Tuesday, January 21, 2014

2014 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት፡- ኢትዮጵያ (HRW)

 2014 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት፡- ኢትዮጵያ (HRW)

Image
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ።
መንግስት በሃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ መግባቱን የተቃወሙ ሙስሊሞች ዓመቱን ሙሉ በጸጥታ ሃይሎች የዘፈቀደ እስር፣ እገታ፣ ድብደባ እና ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. የታሰሩት 29ኙ የተቃውሞው መሪዎች የፍርድ ሂደት ከጥር ወር 2013 ጀምሮ ለህዝብ፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ እና ለቤተሰብ አባላት ዝግ ተደርጓል፡፡ እጅግ አወዛጋቢና መሠረታዊ ግድፈት ያለባቸውን ድንጋጌዎች በያዘው የሃገሪቱ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ መሰረት ጥፋተኛ የተባሉ የተቃዋሚ መሪዎች እንዲሁም አራት ጋዜጠኞች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ከሃገር ውስጥ በሚገኝ ገቢ እና ከውጭ በሚመጣ እርዳታ በሚደገፉ ስፋት ያላቸው የልማት ፕሮግራሞች አፈጻጸም ምክንያት የአንዳንድ ማህበረሰብ ተወላጅ ነዋሪዎች ያለበቂ ምክክር ወይም ምንም አይነት ካሳ ሳይከፈላቸው ከመኖርያቸው እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ሃይል፣ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይፈጸማሉ፤ ለምሳሌ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚገኙ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት የኖሩበት መሬት መንግስት ለሚያካሂደው የስኳር መስኖ ልማት ይፈለጋል በሚል መፈናቀላቸው እንደቀጠለ ነው።
በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት
ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር የሚይዙት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ አድርገዋል፡፡ የተቃውሞው መነሻ ምክንያት መንግስት በእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ውስጥ እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የአወሊያ መስጊድ ላይ ይፈጽማል የተባለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ነው፡፡
የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹን ለመግታት መንግስት ሃይል ተጠቅሟል፤ የዘፈቀደ እስር እና ድብደባ በተቃዋሚዎቹ ላይ ፈጽሟል፤ እነዚህ ሕገ ወጥ ተግባራት በሀምሌ 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው በጥቅምት 2012 ዓ.ም በጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ክስ በተመሰረተባቸው 29 ታዋቂ የተቃውሞ እንቅስቃሴው መሪዎች ላይም ተፈጽመዋል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቱን መገናኛ ብዙሃንን፣ ዲፕሎማቶችን እና የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ህዝብ እንዳይከታተለው ከጥር ወር ጀምሮ ዝግ አድርጎታል፡፡ አንዳንዶቹ ተከሳሾች በእስር ላይ እያሉ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። እንዲሁም እንዳንዶቹ ተከሳሾች ለሁለት ወራት ያህል የሕግ አማካሪ ወይም ጠበቃ ያላገኙበት ሁኔታና ከቤተዘመድ ጋር ለመገናኘት የነበረውን ችግር ጨምሮ የፍርድ ሂደቱ በሕግ በተቀመጡ ስርዓቶች አግባብ መካሄዱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ በርካታ ግድፈቶች ተፈጽመዋል።
በተከሳሾቹ ላይ በመንግስት ቴሌቪዥን ውንጀላ እና ክስ ያለበት መረጃ በማስተላለፍ መንግስት ተከሳሾቹ ከፍርድ ውሳኔ በፊት ነጻ ሆነው የመገመት መብታቸውን የሚጋፋ ድርጊት ፈጽሟል። መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) ጃሃዳዊ ሃረካት የሚል ርዕስ ያለው ፕሮግራም በጥር ውስጥ የተላለፈ ሲሆን ፊልሙ ከተከሳሾቹ ውስጥ አምስቱ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት በቁጥጥር ስር እያሉ የተቀረጸ ክፍል አካቷል። ፕሮግራሙ የተቃውሞው መሪዎችን እንደ አሸባሪዎች በመቁጠር የሙስሊሞቹን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከአክራሪ የእስልምና ሃይሎች ጋር አነጻጽሯል፡፡
እስሩ እንዳለ ቢሆንም በ2013ም ተቃውሞው ቀጥሏል፡፡ በነሃሴ ወር መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የረመዳን ወር መጨረሻ የሆነው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሚከበርበት ዕለት የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአይን እማኞች በአዲስ አበባ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተው እንደነበረ የገለጹ ሲሆን ታማኝ ምንጮች ደግሞ ሰልፈኞቹን ለመበተን ፖሊስ ከተገቢው በላይ ሃይል እንደተጠቀመ እና ለጊዜውም ቢሆንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፎ አዲስ መጭ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፤ ሰልፉ በስምንት ዓመት ጊዜ ውስጥ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው፡፡ የጸጥታ ሃይሎች የሰማያዊ ፓርቲን ጽህፈት ቤት ጥሰው በመግባት በርካታ ሰዎችን በማሰራቸውና የፓርቲውን ንብረቶች በመውረሳቸው ምክንያት ፓርቲው በነሀሴ ወር ሊያካሂድ አቅዶ የነበረው ሰልፍ ተሰርዟል። ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ብሎ ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ለመንግስት አቅርቦ የነበረው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ነበር።
የዘፈቀደ እስር እና ጎጂ አያያዝ
የዘፈቀደ እስር እና በእስር ቤቶች የሚደረግ ጎጂ አያያዝ ከፍተኛ ችግር መሆኑን ቀጥሏል፡፡ ተማሪዎች፣ የተቃዋሚ ጎራ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች እና ሌሎችም የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት መብታቸውን መግለጽ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው በዘፈቀደ ይታሰራሉ፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካ ምክንያት የሚያዙ ሰዎች ላይ በተለይም እነዚህ ሰዎች ከክስ ወይም ከፍርድ ሂደት በፊት በሚታሰሩበት እና ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው አዲስ አበባ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል ጎጂ አያያዝ ይፈጸማል፡፡ በሃይል በማስገደድ ከእስረኞች መረጃ፣ የእምነት ቃል እና ሃሳብ ለማውጣጣት እስከ ማሰቃየት የሚደርስ ጥቃት እና ሌሎች ጎጂ አያያዞች የሚፈጸሙባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው።
የተያዙ ሰዎች በተለይ ክስ ከመመስረቱ በፊት ብዙ ጊዜ የህግ አማካሪ እንዳያገኙ ይደረጋል፡፡ ያልተገባ አያያዝ የተፈጸመባቸው እስረኞች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከፍርድ ቤቶች የሚያገኙት መፍትሄ እጅጉን ውሱን ነው፤ አንዲሁም እስር ቤቶች እና ሌሎች የማቆያ ቦታዎች በገለልተኛ መርማሪዎች በመደበኛነት እንዲጎበኙ አይፈቀድም፡፡ ከመንግስት ጋር ቀረቤታ ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የተወሰኑ እስረኞችን እና እስር ቤቶችን የጎበኘ ቢሆንም በማንኛውም ገለልተኛ የሰብዓዊ መብቶች ወይም ሌላ ድርጅት መደበኛነት ያለው የክትትልና የምርምራ ስራ አይሰራም።
በሃምሌ ወር ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረው የአውሮፓ ፓርላማ የልዑካን ቡድን አባላት አስቀድሞ ፈቃድ ተሰጥቶአቸው የነበረ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚገኘውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳይጎበኙ በባለስልጣናት ተከልክለዋል።
ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት
በ2009 ዓ.ም የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት በከፍተኛ ደረጃ ተገድቧል፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጁ በዓለም ላይ ካሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ከወጡ በጣም አፋኝ ህጎች አንዱ ነው፡፡ በሰብዓዊ መብቶች፣ መልካም አስተዳደር፣ ግጭት አፈታት፣ እና የሴቶች፣ የህጻናት እና አካል ጉዳተኛ ሰዎች መብቶች ዙሪያ አድቮኬሲ የሚሰሩ ድርጅቶች ከጠቅላላ ገቢያቸው 10 በመቶ በላይ እርዳታ ከውጭ ምንጮች መቀበል እንደማይችሉ ይደነግጋል፡፡
በዚህ ሕግ ሳቢያ እጅግ መልካም ስም የነበራቸው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ይሰሩ የነበረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የቀነሱ ሲሆን ሌሎቹም ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ስራዎችን መስራት ጭራሹኑ አቁመዋል። በርካታ ታዋቂ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች በተፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት ሃገሪቱን ለቀው ተሰደዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በከፍተኛ የመንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፤ እንዲሁም በርካታ ጋዜጠኞች ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ ያካሂዳሉ፡፡ መንግስትን በፅኑ የሚተቹ ድረ ገጾች እና ጦማሮች በመደበኛነት ይዘጋሉ እንዲሁም የውጭ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች በተደጋጋሚ ይታፈናሉ። ለነጻ የሃገር ውስጥ ጋዜጦች የሚሰሩ ጋዜጠኞች የሚደርስባቸው ተከታታይ ጥቃት እና ማስፈራራያ እንደቀጠለ ነው።
የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ የፖለቲካ ተፎካካሪዎችን ለማጥቃት፣ ነጻ ሃሳብን ለማፈን፣ እንዲሁም ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በሐ

No comments:

Post a Comment