በአካባቢው ላይ የኤርትራ አገዛዝ የፈጸመው አድራጎት ተፈጻሚነት ያላቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕጎች ተብለው የሚጠሩትን
እ.ኤ.አ የ1949 ዓ.ም. የጄኔቫ ኮንቬንሽንና ተጨማሪ ፕሮቶኮሎች ጋር አጣምሬ በመተንተን ‹‹ከባድ ጥሰት›› መፈጸሙን በማረጋገጥ
ተከራክሬ ነበር፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአይደር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የቦምብ ናዳ በማውረድ 60 ሰዎችን፣ ሕፃናት ተማሪዎችን ጨምሮ
በመግደልና ሌሎች 168 ሲቪል ሰዎችን አካል በማጉደሉ ‹‹ከባድ ጥሰት በመፈጸም ወይም ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠሩ ሰዎች
ዜግነታቸው ምንም ይሁን ምንም ታድነው ለፍርድ ለማቅረብ›› የ1949 የጄኔቫ ኮንቬንሽን ግዴታ ይጥላል፡፡
በወቅቱ የእኔ የአጭር ጊዜ ሥጋት የነበረው ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ባገኘችው ድል ምክንያት በተፈጠረው ሐሴት መሀል የአየር ጥቃት
ሰለባ በሆኑት ላይ የጦር ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች ክስና የወንጀል ፍትሕ ጉዳይ እንዳይረሳና ቸል እንዳይባል ወይም ለደርድር አንዳይቀርብ
የሚል ነበር፡፡
እንደተገመተው የተሸነፈውና የተርበደበደው የኤርትራው መሪ በድንገትና በሥልት በአግባቢዎችና በአፍሪካ ኅብረት የቀረበውን የጦርነት
ማቆም ስምምነት ፈረመ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ስምምነት የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚለውን ጉዳይ አይመለከትም ነበር፡፡
በዚህም ምከንያት ‹‹ማንኛውም የሰላም ስምምነት፣ የጦርነት ማቆም ወይም ማንኛውም የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራ ጋር
የሚፈራረመው ጊዜያዊና ዘላቂ ጦርነት እንዳይካሄድ የሚደረግ ስምምነት የጦር ወንጀል ተጎጂዎችን ችላ የሚል ከሆነ ግቡን አይመታም፤››
በማለት ገልጬ ነበር፡፡
በዚያን ወቅት የኤርትራን የጦር ወንጀለኞች አፈላልጎ በመያዝ በአገር ውስጥ ወይም በዓለም አቀፍ ችሎት ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን
ተግባራዊ ችግር በሚገባ አውቅ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ‹‹በመጀመሪያ ሲታይ ከአገር ውጪ የሚኖሩ የጦር ወንጀለኞችን በተለይም ባለሥልጣናትን በአገር ውስጥም ሆነ በሌላ
በተሰየመ ዓለም አቀፍ ችሎት ለማቅረብ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢመስልም፣ መንግሥታችን ተገቢውን ጥረት አድርጎ ከበድ ያለውን
ግዴታውን መወጣት አለበት፡፡ በኤርትራ አየር ጥቃት የሞቱትንና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን፣ ወንድሞችና
እህቶች በመገናኛ ብዙኃን በማሳየትና በበራሪ ወረቀቶች ላይ አትሞ በማውጣት ሕዝብ እንዲያውቃቸው ማድረጉ ብቻውን በቂ አይደለም፡
፡ ከይስሙላ ያለፈና ትርጉም ያለው ጠንከር ያለ ሕጋዊ ዕርምጃ በተቻለ ፍጥነት መወሰድ አለበት፤›› በሚል ተከራክሬ ነበር፡፡
ኅዳር 29 ቀን 1993 ዓ.ም. ሁለተኛው ፓርላማ ባልተለመደ ሁኔታ ዓርብ ከሰዓት በኋላ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበለትና
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረውን ጦርነት ለማቆም በተዘጋጀ ረቂቅ ስምምነትና የሕግ ረቂቅ ላይ ተነጋግሮ ለማፅደቅ ተሰበሰበ፡፡
በወቅቱ ከ557 የፓርላማው አባላት መካከል 447 ያህሉ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ነበር፡፡
ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለፓርላማው የቀረበውን የመጨረሻውን የስምምነት ቅጂ ከመገባደዱ በፊት በኢትዮጵያና በኤርትራ
መንግሥታት መካከል የተደረገውን ውይይት፣ ድርድርና የአግባቢዎችን ጥረቶች በተመለከተ ዝርዝርና ሰፋ ያለ መግለጫ ለፓርላማው
አቀረቡ፡፡
ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ መግለጫ በኋላ ተቃዋሚው የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የፓርላማ ተመራጭ የነበሩት አቶ
ሰይፉ ሰብስቤ የፓርቲያቸው አቋም መሆኑን በመግለጽ በንባብ ስሜት የሚቀሰቅሱ ነቀፋዎችን በረቂቅ ስምምነቱ ላይ አቀረቡ፡፡ በረቂቅ
ስምምነቱ ላይ በፓርቲያቸው ከተነሱት አምስት ነጥቦች መካከል ‹‹ሻዕቢያ በአይደር ትምህርት ቤት ሕፃናት ላይ ለፈጸመው ጭፍጨፋ
የሕይወት ካሳ ከመክፈል ባሻገር በጦር ወንጀለኝነት እንዲጠየቅ የሚሉት ነጥቦች በዝርዝር መካተት ይኖርበታል፤›› የሚለው ይገኝበታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ግን በዚህ ሐሳብ አልተስማሙም፡፡ ምክንያታቸውንም ሲገልጹ፣ የጦር ወንጀለኝነትን በተመለከተ እርሳቸው
አስከሚያውቁት ድረስ ከመማረኩ በፊት በጦር ወንጀለኝነት ተይዞ ፍርድ ቤት የቀረበ መሪ አለመኖሩን፣ ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች የኢራቁን
ፕሬዚዳንት (ሳዳም ሁሴን) እና የዩጎዝላቪያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ስሎቮዳን ሚሎሶቪችን የጦር ወንጀለኞች ናቸው የሚል አቋም
ቢኖራቸውም፣ እነዚህን መሪዎች ፍርድ ቤት ለማቅረብ መማረክ እንደሚጠይቅ፤ ይህ ማለት ግን የኤርትራ መሪዎች የጦር ወንጀለኞች
አይደሉም ማለት ባለመሆኑ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሻዕቢያ መሪዎች በጦር ወንጀለኝነት እንዲጠየቁ ያሳለፈውን ውሳኔ
ትክክለኝነትና ለፍርድ መቅረብ እንደሚኖርባቸው በመንግሥት ዘንድ እንደሚታመን አስረድተው ነበር፡፡ አክለውም ‹‹በዚህም ምክንያት›› ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩ፣ ‹‹ይህን ጉዳይ በመደራደሪያነት ማቅረብ አላስፈለገም፡፡›› አቶ
ሰይፈ ለማ የተባሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣንና የሕግ ባለሙያም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ጋር እንደሚስማሙ በመግለጽ፣
በሥልጣን ላይ ያለ መሪ በጦር ወንጀለኝነቱ ለፍርድ ማቅረብ የሚቻል ቢሆን ኖሮ ሳዳም ሁሴን ቀዳሚ ይሆኑ እንደነበር፣ ምክንያቱም
ኢራቅ ኩዌትን በወረረች ጊዜ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ኃያላን መንግሥታት ኢራቅን በኃይል ካስወጡ በኋላ ሳዳም ሁሴንን በጦር
ወንጀለኝነት ከመፈረጅ አልፈው ለፍርድ ሊያቀርቧቸው አለመቻላቸውን አመልክተዋል፡፡
የተሰጠው መግለጫ በቂ ባይሆንም ሪቂቅ ስምምነቱ ግን በአብዛኛው የፓርላማው እንደራሴዎች ተቀባይነት አግኝቶ ፀድቆና ረቂቅ አዋጁም
‹‹በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በኤርትራ መንግሥታት መካከል የተደረገ የሰላም ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ ቁጥር
225/1993›› ተብሎ ወጥቷል፡፡
ከአራት ቀናት በኋላ ማለትም ታኅሣሥ 2 ቀን 1993 ዓ.ም. የተዋጉት ሁለቱ አገሮች መሪዎች ጎን ለጎን በመቀመጥ ኋላ ላይ ‹‹የአልጀርስ
ስምምነት›› የተባለውን የሁለቱንም አገሮች ሉዓላዊነት ለማክበርና በሁለቱም አገሮች መካከል የነበረውን ጦርነት ለዘለቄታው ለማቆም
ቃል የተገባበትን ሰነድን ፈረሙ፡፡ ስምምነቱ ከዚህ በተጨማሪ የድንበር ጉዳዮችንና በጦርነቱ ምክንያት ከሚነሱት የካሳ ጥያቄዎች ጋር
በተያያዘ ገለልተኛ የግልግል ኮሚሽኖች እንደሚቋቋሙ ይገልጻል፡፡
በአልጀርስ ስምምነት መሠረት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት የግልግል ችሎቶች እንዲቋቋሙ ተደርጎ በዚህም
ምክንያት በጊዜው በሁለቱም አገሮች መካከል የነበረው ደም ያፋሰሰውና ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ጦርነት ወደ ‹‹ድንበር ግጭት›› እና
‹‹የካሳ ጥያቄ›› ጭብጦች እንዲወርድ ተደረገ፡፡ ምንም እንኳን በፓርላማው በነበረው መግለጫ ላይ ወደፊት የሻዕቢያ መንግሥት ሠራዊት
ቅነሳ (Demilitarization) እና የመልካም ጉርብትና (Normalization) የተለያዩ ስምምነቶች እንዲያደርግ መታቀዱ የተገለጸ ቢሆንም፣
እነኚህ ስምምነቶች ግን እስካሁን ድረስ አልተደረጉም፡፡
የኢትዮጵያ ፓርላማ አስቀድሞ የኤርትራ መሪዎችን የጦር ወንጀለኞች ናቸው በማለት ሰይሞ በጦር ወንጀል ችሎት እንዲቀርቡ የጠየቀ
ቢሆንም፣ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ እንደራሴዎቹ ግን ይህ የቀድሞው ውሳኔያቸው ተፈጻሚ እንዲሆን በሚያስችለው ረቂቅ የአልጀርስ
ስምምነቱ ውስጥ እንዲካተት ሳይወስኑ ቀርተዋል፡፡
በውጤቱም ምንም እንኳን የአልጀርስ ስምምነት ስለዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ፣ ስለ 1949 የጄኔቫ ስምምነትና የጦር ጉዳተኞች
እንዲሁም የጦር ምርኮኞች ልውውጥ ሕግጋቶችን ቢያጣቅስም፣ ስለጦር ወንጀል ተጠርጣሪዎች የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ፍርድ የመቅረብ
ጉዳይ በአጠቃላይ ስለአይደር በቦምብ መጠቃት በተለይ የሚገልጸው አልነበረም፡፡ በድኅረ ጦርነት ጊዜያትም ይህ ነገር የኢትዮጵያ
መንግሥት ዋና ተግባር ወይም ጉዳይ አልነበረም፡፡
በኢትዮጵያና በኤርትራ የካሳ ኮሚሽን ቀርበው ከነበሩት በርካታ የካሳ ጥያቄ ጉዳዮች ውስጥ ‹‹የመቐለው የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት
ጉዳት›› ይገኛል፡፡ የካሳ ኮሚሽኑ ኤርትራን ‹‹በግንቦት ወር 1990 ዓ.ም. በመቐለው የአይደር ትምህርት ቤት ላይ ከጦር አውሮፕላን
በተጣሉ የክላስተር ቦምቦች በጦርነት ላይ ያለን መብትን መጣሷን ማረጋገጡ››፣ በመቀጠልም ኮሚሽኑ እንዳመለከተው ‹‹ምንም እንኳን
ኤርትራ ስለተገደሉትና አካላቸው ስለጎደሉ ሰዎች ቁጥር ባትከራከርም›› ለእያንዳንዱ ተጎጂ በቀረበው የካሳ ጥያቄ የገንዘብ መጠን ላይ ግን
እንዳልተስማማች አመልክቷል፡፡
የካሳ ኮሚሽኑም ‹‹በዓለም አቀፍ ሕግ ላይ የተፈጸመውን ከባድ ጥሰት የያዘውን ውጤት በመከተልና ከግምት ውስጥ በመክተት ኮሚሽኑ
በመቐለ የአይደር ትምህርት ቤት ላይና አካባቢ በተጣሉት የክላስተር ቦምቦች ምክንያት ለተፈጸመው የሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የሕክምና
ወጪና በንብረት ላይ ለደረሰው 2.5 ሚሊዮን ዶላር ፈርዷል፤›› በማለት ደምድሟል፡፡
የፍትሐ ብሔር ኃላፊነት የወንጀል ኃላፊነት ሊያስከትል አይችልም፡፡ ምክንያቱም በወንጀል ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ የማስረዳት ሸክምን
ይጠይቃል፡፡ ሆኖም የኮሚሽኑ ግኝት እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ኤርትራ በአየር ጥቃቷ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ሕጎችን
መጣሷን አረጋግጧል፡፡ በኤርትራም በኩል በካሳ ኮሚሽኑ ፊት ስለሞቱትና አካላቸው ስለጎደሉ ሰዎች በማስተባበል የቀረበ ምንም ዓይነት
ክርክር የለም፡፡ ይልቁንም ኤርትራ ለአድራጎትዋ ኃላፊነት ወስዳለች፡፡
በአይደር ትምህርት ቤትና አካባቢው ለተፈጸመው ከባድ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት የሕግ ጥሰት የኤርትራ መንግሥት ኃላፊነቱን ወስዶ
የጉዳት ካሳ መጠኑ ተወስኗል፡፡ ለተፈጸመው የወንጀል ድርጊት የግል ተጠያቂነትን በተመለከተ አድራጊዎቹ ተይዘውና ምርመራ
ተካሂዶባቸው በፍርድ መወሰን ይገባዋል፡፡ በዚህ ረገድ የካሳው ኮሚሽን ፍርድ ምርመራውን ለመጀመርና ክስ ለማቅረብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ በተጠርጣሪው ወንጀለኛ ላይ የምትወስደው ዕርምጃ የዓለም አቀፍ ድጋፍና ተቀባይነት እንዲኖረው
ለማድረግ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
ሀብቶም አገሩንና መንግሥቱን በመክዳት ጂቡቲን ጥገኝት ጠይቋል፡፡ እንደ ዜና ዘገባዎች፣ በአይደር በሲቪል ዒላማዎች ላይ የክላሰተር
ቦምቦችን በመጣል በትምህርት ቤት ሕፃናትና ሲቪሎች ላይ አሰቃቂ ግፍና የአካል ማጉደል የፈጸመው ይህ ሰው ነው፡፡
ይህ ተጠርጣሪ አሁን የሚገኘው በጂቡቲ ሲሆን ጂቡቲ ደግሞ ኢትዮጵያ ወንጀለኛን አስተላልፎ ለመስጠት የሁለትዮሽ ዓለም አቀፍ
ስምምነት ከተፈራረመቻቸው ሁለት አገሮች አንዷ ነች፡፡ የኢትዮጵያና የጂቡቲ መንግሥታት ወንጀለኛን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት
ያደረጉት ሚያዚያ 28 ቀን 1986 ዓ.ም. ነበር፡፡ ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ፓርላማ አዋጅ ሆኖ በመፅደቅ አዋጅ ቁጥር 104/1987 ተብሎ
የአገሪቱ ሕግ ሆኖ ወጥቷል፡፡
የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበረውና አሁን አንደገና የብሔራዊ መረጃና ደኅንት አገልግሎት በሚል በድጋሚ የተደራጀው መሥሪያ
ቤት በአዋጁ መሠረት ‹‹ስምምነቱን በሥራ ላይ የማዋል ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡››
በዚህ ስምምነት መሠረት በዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ በተፈጸመ ወንጀል ተከሰው የነበሩ የደርግ መንግሥት ባለሥልጣናት
ተላልፈው ከጂቡቲ ለኢትዮጵያ እንዲሰጡና የክስና የፍርድ ሒደታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል፡፡ ይህ ስምምነት ከቅርብ ዓመታት በፊት
ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ከድተው ወደ ጂቡቲ ገቡ የተባሉ ፓይለቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲተላለፉ ለማድረገ የሕግ መሠረት መሆኑ
የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ይሁን እንጂ ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት ምን እያከናወነ እንዳለ ለማወቅ ግልጽ አይደለም፡፡ ታሪካዊ የሆነውንና የኤርትራን መሪዎችን በጦር
ወንጀለኝነት በመፈረጅ ውሳኔ ሰጥቶ ላለፉት 15 ዓመታት በውሳኔዎች መደርደሪያ ላይ ሰቅሎት የቆየውን ዛሬ አንዱ በውሳኔው የሚሸፈነው
ተጠርጣሪው ወንጀለኛ አፍንጫው ድረስ መጥቶ ሳለ፣ እንዴት አድርጎ የቀድሞውን ውሳኔውን ለማስፈጸም እንደተዘጋጀ ፓርላማው
ማንኛውንም ዓይነት መግለጫ አልሰጠም ወይም የአፈጻጸም ዕቅዱንም አልገለጸም፡፡
ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምሳሌም የኢዴፓ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ፓርቲና የግል
ተመራጭ የነበሩት አቶ በድሩ አደምን የመሳሰሉት የአልጀርስ ስምምነት በፓርላማው ለመፅደቅ ሲቀርብ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያቀርቡ
የነበሩት በሙሉ፣ ዛሬ በሚያሳዝን ሁኔታ ጭጭ ማለታቸው አስገራሚ ሆኖ ይታያል፡፡
ከዚህም በከፋ ሁኔታ ለትግራይ ሕዝብ የታገልኩኝና የትግራይን ሕዝብ እወክላለሁ የሚለውም ሕወሓት ስለሀብቶም ተላልፎ መሰጠት
የገለጸው ነገር የለም፡፡ የአይደር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝበት የመቐለ ከተማ የሕዝብ እንደራሴዎችም የተነፈሱት አንድም ቃል
የለም፡፡
የሚያስገርመው አሳዛኙ የአይደር ጭፍጨፋ በትግራይም ሆነ በሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ ቁጣን የቀሰቀሰና ኢሕአዴግ መር በሆነው
መንግሥት ላይ ቅሬታ የነበራቸውን ኢትጵያዊያንን ጭምር ለአገራቸው አንድ አቋምና ድጋፍ እንዲሰጡ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ
አይደር በወቅቱ የመላውን ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ለማሰባሰብ ቁልፍ ሚና እንዳልተጫወተ ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ ይህ ሁሉ የተረሳ
ይመስላል፡፡
ግራ በሚያጋባ ሁኔታ በደርግ ዘመነ መንግሥት በአየር ጥቃት ወደ ሁለት ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች በተገደሉባት ሐውዜን ከተማ የክልሉ
መንግሥት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት በየዓመቱ ቀኑ ለሞቱት ሰዎችና ለሌሎችም ተብሎ የሰማዕታት ቀን ተብሎ እንዲታወስ ቢደረግም፣
አይደር ግን በዚህ መንገድ አልታወሰችም፡፡ የክልሉ መንግሥት ይህንን ያደረገው ምናልባት የኢትጵያንና የኤርትራን የመልካም ጉርብትና
ግንኙነት ሊጎዳ ወይም ሊያውክ ይችል ይሆናል ብሎ እንደሆነ መጠርጠር ይቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጣሊያን ፋሺስቶች በ1929 ዓ.ም.
በአዲስ አበባ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በየዓመቱ መከበሩ በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት አላወከውም፡፡
በአሜሪካ በፐርል ሃርበር ላይ የጃፓን ካሚካዘስ ኅዳር 28 ቀን 1934 ዓ.ም. በአሜሪካ የባህር ኃይል ላይ በሰነዘረው ጥቃት 2,400 ሰዎች
የተገደሉበትና ከ1,200 ሰዎች በላይ ደግሞ የቆሰሉበትን ጨምሮ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የሁለተኛ ዓለም ጦርነት መታሰቢያዎች አሉ፡፡ ይህ
ጥቃት በየዓመቱ በአሜሪካ የሚከበር ቢሆንም፣ በአሜሪካና በጃፓን መካከል ያለውን ግንኙነት እስከ ዛሬ ድረስ ጤናማ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
አስካሁን ድረስ የካሳ ኮሚሽኑ ከወሰነው ከ2.5 ሚሊዮን ዶላር ላይ የአይደር ተጎጂ ቤተሰቦች ሳንቲም ያላገኙበት ምክንያት ለምን እንደሆነ
አይታወቅም፡፡ ይህም ሆኖ ግን ጭራሹኑ ዛሬ ይህንን ጭፍጨፋ ማድረጉ የሚጠረጠረው ፓይለት ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ እንዲመጣ
ምንም ጥረት አለመደረጉን ስንመለከት፣ ምናልባት የአይደር ተጎጂዎች ፍትሕ ሊነፈጉ ይችሉ ይሆናል የሚል ግምት ፈጥሯል፡፡ ዕውን ሕዝባችንና መንግሥታችን ለሕግና ለፍትሕ ማናቸውም ዓይነት አክብሮት አላቸውን? ለእነዚህ ሕፃናት፣ ተማሪዎችና ንፁኃን ሰላማዊ
ዜጎቻችን አሰቃቂ ጉዳይ እንደ ሰብዓዊ ፍጥረትና ኢትዮጵያዊያን እኛ ምንም ምላሽ አለመስጠታችን የፍትሕ መርሆዎችንና ሰብዓዊ
መብቶችን ለማስከበር በግልጽ ያለብንን ደካማና የተሸመደመደ አቋም ያመለክታል፡፡
ሀብቶም በአገሩ ብሔራዊ ጀግና ተደርጎ ተቆጥሮ ምናልባትም ለአድራጎቱ በአምባገነኑ የኤርትራ መንግሥት እንደ ጀብዱ ተግባር
ተሸልሞበት ይሆናል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ አገዛዙን ለሚቃወሙ ለኤርትራ ዜጎችም፣ አገዛዙን በመቃወም በድፍረት የመክዳት ውሳኔ የወሰነ
ጀግናም ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡
ነገር ግን እንደማናቸውም ሰብዓዊ ፍጥረት አብዛኛዎቹ ኤርትራዊያን በአይደር የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊት በአዎንታ ይቀበሉታል የሚል
እምነት ፈፅሞ አይኖረኝም፡፡ ማንም ራሱን የሚያከብር ኤርትራዊ በሕፃናት ላይ ግድያን በመፈጸምና አካል በማጉደል የሚጠረጠር
ኤርትራዊ ምርመራ ተደርጎበት ለፍርድ መቅረቡን የሚቃወሙ ያሉ አይመስለኝም፡፡
ጂቡቲ እ.ኤ.አ በ1949 የወጡ የጄኔቫ ኮንቬንሽንና ተጨማሪ ፕሮቶኮሎቹን ካፀደቁት 195 አገሮች ውስጥ አንዷ ነች፡፡ በዚህ መሠረት
‹‹ከባድ ጥሰት በመፈጸም ወይም ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠሩ ሰዎች ዜግነታቸው ምንም ይሁን ምንም ታድነው ለፍርድ ለማቅረብ››
የሕግ ግዴታ አለባት፡፡ በመሆኑም ከኢትዮጵያ መንግሥት ምንም ዓይነት ኦፊሴላዊ ጥያቄ ባይቀርብላትም እንኳን ጂቡቲ የጦር ወንጀሎችን
ከመመርመርና በጦር ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ለፍርድ ከማቅረብ ከተጣለባት ዓለም አቀፍ ግዴታዋ ራሷን ማሸሽ አትችልም፡፡
በመሆኑም የጂቡቲ መንግሥት ለሀብቶም የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ መስተንገዶ ማቅረብ ሳይሆን ማድረግ ያለባት ዓለም አቀፍ ግዴታዋን
ለመፈጸም አስፈላጊውን ዕርምጃ መውሰድ ነው፡፡
ሟቹ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ለፓርላማው እንደሰጡት መግለጫ ሳይሆን፣ የሳዳም ሁሴንንና የስሎቮዳን ሚሎሶቪችን መያዝ፣
መመርመርና በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ችሎቶች ለፍርድ መቅረባቸውን በሕይወት ዘመናቸው ለማየትና ለመመስከር በቅተዋል፡፡
እነኚህን ሰዎች መማረክ አስቸጋሪ በሆኑባቸው ጊዜያት የጦር ወንጀለኞች ተብለው መሰየማቸው በኋላ ለተከናወኑት የመያዝ፣
የመመርመር፣ የመከሰስና ለፍርድ የማቅረብ ሒደት በከፍተኛ ደረጃ ጠቅሟል፡፡
የኢትዮጵያ ፓርላማ በተመሳሳይ ሁኔታ የኤርትራን ባለሥልጣናት ከዓመታት በፊት የጦር ወንጀለኞች በማለት ሰይሟቸዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ
በጣም የተመቻቸ የሕግ ከባቢያዊ ሁኔታዎችና የሸሹ ወንጀለኞችን ለመያዝና ለኢትዮጵያ ለማስረከብ በጂቡቲ በኩል የተሟሉ ቅድመ
ሁኔታዎች አሉ፡፡ ቢያንስ ሀብቶምን እንደ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ለመያዝና ለመማረክ ተግባራዊ ማነቆ የለም፡፡ ምክንያቱም የሚገኘው ጂቡቲ
በመሆኑ ከረዥሙ የሕግ ወጥመድ ሊያመልጥ አይቻለውም፡፡ የሀብቶም መያዝ፣ መመርመር፣ መከሰስና ለፍርድ መቅረብ ደግሞ የሕፃናቱና
የሰላማዊ ዜጎቻችን የጭፍጨፋ መነሻ፣ ዓላማው፣ የተፀነሰብትም ምክንያት ክፉም ይሁን ደግ እውነታው አደባባይ እንዲወጣ ያደርገዋል፡፡
ፍትሕ ማለት ደግሞ እውነትን ለአደባባይ ማውጣት እንጂ እውነትን መቅበርና ማድበስበስ ማለት አይደለም፡፡ በመሆኑም ሀብቶምን
ለፍትሕ የማቅረብ ተጨባጭ ዕርምጃ መውሰዱ ‹‹የመለስን ራዕይና ውርስ እንተገብራለን›› በሚል ቃል ለገቡ የተተወ ኃላፊነትም ጭምር
መሆኑ ልብ ይሏል፡፡
ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን የዛሬ 15 ዓመት በጻፍኩት ጽሑፍ ላይ እንደደመደምኩት ‹‹የጦር ወንጀለኞች ለፍትሕ ሳይቀርቡና ሳይቀጡ
እንደዋዛ ነፃ ወይም ማምለጥ ከቻሉ፣ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለብሔራዊ ሉዓላዊነታችን ውርደት ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ
በአይደር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በአካባቢው በተቃጣ የአየር ድብደባ ድርጊት የሞት፣ የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት በደረሰባቸው
ልጆቻችን፣ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ላይ ከኤርትራዊያን የጦር ወንጀለኞች ጋር በመተባበር ሌላ ከባድ ወንጀል የመፈጸም ያህል
ይሆናል፡፡››
ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው
johnwaa@hotmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
January 20, 2014

No comments:
Post a Comment