በትግራይ አፅቢ ግጭቱ ለጊዜው ቆሟል! ህዝቡ እንዳይንቀሳቀስ በፌደራል ፖሊስ ተከቧል!
(EMF) ትላንት በትግራይ ክልል፣ አፅቢ ወረዳ ስለተቀሰቀሰው ግጭት፤ ከስፍራው አብርሃ ደስታ መዘገቡ ይታወሳል። ዛሬ ስላለው ሁኔታ ደግሞ እንዲህ በማለት ዘገባውን ቀጥሏል።
ግጭቱ ለጊዜው ቆሟል። መከላከያ ሰራዊት የሃይል እርምጃ ከመውሰድ ታቅቦ ህዝቡ እንዲበተን ተማፅኗል። በፖሊስ የታሰሩትን ነገ (ዛሬ ዓርብ 09/05/06 ዓም) እንደሚፈቱ ቃል ገብቷል። ድራማው ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት (7:00) ላይ ተፈፅሟል። ድርድሩ ዛሬ ዓርብ ይቀጥላል።
አካባቢው በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ይገኛል። የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ (ሕነይቶ) በፖሊስ የታሰሩትን ወገኖቹ ለመቀበል ባከባቢው እየተሰባሰበ ነው። የተያዙትን ሰዎች ግን እስካሁን ድረስ ባከባቢው የሉም። በነሱ ምትክ ብዙ የፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን (ከመከላከያዎች ጋር በመሆን) እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።
ትናንት በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ስፍራ የተወሰዱ ያከባቢው ነዋሪዎች ብዛታቸው በውል አይታወቅም። ህዝብ እያየ ፖሊስ እየደበደበ የወሰዳቸው አራት ሰዎች ግን የሚከተሉ ናቸው።
(1) ታደሰ ሃይሉ
(2) አሰፋ ካሕሳይ
(3) ገብረእግዚአብሄር ገብረሚካኤል
(4) የአቶ ግርማይ ግብረየሱስ ልጅ (የ16 ዓመት ወጣት) ናቸው።
(2) አሰፋ ካሕሳይ
(3) ገብረእግዚአብሄር ገብረሚካኤል
(4) የአቶ ግርማይ ግብረየሱስ ልጅ (የ16 ዓመት ወጣት) ናቸው።
የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በታሪክ ይህን ያህል ግፍ ያደረሰበት መንግስት እንዳልነበረ አስተያየት ሰጪዎች እየተናገሩ ነው። አስተያየት ሰጪዎቹ ለመብት ጥያቄ ይህን ያህል ግፍ መፈፀም አግባብነት የለውም ይላሉ።
(ዓርብ ጠዋት አምስት ሰዓት ነው የተፃፈው)።
ህዝቡ እንዳይንቀሳቀስ በፌደራል ፖሊስ ተከቧል
—————————— —————
——————————
አሁን ዓርብ ከጠዋቱ አምስት ሰዓት ተኩል ነው። ዓመፁ ወደ ሌላ አከባቢ እንዳይሰፋ በመፍራት የፌደራል ፖሊሶች አከባቢው ከበውታል፤ ህዝቡም በፖሊስ ተከቧል። የፖሊስ አዛዦች ህዝቡን እያስፈራሩ ይገኛሉ። ህዝቡም መብቱ እንዲከበርለትና ታፍነው የተወሰዱ ወገኖቹ (ትናንት ማታ በተገባላቸው ቃል መሰረት) እንዲፈቱ እየጠየቀ ነው። አከባቢው ግን ተከቧል። ካከባቢው መውጣትና ወደ አከባቢው መግባት ተከልክሏል። አንድ ባህረ ገብሩ የተባለ ያከባቢው ኗሪ ካከባቢው ወደ አፅቢ ከተማ ሲጓዝ በፖሊስ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዷል።
ህዝቡ ታፍነው የተወሰዱ ያከባቢው ኗሪዎች ፖሊስ ይደበድባቸዋል፣ ይገድላቸዋል በሚል ስጋት ተጨናንቀዋል። ሳይፈቱም ህዝቡ እንደማይበተን አስታውቀዋል። የፖሊስ ማስፈራርያው ግን አይሏል። ባከባቢው በዜጎች ላይ ግፍ ሲደርስ የተለመደ በመሆኑ የተያዙት ሰዎች ድብደባና ግድያ እንደሚጠብቃቸው ይገመታል።
ባከባቢው (አፅቢ ወንበርታ) እስካሁን ድረስ (ከዚህ ቀደም ማለት ነው) ታደሰ ጊደይ አባዲ የተባለ የሩባ ፈለግ ኗሪ በመንግስት አካላት በጥይት ተገድላል። የአቶ ገብረሂወት (ስሙ ለግዜው አልያዝኩትም) ልጅም በመንግስት አካላት በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል። አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ (ጣብያ ፈለገወይኒ)፣ አቶ ታደሰ መዝገቦ (ጣብያ ሩባ ፈለግ)፣ አቶ ህይወት አባይ (ጣብያ ሩባ ፈለግ) ወዘተ በፖሊስ ድብድባ (ቶርቸር) እንደደረሰባቸው ታውቋል: ከፍተኛ የስነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል።።
ከዚህ በመነሳት ታፈነው በተወሰዱ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ቅሬታ አለ። ፖሊስ ግን ህዝቡን ከቦ አላንቀሳቅስ ብሏል።
(በ 5:55)
————————–
የህወሓት አመራር አባላት ባከባቢው ይገኛሉ
————————————
————————————
አከባቢው በብዙ የወረዳና የክልል ፖሊሶች፣ የፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ ሰራዊት ተከቦ ህዝቡም እንዳይንቀሳቀስ ታግቶ በመከላከያ ሰራዊት የታጀቡ የዞንና ክልል አስተዳዳሪዎች (የህወሓት ባለስልጣናት) ህዝቡን እያነጋገሩ ነው። ባለስልጣናቱ ህዝቡ ዓመፁ የቀሰቀሰው ማን እንደሆነ፣ ለምን የሃይል መንገድ መጠቀም እንደመረጠ ወዘተ በማስፈራራት እየጠየቁ ነው። ህዝቡም የመሬቱ ካሳ ወይ ተለዋጭ መሬት የማግኘት መብቱ እንዲከበርለት፣ ታፍነው የተወሰዱ እንዲፈቱ ይጠይቃል። መግባባት የለም። የህዝቡ ጥያቄ ያናደዳቸው አስተዳዳሪዎች ህዝቡ ትናንት የቀሰቀሰው ዓመፅ “ስህተት” መኖሩ ካላመነ ወደ ቤቱ እንዲሄድ እንደማይፈቅዱለት እያስፈራሩት ነው። ህዝቡ በሃይል ዓፍነው ይዘውታል (በፀጥታ ሃይል ብዛት)። የኢህአዴግ የደህንነት ሰዎች እዛው ይገኛሉ። ካከባቢው ለመውጣትና ወደ አከባቢው ለመግባት የሞከሩ የአከባቢው ኗሪዎች እየታሰሩ ነው። እስካሁን ሰባት ሰዎች ታስረዋል (አንድ ሃፍቱ ገብረመድህን የተባለ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባል ጨምሮ)።
ዓርብ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ተፃፈ።
———————————
የአፅቢ ወንበርታ ህዝባዊ ዓመፅ
————————————-
ትልቁ ኪሳራ
————————————-
ትልቁ ኪሳራ
የትናንትው የአፅቢ ወንበርታ ህዝባዊ ዓመፅና የፖሊሶች ተኩስ (የነበረውን አጠቃላይ ግጭት) በካሜራና በሞባይል ሲቀርፁ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የግጭቱ ሙሉ ሂደት ቀርፀው ለህዝብ ለመበተን ዉቅሮ ከተማ ሊገቡ ሲሉ በልዩ የህወሓት የደህንነት ሃይሎች ተይዘዋል። ታፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል። ሞባይላቸውና ካሜራቸው ተነጥቀዋል። ህወሓቶች የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በደልና ዓመፅ ሌሎች ህዝቦች እንዳይሰሙት ለማፈን በማቀድ ቪድዮውን ይዘውታል። መረጃው መበተኑ ግን አይቀርም። ለኔ ግን ትልቅ ኪሳራ ነው።
ይህን የተደረገው ዓርብ 09/05/06 ዓም ከቀኑ ስምንት ከአርባ (8:40) ነው።
No comments:
Post a Comment