(Mo Farah Foundation and Africa’s dictatorial leaders )
(ዘንድሮስ ተሸላሚ ያገኝ ይሆን ወይ?)
Thewodros Getachew
November 9, 2013
(ዘንድሮስ ተሸላሚ ያገኝ ይሆን ወይ?)
Thewodros Getachew
November 9, 2013
በአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ ከጥቂት ወራት በፊት የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ኮንፈረንስ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን ኮንፈረንሱ አፍሪካ ውስጥ ስላለው የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ በተመለከተ እንዲሁም አህጉሪቷ ወደፊት ስለሚኖሩዋት እድሎችና ስላጋጠሙዋት ችግሮች ከተለያዩ ሃገራት ከመጡ ፖለቲከኞ፤ ታዋቂ ግለሰቦችንና ጋዜጠኖችን ጨምሮ የተካሄደ ነበር።
በዛን ኮንፈረንስ ላይ ከዋንኟዎቹ ተናጋሪዋች ውስጥ የነበሩት አደራ ጠባቂው ጠ/ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሰፈነው አስገራሚ ዲሞክራሲና እድገት የተለመደውንና ማቆሚያ ያልተገኝለትን የመንግስታቸውን ቅጥፈት ለማስተጋባት ተጠቅመውበታል። ይሁንና ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ እንደሳቸው አባባል ሞልቶ ከተረፈ እንዴት ከ90 ሚሊዮን
ህዝብና 90 ምናምን ፓርቲ በላይ እንዳለ በሚነገርባት ሃገር ውስጥ አንድ ፓርቲ ብቻ በአንባገነንነት ሃገሪቷን በሞኖፖል ለ 23 አመታት ሊገዛ እንደቻለ ወይም የሃገሪቷ ፓርላማን 99.6% ከአንድ ፓርቲ ብቻ የተወጣጣ አባላትን ይዞ የፓርቲ ጉባኤ እንደመሰለ ግን ሊያስረዱ አልቻሉም ነበር ።
በርግጥ ይሄ ባጠቃላይ የአገዛዙ ባህሪ መሆኑ የታወቀ ነው በትክክል ከእውነታው ጋር የተጋጨ ወይንም መረጃዎቹን አዛብቶ ፤አባዝቶ፤ ቀንሶ፤ ጨምሮ የተሳሳተ/distorted አድርጐ ማቅረብ የተለመደና የስርአቱ አንድ አካል የሆነ እውነት ነው።
ሃገሪቷ ውስጥ በየቦታው በአገዛዙ የሚፈጸመው የሰብእዊ መብት ጥሰት፤ በየእስር ቤቱ ታጉረው የሚገኙት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኟች እንዲሁም የፍትህ ስርእቱ የመንግስት እና የግብረአበሮቹ የማጥቂያ መሳሪያ መሆንና ስር የሰደደው ሙስና ሌሎችም በርካታ
ምክንያቶች ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት በየትኛውም መለኪያ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ምሳሌ ለመሆን አያስችላትም አለመሆንም ብቻ ሳይሆን ወደዛ የሚደረገውን ጉዞ ገና አልጀመረችም፤ በተለያየ ግዜ ዲሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ልትጀምርባቸው የምትችልባቸው ወርቃማ አጋጣሚዎች ደግሞ በአንባገነኖች ጥቂት ለማይባሉ ግዜዎች ከሽፈዋል።
ለማንኛውም ሱዳን ውስጥ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር 1946 የተወለደው ዶ/ር መሃመድ ሞህ ኢብራሂም የሱዳን ብሪቲሽ የሞባይል ቴሌኮምንኬሽን ባለቤትና ፣ ሴልቴል/ celtel የተባለው ድርጅት መስራችና ባለቤት የነበረ ሲሆን በ 2005 ድርጅቱን በ 3.4 ቢሊዮን ብር ከሽጠ በሓላ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን አፍሪካ ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማበረታታት በሚል እንዲሁም ጎን ለጎን ደሞ የየሃገሮቹን የመልካም አስተዳደር ብቃት ደርጃ የሚለካና የሚገመግም Mo Ibrahim index የሚባል ድርጅት በዚሁ ግለሰብ እማካኝነት ተቋቍሞ ከ2007 ጀምሮ የመልካም አስተዳደር መስፈርት ላሟሉ መሪዋች የመነሻ ሸልማት 5 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር አንዲሁም በየአመቱ አስከ ህይወታቸው መጨረሻ ድረስ የ 200ሺ የአሜሪካ ዶላር ለነዚሁ ሃገራቸው ውስጥ መልካም አስተዳደረንና ፤ዲምክራሲን፤ ሰላም ላሰፈኑ መሪዋች እያበረከት ይገኛል ።
Dr. Mohamed “Mo” Ibrahim (born 1946
በ 2007 አንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የተመሰረተ ፋውንዴሽን በየአመቱ ከአፍሪካ መሪዎች መካከል በመልካም አስተዳደር በዲምክራሲ በሰላም በፍትሕ አንዲሁም በኢኮኖሚ ሃገራቸው ውስጥ ለውጥ ያመጡ በሰላም አና በህገመንግስቱ መሰረት ስልጣን የለቀቁ ወይም
ያስረከቡ መሪዎችን ለመሸለም እንዲሁም ለማወደስ ተብሎ የተቐቐመ ድርጅት ነው።
በየአመቱ
በሚሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር መድቦ መልካሙን የአፍሪካ መሪና
አስተዳዳሪ ለመሸለም ተዘጋጅቶ የሚጠበቀው ፋውንዴሸን መልካም መሪዋችን
የመለየት ሳይሆን የማግኝት ከባድ ፈተና አንደገጠመው ለማወቅ ከተመሰረተበ ግዜ ጀምሮ ለመሸለም የበቁት የአፍሪካ መሪዎች ኔልሰን
ማንዴላን ሳይጨምር ሶስት ብቻ መሆናቸው ማወቅ ብቻ ይበቃል።
ፋውንዴሽኑ
በተቋቋመበት አመት ማለትም 2007 አንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የመጀምሪያውን ሽልማት ለማግኝት የበቁት የሞዛምቢኩ መሪ
ቺሳኖ ለሽልማት ያበቃቸው አገራቸው ውስት ባመጡት ሰላምና ብሄራዊ አርቅ አንዲሁም ዲሞክራሲና መረጋጋት ከኢኮኖሚያዊ አድገት ጋር
የሽልማቱ ተቋዳሽ አንዲሆኑ አስችሎዋቸዋል።
president Joaquim Alberto Chissano
በ 2008 ደሞ የቦትስዋናው መሪ ሞጋኢ ፪ ኛውን ሽልማት ባገራቸው ውስጥ ባመጡት ሰላምና መረጋጋት አንዲሁም በ ኤችአይቪ ኤድስ ላይ ባስመዘገቡት ስኬት ሽልማቱን ተረክበዋል።
በ 2008 ደሞ የቦትስዋናው መሪ ሞጋኢ ፪ ኛውን ሽልማት ባገራቸው ውስጥ ባመጡት ሰላምና መረጋጋት አንዲሁም በ ኤችአይቪ ኤድስ ላይ ባስመዘገቡት ስኬት ሽልማቱን ተረክበዋል።
በ 2009 አና በ 2010 ግን ፋውንዴሽኑ ተሸላሚ መሪ ከአፍሪካ ምድር ማግኝት ሳይቻለው ቀርቶዋል በመሆኑም ለሸልማቱ አዘጋጅቶት የነበረዋን ገንዘብ ወደ ካዝናው መልሶታል
በ 2011
ግን አፍሪካ ውስጥ በአግር በፈረስ ሲያስፈልግ የነበርው መልካም የአገር አስተዳዳሪ ከወደ ኬብቨርዲ ተገኝቶዋል ፕሬዝዳንት ፔድሮ
ደ ቨሮና አገራቸውን ወደ ሞዴል ዲምክራሲ ከሚባሉት የአፍሪካ አገራት ተርታ በማሰለፋቸው ሽልማቱን ወደ ቤታቸውና ወደ አገራቸው ለማስገባት በቅተዋል።

President Pedro de Verona Rodrigues Pires, Cape
Verde

የም ኢብራሂም ፋውንዴሽን በሚሊዮን ዶላር የለጠፈበት የመልካም አስተዳዳሪ መሪ ሽልማት በ ፰ አመት ውስጥ ማግኝት የቻለው ፫ በስልጣን ላይ ያሉ መሪዋች አነዚሁ ብቻ ነበሩ
ከ2011 በኸዋላ ግን ተሸላሚ ሳያገኝ ወደ 2014 አየሄደ ነው ዘንድሮም ተሸላሚ ማግኝት ባልመቻሉ የሚሸልሙት መሪ ባይገኙ የሚሸልሙት ቡድን ለማግኝት ይመስላል ይሄንን የአግር ዃስ ውድ ድር ያዘጋጁት።
ከአንድ ቢሊዮን ህዝብ በላይ ያላት አፍሪካ 61 አገራትን ያካተተ አህጉር የሚመሩ 61 መሪዋች መካከል አንድ አንኳን ለዚህ ሸልማት የሚበቃ መሪ ማግኝት አለመቻል ከባድ ሃዘን ላይ የሚጥል አሳፋሪ ክስተት ነው http://listofafricancountries.com/።
አለም በሌላኛው ጫፍ በዲምክራሲ አና በሰባአዊ መብት መክበር ሲከንፍ ጉደኛዋ አፍሪካ ደም በብዙ እርቀት ከነዚንህ እሴቶች በተቃራኒው አየራቀች ትገኛለች አፍሪካ ውስጥ አገሮቹን የሚመሩ መሪዋች ስልጣን ላይ ተጣብቀው ያለምንም ይሉኝታ በ 21 ክፍለዘመን በፍጽም አንባፈነናዊ አገዛዝ ይሄንን ግዙፍ አህጉር ህዝብ አያንገላቱትና አያላጉት ይገኛሉ።
በተለይም ደሞ በአፍሪካው ቀንድ ከአንዱ የእርስ በእርስ ጦርነት ወደ ሌላው ከአንዱ አንባገነን ወደ ሌላውኛው እየተሸጋገረ ዜጎችም ጦርነቱንና የአንባገነኖችን ዱላ በመሸሽ በመላው አለም
ላይ አንደ አሸዋ ተበትነው ይገኛሉ በዚህ ሂደት ላይ ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በተለይም ደግሞ የአፍሪካው ቀንድ ከአንዱ የእርስ በእርስ ጦርነት ወደ ሌላው ከአንዱ አንባገነን ወደ ሌላውኛው እየተሸጋገረ ዜጎችም ጦርነቱንና የአምባገነኖችን ዱላ በመሸሽ በመላው አለም
ላይ አንደ አሸዋ መበተን ግድ ብሎዋቸዋል በዚህ ሂደትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ኢትዮጵያም ምንም እንኳን
ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ራሷን ጠብቃ መቆየት ከመቻልዋም በላይ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ነጻነታቸውን አንዲያገኙ ከፍተኛ እገዛ በማድረግ
የጥቁር ህዝቦች ኩራት ለመሆን ብትበቃም ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደርን በሃገራ በማስፈን ምሳሌ መሆን አልቻለችም በመሆኑም የአጉሪቷ
ጭራ ሆና በማዝገም ላይ ትገኛለች።
No comments:
Post a Comment