በጋዜጣው ሪፖርተር
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የማንዴላን ሞት በማስመልከት ሰሞኑን ከኤስቢኤስ ሚዲያ ጋር
ባደረጉት ቃለመጠይቅ ማንዴላ እንደተፈቱ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት የ100ሺ ዶላር ገንዘብ ልገሳ እንዳደረጉላቸው አስታወቁ።
ኮሎኔል መንግስቱ በዚሁ ቃለምልልሳቸው ማንዴላ እንደተፈቱ መጀመሪያ ዙምባቡዌ ቀጥሎም ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አስታውሰው ኢትዮጵያ የመጡት በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመካፈል እንደነበር ጠቅሰዋል። ለስብሰባ አዲስአበባ በመጡበት ወቅት ገና የመፈታታቸው ጊዜ ስለነበር ጠና ያለ ሕመም አጋጥሞአቸው በአዲስአበባ አንድ ሳምንት የፈጀ ሕክምና መከታተላቸውና
ማስታመማቸውን ገልጸው በዚህ አጋጣሚ ስለግለታሪካቸው፣ ስለእስራቸው ሁኔታ በስፋት የመወያየት ዕድል እንዳጋጠማቸው
ተናግረዋል። በወቅቱ ገና ከእስር የተፈቱበት ወቅት ስለነበር ምን እንድርግልዎ ብለው
እንደጠየቁዋቸውና እሳቸውም ምንም እንደማይፈልጉ ምላሽ እንደሰጡዋቸው
የተናገሩት ኮሎኔሉ በራሳቸው ውሳኔ የ100ሺ ዶላር ገንዘብ በቼክ እንደለገሱዋቸው አስረድተዋል።
ማንዴላ በወቅቱ
ሶሻሊዝምን ማራመድ
ይፈልጉ እንደነበርና የሶቪየት
ህብረት መፈራረስ ጉዳይ ላይ
በቂ መረጃ ስላልነበራቸው
ስለሁኔታው እንዲያስረዱዋቸው
እንደጠየቁዋቸው ኮሎኔል
መንግስቱ ተናግረዋል። እሳቸውም
ስለሁኔታው ካስረዱዋቸው በኋላ
ደቡብ አፍሪካ ሶሻሊዝም ለመከተል
ከመወስንዋ በፊት የዓለም ሁኔታን
በደንብ እንዲመረምሩ ምክር
እንደለገሱዋቸው ተናግረዋል።
ማንዴላ ከሰልጣናቸው
ከወረዱ በኋላ በደቡብ አፍሪካ
በስደት ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን
ችግር እንደገጠሙዋቸው በሰሙ
ጊዜ በወቅቱ በስልጣን ላይ ለነበሩት
ታምቦ ምቤኪ ኢትዮጵያዊያን
ማንም እንዳይነካ በሚል ማሳሰቢያ
በመስጠታቸው ችግሩ መፈታቱን
ኮሎኔሉ አስታውሰዋል።
በዙምባቡዌ ስደት
ላይ እያሉ በአንድ ስብሰባ ላይ
ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የመተያየት
ዕድል ገጥሞአቸው እንደነበር
ያስታወሱት ኮሎኔል መንግስቱ
ነገርግን በሰው መብዛት ምክንያት
ለመነጋገር እንዳልቻሉ ጠቅሰዋል።
ማንዴላና የተወሰኑ
ተከታዮቻቸው በአፄ ኃይለስላሴ
ዘመነ መንግስት ለመጀመሪያ
ጊዜ ወደኢትዮጵያ ሲመጡ
ወጣት እንደነበሩ የሚናገሩት
ኮሎኔል መንግስቱ የሰሙትን
መረጃ ዋቢ አድርገው ሲናገሩም
ማንዴላ በስውር ወደኢትዮጵያ
መጥተው ወታደራዊ ስልጠና
መከታተላቸውን፣ በወቅቱ
የአሜሪካ እና የእስራኤል
መንግስታት ለደቡብ አፍሪካ
አፓርታይድ መንግስት ይወግኑ
ስለነበር ሁኔታውን እግር
በእግር ሲከታተሉት እንደቆዩ
አስታውሰዋል። በኋላም ማንዴላ
ከአዲስአበባ ወደሞሮኮ ሄደውና
ጎብኝተው ወደደቡብ አፍሪካ
ሲመለሱ ተይዘው እንደታሰሩ
ተርከዋል።

No comments:
Post a Comment