Saturday, October 5, 2013

ፓርላማ፣ ኢትዮጵያውያንን ሳያማክር አዲስ ፕሬዚዳንት ይመርጥላቸዋል

የፕሬዚዳንቱ ስልጣን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ ፓርላማውን፣ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክርቤትን ሁሉ ይነካል።
ፕሬዚዳንቱ ሳይፈቅድ፣ ጠ/ሚሩ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረጎችን መስጠትና አምባሳደሮችን መሾም አይችልም።
ብዙዎች ቢያናንቁትም የፕሬዚዳንቱ ስልጣን ቀላል አይደለም። “ስልጣኑ ተሠርቶበታል ወይ?” ነው ጥያቄው።

ኢ ህአዴግ በተለመደው የ ም ስ ጢ ራ ዊ ነ ት ባ ሕ ር ይ ው ፣ ለፕሬዚዳንትነት ማንን በእጩነት እንደሚያቀርብ
ሳይነግረን ይሄውና የምርጫው ቀን ደረሰ። ባዕድ መሰልነው እንዴ የሚደብቀን? ዜችን ከመናቅ ይሁን ከመፍራት፣ ሕግን ባለማክበር ይሁን በቸልተኝነት… ምንም ሆነ ምን፣ ዜጎች በሰኞው የፕሬዚዳንት
ምርጫና በእጩዎች ላይ ሃሳባቸውን እንዳያቀርቡና እንዳይወያዩ እድል ተነፍጓቸዋል - በኢህአዴግና
በፓርላማው። ታዲያ የዜጎች ድርሻ ምንድነው? … ያው እንደተለመደው፣ “ተመልካች” መሆን ብቻ!
በቃ፤ ሰኞ እለት ቴሌቪዥን ከፍተው፣ አንድ ሰው ፕሬዚዳንት ሆኖ ሲሾም መመልከት ብቻ! ለነገሩ፣ የአገራችን ችግር የገዢው ፓርቲ ብቻ አይደለም። ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ያው ናቸው። አንዳንዶቹም የባሱ! “ለፕሬዚዳንትነት በእጩነት
የሚቀርበው ሰውxf ማን እንደሆነ ለዜጎች ተገልጾ ውይይት መካሄድ አለበት” ብሎ የኢህአዴግንና
የፓርላማውን ድብቅነት የተቸ አንድም የተቃዋሚ ፓርቲና ፖለቲከኛ የለም።
ኢህአዴግ ከዜጎች ጋር በአደባባይ ከመወያየት ይልቅ የጓዳ ምስጢራዊነትን፣ ፓርላማውም በግልፅነት ዜጎችን ከማገልገል ይልቅ የጓሮ ድብቅነትን የፕሬዚዳንቱ ስልጣን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ ፓርላማውን፣ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክርቤትን ሁሉ ይነካል።
ፕሬዚዳንቱ ሳይፈቅድ፣ ጠ/ሚሩ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረጎችን መስጠትና አምባሳደሮችን መሾም አይችልም።
ብዙዎች ቢያናንቁትም የፕሬዚዳንቱ ስልጣን ቀላል አይደለም። “ስልጣኑ ተሠርቶበታል ወይ?” ነው ጥያቄው።
ፓርላማ፣ ኢትዮጵያውያንንሳያማክር አዲስ ፕሬዚዳንት ይመርጥላቸዋል
መምረጣቸው ሳያንስ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች እንዲህ መሆናቸው አይገርምም?
ድብቅነትን በመተቸት ግልፅነት እንዲሰፍንና የዜጎች የሃሳብ ነፃነት እንዲሰፍን ሲጠይቁ የማናያቸው፣
ኢህአዴግን ወይም መንግስትን በመፍራት አይደለም። በፕሬዚዳንቱ ምርጫ ዙሪያብዙ
ትችቶችን ለመደርደር አልሰነፉም - በተለይ ደግሞ የፕሬዚዳንቱን ስልጣን በማናናቅ።
በአላዋቂነት ይሁን በደንታቢስነት… ምክንያቱ ባይታወቅም፣ የፕሬዚዳንቱን ስልጣን ማጣጣል በኛ
አገር በጣም የተለመደ ነገር ነው። ለነገሩ፣ በአገራችን ኋላ ቀር ባህል ውስጥ፣ የመንግስት ስልጣን… “ሕግ
የማያግደው አድራጊ ፈጣሪና ፈላጭ ቆራጭ” ካልሆነ፤ ብዙዎቻችን ያን ያህል አናከብረውም፤ እውነተኛ
ስልጣን ሆኖ አይታየንም። ለዚህ ይመስለኛል፣ የፕሬዚዳንቱን ስልጣን ማናናቅ እንደ አዋቂነት
የሚቆጠረው - በሕግ የተገደበ ስልጣን ስለሆነ! የኢህአዴግ የድብቅነት ባህልኢህአዴግና አጋሮቹ በ99.5% በላይ
የተቆጣጠሩት ፓርላማ፣ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የሚኒስትሮች ሹም ሽርና ሽግሽግ እንዴት እንደተካሄደ
ታስታውሱ ይሆናል። ባታስታውሱትም ችግር የለውም። እንደተለመደው ነው… አንድ የፓርላማ
ስብሰባ ላይ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መጥተው፣ ለሹመት የታጩ ሰዎችን በስም ይዘረዝራሉ።
“እገሌ፣ ይህንንና ያንን ተምሯል፤ እዚህና እዚያ
ሰርቷል” የሚል፣ “የአጭር አጭር የመተዋወቂያ ገለፃ
ይነበባል - ከሦስት ዓረፍተ ነገር ያልበለጠ። ከዚያ
አንድ ሁለት ጥቅል አስተያየቶች በአጭሩ ይቀርቡና
የፓርላማ አባላት ድምፅ ይሰጣሉ። የሚኒስትሮቹ
ሹመት ይፀድቃል። እስከዚያች የስብሰባ ሰዓት
ድረስ፣ ለሚኒስትርነት የታጩት ሰዎች እነማን
እንደሆኑ አይታወቅም፤ በምስጢር ተደብቆ
ይቆያል። የፓርላማ አባላት እንኳ፣ “ማን በእጩነት
ይቀርባል?” ተብለው ቢጠየቁ፣ ከስብሰባው በፊት
እንደማያውቁ ነው የሚናገሩት።
ለሚኒስትሮች ሹመት የሚሰጠው አቅምና
ብቃታቸው እየታየ መሆን እንዳለበት ሕገመንግስቱ
በግልፅ ይደነግጋል። የእጩ ተሿሚዎችን አቅምና
ብቃት የመመዘን ስልጣንና ሃላፊነት የፓርላማው
የመሆኑን ያህል፤ በእጩዎቹ አቅምና ብቃት ላይ
መረጃ መስጠትና ሃሳብ መግለፅ ደግሞ የእያንዳንዱ
ዜጋ ነፃነትና መብት ነው። መንግስት፣ የግልፅነት
አሰራርን በመከተል እቅዶቹን በይፋ የማስታወቅ
ግዴታ በህግ የተጣለበት በሌላ ምክንያት አይደለም።
በእቅዶቹ ላይ ዜጎች ሃሳባቸውን የመግለፅና
የመወያየት ነፃነት ስላላቸው ነው። “መንግስት
እና ፓርላማው የህግ የበላይነትን በማክበር
ሃላፊነታቸውን ለማሟላት፣ የዜጎችንም መብትና
ነፃነት ለማክበር ፈቃደኛ ቢሆኑ”… ብለን እናስብ።
ያን ያህልም ውስብስብ አይደለም።
ለሚኒስትርነት ወይም ለፕሬዚዳንትነት
የሚታጩ ሰዎች እነማን እንደሆኑ፣ ከሳምንታት
አስቀድሞ የፓርላማ አባላት እንዲያውቁት ይደረግና፣
ለዜጎችም በይፋ ይገለፃል። ያኔ፣ የእጩዎቹን ማንነት
በማጥናትና መረጃ በመሰብሰብ፣ ብቃታቸውንና
የስነምግባር ደረጃቸውን የመመዘን እድል
ይፈጠራል። ዜጎችና የፓርላማ አባላት፣ ሃሳብ
ለመለዋወጥና ለመወያየት ጊዜ ያገኛሉ። በእጩዎቹ
ብቃትና ድክመት ወይም የስነምግባር ፅናትና
ብልሹነት ላይ፣ የሚያስመሰግን ወይም የሚያስወቅስ
ተጨባጭ መረጃ ያላቸው ሰዎች፣ ማስረጃቸውን
ለፓርላማ አባላት በማካፈል ይተባበራሉ -
ሃሳባቸውን የመግለፅ ነፃነታቸውን በመጠቀም።
እንዲህ፣ በስልጣኔ ደህና የተራመዱ አገራት ውስጥ
እንደሚደረገው፣ ግልፅነትና ጨዋነትን የተላበሰ፣
የህግ የበላይነትና የዜጎች ነፃነትን ያከበረ አሰራር
ቢፈጠር፣ በሙስናና በብቃት ጉድለት የሚፈጠሩ
ግርግሮች በቀነሱ ነበር። ይሄ ግን አልሆነም።
መንግስት በህግ የተጣለበትን የግልፅነት አሰራርን
ወደ ጎን ብሎ፣ ለፕሬዚዳንትም ሆነ ለሚኒስትር
ሹመት በእጩነት የሚያቀርባቸውን ሰዎች በምስጢር
ደብቆ ይይዛል። የተሿሚዎችን ብቃትና ስነምግባር
ፈትሸው እየመመዘን ህገመንግስታዊ ሃላፊነት
የተጣለባቸው የፓርላማ አባላትም፣ ሃላፊነታቸውን
መወጣት ያቅታቸዋል። በአንድ ስብሰባ ላይ የእጩ
ሚኒስትሮች ወይም የእጩ ፕሬዚዳንት ስም ዝርዝር
የሚቀርብላቸው የፓርላማ አባላት፤ እዚያው
ስብሰባ ላይ የእጩዎችን የቀድሞ የሥራ ትጋትና
ስንፍና፣ ስኬትና ውድቀት መርምረው፣ የወደፊት
አላማቸውንና ሃሳባቸውን ፈትሸው፣ ብቃትና
አቅማቸውንም ሁሉ በአምስት ደቂቃ ውስጥ
መዝነው፣ በአምስት ደቂቃ ውስጥ የሁሉንም ሹመት
ማፅደቅ የሚችሉት እንዴት ነው? አንድ ሾፌር፣ አንድ
ነርስ ወይም አንድ የመዝገብ ቤት ሰራተኛ ለመቅጠር
እንኳ ከዚህ የበለጠ ጊዜ ያስፈልጋል። የብቃትና
የስነምግባር ጉዳዮችን ለመመርመርና ለመመዘን
ይቅርና፣ የሚኒስትሮችን ስም በወጉ ለማወቅ እንኳ
በቂ ጊዜ አያገኙም። 

No comments:

Post a Comment